ጠብ ያለሽ በዳቦ – የአክራሪ ሙስሊሞች መሰሪ ስልት

ጠብ ያለሽ በዳቦ – የአክራሪ ሙስሊሞች መሰሪ ስልት


አክራሪ ሙስሊሞች ከሚታወቁባቸው እኩይ አካሄዶች መካከል አንዱ አካባቢያዊና ግለሰባዊ አጀንዳዎችን አገራዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ መልክ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡ በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ሕዝበ ሙስሊሙን ሊያስቆጡ የሚችሉ “ቅመማ ቅመሞችን” በመጨማመርና መርዝ በተነከረ እጃቸው በማማሰል ነገሮችን በማወሳሰብ ስውር አጀንዳቸውን ከግብ ለማድረስ መጠቀምን ተክነውበታል፡፡ ለዚህ የሚሆኑ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ሰልማን ረሽዲ የተሰኘው እንግሊዛዊ ደራሲ በ 1988 እ.ጎ.አ. “The Satanic Verses” በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሐፉ ውስጥ ሙሐመድን የሚተች መልእክት አስፍሯል በሚል አክራሪ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ ተቃውሞ አስነስተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አክራሪዎቹ የሙስሊሞችን ቁጣ ለመቀስቀስ የተጠሙት ዘዴ የረሽዲን ጽሑፍ የሙስሊሞችን ቁጣ ሊቀሰቅስ በሚችል መንገድ ማቅረብ ነበር፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ሙሐመድን ይተቻል የተባለው ክፍል ሙሐመድን በስም የማይጠቅስና ቢጨመቅ ከአንድ ገጽ ያልዘለለ ቢሆንም ሙሉ መጽሐፉ ነቢያቸውን የሚሳደብ በማስመሰል አስወርተዋል፡፡ ረሽዲ አንድ ግለሰብ ቢሆንም መጽሐፉን በእስልምና ላይ የተቃጣ የምዕራባውያን ትንኮሳ በማስመሰል ማቅረብ ሌላው ቁጣን የመቀስቀሻ ዘዴ ነበር፡፡ በወቅቱ ዓለም አቀፋዊ ትኩረትን ሲሻ የነበረው የኢራኑ አያቶላህ ሮሆላህ ኾሜይኒ ረሽዲን በከሃዲነት በመፈረጅ በተገኘበት እንዲገደል ‹‹ፋትዋ›› አውጥቶበት፡፡ “ሃይማኖትህ ተደፈረ” በሚል ቅስቀሳ መላው ሕዝበ ሙስሊም ለተቃውሞ እንዲነሳ ዓለም አቀፍ ጥሪ ከአክራሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ ሲሰማ ነበር፡፡ ጥሪውን ተከትሎ ምድር አንቀጥቅጥ ሰልፎች በመላው አውሮፓና በሙስሊም አገራት ተደረጉ፡፡ በርካታ ሰዎችም ተገደሉ፡፡ ነፍሱን ለማትረፍ ራሱን ለመሰወር የተገደደው ረሽዲም ይቅርታን በመጠየቅ ወደ እስልምና መመለሱን ቢያሳውቅም አክራሪዎች የእርሱን መጽሐፍ እንደ ሰበብ (Pretext) ተጠቀሙት እንጂ መነሻቸውም ግባቸውም እርሱ ባለመሆኑ ውጥረቱ ሊረግብ አልቻለም፡፡ እነሆ ያኔ በምድረ አውሮፓ ላይ ራሱን ቀና ያደረገው አክራሪ እስልምና እስከ አሁን ድረስ እየተንጠራራ የሰዎችን የመናገር መብት በመገደብ አልፎም በሽብር የምዕራቡን ዓለም በመናጥ የሰቆቃ ምንጭ መሆኑን ቀጥሏል፡፡

‹‹ጂላንድ ፖስተን›› የተሰኘው የዴንማርክ ጋዜጣ የሙሐመድን ካርቱን ይዞ በመውጣቱ ሳብያ በተመሳሳይ አክራሪዎች ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርገውት ነበር፡፡ በጋዜጣው ላይ የታተመውን ምስል እንዳለ ለሕዝበ ሙስሊሙ በማሳየት ለተቃውሞ መቀስቀስ ብዙም ውጤት እንደማይኖረው የተገነዘቡት አክራሪዎች፤ እናከብረዋለን፣ እንሞትለታለን የሚሉትን ነቢያቸውን እርቃኑን ውሻ ከኋላ $%#@*! ሲያደርገው የሚያሳይ ፀያፍ ምስል በመሳል ሕዝበ ሙስሊሙን አስቆጥተው አደባባይ እንዲወጣ አድርገውታል፡፡ በዚያን ጊዜ የተፈጸመው አስነዋሪ ተግባር ፅንፈኞች የሚፈልጉትን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግብ እስከመቱ ድረስ ለሃይማኖታቸው ግድ የሌላቸው መሆናቸውን በጥሩ ሁኔታ ያሳየ ነበር፡፡ ብዙ መሰል አጋጣሚዎችን መጥቀስ ይቻላል።

ሰሞኑን አንድ ግለሰብ ሙሐመድን ተሳደበ በሚል ብዙ አክራሪ ሙስሊሞች በግለሰቡ ላይ መንግሥት እርምጃ ካልወሰደ እንዲህና እንዲያ እናደርጋለን በማለት ሲዝቱ ተመልክተናል። እኔ እንደ አንድ በሃይማኖታዊ ውይይቶች ውስጥ እንደሚሳተፍ ሰው ማስረጃ ሊቀርብለት በማይችል ሁኔታ ትችት ማቅረብ አልፎም መሳደብ ትክክል ነው ብዬ አላምንም። ነገር ግን አንድ ግለሰብ ፌስቡክ ላይ አጉል ነገር ጻፈ ተብሎ አገራዊና መንግሥታዊ አጀንዳ በማድረግ ሕይወትን እስከ ማጥፋት መዛትና መንግሥትን ለማስፈራራት መሞከር በምንም መንገድ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። ኢትዮጵያ በሸሪኣ የምትተዳደር አገር አይደለችም። ሙሐመድም ሆነ ሌላ ታሪካዊ ስብዕና ተሰደበ በሚል አንድን ግለሰብ ለፍትህ እንዲቀርብ የሚያስገድድ ሕግ እስካሁን የለንም። ስማቸው ጭራሽ ተሰምቶ የማይታወቅ ግለሰቦች እዚህም እዚያም ፌስቡክ ላይ ከሚጽፉት ነገር ተነስቶ አገርን ማወክ አክራሪዎች አጀንዳ በመፍጠር ስውር ዓላማቸውን ለማሳካት የሚጠቀሙት ስልት ነው። ተጠያቂነት ካስፈለገ ርዕስ ፈልገው አገር ለማወክ ሕግ አስከባሪ አካላትን ሲያስፈራሩና ነፍስ ለማጥፋት ሲዝቱ የነበሩት ሙጅብ አሚኖን የመሳሰሉት አክራሪዎች ሊጠየቁ ይገባል!

ለአክራሪ ሙስሊሞች ያለኝ መልእክት እናንተ የምትከተሉት የጽንፈኝነት አካሄድ እንኳንስ አብዛኛው ሕዝብ የክርስትና እምነት ተከታይ በሆነባትና ቁልፍ ዓለም አቀፍ ሚና ባላት በአገራችን ይቅርና በሙስሊም አገራት እንኳ ሊሠራ አልቻለም የሚል ነው፡፡ በሊብያ፣ በሶማሊያ፣ በማሊ፣ በኢራቅ፣ በሦርያና በመሳሰሉት አገራት አክራሪ የእስላም መንግሥት የመመሥረት ጥረት ከሽፎ አገራቱን ለከፋ ችግር ዳርጓል፡፡ በግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ የተከናነበውን ውርደት አስታውሱ፡፡ ሳዑዲ አረብያም እንደማያዋጣት አውቃ እያለዘበች ነው፡፡ የኢራን ኢስላማዊ መንግሥት እየተንገዳገደ ነው፡፡ አጋጣሚዎችን ጠብቃችሁ ሰበብ እየፈለጋችሁ ልታመጡት የምትፈልጉት እስላማዊ መንግሥት ህልም ብቻ መሆኑን እንዴት ማስተዋል ተሳናችሁ? የናንተ የክፋት መርዝ ልክ እንደ ሌሎቹ የሙስሊም አገራት ሁሉ አስቀድሞ እናንተኑ እንደሚያጠፋ አስተውሉ።


ልዩ ልዩ