“ስለዚህ ነገሮች ሁሉ የመሰከረና እነዚህን ነገሮች የጻፈው ይህ ደቀመዝሙር ነው” ይህ የማን ንግግር ነው?

 


27. የዮሐንስ ወንጌል ጸሐፊ “ዮሐንስ የተባለው የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነው” ተብሎ ይገመታል፡፡ የዮሐንስ ወንጌል 21፡24 ላይ “…ስለዚህ ነገሮች ሁሉ የመሰከረና እነዚህን ነገሮች የጻፈው ይህ ደቀመዝሙር ነው፡፡ የእርሱም ምስክርነት እውነት እንደሆነ እናውቃለን” ይላል፡፡ ይህ የማን ንግግር ነው? “እናውቃለን” የሚለውን እያለ ያለው ማነው? ዮሐንስ ስለ ራሱ ነው እንዲህ የሚለው ወይስ ሌላ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ነው ይህን እየፃፈያለው?

ዮሐንስ እንዲህ ብሎ ሊጽፍ ቢችልም ነገር ግን ይህ ክፍል በዮሐንስ ደቀ መዛሙርት የተጻፈ ሊሆን እንደሚችል ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ ማርቆስና ሉቃስ የሐዋርያት ደቀ መዛሙርት ሆነው ሳሉ ሙሉ መጻሕፍትን የመጻፍ ሥልጣን ካገኙ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ምስክርነቱ እውነት መሆኑን እንደሚያውቁ ቢገልፁና የጸሐፊውን ማንነት የሚያስረግጥ ምስክርነት ቢሰጡ በጎ ነገር ነው፡፡ መጽሐፉ በዚህ መልኩ እንዲጠናቀቅ የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ነበር፡፡