ኢየሱስ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነበርን? ከነበረ “የነበረው ራሱ ከአብ የተወለደ ነው ትሉ የለምን?
19. ክርስቲያኖች እንደሚሉት ኢየሱስ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነበርን? ከመወለዱ በፊትስ ነበር ወይንስ አልነበረም? ምላሹ “ነበር” ከሆነ “የነበረው ራሱ ከአብ የተወለደ ነው ትሉ የለምን? “አልነበረም” ከሆነ ታዲያ ከጊዜ በኋላ የተገኘ ነገር “ዘለዓለማዊ” ነው ይባላልን?
መወለዱን ስንናገር ከአብ በዘለዓለማዊ መገኘት (Eternal Generation) መገኘቱን ለማመልከት እንጂ በጊዜ የተገደበ መሆኑን ለማመልከት ባለመሆኑ ይህ ጥያቄ በተሳሳተ መረዳት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ መጀመርያ እንደሌለው ነገር ግን በመጀመርያ እንደነበረ የሚናገር ሲሆን የዓለም ፈጣሪ መሆኑን ያስተምራል (ዮሐንስ 1፡1-18)፡፡ እርሱ የዘለዓለም አባት (ዘለዓለማዊነትን ያስገኘ) እንጂ በጊዜ የተገደበ አይደለም (ኢሳይያስ 9፡6)፡፡