1ኛ ዮሐንስ 5፡7 “የሚመሰክሩት መንፈሱና ውሃው፤ ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ” የሚለው ጥቅስ ላይ የተነሳ ጥያቄ!

 


20. 1ኛ ዮሐንስ 5፡7 ″መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው፡፡ የሚመሰክሩት መንፈሱና ውሃው፤ ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ” ይላል፡፡ እነዚህ ሦስት ምስክሮች እኩል ናቸውን? ደም ውኀን ሊተካ ይችላልን? ውኀስ በማንኛውም መልኩ “እንደ መንፈስ ነው” ማለት ይቻለናልን? ልክ መንፈሱ ደሙና ውሃው ሦስት የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑት ሦስቱም የመጀመሪያ ምስክሮች እነርሱም አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅድስ የተለያዩ ናቸውን?

ውኀው የክርስቶስን የማንፃት ኃይል የሚያሳይ ሲሆን ደሙ መስዋዕትነቱን ያመለክታል፡፡ ሰው በክርስቶስ ሲያምን የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እንዲሁም የመቀደሱንና የኃጢአት ይቅርታን የመቀበሉን ዋስትና ስለሚያገኝ በእውነተኛ መንገድ ላይ ለመሆኑ ሌላ ውጪያዊ ምስክር አያሻውም፡፡ ጥቅሱ ከዚህ የተለየ መልዕክት ስለሌለው ከሥላሴ ጋር ማያያዝ አስፈላጊ አይደለም፡፡[12]