አንዲት ዛፍ ለነቢዩ ነገረችው?

አንዲት ዛፍ ለነቢዩ ነገረችው?


ሙሐመድ ነቢይነቱን ካወጀ በኋላ በመጀመርያዎቹ አሥር ዓመታት ብዙ ተከታዮችን የማፍራት ምኞቱ ሊሳካ ባለመቻሉ ምክንያት የራሱንና የተከታዮቹን ስነ ልቦና የሚጠብቅባቸውን ዘዴዎች ይፈጥር ነበር፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ ጋኔኖች የእርሱን ነቢይነት ተቀብለው መስለማቸውን መናገሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት “ሱረቱ አል-ጂን” (የጋኔን ምዕራፍ) የሚል የቁርአን ሱራ እንደወረደለት ተናግሯል፡፡ ለመሆኑ ጋኔኖች ቁርአንን ሰምተዋል የሚለውን ታሪክ ለሙሐመድ የነገረው ማን ነው? ጉዳዩ የፈጠራ ታሪክ መሆኑን ከጥርጣሬ በጸዳ ሁኔታ የሚያሳይ ማስረጃ በእስላማዊ ሐዲሳት ውስጥ ይገኛል፡-

Narrated `Abdur-Rahman:

“I asked Masruq, ‘Who informed the Prophet (ﷺ) about the Jinns at the night when they heard the Qur’an?’ He said, ‘Your father `Abdullah informed me that a tree informed the Prophet (ﷺ) about them.'” (Sahih al-Bukhari Vol. 5, Book 58, Hadith 199)

“መስሩቅን እንዲህ ስል ጠየቅሁት፡- ‹‹ጂኒዎች ቁርአንን በሰሙበት ምሽት ስለ ጉዳዩ ለነቢዩ የነገራቸው ማን ነው?›› እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፡- ‹‹አንዲት ዛፍ ስለ እነርሱ ለነቢዩ መናገሯን አባትህ አብዱላህ ነግሮኛል››፡፡ (ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 5፣ መጽሐፍ 58፣ ቁጥር 199)
ውድ ሙስሊሞች እንዲህ ባሉ የፈጠራ ታሪኮች ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት ወደ ሰማይ ያደርሰናል ብላችሁ እንዴት አመናችሁ?