ብዙ ሰዎች የኢየሱስን ታሪክ ከጻፉ ታድያ እነዚያ ብዙዎቹ የጻፉት የት ገቡ?

 


17. ሉቃስ “ብዙዎቹ ታሪኩን የተቻላቸው ያህል ጽፈውት ይገኛል” ሲል ብዙ ሰዎች የኢየሱስን ታሪክ እንደጻፉ ነግሮናል፡፡ ታድያ እነዚያ ብዙዎቹ የጻፉት የት ገቡ?

መጻሕፍቱ የክርስቶስን ታሪክ ለማስተማር በወቅቱ አገልግለው ይሆናል፡፡ ነገር ግን የክርስቶስን ታሪኮች ለመጻፍ የተደረጉ ሙከራዎች መሆናቸውን እንጂ እንደ አራቱ ወንጌላት በሐዋርያት እጅና ዕውቅና የተጻፉ ስለመሆናቸው ምንም ማስረጃ የለም፡፡ ነገር ግን አሁን በእጃችን ከሚገኙት ወንጌላት የተለየ መረጃ ሊሰጡን እደማይችሉ እርግጠኞች ሆነን መናገር እንችላለን፡፡ ሉቃስ የሚያውቃቸው ጽሑፎች ይዘት እርሱ ከጻፈው የተለየ ቢሆን ኖሮ ባልጠቀሳቸው ነበር፡፡ የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመታት የተጻፉ መጻሕፍት ተጠብቀው መቆየት የሚችሉት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ባለ አክብሮትና ጥንቃቄ ከተያዙና ከተገለበጡ ብቻ ነው፡፡