“አምላክ ሰውን በመፍጠሩ ተጸጸተ” ማለት አግባብነት አለውን? ሰውን ሲፈጥር ሰው ምን እንደሚያደርግ አስቀድሞ አያውቅምን?
7. ዘፍጥረት 6፡6 “እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተፀፀተ፤ በልቡም እጅግ አዘነ” ይላል፡፡ እግዚአብሔር እንደ ደካማው ፍጥረት እንደሰው ባደረገው ይፀፀታልን? በመሠረቱ “ጸጸት” ማለት አንድ ሰው አንድን ድርጊት ያደርግና በኋላ ያደረገው ድርጊት በጠበቀው መልኩ ሳይሆንለት ሲቀር ነው፡፡ ይህ ለሰው የተገባ ባህሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው አስቀድሞ የነገርን ፍጻሜ ማወቅ አይችልምና፡፡ አምላክ ግን ሁሉን የሚያውቅ ጌታ ስለሆነ በሚሰራው ሥራ አይጸጸትም፡፡ ታዲያ “አምላክ ሰውን በመፍጠሩ ተጸጸተ” ማለት አግባብነት አለውን? ሰውን ሲፈጥር ሰው ምን እንደሚያደርግ አስቀድሞ አያውቅምን? የማያውቅ ከሆነ ሁሉን አዋቂ አይደለም ማለት ነው፡፡ ታድያ ይህ አምላክ መሆን ይችላልን? ወይስ ይህ የአምላክ ሳይሆን የሰው ቃል ነው?
ተከታዮቹም ጥያቄዎች ተያያዥ ናቸው፡- ለማንበብ ይህንን ይጫኑ!