ስለ ሥላሴ አንድም ማስረጃ በሌለበት የኒቅያን መግለጫ ብቻ በመንተራስ ከራሳችን ምሳሌ እየሰጠን ለማሳመን እንዴት እንጥራለን?

 


12. ስለ ሥላሴ አንድም ማስረጃ በሌለበት የኒቅያን መግለጫ ብቻ በመንተራስ ከራሳችን ምሳሌ እየሰጠን ለማሳመን እንዴት እንጥራለን? ስለ ሥላሴ የምናስረዳው በማስረጃ ነው ወይስ በምሳሌ?

ስለ ሥላሴ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ሆነ ቅድመ ኒቅያ በነበሩት ሐዋርያዊ አባቶች ጽሑፎች ውስጥ ኁልቁ መሳፍርት የሌላቸው ማስረጃዎች አሉ፡፡ አሕመዲን ለማስረጃዎቹ ልባቸውን ዝግ ካደረጉ ምንም ልንረዳቸው አንችልም፡፡ ስለ ሥላሴ የምናስረዳው በማስረጃም በምሳሌም ነው (እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ ሊገልጥ የሚችል ምሳሌ እንደሌለ ግን እናምናለን)፡፡ ምሳሌዎቹ ማስረጃዎቹን ይበልጥ ለመገንዘብ የሚረዱ ከሆነ መጠቀም ምኑ ላይ ነው ስህተቱ? የፈጣሪን አንድነት በምሳሌ መግለጥ ስህተት ከሆነ ሙስሊሞች የአላህን አንድነት ለመግለጥ አንድ ጣታቸውን የሚቀስሩት ለምን ይሆን?