አምላክ ተኝቶ ሰው “ንቃ”  ብሎ ይቀሰቅሰዋልን? ለመሆኑስ አምላክ ይረሳልን?

 


4. መዝሙር 44፡23-24 “ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፤ ለዘለዓለም አትጣለን፡፡ ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? መከራችንንና መጠቃታችንን ለምን ትረሳለህ” ይላል፡፡ አምላክ ተኝቶ ሰው “ንቃ”  ብሎ ይቀሰቅሰዋልን? ለመሆኑስ አምላክ ይረሳልን? ታዲያ ይህን አምላክ ነው ሙስሊሞች እንዲያምኑበት ክርስቲያኖች የሚጣሩት? ወይስ ይህ የአምላክ ቃል አይደለም?

ይህ መዝሙር በአሣቃቂ መከራ ውስጥ ሲያልፉ የነበሩ ሰዎች የዘመሩት ነው፡፡ እግዚአብሔር የተዋቸውና የጣላቸው የመሰላቸው ሰዎች እግዚአብሔር እንዲረዳቸው የተማፀኑበት ነው፡፡ “ንቃ፣ ስለምን ትተኛለህ፣ ተነስ” የሚሉት ቃላት ዘይቤያዊ ሲሆኑ በቀጥታ መተርጎም የለባቸውም፡፡ ዘማሪያኑ በመከራ ውስጥ መሆናቸውንና እግዚአብሔር እነርሱን ከመርዳት በመዘግየቱ ማዘናቸውን ብቻ የሚገልፁ ናቸው፡፡ እዚሁ መዝሙረ ዳዊት ውስጥ “እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም” ተብሎ ተጽፏል (121፡4)፡፡