ሉቃስ 1፡1-4 ላይ “ብዙዎች ታሪኩን የተቻላቸው ያክል ጽፈው ይገኛል” ያለው ሌላ ወንጌል ይሆን?

 


15. ሉቃስ 1፡1-4 ላይ “በእኛ መካከል ስለ ተፈፀሙት ነገሮች ብዙዎች ታሪኩን የተቻላቸውን ያክል ጽፈውት ይገኛል፣ ይህም ታሪክ ከመጀመሪያው አንስቶ የዐይን ምስክሮች የቃሉ አገልጋዮች የነበሩ ያስተላለፋልን ነው፡፡ ክብር ቴዎፍሎስ ሆይ! እኔም በበኩሌ ሁሉን ከመሠረቱ በጥንቃቄ ከመረመርሁ በኋላ ታሪኩን ቅደም ተከተሉን በጠበቀ ሁኔታ ልጻፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፣ ይህንን የማደርገው የተማርከው እውነት መሆኑን እንድታውቅ ነው” ብሏል፡፡ በዚህ ጥቅስ ላይ “ብዙዎች ታሪኩን የተቻላቸው ያክል ጽፈው ይገኛል” ያለው ይሁን ሌላኛው ወንጌል?

አይደለም፣ የክርስቶስን ወንጌል በማጣመም አንዳንድ ቀናዒ አይሁዳውያን የሰበኩትን “ወንጌል” ነው፡፡ የገላቲያ መልዕክት ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ይህንን የተለየ “ወንጌል” ለመቃወም የተጻፈ ነው፡፡ ጠያቂው የማይገናኙ ጥቅሶችን በማገናኘት አዲስ ምናባዊ ታሪክ ለመፍጠር ከሚደክሙ በሰከነ መንፈስ እውነትን ለማወቅ መረጃዎችን ቢያገላብጡ መልካም ነበር፡፡