የትኞቹ መጽሐፍት ናቸው “ቅዱሳን” በሚለው ላይ ብርቱ ክርክር በድምፅ ብልጫ ነው የተወሰነው፡፡

 


10. የትኞቹ መጽሐፍት ናቸው “ቅዱሳን” በሚለው ላይ ብርቱ ክርክር ነበር፡፡ በመጨረሻም ጉዳዩ በድምፅ ብልጫ ነው የተወሰነው፡፡ ክርክር መነሳቱ በራሱ ዛሬ ባሉበት መጽሐፍት ላይ ጥቂትም ቢሆን ጥርጣሬን አያጭርምን?

አዲስ ኪዳንን በተመለከተ “ብርቱ” ክርክር መኖሩንም ሆነ በድምፅ ብልጫ መወሰኑን የሚያመለክት የታሪክ ማስረጃ የለም፡፡ ነገር ግን ቁርኣንን በተመለከተ የትኞቹ ሱራዎች መካተት እንዳለባቸው በመጀመርያዎቹ ሙስሊሞች መካከል ብርቱ ክርክር ነበር፡፡ በመጨረሻም ጉዳዩ ኡስማን በተሰኘው ካሊፋ አስገዳጅነት ወደ ፍፃሜ የመጣ ሲሆን እርሱ የመረጠው ጸድቆ በፊት የነበሩት መጻሕፍት በሙሉ እንዲቃጠሉ ተደርጓል፡፡