አምላክ ከአፍንጫው ጭስ ይወጣል?

 


15. 2ኛ ሳሙኤል 22:9-11 “በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮህኩ፤ እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ፡፡ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ በሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቆጥቶአልና ራዱ፡፡ ከአፍንጫው የቁጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ፡፡ ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ፡፡ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ” ይላል፡፡ ይህ የአምላክ ባሕሪ ነውን?

የእግዚአብሔርን ቁጣ ለመግለፅ የተነገረ ግነታዊ ዘይቤ እንጂ ቀጥተኛ ንግግር ባለመሆኑ ቃል በቃል መተርጎም ትክክል አይደለም፡፡