ለምንድነው መጽሐፍ ቅዱስ ባሪያ አይንገስ የሚለው?

 


  1. ምሳሌ 30:21-23 “ምድር በሦስት ነገር ትናወጣለች፤ እንዲያውም መሸከም የማትችላቸው አራት ነገሮች ናቸው፤ ባርያ ሲነግሥ፤ ሰነፍ እንጀራ ሲጠግብ፤ የተጠላች ሴት ባል ስታገባ፤ ሴት ባሪያ በእመቤትዋ እግር ስትተካ” ይላል፡፡ ምናለ ባርያ ቢነግሥ? ምናለ የተጠላች ሴት ብታገባ? ሴት ባሪያ በእመቤቷ ብትተካስ? ክርስቲያኖች የሚያመልኩት አምላክ በሰው እኩልነት አያምንምን? ወይስ ይህ የአምላክ ቃል አይደለምን?

ጠያቂው ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት የሌላቸውና በዕውቀት ያልበቁ ሰዎች በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ሥልጣን ላይ ቢወጡ ችግር የለውም እያሉ ነውን? በእርግጥ ጥቅሱ ባርያ መንገሥ የለበትም፣ የተጠላች ሴት ማግባት የለባትም ወይም ሴት ባርያ በእመቤቷ መተካት የለባትም እያለ አይደለም ነገር እነዚህ ሰዎች ይህንን ክብር ሲያገኙ ከመጠን በላይ ራሳቸውን እንደሚቆልሉና የተናጋ ስነ ልቦና ስላላቸው ለበቀል እንደሚነሳሱ ለመግለፅ የተነገረ ግነታዊ ዘይቤ ነው፡፡ እንዲያ ያሉ ሰዎች ይህንን ክብር ሲያገኙ ችግር ስለሚፈጥሩ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ስለ እኩልነት ሊሰብኩን የሚዳዳቸው ጠያቂያችን የገዛ ሃይማኖታቸው በሰው ልጆች እኩልነት እንደማያምን ልባቸው ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፡፡ በቁርኣን መሠረት ወንዶች ከሴቶች ብልጫ አላቸው (2፡228)፣ የአንድ ወንድ ምስክርነት ከሁለት ሴቶች ጋር እኩል ነው (2፡282)፣ የወንዱ የውርስ ድርሻ ከሴቷ እጥፍ ነው (4፡11)፡፡