አምላክ በአመንዝራነት ያዛልን?

 


19. ትንቢት ሆሴዕ 1፡2 “እግዚያብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው ይላል፡፡ አምላክ በአመንዝራነት ያዛልን? በዝሙት ላይ የፈጣሪ አቋም ይህ ነውን?

እግዚአብሔር የሆሴዕን ሕይወት ለእስራኤል ማስተማርያ ለማድረግ ስለፈለገ አመንዝራ ሴት እንዲያገባ አዘዘው እንጂ አመንዝር አላለውም፡፡ ሆሴዕ ያገባት ሴት አመንዝራና ምግባረ ብልሹ ብትሆንም እርሷን የሚወድበትና የሚታገስበትን ፀጋ ሰጥቶታል፡፡ ዛሬም በማሕበረሰባችን ውስጥ ከእንደዚህ ዓይነት ሴቶች ጋር በመጋባት የሚኖሩ ወገኖች አሉ፡፡ ይህ የግለሰቦቹን ጥንካሬና ታጋሽነት የሚያሳይ እንጂ በፍፁም የሚያስወቅስ አይደለም፡፡ የሆሴዕ ታሪክ እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ ሌሎች አማልክትን ቢያመልኩም እንደታገሳቸውና እንደወደዳቸው የሚያሳይ ትዕምርታው ትንቢት ነው፡፡ ታሪኩ ዘይቤያዊ እንጂ በተግባር የተፈፀመ እንዳልሆነም የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ብዙዎች ናቸው፡፡