ኢየሱስ እንደነገረን ሐዋርያት ኢየሱስ ምን መሆኑን አመኑ? ከአምላክ መላኩን! ታዲያ ለምን ክርስቲያኖች በተቃራኒው ተረዱ?

 


3. ዮሐንስ 17፡6-9 እንዲህ ይላል፦ “ከነዚህ ከዓለም ለሠጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገልጬላቸዋለሁ፡፡ የአንተ ነበሩ ለእኔ ሰጠኸኝ፣ እነርሱም ቃልህን ጠብቀዋል፡፡ የሰጠኸኝ ሁሉ ካንተ እንደሆነ አሁን አውቀዋል፥ ምክኒያቱም የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸው ተቀብለዋል፤ እኔም ካንተ እንደወጣሁ በርግጥ አውቀዋል አንተ እንደላክኽኝም አምነዋል፡፡ እነርሱ የአንተ ስለሆኑ፣ እጸልይላቸዋለው፣ ለሠጠኸኝና የአንተ ለሆኑት እንጂ ለዓለም አልጸልይም፡፡” ኢየሱስ እንደነገረን ሐዋርያት ኢየሱስ ምን መሆኑን አመኑ? ከአምላክ መላኩን! ታዲያ ለምን ክርስቲያኖች በተቃራኒው ተረዱ?

በጥቅሱ መሠረት ሐዋርያት ኢየሱስ በአብ የተላከ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ከአብ የወጣ መሆኑንም ጭምር ነው ያመኑት፡፡ ይህ ደግሞ ኢየሱስ ከአብ ባሕርይ የተገኘ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ የመለኮትነቱ ማስረጃ ነው፡፡ በተጨማሪም ሐዋርያቱ “ኢየሱስ በአብ የተላከ ምን መሆኑን ነው የማኑት”? ብሎ መጠየቅም አስፈላጊ ነው፡፡ ሐዋርያቱ ኢየሱስ እንደ ማንኛውም ነቢይ በአብ የተላከ መልዕክተኛ መሆኑን ሳይሆን በአብ የተላከ ቅዱስ ልጁ እና ጌታ መሆኑን ነው ያመኑት (ማቴዎስ 14፡33፣ 16፡16-17፣ ዮሐንስ 13፡13-14)፡፡ ይህ ደግሞ የጠያቂውን እምነት ከስረ መሠረቱ የሚንድ ግንዛቤ ነው፡፡