ወልድ መንፈስ ነው

ወልድ መንፈስ ነው

ወንድም ሳሚ


ከሐዋርያት ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ከቀጠለውና መጽሐፍ ቅዱስም በግልጽ ከሚያስተምራቸው ትምህርቶች አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ መንፈስ መሆን ነው። እንደ ትክክለኛው የክርስትና አስተምህሮ ወልድ አምላክ ነው (ዕብ 1:8 1ዮሐ 5:20 ዮሐ 1:1) ያ አምላክ የሆነው ወልድ ደግሞ ኃጢአትን ለማስተሰረይ ሰው ሆኖ ወደ ዓለም መጥቷል (ዮሐ 1:14 ፊሊ 2:7 1ዮሐ 4:10) ይህ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ሲሆን ከሐዋርያት ዘመን አንስቶ እስካሁን ዘመን ድረስ በክርስቲያኖች የሚታመነው እምነት ነው።

ነገር ግን ይህን እውነተኛ የክርስትና አስተምህሮ የሐዋርያት ቤተ-እምነት ተከታዮች ወይንም በተለምዶ የOnly Jesus አማኞች አጥብቀው ይቃወሙታል። እንደ እነርሱ አስተምህሮ ወልድ በስጋ የመጣው አምላክ ሳይሆን አብ የተገለጠበት የሥጋ ሰውነት ነው። ስለዚህ እንደ እነርሱ እምነት ከሆነ፥ ወልድ አምላክ አይደለም፥ በስጋ የተገለጠውም እርሱ አይደለም።

እነዚህ ወገኖች ለዚህ አስተምህሮ ማስረጃ ነው ብለው ከሚያቀርቧቸው ሀሳቦች አንዱ “ወልድ መንፈስ ነው የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የለም፥ መለኮት ደግሞ መንፈስ ስለሆነ ወልድ መለኮት ሊሆን አይችልም፥ መንፈስ አይደለምና” የሚለው ሀሳብ ነው። ይህ ግን ፈጽሞ ስህተት የሆነና ከክርስትና ውጪ የሆነ አረዳድ ነው።

ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ወልድ መንፈስ ነው!

ወልድ መንፈስ መሆኑን ከሚያረጋግጡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች የመጀመሪያውን እንመልከት፦

ማስረጃ አንድ

“እንዲሁ ደግሞ። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” (1ቆሮ 15:45)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ኋለኛው አዳም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን። ዘፍ 2:7 ላይ እንደተጻፈው ፊተኛው ሰው አዳም በእግዚአብሔር ሲፈጠር ሕያው ነፍስ መሆኑን ከተናገረ በኋላ ኋለኛው አዳም ክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ እንደሆነ ይናገራል።

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መንፈስ ሆኖ ሕይወትን ሊሰጥ የሚችለው መለኮት ነው፦

እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ” (ዘዳ 30:20)

የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን” (መዝ 36:9)

“አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ” (ነህ 9:6)

“አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ (I make alive) እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ ከእጄም የሚያድን የለም” (ዘዳ 32:39)

እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም (make alive) ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል” (1ሳሙ 2:6)

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐ 4:24) ይህ መንፈስ የሆነው እግዚአብሔር ደግሞ ከላይ እንደተመለከትነው ሕይወትን ይሰጣል። ስለዚህ ከዚህ ተነስተን “ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ” ሲል መለኮት ማለት እንደሆነ እንረዳለን። ከመለኮት በቀር ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ የለምና

ከዚህ አንጻር 1ቆሮ 15:45 እንዴት የወልድን መንፈስነት እንደሚያሳይ ነጥብ በነጥብ እንመለከት

1) ሕይወትን የሚሰጠው መንፈስ ኋለኛው አዳም ነው

በ1ቆሮ 15:45 ሕይወትን የሚሰጠው መንፈስ ኋለኛው አዳም እንደሆነ ተገልጿል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ ኋለኛው አዳም ወይንም ኋለኛው ሰው ወልድ ነው፦

“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ” (ሮሜ 8:3-4)

በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር ከሥጋ የተነሳ ስለደከመ፥ ለሕግ ያልተቻለውን የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ እንደላከ ሲናገር እንመለከታለን። ስለዚህ በስጋ የመጣው፥ የስጋ ባህርይን የራሱ ያደረገው ልጁ ነው። ይህ ኋለኛው ሰው ወይንም ኋለኛው አዳም በስጋ ተልኮ የመጣው ወልድ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። አባቱ በስጋ/በሰዋዊ ባህርይ ልኮት የመጣው እርሱ ነውና።

አስተውሉ! ሮሜ 8:3 እግዚአብሔር ልጁን “” ኃጢአተኛ ስጋ ምሳሌ ላከው ይላል እንጂ ልጁ “” የኃጢአተኛ ስጋ ምሳሌ ነው አይልም። ስጋ ልጁ በአባቱ የተላከበት ሌላ ባህርይ እንጂ እርሱ ራሱ ያንን ስጋ አይደለም። ልጁ ራሱ መገለጫ ስጋ/ሰውነት ነው ከተባለ ስጋ በስጋ ተላከ ወደሚል absurdity ያመራል። ወልድ ኋለኛውን አዳም የሆነው ጊዜው በደረሰ ጊዜ አብ በስጋ ስለላከው ነው። መገለጫ ስጋ ቢሆን ግን በስጋ ተላከ ባልተባለለት ነበር።

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ እንደሚያነጻን ሲናገር እንመለከታለን። ይህ ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ደም አለው ማለት ነው። ደም ደግሞ የሰዋዊ ባህርይ ወይም የሰውነት አንዱ መገለጫ በመሆኑ ሰው የሆነው፥ ኋለኛው አዳም ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ይህ ደም ያለው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ከዚህ እንረዳለን።

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ በስጋ ከዳዊት ዘር እንደተወለደ ሲናገር እንመለከታለን። የልጁ ከዳዊት ዘር በስጋ መወለድ አስቀድሞ የተተነበየ እውነት ነው (መዝ 132:11) በሐዋርያት ስብከትም ይህ በተደጋጋሚ ተረጋግጧል (ሐዋ 2:30-31 ሐዋ 13:22-23) ስለዚህ ኋለኛው አዳም ይህ ከዳዊት ዘር በስጋ የተወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ከዚህ ተነስተን ኋለኛው አዳም የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን” (ሮሜ 5:10)

በዚህ ስፍራ ላይም ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር በልጁ ሞት እንደታረቀን ሲናገር እንመለከታለን። የክርስቶስ ኢየሱስ ሞት በስጋ የተከናወነ ሞት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል (1ጴጥ 3:18) ስለዚህ በሥጋ የሞተው ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ኋለኛው አዳም ይህ በመስቀል ላይ ሞትን የሞተበት ሥጋ የነበረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ከዚህ ተነስተን ኋለኛው አዳም ወልድ መሆኑን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

“26 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና። እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። 27 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ። ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ 28 ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። 29 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣውም” (ማቴ 26:26-29)

በዚህ ስፍራ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋውን እና ደሙን እንዲበሉና እንዲጠጡ ለሐዋርያት ሲሰጣቸውና በአባቱ መንግስት ከዚያ ወይን እስኪጠጣ ድረስ ከዚያ ቀን ጀምሮ እንደማይጠጣ ሲናገር እንመለከታለን። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ አባት ያለው ወልድ ስለሆነ (2ዮሐ 1:3) ስጋዬ ብሎ እየተናገረ ያለው ወልድ ለመሆኑ ይህ ተጨባጭ ማሳያ ነው። ስለዚህ ከዚህ ተነስተን ስጋ ያለው ወልድ መሆኑን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

አስተውሉ! ወልድ መገለጫ ስጋ/ሰውነት ቢሆን ኖሮ “ሥጋዬ” የሚለው ንግግሩ “ስጋ ስጋ አለው” ወይም “ስጋ የስጋ ባለቤት ነው” ወደሚል absurdity ያመራ ነበር። ራሱን የቻለ ማንነት እንጂ ስጋ ያለው (ዳን 7:15) መገለጫ ስጋ/ሰውነት የስጋ ሰውነት ሊኖረው አይችልም። እርሱ ራሱ ስጋ ነውና ሌላ ስጋ ሊኖረው አይችልም። ወልድ ኋለኛውን አዳም የሆነው ይህ ሰውነት/ሰዋዊ ባህርይ ስላለው ነው።

➢ በ1ቆሮ 15:45 ላይ ግን ይህ ኋለኛው አዳም ወይንም ወልድ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። ስለዚህ ኋለኛው አዳም ወይንም ወልድ ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል መንፈስ ነው ማለት ነው! ይህ ለወልድ መንፈስነት የማይታበል ማስረጃ ነው

ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው፥ ወልድ በስጋ የመጣው አምላክ ነው (ሮሜ 8:3 ዮሐ 1:14 ፊሊ 2:7) ስለዚህ በስጋ ከመጣ በኋላ አምላክም (መንፈስ) ሰውም (ስጋ) ተብሎ ይጠራል። መለኮታዊውም ሰዋዊውም ባህርይ አለውና። በ1ቆሮ 15:45 ኋለኛው አዳምም (ሰውም) ሕይወት የሚሰጥ መንፈስም (አምላክም) የተባለው ለዚያ ነው። በስጋ የተገለጠው አምላክ ስለሆነ ነው። ሁለቱም ባህርያት ስላሉት ከሰውነቱ ባሻገር መንፈስም/አምላክም ነው።

አስተውሉ! በ1ቆሮ 15:45 ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ የተባለው ራሱ ኋለኛው አዳም ወይም ወልድ እንጂ በኋለኛው አዳም ውስጥ አለ የሚባልለት ማንነት አይደለም!

እንደ ሐዋርያት ቤተ-እምነት ተከታዮች አስተምህሮ ወልድ መገለጫ ሰውነት ወይም ስጋ ሲሆን መንፈስ የሆነው ደግሞ በውስጡ ያለው አብ ነው። ስለዚህ እንደ እነሱ እምነት መንፈስ ሊባል የሚችለው ወልድን መገለጫ ስጋ አድርጎ የመጣው አብ እንጂ ራሱ ወልድ አይደለም። ይህ ግን ፍጹም ስህተት ነው።

በ1ቆሮ 15:45 ላይ መንፈስ የተባለው ራሱ ኋለኛው አዳም/ወልድ ነው! እንጂ በኋለኛው አዳም ውስጥ ያለ ማንነት አይደለም። ክፍሉም “በኋለኛው አዳም ውስጥ ያለው ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” አይልም። ራሱ ኋለኛው አዳም ወይም ወልድ ነው ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ የተባለው። ስለዚህ መንፈስ የተባለው ወልድ አይደለም ማለት አይቻልም።

2) ወልድ ሕይወት ይሰጣል

በ1ቆሮ 15:45 ኋለኛው አዳም ሕይወት የሚሰጠው መንፈስ ተብሏል። ይህ ማለት ኋለኛው አዳም ሕይወትን ይሰጣል ማለት ነው። ልክ ኋለኛው አዳም ወልድ መሆኑ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደተገለጸው ሁሉ፥ የወልድ ሕይወት ሰጪነትም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተገልጿል፦

“አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል” (ዮሐ 5:21)

“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ” (ዮሐ 5:25)

“28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። 29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም” (ዮሐ 10:28-29)

– አባት ያለው ወልድ በመሆኑ (2ዮሐ 1:3) በዚህ ቦታ ላይ አባቴ እያለ ያለውና የዘላለምን ሕይወት እሰጣቸዋለሁ እያለ ያለው ወልድ መሆኑ ግልጽ ነው።

“ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ 14:6)

– ወደ አብ መግቢያው ወልድ በመሆኑ (ዕብ 7:25) በዚህ ቦታ ላይ ወደ አብ ብቸኛው መግቢያ ነኝ እያለ ያለውና ሕይወትም ነኝ እያለ ያለው ወልድ መሆኑን ያሳያል

“ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው” (ዮሐ 17:1-2)

ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም” (1ዮሐ 5:12)

➢ ይህ በ1ቆሮ 15:45 ሕይወትን ይሰጣል የተባለው መንፈስ ወይም ኋለኛው አዳም ወልድ ለመሆኑ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ነው። በዚህ ክፍል ላይ ለወልድ የተባለው ነገር በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ለወልድ ተብሏልና። ይህ ሕይወትን የሚሰጠው መንፈስ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

አስተውሉ! በ1ቆሮ 15:45 ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ የተባለው ራሱ ኋለኛው አዳም ወይንም ወልድ እንጂ በኋለኛው አዳም ውስጥ ያለ ማንነት አይደለም! ክፍሉ “ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” ይላል እንጂ “በኋለኛው አዳም ውስጥ ያለው ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” አይልም!

ስለዚህ ክፍሉ እንደዛ ስለማይል ማንም ሰው በ1ቆሮ 15:45 መንፈስ የተባለው ኋለኛው አዳም/ወልድ ሳይሆን በውስጡ ያለው አብ ነው ብሎ መከራከር አይችልም። በክፍሉ ላይ መንፈስ መሆኑ የተነገረለት ራሱ ኋለኛው አዳም ወይም ወልድ እንጂ ሌላ ተደራሲ አይደለምና።

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው፥ ሕይወት የሚሰጥ መንፈስም (መለኮት) ደግሞም ኋለኛው አዳምም (ስጋም) ሊባል የቻለው በስጋ ስለለተገለጠ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ 1ቆሮንቶስ 15 በሚጽፍበት ወቅት ስጋዌው ተከናውኖ ስለነበር፥ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መለኮታዊውም ሰዋዊውም ባህርይ አለው ብሎ መናገር ይቻላል። ሐዋርያው በሁለቱም ስያሜ የጠራው ለዚህ ነው።

ማስረጃ ሁለት

“14 ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና። 15 ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል 16 ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል። 17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። 18 እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን” (2ቆሮ 3:14-18)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በክርስቶስ ኢየሱስ የማያምኑ አይሁዳውያን ስለነበሩበት መንፈሳዊ ሁኔታ ይናገራል። በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላመኑ አሳባቸው ደንዝዟል፥ የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ብሉይ ኪዳን ሲነበብ እንኳ ተከድኖባቸዋል (ቁ.14) የዚህ ሁሉ መንፈሳዊ እውርነት መንስኤው በክርስቶስ ባለማመናቸው በመሆኑ፥ ወደ ክርስቶስ ዘወር ሲሉ መጋረጃው ይሻራል። ይህንኑ ሀሳብ በቁ.15 ላይ በመድገም የሙሴ መጻሕፍት ሲነበቡ ያ መጋረጃ በልባቸው እንደሚኖር ገልጾ፥ ወደ ጌታ ዘወር ባለ ጊዜ ግን መጋረጃው እንደሚወሰድ ይናገራል። ይህን ከተናገረ በኋላ ነው በቁ.17 ላይ ጌታ መንፈስ መሆኑን የሚናገረው።

ይህ ክፍል እንዴት የወልድን መንፈስነት እንደሚያሳይ ነጥብ በነጥብ እንመልከት

1) አይሁዳውያን ያላመኑት ማንን ነው?

ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ቆሮ 3:14-18 አይሁዳውያን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለማመናቸው ምክንያት ስላሉበት መንፈሳዊ ጨለማ ይናገራል። ክርስቶስን ባለማመናቸው አሳባቸው ደነዘዘ፥ ብሉይ ኪዳን በተነበበ ጊዜ ሁሉ በልባቸው መጋረጃ ይኖራል። ያ መጋረጃ ግን የሚነሳው በክርስቶስ ነው። በልባቸው ያለው መንፈሳዊ ጨለማ የሚነሳው በእርሱ ሲያምኑ ነው። እስካላመኑበት ድረስ ግን ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል።

ስለዚህ ጥያቄው አይሁዳውያን ያላመኑት በማን ነው? የሚል ይሆናል

መጽሐፍ ቅዱስ አይሁዳውያን ያላመኑት፥ እርሱን ባለማመናቸውም ምክንያት መንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ የገቡት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ይናገራል፦

“63 ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም። አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው። 64 ኢየሱስም። አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው። 65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ። ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ” (ማቴ 26:63-65)

“61 እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና። የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው። 62 ኢየሱስም። እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ። 63 ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና። ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል? 64 ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ። ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት” (ማር 14:61-64)

“70 ሁላቸውም። እንግዲያስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን? አሉት። እርሱም። እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትላላችሁ አላቸው። 71 እነርሱም። ራሳችን ከአፉ ሰምተናልና ከእንግዲህ ወዲህ ምን ምስክር ያስፈልገናል? አሉ” (ሉቃ 22:70-71)

“እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር” (ዮሐ 5:18)

“አይሁድም መልሰው። እኛ ሕግ አለን፥ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባዋል፥ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና አሉት” (ዮሐ 19:7)

➢ ስለዚህ ይህን የእግዚአብሔርን ልጅ ስላላመኑ በ2ቆሮ 3:14-18 ላይ ያለው መንፈሳዊ ጨለማና የሀሳብ መደንዘዝ ውስጥ ገብተዋል። ነገር ግን ወዳልተቀበሉት ወደ ክርስቶስ ሲዞሩ መጋረጃው ይሻራል።

ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያለው መጋረጃ የሚሻረው በእግዚአብሔር ልጅ ነው! ሳይቀበሉት የቀሩት እርሱን ስለነበር፥ ወደ እርሱ ሲዞሩ ይሻራል ሲል እያመለከተ ያለው ራሱን ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ልጅ ነው። ከመጀመሪያውም ያልተቀበሉት እርሱን ነውና

አይሁዳውያን እግዚአብሔር አብን አንቀበልም አይሉም፥ ምንም እንኳ ያለ ልጁ አብን ማወቅ ባይቻልም በአብ እንደሚያምኑ ይናገሩ ነበር (ዮሐ 8:41) እነርሱ አንቀበልም ያሉት የእግዚአብሔርን ልጅ ነው። ስለዚህ ዘወር አሉ ከተባለም ዘወር ማለት ያለባቸው ወደዚህ ወዳልተቀበሉት የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ይህ በ2ቆሮ 3:14 ላይ ክርስቶስ የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያረጋግጣል።

በ2ቆሮ 3:14 ክርስቶስ የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የምናውቅበት ሌላኛው መንገድ፥ ሐዋርያው ጳውሎስ በዚያው በ2ቆሮንቶስ መጽሐፍ ውስጥ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በመግለጹ ነው፦

“በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል” (2 ቆሮ 1:19)

በመጀመሪያው የቆሮንቶስ መልእክቱ ላይም ክርስቶስ ወልድ መሆኑን ገልጿል፦

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (1ቆሮ 1:9)

✍️ ከዚህ ባሻገርም በሌሎች መልእክቶቹም ላይ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተናግሯል፦

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” (ገላ 2:20)

✍️ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊያንም ክርስቶስ የሚባለው ወልድ እንደሆነ በተደጋጋሚ ተገልጿል፦

“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው” (1ዮሐ 1:3)

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7)

“ትእዛዚቱም ይህች ናት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ” (1ዮሐ 3:23)

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

“ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ” (2ዮሐ 1:3)

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ ብቻ ነው። አብ አንድም ቦታ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቶ አያውቅም። ስለዚህ በ2ቆሮ 3:14-18 ላይም ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ መሆኑን ከራሱ ከ2 ቆሮንቶስ መጽሐፍ፥ ከመጀመሪያው የቆሮንቶስ መጽሐፍና ከተቀረው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ እናረጋግጣለን። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው ሁሌም ቢሆን ክርስቶስ የሚባለው ወልድ ነው። እንደውም ከላይ በጠቀስናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ አብ ከክርስቶስ በማንነት ተለይቶ ተጠርቷል። ይህ በእርግጥም በ2ቆሮ 3:14-18 ክርስቶስ የተባለው ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

ክርስቶስ የሚለው ቃል በግሪክ “ኽሪስቶስ/Χριστός” የሚለው ሲሆን ትርጉሙም “የተቀባ/the anointed one” ማለት ነው (Strong’s Concordance G3444) ስለዚህ በዚህ ስያሜ የሚጠራው አካል የተቀባ አካል ነው ማለት ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ ነው፦

“8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል” (ዕብ 1:8-9)

በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ” (ሐዋ 4:27-28)

በዕብ 1:8-9 እና በሐዋ 4:27-28 ላይ “ቀባህ” እና “የቀባኸው” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ኤኽሪሴን/ἔχρισέν” የሚለው ቃል ሲሆን መቀባትን ያመለክታል። “ኽሪስቶስ” የሚለውም ቃል የመጣው ከዚሁ ቃል ነው። ስለዚህ በ2ቆሮ 3:14-18 ሆነ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ “ክርስቶስ” ተብሎ የተጠራው አብ ነው ማለት አይቻልም። አብ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቷል ከተባለ አብ ተቀብቷል ማለት ይሆናል። አብ ተቀብቷል የሚል አስተምህሮ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሌለ ሁሌም ክርስቶስ የሚባለው ወልድ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

ከላይ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ እንደተመለከትነው ወልድ አምላክ ነው (1ዮሐ 5:20 ዕብ 1:8) ይህ አምላክ የሆነው ወልድ የተቀባ ሊሆን የቻለው ሊቀባ የሚችልን ባህርይ የሰውነትን ባህርይ የራሱ በማድረጉ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የሚችለው ሰው ሲሆን (1ሳሙ 16:13 1ሳሙ 10:1) ወልድ ሊቀባ የቻለው መለኮት ስላልሆነ ሳይሆን ከዚህ ከመጣበት የሰውነት ባህርይ (ሮሜ 8:3 ፊል 2:7) የተነሳ ነው።

ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ ነው ማለቱ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጥያቄ የሌለው እውነታ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ለሐዋርያት እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ይህ አወዛጋቢ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ለእነርሱ ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራው አብም ወልድም ነው። ክርስቶስ ሲል ሁሌም ወልድን ነው የሚያመለክተው የሚል ክርስቲያናዊ አረዳድ የላቸውምና። ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ ክርስቶስ የተባለው ወልድ መሆኑን በማስረጃ ማስረዳት አለብን

2) በ2ቆሮ 3:14 ላይ ክርስቶስ/የእግዚአብሔር ልጅ በዚያው አውድ ጌታ መሆኑ ተገልጿል

በ2ቆሮ 3:14 ላይ ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፥ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና ይላል። ይህ ማለት ያ ያሉበት መንፈሳዊ እውርነት የሚሻረው በክርስቶስ ነው ማለት ነው። ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው ደግሞ ክርስቶስ የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ ነው

በሚያስገርም ሁኔታ በቁ.14 ላይ የተነገረው ሀሳብ በቁ.15-16 ላይ ተደግሞ እንመለከታለን። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፥ ወደ ጌታ ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል ይላል። በቁ.14 ላይ ያለው ራሱ ሀሳብ ተደግሟል። ልዩነቱ ግን በቁ.14 ላይ መጋረጃው በክርስቶስ ይሻራል ብሎ፥ በቁ.15-16 ላይ ግን ወደ ጌታ ዘወር ባለ ጊዜ ይሻራል በማለት ክርስቶስን/የእግዚአብሔርን ልጅ ጌታ ብሎ ይጠራዋል። በቁ.14 ላይ ክርስቶስ/የእግዚአብሔር ልጅ ይሰራዋል ያለውን ነገር በቁ.15-16 ላይ ጌታ ይሰራዋል ብሏልና። ያ ጌታ ራሱ ክርስቶስ/ወልድ ነው

✍️ ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ቆሮ 3:15-16 ጌታ የሚለው ወልድን/ክርስቶስን እንደሆነ የምናውቅበት ሌላኛው መንገድ በመጀመሪያው የቆሮንቶስ መልእክቱ ወልድን/ክርስቶስን ጌታ ብሎ መጥራቱ ነው፦

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (1ቆሮ 1:9)

✍️ በሌሎቹ መልእክቶቹም ወልድን/ክርስቶስን ጌታ ብሎ ጠርቶታል፦

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

“8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል 10 ደግሞጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ 11፤ እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ 12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል” (ዕብ 1:8-12)

➢ ስለዚህ በሌሎች መልእክቶቹም ሐዋርያው ጳውሎስ ወልድ ጌታ እንደሆነ መናገሩ፥ በ2ቆሮ 3:15-16 ላይ ጌታ ያለው ክርስቶስን/ወልድን እንደሆነ ተጨማሪ ማሳያ ነው።

3) በቁ.15-16 ጌታ የተባለው ክርስቶስ/ወልድ መንፈስ መሆኑ በቁ.17 ላይ ተገልጿል

በቁ.14 ላይ የተጠቀሰው ክርስቶስ/ወልድ በቁ.15-16 ጌታ ተብሏል። አውዱና ያደርጋል የተባለው ነገር (መጋረጃውን ማንሳቱ) ጌታ የተባለው ራሱ ክርስቶስ/ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። በተጨማሪም በሌሎቹ መልእክቶቹ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስን/የእግዚአብሔርን ልጅ ጌታ ብሎ ጠርቶታል። ይህ በእርግጥም በቁ.15-16 ላይ ጌታ እያለ ያለው ክርስቶስን/የእግዚአብሔርን ልጅ እንደሆነ ተጨማሪ ማሳያ ነው

በቁ.16 ላይ ጌታ ያለውን ክርስቶስን/ወልድን በቁ.17 ላይ መንፈስ መሆኑን ይናገራል፦

ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ” (2ቆሮ 3:17)

ከላይ ለማየት እንደሞከርነው በአውዱ “ክርስቶስ” እየተባለ ያለው “ጌታ” እየተባለ ያለው ወልድ መሆኑን በአውዳዊና በሁሉን-አቀፋዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች አይተናል። በ2ቆሮ 3:14-18 ዋና ተደራሲ ሆኖ “ክርስቶስ” እና “ጌታ” የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው። ስለዚህም በአውዱ መሰረት ፍሰቱን ጠብቆ ቁ.17 ላይ መንፈስ እንደሆነ የተነገረለት ጌታ ወልድ ነው። ይህ ወልድ መንፈስ ለመሆኑ ግልጽና ማስረጃ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስ ወልድ መንፈስ መሆኑን አስቀድሞ በመጀመሪያ የቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ እንደተናገረ አይተናል (1ቆሮ 15:45) ኋለኛው አዳም ወይንም ወልድ ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ እንደሆነ ገልጾ ነበር። ስለዚህ በሁለተኛው የቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስን መንፈስ ብሎ ሲጠራው ቀድሞ የተናገረውን ነገር በድጋሚ በመናገር እያረጋገጠውና አጽንዖት እየሰጠው ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ከላይ ለመናገር እንደሞከርነው ከአውዱ ባሻገር ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ቆሮ 3:17 ጌታ የሚለው ወልድን/ክርስቶስን እንደሆነ የምናውቅበት ሌላኛው መንገድ በመጀመሪያው የቆሮንቶስ መልእክቱ ወልድን ጌታ ብሎ መጥራቱ ነው (1ቆሮ 1:9) በሌሎቹ መልእክቶቹም ወልድን ጌታ ብሎ ጠርቶታል (ሮሜ 1:3-4 ዕብ 1:8-12) ስለዚህ ከ2ቆሮ 3:14-18 አውድና ከላይ እንደተጠቀሱት አይነት ሌሎች ተያያዥ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተነስተን በ2ቆሮ 3:17 መንፈስ እንደሆነ የተገለጸው ጌታ ወልድ መሆኑን እናረጋግጣለን።

4) በ2ቆሮ 3:14-18 መንፈስ ለሆነው ጌታ የተባሉት ነገሮች ለወልድ ተብለዋል

በ2ቆሮ 3:14-18 ላይ መንፈስ ለሆነው ጌታ የተባሉት ነገሮች በሙሉ ለወልድ የተባሉ ነገሮች ናቸው። በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ወልድ ጌታ መባሉ በዚህ ክፍል ላይ መንፈስ የሆነው ጌታ እርሱ ለመሆኑ ማሳያ እንደሆነው ሁሉ በዚህ ክፍል ላይ መንፈስ ስለሆነው ጌታ የተባሉት ሌሎች ነገሮችም በ2ቆሮ 3:14-18 መንፈስ ነው የተባለለት ጌታ ወልድ ለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃዎች ናቸው። እንመልከተው፦

ሀ) በ2ቆሮ 3:14-10 ላይ ያለው ጌታ መንፈሳዊ አብርሆት ይሰጣል

“14 ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና። 15 ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል 16 ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል” (2ቆሮ 3:14-16)

✍️ በዚህ ክፍል ላይ አይሁዳውያን ክርስቶስን ባለመቀበላቸው ምክንያት ያለባቸው መጋረጃ ወይንም ግርዶሽ የሚነሳው በዚህ መንፈስ በሆነው ጌታ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ ቦታ ላይ የተባለው ነገር መንፈስ የሆነው ጌታ ልጁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም ለሰዎች መንፈሳዊ አብርሆትን የሚሰጠው ልጁ ነውና፦

“ስለዚህ አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል ይላል” (ኤፌ 5:14)

በዚህ ስፍራ ላይ ተኝቶ ለነበረ ሰው ብርሃንን የሚያበራው ክርስቶስ እንደሆነ ተገልጿል። ክርስቶስ ያበራልሃል ማለት መንፈሳዊ አብርሆትን የሚሰጠው እርሱ ነው ማለት ነው። ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው “ክርስቶስ” የሚለው የግሪክ ቃል የተቀባ ማለት ሲሆን በዚህ ስያሜ የሚጠራው የተቀባ አካል ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ በመሆኑ (ዕብ 1:8-9 ሐዋ 4:27-28) በኤፌ 5:14 ለተኛው ሰው ያበራለታል የተባለው ክርስቶስ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

ሲቀጥል በዚያው በኤፌሶን 5 አውዱ ይህ የሚያበራልን ክርስቶስ መስዋዕት ሆኖ እንደነበር ተገልጿል፦

“ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ” (ኤፌ 5:2)

ስለዚህ ይህ ተኝቶ ለነበረው ሰው የሚያበራው ክርስቶስ ራሱን መስዋዕት አድርጎ የሰጠው ክርስቶስ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ መስዋዕታዊ ሞት (sacrificial death) የሞተው ወልድ ነው (ዕብ 1:2 ዕብ 9:28 ዕብ 10:12-13 ሮሜ 5:10) ስለዚህ በኤፌሶን 5 ላይ መስዋዕት ሆኗል የተባለው፥ የተኛውም ሰው እንዲነቃ የሚያበራለት ክርስቶስ ወልድ ማለት ነው። አብ መስዋዕት ሆነ የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የለም። ስለዚህ አይሁዶች ዓይናቸው እንዲበራ ወደ እርሱ ዘወር ሊሉ የሚገባው መንፈስ የሆነው ጌታ ወልድ ነው ማለት ነው።

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

በዚህ ስፍራ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነተኛ የሆነውንም እናውቅ ዘንድ ልቦናን እንደ ሰጠን እናውቃለን ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔርን እናውቅ ዘንድ መንፈሳዊ አብርሆትን የሰጠን የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ይህ አይሁዶች ዓይናቸው እንዲበራ ወደ እርሱ ዘወር ሊሉ የሚገባው መንፈስ የሆነው ጌታ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ያሳያል።

ለ) መንፈስ ቅዱስ በ2ቆሮ 3:14-18 ላይ የተጠቀሰው ጌታ መንፈስ ነው

“ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ” (2ቆሮ 3:17)

✍️ በዚህ ቦታ ላይ መንፈስ ቅዱስ መንፈስ መሆኑ የተነገረለት ጌታ መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ በዚህ ክፍል ላይ መንፈስ ነው የተባለው ጌታ ልጁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የልጁ መንፈስ ነው፦

“ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ” (ገላ 4:6)

በገላ 4:6 እንደተገለጸው በአማኞች ውስጥ የተላከው መንፈስ የልጁ መንፈስ ነው። አማኞች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ሲሆኑ (1ቆሮ 3:16) ይህ በእነርሱ የሚኖረው መንፈስ የልጁ መንፈስ እንደሆነ በገላ 4:6 ተገልጿል። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የልጁ መንፈስ መሆኑ በ2ቆሮ 3:14-16 ላይ የተገለጸው መንፈስ የሆነው ጌታ ልጁ መሆኑን ያረጋግጣል። በሁለቱም ስፍራዎች መንፈስ ቅዱስ የእርሱ መንፈስ መሆኑ ተገልጿልና።

“እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም” (ሮሜ 8:9)

በዚህ ስፍራ ላይም መንፈስ ቅዱስ የወልድ መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። ማንም የክርስቶስ መንፈስ ከሌለው የክርስቶስ ወገን እንዳልሆነ ይናገራል። እውነተኛ አማኞች የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያዎች ሲሆኑ (ሐዋ 13:9) ይህ በእነርሱ ዘንድ ያለው መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ መንፈስ ነው። ክርስቶስ የሚለው ቃል የተቀባለ ማለት ሲሆን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ ነው (ዕብ 1:8-9 ሐዋ 4:27-28) ስለዚህ የክርስቶስ መንፈስ ማለት የወልድ መንፈስ ማለት ነው። ይህ በ2ቆሮ 3:14-18 ላይ መንፈስ የተባለው ጌታ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። በዚያም ክፍል ላይ መንፈስ ቅዱስ የእርሱ መንፈስ መሆኑ ተገልጿልና

“በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር” (1ጴጥ 1:11)

በዚህ ስፍራ ላይም መንፈስ ቅዱስ የወልድ መንፈስ መሆኑ ተገልጾ እንመለከታለን። የጥንት ነቢያት የተናገሩበት መንፈስ የክርስቶስ መንፈስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። የብሉይ ኪዳን ነቢያት ይናገሩ የነበሩት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሲሆን (ሕዝ 3:22-24 ሕዝ 11:5) ይህ የተናገሩበት መንፈስ የክርስቶስ መንፈስ ነበር። ክርስቶስ ወይም የተቀባው ደግሞ ወልድ በመሆኑ (ዕብ 1:8-9 ሐዋ 4:27-28) የክርስቶስ መንፈስ ማለት የወልድ መንፈስ ማለት እንደሆነ ያሳያል። ይህ በ2ቆሮ 3:14-18 ላይ መንፈስ የተባለው ጌታ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። በዚያም ክፍል ላይ መንፈሱ የእርሱ እንደሆነ ተገልጿልና።

ሐ) አማኞች በ2ቆሮ 3:14-18 ላይ የተጠቀሰውን መንፈስ የሆነውን ጌታ መምሰል አለብን

“17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። 18 እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን” (2 ቆሮ 3:17-18)

✍️ በዚህ ቦታ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች መንፈስ እንደሆነ የተነገረለትን ጌታ መምሰል እንዳለባቸው ይናገራል። ይህ በዚህ ክፍል ላይ መንፈስ ነው የተባለው ጌታ ልጁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም እንደ እግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ አማኞች መምሰል ያለባቸው ልጁን ነው፦

“ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና” (ሮሜ 8:29)

በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞች የልጁን መልክ እንዲመስሉ ቀድሞም እንደተወሰነ ሲናገር እንመለከታለን። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የክርስቶስ ወንድሞች የሚባሉት አማኞች ሲሆኑ (ዕብ 2:13-15) እርሱ በእነርሱ መካከል በኩር ይሆን ዘንድ መምሰል ያለባቸው እሱን እንደሆነ ተገልጿል። ስለዚህ በሁለንተና ልንመስለው የሚገባው ወልድ ያ የእርሱን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን የተባለለት መንፈስ የሆነው ጌታ እንደሆነ ያሳያል።

“እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ” (1ቆሮ 11:1)

በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እርሱ ክርስቶስን እንደሚመስል ክርስቲያኖችም እርሱን እንዲመስሉ ሲያዝ እንመለከታለን። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስን ከመሰለ አማኞች ሁሉ (ሐዋርያትንም ጨምሮ) ሊመስሉት የሚገባው ክርስቶስን እንደሆነ ያረጋግጣል። ክርስቶስ ወይም የተቀባው ተብሎ የሚጠራው ደግሞ የተቀባው ወልድ በመሆኑ (ዕብ 1:8-9 ሐዋ 4:27-28) እኔ ክርስቶስን እንደምመስል ማለት እኔ ወልድን እንደምመስል ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። በተጨማሪም በ1ቆሮንቶስ 11 አውድ ክርስቶስ የተባለው እግዚአብሔር ራሱ የሆነለት ወልድ እንደሆነ ተገልጿል (1ቆሮ 11:3) ስለዚህ በአውዱ ክርስቶስ የተባለው ወልድ ነው። ይህ ማለት ልንመስለው የሚገባው ወልድ ያ የእርሱን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን የተባለለት መንፈስ የሆነው ጌታ እንደሆነ ያረጋግጣል።

ስለዚህ ከላይ ጀምሮ በአውዱና ከአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንጻር ስንመለከተው በ2ቆሮ 3:14-18 መንፈስ እየተባለ ያለው ወልድ ነው። ወልድ መንፈስ እንደሆነ ጊዜው ሲደርስ ግን በስጋ እንደተገለጠ ከሚያረጋግጡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች አንዱ ይህ ነው።

ማስረጃ ሶስት

“5 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። 6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ 7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ 8 በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” (ፊል 2:5-8)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ትህትና ሲያስተምር እንመለከታለን። እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር (ቁ.3) ካለ በኋላ ለትህትና ታላቁን ምሳሌ ያነሳል። እርሱም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ሀሳብ በእናንተ ዘንድ ይሁን ካለ በኋላ (ቁ.5) ስለ ክርስቶስ ዘላለማዊ አኗኗር መናገር ይጀምራል።

እርሱም በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ፥ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም። ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ ይላል።

✍️ ይህ ወልድ መንፈስ እንደነበረው የሚያሳየው እንዴት ነው?

ፊሊ 2:5-8 ወልድ መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያሳያል። ነጥብ በነጥብ እንመልከተው።

1) በፊሊ 2:5-8 እየተወራ ያለው ስለ ማን ነው?

እኛ ክርስቲያኖች በፊሊ 2:5-8 ላይ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ እናውቃለን። ጥያቄ የሚነሳበትም ጉዳይ አይደለም። ነገር ግን የሐዋርያት ቤተ-እምነት ወገኖቻችን ፊሊ 2:5-8 ላይ እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ ነው ብለው አያምኑም። ፊሊ 2:5-8 እየተናገረ ያለው እግዚአብሔር ስለሚናገረው ንግረተ-ቃል ነው የሚል አስተምህሮ አላቸው። ይህ ግን ስህተት ነው።

ምክንያቱም በፊሊ 2:5-8 እየተወራ ያለው ስለ ወልድ ነው። ስለ ወልድ እየተወራ መሆኑን በብዙ መንገዶች ማወቅ እንችላለን። አንድ በአንድ እንየው

ሀ) በቁ.5 ላይ “በክርስቶስ ኢየሱስ” የነበረ ሀሳብ ይላል

በቁ.5 ላይ “በክርስቶስ ኢየሱስ” የነበረ ሀሳብ በእናንተ ዘንድ ይሁን ይላል። ከላይ ባሉት ቁጥሮች ላነሳው የትህትና ሀሳብ ትልቁ ምሳሌ እርሱ ነውና። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ “ኢየሱስ ክርስቶስ” የሚለው ስም የወልድ ስም ነው፦

“ትእዛዚቱም ይህች ናት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ” (1ዮሐ 3:23)

“31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። 32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል” (ሉቃ 1:31-32)

✍️ “ኢየሱስ ክርስቶስ” የሚለው መጠሪያም እንደ መጠሪያ ያገለገለው ለወልድ ነው፦

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (1ቆሮ 1:9)

“በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል” (2 ቆሮ 1:19)

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው” (1ዮሐ 1:3)

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7)

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

“ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ” (2ዮሐ 1:3)

➢ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ እንደሚጠራ ከመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ በጣም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። በተቃራኒው ግን አብም ሆነ መንፈስ ቅዱስ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብለው የተጠሩበት አንድም አጋጣሚ የለም።

ወይንም ደግሞ ወልድን ያልሆነ ንግረተ-ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራበት አንድም ቦታ የለም። ስለዚህ በፊሊ 2:5 ላይ “በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ሀሳብ” ማለቱ ያ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ነበር የተባለለት ማንነት ወልድ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የወልድ ስያሜ ነውና

ሲቀጥል በፊሊ 2:5 ላይ “በክርስቶስ” ኢየሱስ የነበረ ሀሳብ ይላል። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው “ክርስቶስ” የሚለው ቃል በግሪክ “ኽሪስቶስ/Χριστός” የሚለው ሲሆን ትርጉሙም “የተቀባ/the anointed one” ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ስያሜ የሚጠራው አካል የተቀባ አካል ነው ማለት ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ ነው፦

“8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል” (ዕብ 1:8-9)

በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ” (ሐዋ 4:27-28)

በዕብ 1:8-9 እና በሐዋ 4:27-28 ላይ “ቀባህ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ኤኽሪሴን/ἔχρισέν” የሚለው ቃል ሲሆን መቀባትን ያመለክታል። “ኽሪስቶስ” የሚለውም ቃል የመጣው ከዚሁ ቃል ነው። ስለዚህ በፊሊ 2:5 ሆነ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ “ክርስቶስ” ተብሎ የተጠራው አብ ነው ማለት አይቻልም። አብ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቷል ከተባለ አብ ተቀብቷል ማለት ይሆናል። አብ ተቀብቷል የሚል አስተምህሮ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሌለ ሁሌም ክርስቶስ የሚባለው ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል።

በፊሊ 2:5 ላይ “ክርስቶስ ኢየሱስ” የተባለው ንግረተ-ቃል ሳይሆን ራሱ አብ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህ ግን ትክክል አይደለም። ምክንያቱም ቀጥሎ በቁ.6 ላይ በእግዚአብሔር/አብ መልክ ሲኖር እንደነበር ተገልጿል። ስለዚህ በቁ.5 ላይ “ክርስቶስ ኢየሱስ” የተባለው አብ ከሆነ፥ አብ በአብ መልክ ሲኖር ነበር ወደሚል absurdity ያመራል። ከዚህ የተነሳ በቁ.5 ላይ “ክርስቶስ ኢየሱስ” የተባለው ሁሌም በዚህ ስም የተጠራው ወልድ እንጂ አብ ሊሆን አይችልም።

ለ) በቁ.7 ላይ የባሪያን መልክ ይዞ በሰው ምሳሌ ሆነ ይላል

በፊሊ 2:5-8 እየተወራ ያለው ስለ ወልድ መሆኑን ሌላው የምናውቅበት መንገድ፥ በቁ.7 ላይ የባሪያን መልክ ይዞ በሰው ምሳሌ ሆነ ማለቱ ነው። ይህ ማለት በእግዚአብሔር መልክ ሲኖረው የነበረው ማንነት የባሪያን መልክ በመያዝ ሰው ሆኖ መጥቷል ማለት ነው። ይህ በፊሊ 2:5-8 እየተወራ ያለው ስለ ወልድ ለመሆኑ ሌላኛው ማረጋገጫ ነው

✍️ ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ሰው ሆኖ የመጣው ወልድ ነው፦

“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ” (ሮሜ 8:3-4)

➢ በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር ከሥጋ የተነሳ ስለደከመ፥ ለሕግ ያልተቻለውን የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ እንደላከ ሲናገር እንመለከታለን። ስለዚህ በሮሜ 8:3 በስጋ የመጣው፥ የስጋ ባህርይን የራሱ ያደረገው ልጁ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ፊሊ 2:5-8 ላይ እንደሚለው የባሪያን መልክ በመያዝ ሰው ሆኖ የመጣው ሮሜ 8:3 ላይ በስጋ ተልኮ መምጣቱ የተነገረለት ወልድ ነው ማለት ነው። ስለዚህ በፊሊ 2:5-8 እየተወራ ያለው ስለ እግዚአብሔር ልጅ ነው

“13 ስለዚህም ምክንያት። ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም። እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም። እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። 14-15 እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። 16 የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” (ዕብ 2:13-16)

✍️ በዚህ ስፍራ ላይ የዕብራዊያኑ ጸሐፊ ስለ ክርስቶስ ስጋዌ ሲናገር እንመለከታለን። በቁ.13 ላይ ጸሐፊው በመንፈስ ቅዱስ ጠንሳሽነት “እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች” የሚለውን የክርስቶስን ንግግር ከዘገበ በኋላ ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው እንደማያፍር ይገልጻል። ስለዚህ በቁ.14-15 እርሱ እየተባለ ያለው ወንድሞች ያሉት ማንነት ነው ማለት ነው። በቀጣዩ ቁጥር እየተወራ ያለው እግዚአብሔር ልጆቹን ስለ ሰጠው፥ ልጆቹም ወንድሞቹ ስለ ሆኑለት አካል ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ወንድሞች ያሉት ወልድ እንደሆነ ይናገራል፦

ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና” (ሮሜ 8:29)

ስለዚህ በዕብ 2:13-16 እየተወራ ያለው ስለ ወልድ ነው ማለት ነው። ለዚያም ነው ቁ.13 ላይ ራሱን በማንነት ከእግዚአብሔር/ከአብ ነጥሎ “እግዚአብሔር የሰጠኝ” ያለው። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ወልድ ነውና። ስለዚህ በቀጣዮቹ ቁጥሮች ላይ የተባለው ነገር በሙሉ ስለ ወልድ የተባለ ነገር እንደሆነ በዚህ እናረጋግጣለን።

ቀጥለው ባሉት በቁ.14-15 ላይ ይህ ወንድሞች ያሉት ማንነት ወይም ወልድ፥ ልጆቹ በስጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ በተጨማሪም በሞት ላይ ስልጣን ያለውን እርሱም ዲያቢሎስን ሊሽር፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በስጋና በደም ተካፈለ ይላል። ወይንም ስጋና ደም ያለው ሰው ሆነ

ስለዚህ ከዕብ 2:14-15 እንደምንረዳው ስጋና ደምን በመካፈል ሰው የሆነው ወንድሞች ያሉት ወልድ ነው። ይህ በፊሊ 2:7 ላይ የባሪያን መልክ ይዞ ሰው የሆነው ማንነት ይህ ራሱ ወንድሞች ያሉት ወልድ ለመሆኑ ማስረጃ ነው። በፊሊ 2:5-8 ላይ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ ከዕብ 2:14-15 መረዳት እንችላለን። በዕብ 2:13-16 ላይ በስጋና በደም የተካፈለው ወልድ መሆኑ ተገልጿልና

✍️ ይህ እውነታ ደግሞ በዕብ 2:16 አጽንኦት ተሰጥቶት ተነግሯል

“የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” (ዕብ 2:16)

ከቁ.14 ጀምሮ ስጋና ደምን ስለመካፈል ወይም በስጋ ስለመምጣት በተነገረበት በዚያው አውድ ቁ.16 ላይ ያው ራሱ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃምን ዘር እንደያዘ ተገልጿል። አውዱ ስጋና ደምን ስለመካፈል ስለሆነ የሚናገረው፥ የአብርሃምን ዘር ይዟል ሲል ስለዚያ ስጋና ደም መካፈል ወይንም በስጋ ስለመምጣት እየተናገረ እንደሆነ ግልጽ ነው። ያ ወንድሞች ያሉት ወልድ የአብርሃምን ዘር በመያዝ ስጋና ደምን ተካፍሏል።

➢ ለእኛ ለክርስቲያኖች ይህ ምንም ጥርጥር የሌለበት እውነታ ቢሆንም ለሐዋርያት እምነት ተከታዮች ግን አይደለም። እንደ እነርሱ አረዳድ ዕብ 2:16 የሚያመለክተው ስጋዌን ከሚያመለክተው አውዱ ተገንጥሎ ርዳታን ወይም እገዛን ነው። አውዱ ግን ይህን አይፈቅድም። በአውዱ እየተነገረ ያለው በስጋና በደም ስለ መካፈል ስለሆነ፥ ወንድሞች ያሉት ወልድ የአብርሃምን ዘር መያዙ ሰው ሆኖ መምጣቱ እንደሆነ እንረዳለን።

ሌላው አስገራሚው ነጥብ ፊሊ 2:7 እና ዕብ 2:16 ስጋዌውን የገለጹበት መንገድ አንድ አይነት መሆኑ ነው። በሁለቱም ክፍሎች ስጋዌው የተከናወነው “በመያዝ” እንደሆነ ተገልጿል። ፊሊ 2:7 ላይ “..የባሪያን መልክ #ይዞ..” የሚል ሲሆን፥ ዕብ 2:16 ላይ ደግሞ “..የአብርሃምን ዘር ይዞአል..” ይላል። የተጠየቀሙትም የግሪክ ቃል አንድ አይነት ቃል ነው። ይህ ከምንም በላይ በፊሊ 2:5-8 ላይ የባሪያን መልክ ያዘ የተባለለት በዕብ 2:13-16 ስጋና ደምን ተካፈለ የተባለለት ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

ሐ) በቁ.6 ላይ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚተካከል ተገልጿል

በፊሊ 2:5-8 እየተወራ ያለው ስለ ወልድ መሆኑን የምናውቅበት ሌላው መንገድ፥ በቁ.6 ላይ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከሉ ተገልጿል። ምንም እንኳ መቀማት እንደሚገባ ባይቆጥረውም ከእግዚአብሔር ጋር መተካከል ወይም እኩልነት/equality አለው። ይህ በፊሊ 2:5-8 እየተወራ ያለው ስለ ወልድ ለመሆኑ ሌላኛው ማረጋገጫ ነው

✍️ ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከአብ ጋር የሚተካከለው ወልድ ነው፦

“17 ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። 18 እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር” (ዮሐ 5:-17-18)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ እንደጠራው ሲናገር እንመለከታለን። በዮሐ 5:18 ተናጋሪው አይሁዳውያኑ ሳይሆኑ ራሱ ሐዋርያው ዮሐንስ ነው። ክርስቶስ አባቴ እስከ ዛሬ ይሰራል እኔም እሰራለሁ ሲል ይህን ያለው ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን እኩልነት በሚያሳይ መንገድ እንደሆነ ሐዋርያው ዮሐንስ እየተረጎመልን ነው። በአብና በወልድ መካከል የስራ አንድነት እንዳለና ያም የስራ አንድነት ከእኩልነት የተነሳ እንደሆነ ክፍሉ ያስረዳል።

በዮሐ 5:17-18 ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚተካከል የተነገረለት ወልድ ነው። በቁ.17 ላይ “..አባቴ ይሰራል..” በማለቱ ይህ ከአብ ጋር የስራ አንድነት ያለው ማንነት አባት ያለው ማንነት እንደሆነ ያሳያል። እርሱም ወልድ ነው። ቀጥሎም በቁ.18 ላይ “ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ እግዚአብሔርን አባቴ ስላለ” ማለቱን ሐዋርያው ዮሐንስ በመግለጹ፥ ይህ ከእግዚአብሔር ጋር የሚተካከለው ማንነት እግዚአብሔር አባቱ የሆነለት ልጁ ወልድ እንደሆነ ያሳያል።

▶️ ስለዚህ በፊሊ 2:5-8 ላይ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ነበር፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ባለመቁጠር የባሪያን መልክ በመያዝ ሰው ሆነ የተባለለት ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህን ከክፍሉም አውድ፥ ከተቀረውም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ አይተናል

ስለዚህ አሁን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ…በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ማለት ምን ማለት ነው? የሚለው መሆን አለበት። በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ማለት ምን ማለት ነው?

➢ በፊሊ 2:6 ላይ መልክ ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ሞርፊ/μορφή” የሚለው ቃል ሲሆን “ባህርይ/nature” ወይም “ሕላዌ/essence” የሚል ትርጉም አለው።

የLexicon ማስረጃ፦

“Perhaps from the base of meros (through the idea of adjustment of parts); shape; figuratively, nature — form” (Strong’s 3334)

“properly, form (outward expression) that embodies essential (inner) #substance so that the form is in complete harmony with the inner essence” (HELPS Word)

✍️ ስለዚህ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ነበር ማለት በእግዚአብሔር ባህርይ ሲኖር ነበር ማለት ነው። ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ባህርይ ሆኖ ይኖር ነበር ማለት ነው። ሲኖርበት የነበረው መልክ/ባህርይ የእግዚአብሔር/የአብ ነው። ይህ ማለት በእርሱና በአብ መካከል የባህርይ አንድነት አለ ማለት ነው

ለዚያም ነው በፊሊ 2:7 ላይ አንድ መልክ ብቻ የተጠቀሰው። ፊሊ 2:7 “በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ” ይላል እንጂ “እግዚአብሔር መልኮች ሲኖር ሳለ” አይልም። መልኩ ነጠላ ነው። እንዲህ ሊባል የቻለበት ምክንያቱም የአብም የልጁ የኢየሱስም የሆነው ባህርይ አንድ ነጠላ ብቻ ስለሆነ ነው። ልጁ ኢየሱስ ከአባቱ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ባህርይ ነው የምንለውን ለዚህ ነው። በአንዱ የእግዚአብሔር መልክ/ባህርይ ሲኖር ነበርና

ስለዚህ ወልድ ክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር አብ ባህርይ ይኖር ስለነበር፥ እግዚአብሔር አብ በባህርይው የሆነውን ነገር ሁሉ ለእርሱም ነው። ከዚያ የአብም የእርሱም (የወልድም) ከሆነው አንዱ ባህርይ የተነሳ ለአብ የተባለው ነገር ለወልድ ተብሏል፥ አብ በባህርይ የሆነውን ነገር ሁሉ ወልድም ነው። ለዚህ ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት፦

1) አብ አምላክ ተብሏል (ዮሐ 6:27)

    ወልድ አምላክ ተብሏል (ዕብ 1:8)

2) አብ ጌታ ተብሏል (ማቴ 11:25)

    ወልድ ጌታ ተብሏል (1ቆሮ 8:6)

3) አብ አልፋና ዖሜጋ ተብሏል (ራዕ 21:6)

    ወልድ አልፋና ዖሜጋ ተብሏል (ራዕ 22:13)

4) አብ መድኃኒት ተብሏል (1ጢሞ 1:1)

    ወልድ መድኃኒት ተብሏል (2ጴጥ 3:18)

5) አብ ሕይወትን ሰጪ ተብሏል (ዮሐ 5:21)

    ወልድ ሕይወትን ሰጪ ተብሏል (ዮሐ 5:21)

6) አብ ብርሃን ተብሏል (1ዮሐ 1:5)

    ወልድ ብርሃን ተብሏል (ዮሐ 9:5)

7) አብ ሐይል ተብሏል (ማር 14:62)

    ወልድ ሐይል ተብሏል (1ቆሮ 1:24)

ከዚህ የበለጡ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ለአብ የተባሉት ነገሮች ለወልድ ተብለዋል። ምክንያቱ ምንድነው ከተባለ የባህርይ አንድነቱ ነው። ልጁ ኢየሱስ ሲኖር የነበረው በአባቱ መልክ/ባህርይ ስለነበር ከዚያ የባህርይ አንድነት የተነሳ አብ በባህርይው የሆነውን ነገር በሙሉ ወልድም ነው። ወልድ በመልክ/ባህርይ ከአብ ጋር አንድ ሆኖ አብ በባህርይው የሆነውን ነገር ላይሆን አይችልምና።

ስለዚህ መጠየቅ ያለብን አንድ ወሳኝ ጥያቄ…አብ በባህርይው መንፈስ ነው ወይ? የሚለው ነው

መጽሐፍ ቅዱስ አብ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ ያስተምራል፦

“23 ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ 24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል” (ዮሐ 4:23-24)

➢ በዚህ ስፍራ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማርያዊቱ ሴት ጋር ሲነጋገር የነገራትን ነገር እንመለከታለን። እርሷ አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፥ እናንተ (አይሁዳውያን) ደግሞ በኢየሩሳሌም ስገዱ ትላላችሁ ብላ ስትጠይቀው፥ በዚያም ተራራ በኢየሩሳሌምም ለአብ የማይሰግዱበት ጊዜ እንደሚመጣና ለአብ በመንፈስና በእውነት እንደሚሰገድ ነገራት።

ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ እንደሆነና፥ የሚሰግዱለትም በእውነትና በመንፈስ እንደሚሰግዱለት ነገራት። በዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተባለው አብ እንደሆነ ከቁ.23 እንረዳለን። ስለዚህ ክርስቶስ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ሲላት እየተናገረ የነበረው ስለ አባቱ ነበር። በፊሊ 2:5-8 በእርሱ መልክ ሲኖር ነበር የተባለለት አባቱ እግዚአብሔር አብ መንፈስ እንደሆነ ገለጸላት።

✍️ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ማለት ምን ማለት ነው?

እግዚአብሔር መንፈስ ነው ሲባል በባህርይው የማይታይ፥ የማይዳሰስ፥ የማይጨበጥ፥ ረቂቅ ነው ማለት ነው። ቁስ አይደለም ወይም ደግሞ ግዙፍ አካል የለውም ማለት ነው። የመንፈስ ትርጉም ይህ ነውና (ሉቃ 24:39) በዮሐ 4:23-24 መንፈስ የሚለው ቃል ገላጭ/adjective ሆኖ ሲሆን የገባው እግዚአብሔር በምንነቱ ምንድነው የሚለውን የሚመልስ ነው።

አብ በባህርይው መንፈስ ከሆነና፥ ልጁ ደግሞ በእርሱ ባህርይ ሲኖር ከነበር..ልጁ ራሱ ምንድነው ማለት ነው?

መንፈስ በሆነው በእግዚአብሔር አብ ባህርይ ሲኖር የነበረው ወልድ መንፈስ ነበር። እግዚአብሔር አብ መንፈስ ሆኖ በእርሱ ባህርይ ሲኖር የነበረው ወልድ መንፈስ ላይሆን አይችልም። አለዚያ በባህርይው ሲኖር አልነበረም ማለት ነው። በባህርይው ሲኖር ከነበር እርሱ በባህርይው የሆነውን ነገር ሁሉ መሆን አለበት። መንፈስ መሆንን ጨምሮ

ከዚህ በፊት ባየናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ወልድ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ከአብ ጋር ካለው የባህርይ አንድነት የተነሳ ነው። አብ መንፈስ እንደተባለው (ዮሐ 4:23-24) ልጁም መንፈስ ተብሏል። ይህ ሊሆን የቻለው የአብም የወልድም ከሆነው አንድ ባህርይ የተነሳ ነው።

➢ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር አብ መልክ/ባህርይ (ሮሜ 1:20) መንፈስ መሆኑ ተገልጿል (ዮሐ 4:23-24) ስለዚህ በዚያ በራሱ ባህርይ ሲኖር የነበረው ወልድ መንፈስ ነው። በእርሱ መልክ ሲኖር የነበረው ጊዜው በደረሰ ጊዜ የባሪያን መልክ በመያዝ ሰው ሆኖ የመጣው እርሱ ነውና።

ወልድ መንፈስ አይደለም ከተባለ ግን ወልድ በአብ መልክ ሲኖር አልነበረም ማለት ነው። ምክንያቱም አንዱ ማንነት መንፈስ ሆኖ፥ በእርሱ መልክ/ባህርይ ሲኖር የነበረው ሌላኛው ማንነት መንፈስ አይደለም ማለት አይቻልም። በእርሱ መልክ/ባህርይ ሲኖር ነበር ማለት የሁለቱን ማንነቶች ፍጹም የሆነ የባህርይ አንድነት ያሳያልና።

እንደ ክርስትና አስተምህሮ ግን አብና ወልድ አንድ ባህርይ ናቸው (ፊሊ 2:6) ያ አንዱ ባህርይ ደግሞ ቁስ የሆነ ባህርይ ሳይሆን መንፈስ የሆነ ባህርይ ነው። ስለዚህ አብም ወልድም በአንድ አምላክነት አንዱን መንፈስ ናቸው። ያ አንዱ መንፈስ የሆነው ባህርይ የአብም የወልድም ነውና። ለዚያ ነው አብም፥ ወልድም መንፈስ ተብለው የተጠሩት

አብና ወልድ አንዱን መንፈስ ናቸው ስንል፥ አንዱን መለኮት ናቸው እያልን ነው። መንፈስ የሚለውን ቃል በዚህ አውድ እንደ ገላጭ/adjective እንጂ እየተጠቀምነው ያለነው እንደ ስም/proper noun አይደለም። የአብም የወልድም የሆነ አንድ መለኮታዊ ባህርይ አለ። ያ አንድ መለኮታዊ ባህርይ ደግሞ መንፈስ የሆነ ባህርይ እንጂ ቁስ የሆነ ባህርይ አይደለም

ስለዚህ አብና ወልድ አንዱን መንፈስ ናቸው ስንል፥ ያን መንፈስ የሆነውን አንዱን መለኮት ናቸው እያልን ነው። በዚህ አውድ መንፈስ የሚለው ቃል ለመንፈስ ቅዱስ እንደሚውለው ስም/proper noun ሆኖ ሳይሆን የገባው ገለጭ/adjective ሆኖ ነው የገባው። የሐዋርያት ቤተ-እምነት ተከታዮች ብዙ ጊዜ የሚጠቀሙት አገላለጽ ይህ በመሆኑ፥ በእነርሱ አገላለጽ ተጠቅሞ መመለስ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው ነው።

ማስረጃ አራት

“2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ 3 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብ 1:2-3)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ልጁ የእግዚአብሔር የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌና የክብሩ ነጸብራቅ እንደሆነ ይናገራል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የሁሉ ወራሽ ሲሆን፥ ዓለማት ሁሉ የተፈጠሩት በእርሱ ነው። ቀጥሎም ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ እንደተቀመጠ ይገልጻል።

“የባህርይው ምሳሌ” የሚለው ሀረግ ፍጹም የባህርይ አንድነትን የሚያመለክት ቃል ነው። ወልድ የአብ ባህርይ ምሳሌ ነው ማለት አብ በባህርይው የሆነውን ነገር በሙሉ ወልድም በባህርይው ነው ማለት ነው። በዕብ 1:3 መሰረት አብ በባህርይው የሆነውን ነገር ወልድ በባህርይው ላይሆነው አይችልም። የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ ነውና።

✍️ በዕብ 1:3 “የባህርይው ምሳሌ” በሚለው ሀረግ “ምሳሌ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ካራክቴር/χαρακτὴρ” ሲሆን “ትክክለኛ ምሳሌ፥ ትክክለኛ አምሳያ፥ ፍጹም አንድ አይነትነት፥ አንድ ነገር የሆነውን ነገር በሙሉ አንድም ሳይቀር መሆን፥ ቁጭ ራሱን” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ነው (Strong’s 5481)

የLexicon ማስረጃ፦

exact representation, exact likeness, From the same as charax; a graver (the tool or the person), i.e. (by implication) engraving ((“character”), the figure stamped, i.e. An exact copy or (figuratively) representation) — express image” [Strong’s G5481]

“properly, an engraving; (figuratively) an exact impression (likeness) which also reflects inner character” [HELPS Word-studies 5481]

✍️ ወልድ የአብ ባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑን የሚገልጸው “ትክክለኛ ምሳሌ” ተብሎ የተተረጎመው “ካራክቴር/χαρακτὴρ” የሚለው የግሪክ ቃል ብቻ ሳይሆን በዚያው በዕብ 1:3 ላይ “ባህርይ” ተብሎ የተተረጎመው “ሁፖስታሲዮስ/ὑποστάσεως” የሚለው የግሪክ ቃል ነው። የዚህ የግሪክ ቃል ትርጉም “ባህርይ፥ ሕላዌ፥ ምንነት” ሲሆን ባህርይን ወይም ሕላዌን ወይም substance or essence ያመለክታል (Strong’s G5287)

የLexicon ማስረጃ፦

“Confidence, substance. From a compound of hupo and histemi; a setting under (support), i.e. (figuratively) concretely, essence, or abstractly, assurance (objectively or subjectively) — confidence, confident, person, substance” [Strong’s exhaustive concordance 5287]

“a support, substance, steadiness, hence assurance” [NAS Exhaustive concordance]

➢ የእነዚህ የሁለት ቃላት ትርጉም ይህ በመሆኑ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ከዚህ ሀሳብ ጋር በሚስማማ መልኩ ተርጉመውታል፦

“በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት #በልጁ ለእኛ ተናገረን። እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብራውያን 1:2-3) አ.መ.ት

➢ ብዙ የኢንግሊዝኛ ትርጉሞችም እንዲሁ ፍጹም ይህንኑ ጽንሰ ሀሳብ በሚያመለክት መንገድ ተርጉመውታል፦

“The Son is the radiance of God’s glory and the exact representation of his being, sustaining all things by his powerful word. After he had provided purification for sins, he sat down at the right hand of the Majesty in heaven” (Hebrews 1:3) NIV

“who being the effulgence of his glory, and the very image of his substance, and upholding all things by the word of his power, when he had made purification of sins, sat down on the right hand of the Majesty on high” (Hebrews 1:3) ASV

“Who, being the outshining of his glory, the true image of his substance, supporting all things by the word of his power, having given himself as an offering making clean from sins, took his seat at the right hand of God in heaven” (Hebrews 1:3) BBE

“He brightly reflects God’s glory and is the exact representation of his being, and upholds the universe by His all-powerful word. After securing man’s purification from sin He took His seat at the right hand of the Majesty on high” (Hebrews 1:3) WNT

“who being the brightness of the glory, and the impress of His subsistence, bearing up also the all things by the saying of his might — through himself having made a cleansing of our sins, sat down at the right hand of the greatness in the highest” (Hebrews 1:3) YLT

“His Son is the radiance of his glory, the very image of his substance, and upholding all things by the word of his power, when he had by himself made purification for our sins, sat down on the right hand of the Majesty on high” (Hebrews 1:3) WEB

“The Son is the radiance of God’s glory and the exact expression of His nature, sustaining all things by His powerful word. After making purification for sins, He sat down at the right hand of the Majesty on high.” (Hebrews 1:3) HCSB

✍️ ስለዚህ ወልድ የአብ ባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ ነው ማለት ወልድ አብ በባህርይ የሆነውን ነገር በሙሉ እርሱም በባህርይው ነው ነው ማለት ነው። አብ በባህርይ ሆኖት፥ ወልድ በባህርይው ያልሆነው ነገር የለም

ይህ ወልድ መንፈስ መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው?

ወልድ የአብ ባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑ ወልድ መንፈስ መሆኑን ያረጋግጣል። ምክንያቱም አብ በባህርይው መንፈስ ነው፦

“23 ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ 24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል” (ዮሐ 4:23-24)

በዚህ ስፍራ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማርያዊቱ ሴት ጋር ሲነጋገር የነገራትን ነገር እንመለከታለን። እርሷ አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፥ እናንተ (አይሁዳውያን) ደግሞ በኢየሩሳሌም ስገዱ ትላላችሁ ብላ ስትጠይቀው፥ በዚያም ተራራ በኢየሩሳሌምም ለአብ የማይሰግዱበት ጊዜ እንደሚመጣና ለአብ በመንፈስና በእውነት እንደሚሰገድ ነገራት።

ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ እንደሆነና፥ የሚሰግዱለትም በእውነትና በመንፈስ እንደሚሰግዱለት ነገራት። በዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተባለው አብ እንደሆነ ከቁ.23 እንረዳለን። ስለዚህ ክርስቶስ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ሲላት እየተናገረ የነበረው ስለ አባቱ ነበር። በዕብ 1:3 የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ እንደሆነ የተነገረለት እግዚአብሔር አብ መንፈስ እንደሆነ ነገራት።

እግዚአብሔር መንፈስ ነው ማለት ምን ማለት ነው?

እግዚአብሔር መንፈስ ነው ሲባል በባህርይው የማይታይ፥ የማይዳሰስ፥ የማይጨበጥ፥ ረቂቅ ነው ማለት ነው። ቁስ አይደለም ወይም ደግሞ ግዙፍ አካል የለውም ማለት ነው። የመንፈስ ትርጉም ይህ ነውና (ሉቃ 24:39) በዮሐ 4:23-24 መንፈስ የሚለው ቃል ገላጭ/adjective ሆኖ ሲሆን የገባው እግዚአብሔር በምንነቱ ምንድነው የሚለውን የሚመልስ ነው።

አብ በባህርይው መንፈስ ከሆነና፥ ልጁ ደግሞ የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ ከሆነ…ልጁ ራሱ ምንድነው ማለት ነው?

መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር አብ የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ የሆነው ወልድ መንፈስ ነበር። እግዚአብሔር አብ መንፈስ ሆኖ የባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ የሆነው ወልድ መንፈስ ላይሆን አይችልም። አለዚያ የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ አይደለም ማለት ነው። የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ ከሆነ፥ እርሱ በባህርይው የሆነውን ነገር ሁሉ መሆን አለበት። መንፈስ መሆንን ጨምሮ

ከዚህ በፊት ባየናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፥ ወልድ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ከአብ ጋር ካለው የባህርይ አንድነት የተነሳ ነው። አብ መንፈስ እንደተባለው (ዮሐ 4:23-24) ልጁም መንፈስ ተብሏል። ይህ ሊሆን የቻለው የአብም የወልድም ከሆነው አንድ ባህርይ የተነሳ ነው። የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ ማለት ይህ ነውና።

➢ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር አብ ባህርይ (ሮሜ 1:20) መንፈስ መሆኑ ተገልጿል (ዮሐ 4:23-24) ስለዚህ የእርሱ ባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ የሆነው ወልድ መንፈስ ነው።

ወልድ መንፈስ አይደለም ከተባለ ግን ወልድ የአብ ባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ አይደለም ማለት ነው። ምክንያቱም አንዱ ማንነት መንፈስ ሆኖ፥ የእርሱ ባህርይ ትክክለኛ ምሳሌ የሆነው ሌላኛው ማንነት መንፈስ አይደለም ማለት አይቻልም። የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ ነው ማለት የሁለቱን ማንነቶች ፍጹም የሆነ የባህርይ አንድነት ያሳያልና። ይህ ወልድ መንፈስ ለመሆኑ ሌላኛው ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

ማስረጃ አምስት

“7 ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን። 8 ስለዚህ። ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል። 9 ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው? 10 ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው” (ኤፌ 4:7-10)

በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ሁሉን የሞላ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን። ከላይ በአንድ ተስፋ እንደተጠራን፥ ከዚያም አንድ አካል፥ አንድ መንፈስ፥ አንድ ጌታ፥ አንድ ሃይማኖት፥ አንድ ጥምቀትና አንድ አምላክ እንዳለ ከተናገረ በኋላ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ጸጋ እንደተሰጠ ይገልጻል።

ከዚያም መዝ 68:18 ለክርስቶስ በመጥቀስ ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ እንደሚል ከገለጸ በኋላ በቁ.9 ላይ ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው ብሎ ይጠይቃል። ማለትም ጥያቄው መጀመሪያ ላይ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል ወርዶ ካልነበር እንዴት ይወጣል የሚል ነው። ከዚያም በቁ.10 ላይ ራሱን ጥያቄ ሲመልሰው ይህ ራሱ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ያው ነው ይላል

✍️ ሁሉን ይሞላ ዘንድ ማለት ምን ማለት ነው?

በኤፌ 4:10 እንደምናነበው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ማለት በሁሉ ስፍራ ይገኝ ዘንድ ማለት ነው። በሁሉ ስፍራ መኖርን ወይም omnipresence የሚያመለክት ቃል ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሁሉን መሙላት” የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር በሁሉ ስፍራ እንደሚገኝ ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ሀረግ ነው፦

“23 እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። 24 ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር” (ኤርምያስ 23:23-24)

እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ (ዮሐ 4:23-24) በመንፈሳዊው ባህርይው አማካኝነት ሰማይንና ምድርን ሊሞላ ይችላል። የእግዚአብሔር ባህርይ ቁስ (matter) ስላልሆነ ቁስ የሆነ ነገር ያሉት ውስንነቶች የሉበትም። ስለዚህ በዚህ መንፈስ በሆነው ባህርይው ሰማይንና ምድርን ይሞላል። እግዚአብሔር በሁሉ ስፍራ ይገኛል ማለት ወይንም omnipresent ነው ማለት ይህ ነው

መንፈስ ያልሆነ ቁስ ሁሉን ሊሞላ አይችልም! ከላይ እንዳየነው ሰማይንና ምድርን የሞላው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ ቁስ አይደለም። ስለዚህ ሁሉን የሚሞላው መንፈስ የሆነ አካል እንደሆነ ከዚህ እንረዳለን። ሁሉን ሞልቶ በሁሉም ስፍራ ለመገኘት መንፈስ መሆን ያስፈልጋል። ቁስ ሁሉን ሊሞላ እንደሚችል የሚያሳይ አንድም ማስረጃ የለም

ስለዚህ በኤፌ 4:10 እንደተገለጸው ክርስቶስም ሁሉን ሊሞላ የቻለው መንፈስ ስለሆነ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ጌታ ክርስቶስ መንፈስ በመሆኑ ሁሉን ይሞላል ሊባልለት ችሏል። ይህ ወልድ መንፈስ ለመሆኑ ሊታበል የማይችል ተጨባጭ ማስረጃ ነው። በኤፌ 4:7 ላይ “እንደ #ክርስቶስ ስጦታ መጠን” ስለሚል በቁ.10 ላይ ሁሉን ይሞላ ዘንድ የተባለው ክርስቶስ/ወልድ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም

በኤፌ 4:7-10 ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ መሆኑ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጥያቄ የሌለው እውነታ ነው። ለሐዋርያት እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ግን ይህ አወዛጋቢ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ለእነርሱ ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራው አብም ወልድም ነው። ክርስቶስ ሲል ሁሌም ወልድን ነው የሚያመለክተው የሚል ክርስቲያናዊ አረዳድ የላቸውምና። ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ ክርስቶስ የተባለው ወልድ መሆኑን በማስረጃ ማስረዳት አለብን

✏️ በኤፌ 4:7-10 ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ መሆኑን እንዴት እናውቃለን?

በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለለት ክርስቶስ ወልድ መሆኑን የምናውቀው በዚህ ክፍል ላይ ለእርሱ የተባሉት ነገሮች በሙሉ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ለወልድ በመባላቸው ነው። ይህ በእርግጥም ሁሉን ይሞላል የተባለለት ክርስቶስ ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል። እንየው፦

ሀ) ወደ ሰማይ ያረገው ወልድ ነው

በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለለት ክርስቶስ ከሰማያት ሁሉ በላይ እንደወጣ ተነግሯል። ከሰማያት ሁሉ በላይ ወጥቷል ማለት ሞቶ ከተነሳ በኋላ ወደ ሰማይ ወደ አባቱ ቀኝ ዐርጓል ማለት ነው። ዕርገቱን የሚናገር ክፍል ነው። ስለዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ያረገው ማነው?

➢ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ወደ ሰማይ ያረገው ወልድ ነው፦

“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ” (ዕብ 4:14)

“2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት #በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ 3 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብ 1:2-3)

“ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት” (ዮሐ 20:17)

“ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ” (ዮሐ16:28)

“ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው” (ዮሐ 17:11)

“32 ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤ 33 ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው” (ሐዋ 2:32-33)

– ከሞት የተነሳውና (1ተሰ 1:9-10) በእግዚአብሔርም ቀኝ ከፍ ከፍ ያለው (ዕብ 1:2-3) ወልድ በመሆኑ በዚህ ክፍል ላይ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል።

የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ እንደሚናገረው ወደ ወደ ሰማይ ወደ አብ ያረገው ወልድ ነው። ስለዚህ በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላ ዘንድ ወደ ከሰማያት በላይ ወጣ የተባለለት ወልድ ነው ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ ሁሉን እንደሚሞላ የተነገረለት ወልድ ነው ማለት ነው። ይህ ወልድ ሁሉን የሚሞላ/በሀሉ ቦታ የሚገኝ መንፈስ እንደሆነ ያረጋግጣል። ሁሉን ለመሙላት መንፈስ መሆን ያስፈልጋልና

አስተውሉ! ሁሉን ይሞላል የተባለለት ራሱ ወደ ሰማይ ያረገው ነው! ኤፌ 4:7-10 ወደ ሰማይ ያረገው ሌላ፥ ሁሉን የሚሞላው ደግሞ ሌላ ነው አይልም! ራሱ ሁሉን የሚሞላው ነው ከሰማያት በላይ ያረገው። ወይንም ደግሞ “በክርስቶስ ውስጥ ያለው ሁሉን ይሞላል” አይልም። ራሱ ክርስቶስ/ወልድ እንጂ ሁሉን ይሞላል የሚለው፥ ወልድን ያልሆነ ግን ወልድ ውስጥ ያለ ማንነት ሁሉን ይሞላል አይልም።

✏️ ወደ ሰማይ ያረገው አብ ሳይሆን ልጁ ክርስቶስ እንደሆነ በዚያው በኤፌሶን መጽሐፍ ተረጋግጧል

ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል” (ኤፌ 1:20-21)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሞት እንዳስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዳስቀመጠው ይናገራል። ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ዓርጎ በአብ ቀኝ እንደተቀመጠ ከዚህ ክፍል እንረዳለን። ስለዚህ ወደ ሰማይ ያረገው አብ ሳይሆን በቀኙ የተቀመጠው ልጁ ክርስቶስ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ውስጥ አብ በአብ ቀኝ ተቀመጠ የሚል አንድም ማስረጃ የለም! እንደ እግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ በአብ ቀኝ የተቀመጠው ልጁ ነው (ዕብ 1:2-3) ስለዚህ በኤፌ 1:20-21 በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ተቀመጠ የተባለለት አብን ያልሆነው ልጁ ክርስቶስ ነው ማለት ነው።

በተጨማሪም በኤፌ 1:20-21 ላይ ልክ እንደ ኤፌ 4:7-10 ዐረገ ያለው ክርስቶስን ነው። ባለፈው ክፍል በስፋት ለማየት እንደሞከርነው ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ ብቻ ነው። አብም ሆነ መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ ተብለው አልተጠሩም። ስለዚህ ይህ በኤፌ 1:20-21 ላይ አረገ የተባለለት ክርስቶስ ወልድ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

በኤፌ 4:7-10 ላይ ግን ሁሉን ይሞላል የተባለለት ከሰማያት ሁሉ በላይ ያረገው ወልድ ነው። ስለዚህ ይህ ወደ ሰማይ ያረገው ወልድ በሁሉ ቦታ የሚገኝ መንፈስ መሆኑን ከምናውቅባቸው መንገዶች አንዱ ነው።

ለ) ወደ ታችኛው የምድር ክፍል ወርዷል

በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለለት ክርስቶስ ወደ ታችኛው የምድር ክፍል እንደወረደ ተነግሯል። ወደ ምድር ታችኛው ክፍል ወርዷል ማለት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ከሞተ በኋላ ወደ ሲኦል ወርዶ ነበር ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምድር በታች የሚለው አገላለጽ ሲኦልን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏልና (ራዕይ 5:3 ፊሊ 2:10) ስለዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ወደ ሲኦል የወረደው ማነው?

➢ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ወደ ሲአል የወረደው ወልድ ነው፦

“31 ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። 32 ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን” (ሐዋ 2:31-32)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የክርስቶስ ነፍስ በሲኦል እንዳልቀረች፥ ስጋውም መበስበስን እንዳላየ፥ እግዚአብሔር እርሱን እንዳስነሳው፥ ለዚህም እነርሱ ምስክሮች እንደሆኑ ሲናገር እናያለን። ይህ ክፍል ወደ ሲኦል ወርዶ የነበረው ወልድ እንደሆነ በማያሻማ መንገድ የሚናገር ክፍል ነው። ነፍሱ በሲኦል አልቀረችም ይላልና።

✍️ ነፍሱ በሲኦል አልቀረችም ማለት ምን ማለት ነው?

ነፍሱ በሲኦል አልቀረችም ማለት ምንም እንኳን ወደ ሲኦል ወርዳ የነበረ ቢሆንም በዚያ አልቀረችም፥ ተመልሳ ከስጋው ጋር ተዋህዳለች ማለት ነው። የሙታን ትንሳኤ የነፍስ መልሳ መዋሃድ ሲሆን (ሉቃ 8:55 1ነገ 7:22) በሲኦል አልቀረችም ሊባል የቻለው፥ ሲሞት ነፍሱ ከስጋው ተለይታ ወደ ሲኦል ስለወረደች፥ ነገር ግን ወርዳ በዚያ ስላልቀረች ነው። ነፍሱ ከመጀመሪያውኑ ወደ ሲኦል ባትወርድ ኖሮ በዚያ አልቀረችም ባልተባለላት ነበርና። ይህ ክርስቶስ ወደ ሲኦል ወርዶ እንደነበር በሚገባ ያረጋግጣል።

በዚህ ክፍል ነፍሱ በሲኦል አልቀረችም ሲል ስጋው በመቃብር አልቀረም ማለት ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ቀጠል ብሎ “ስጋውም መበስበስን አላየም” ይላል። ስጋና ነፍስን ነጣጥሎና ለያይቶ ነው ያስቀመጣቸው። ስለዚህ ነፍሱ በሲኦል አልቀረችም ሲል ሲኦል በሚባለው መንፈሳዊ ስፍራ አልቀረችም ማለቱ እንጂ በምድራዊ መቃብር ውስጥ አልቀረችም ማለት አይደለም።

ይህ ወደ ሲኦል ወርዶ የነበረው ክርስቶስ ወልድ እንደሆነ በምን እናረጋግጣለን?

በሐዋ 2:31-32 ወደ ሲኦል ወርዶ ነበር የተባለለት ክርስቶስ ወልድ መሆኑን የምናውቀው ያ ነፍሱ በሲኦል ያልቀረችው ወልድ ከሞት እንደተነሳ በመገለጹ ነው። ከሞት የተነሳው ደግሞ ወልድ ነው፦

“..ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ..” (1ተሰ 1:9-10)

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ” (1ጴጥ 1:3-5)

“17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። 18 እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ” (ዮሐ 10:17-18)

✍️ ከሞት የተነሳው ወልድ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል። ስለዚህ በሐዋ 2:31-32 ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች፥ ከሞትም እንደተነሳ የተነገረለት ክርስቶስ ወልድ ነው ማለት ነው። ወደ ሲኦል ወርዶ በዚያው ያልቀረው ወልድ ነው።

በኤፌ 4:7-10 ላይ ግን ወደ ምድር ታችኛው ክፍል/ሲኦል የወረደው ክርስቶስ ሁሉን እንደሚሞላ ተገልጿል። ሁሉን ይሞላል የተባለለት ያ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል የወረደው ነው። አሁን ለማየት እንደሞከርነው ደግሞ፥ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል የወረደው ደግሞ ወልድ ነው። ይህ ወልድ በሁሉ ቦታ የሚገኝ፥ ሁሉን የሞላ መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያሳያል።

አስተውሉ! አብ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል ወረደ የሚል አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የለም። ወደ ምድር ታችኛው ክፍል የወረደው ከሞት የተነሳው ወልድ ነው። ስለዚህ በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለው ወልድ እንጂ አብ ሊሆን አይችልም።

“18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ 19 በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው” (1ጴጥ 3:18-19)

✍️ በዚህ ስፍራ ሐዋርያው ጴጥሮስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች በኃጢአት ምክንያት እንደሞተና፥ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት እንደሰበከላቸው ይናገራል። በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሄዶ ሰበከላቸው ማለት ወደ ሲኦል ወርዶ ነበር ማለት ነው።

ነፍሳት ከስጋ ሲለዩ ይሄዱ የነበረው ወደ ሲኦል ሲሆን (ሉቃ 16:23) ክርስቶስም ሄዶ የሰበከላቸው በወኅኒ ለነበሩ ለእነዚህ ነፍሳት ነው። በተጨማሪም ሲኦል ራሱ እንደ ወኅኒ ተገልጿል (ይሁዳ 1:6) ስለዚህ ክርስቶስ ለታሰሩት ነፍሳት ሊሰብክ ወደ ሲኦል ወርዶ ነበር።

ይህ ወደ ሲኦል ወርዶ የነበረው ክርስቶስ ወልድ እንደሆነ በምን እናረጋግጣለን?

በ1ጴጥ 3:18-19 ላይ ወደ ወኅኒ ሄዶ ለታሰሩት ነፍሳት ሰበከላቸው የተባባለት ክርስቶስ ወልድ መሆኑን የምናውቀው በዚያው ክፍል ላይ ስለ ዓመፀኞች በኃጢአት ምክንያት እንደሞተ በመገለፁ ነው። ለኃጢአተኞች የሞተው ደግሞ ወልድ ነው፦

“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን” (ሮሜ 5:10)

“ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” (ገላ 2:20)

“7 እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት 8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ” (ዕብ 5:7-8)

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም” (1ዮሐ 4:10)

ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?” (ሮሜ 8:32)

“17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። 18 እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ” (ዮሐ 10:17-18)

– አብ የሚወደው ወልድን ስለሆነ (ማቴ 3:17) በዚህ ቦታ እየተናገረ ያለው ወልድ መሆኑን ያሳያል።

“37 በኋላ ግን። ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከባቸው። 38 ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው። ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። 39 ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት” (ማቴ 21:37-39)

✏️ ለኃጢአተኞች የሞተው ወልድ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ስለዚህ በ1ጴጥ 3:18-19 ወደ ወኅኒ ሄዶ እንደሰበከ፥ ለኃጢአተኞችም እንደሞተ የተነገረለት ክርስቶስ ወልድ ነው ማለት ነው። ለእነዚያ ነፍሳት ወደ ሲኦል ወርዶ የሰበከላቸው ወልድ ነው።

በኤፌ 4:7-10 ላይ ግን ወደ ታችኛው ምድር/ሲኦል የወረደው ክርስቶስ ሁሉን እንደሚሞላ ተገልጿል። ሁሉን ይሞላል የተባለለት ያ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል የወረደው ነው። አሁን ለማየት እንደሞከርነው ደግሞ፥ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል የወረደው ደግሞ ወልድ ነው። ይህ ወልድ በሁሉ ቦታ የሚገኝ፥ ሁሉን የሞላ መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያሳያል።

አስተውሉ! አብ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል ወረደ የሚል አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የለም። ወደ ወኅኒ ሄዶ የሰበከው የሞተው ወልድ ነው። ስለዚህ በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለው ወልድ እንጂ አብ ሊሆን አይችልም።

“ወይም። በልብህ። ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው” (ሮሜ 10:7)

✍️ በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ትክክለኛ አማኞች “ማን ወደ ጥልቁ ይወርዳል? ማለት” እንደሌለባቸው ሲናገር እንመለከታለን። ምክንያቱም ይህ ክርስቶስን ከሙታን ማውጣት ነውና። ሐዋርያው ይህን የተናገረው በቁ.6 ላይ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል አትበል፥ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው ካለ በኋላ ነው።

“ማን ወደ ጥልቁ ይወርዳል?” ማለት የክርስቶስን ወደ ጥልቁ መውረድ መካድ ነው። ምክንያቱም ክርስቶስ ከሞተ በኋላ ወደ ጥልቁ ወርዷልና። ማን ይህን ሊያደርግ ይችላል ማለት ክርስቶስ አልሞተም፥ ወደ ጥልቁም አልወረደም ብሎ መካድ ይሆናል። ስለዚህም ሐዋርያው ጳውሎስ “ማን ወደ ጥልቁ ይወርዳል?” አትበል ብሏል። የጌታን ወደ ጥልቁ መውረድ መካድ ነው። ይህ ክርስቶስ ወደ ጥልቁ ወርዶ እንደነበር በሚገባ ያረጋግጣል። ወደ ጥልቁ ባይወርድ ኖር እንደዛ ማለት እርሱን ከሙታን ማውጣት ነው ባልተባለ ነበር።

ወደ ጥልቁ ወርዶ የነበረው ክርስቶስ ወልድ እንደሆነ በምን እናረጋግጣለን?

በሮሜ 10:7 ላይ ወደ ጥልቁ ወርዶ እንደነበር የተነገረለት ክርስቶስ ወልድ መሆኑን የምናውቀው በዚያው ክፍል ላይ “..ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው..” በማለት እንደሞተ በመገለጹ ነው። ሞቶ የነበረው ደግሞ ወልድ ነው፦

“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን” (ሮሜ 5:10)

“ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” (ገላ 2:20)

“7 እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት 8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ” (ዕብ 5:7-8)

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም” (1ዮሐ 4:10)

ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?” (ሮሜ 8:32)

“17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። 18 እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ” (ዮሐ 10:17-18)

– አብ የሚወደው ወልድን ስለሆነ (ማር 1:10) በዚህ ቦታ እየተናገረ ያለው ወልድ መሆኑን ያሳያል።

“37 በኋላ ግን። ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከባቸው። 38 ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው። ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። 39 ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት” (ማቴ 21:37-39)

ሞቶ የነበረው ወልድ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ስለዚህ በሮሜ 10:7 ሞቶ እንደነበር፥ ወደ ጥልቁም ወርዶ እንደነበር የተነገረለት ክርስቶስ ወልድ ነው ማለት ነው።

በኤፌ 4:7-10 ላይ ግን ወደ ታችኛው ምድር/ሲኦል የወረደው ክርስቶስ ሁሉን እንደሚሞላ ተገልጿል። ሁሉን ይሞላል የተባለለት ያ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል የወረደው ነው። አሁን ለማየት እንደሞከርነው ደግሞ፥ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል የወረደው ደግሞ ወልድ ነው። ይህ ወልድ በሁሉ ቦታ የሚገኝ፥ ሁሉን የሞላ መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያሳያል።

አስተውሉ! አብ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል ወረደ የሚል አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የለም። የሞተው፥ ወደ ጥልቁም የወረደው ወልድ ነው። ስለዚህ በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለው ወልድ እንጂ አብ ሊሆን አይችልም።

ይህ ማለት ወልድ ሁሉን በመሙላት በሁሉ ስፍራ ይገኛል ማለት ነው። ከላይ ደግሞ በማስረጃ እንዳረጋገጥነው በሁሉ ስፍራ የሚገኘው መንፈስ ነው። አንድ አካል በሁሉ ስፍራ ሊገኝ የሚችለው መንፈስ ከሆነ ብቻ ነው። ስለዚህ ወልድ በሁሉ ቦታ መገኘቱ ከምንም በላይ መንፈስ እንደሆነ ያረጋግጣል።

በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለለት ክርስቶስ ወልድ መሆኑን የምናውቅበት ሌላኛው መንገድ በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ክርስቶስ” ተብሎ የተጠራው ወልድ ብቻ በመሆኑ ነው። ይህ ክርስቶስ የሚለው ስያሜ የአብ ሆነ የመንፈስ ቅዱስ ስያሜ ሆኖ የገባበት አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም፦

“በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል” (2 ቆሮ 1:19)

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (1ቆሮ 1:9)

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው” (1ዮሐ 1:3)

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7)

“ትእዛዚቱም ይህች ናት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ” (1ዮሐ 3:23)

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

“ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ” (2ዮሐ 1:3)

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” (ገላ 2:20)

ኤፌ 4:7 ላይ እንደ “ክርስቶስ” ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን ይላል። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው “ክርስቶስ” የሚለው ቃል በግሪክ “ኽሪስቶስ/Χριστός” የሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙም “የተቀባ/the anointed one” ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ስያሜ የሚጠራው አካል የተቀባ አካል ነው ማለት ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ ነው፦

“8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል” (ዕብ 1:8-9)

በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ” (ሐዋ 4:27-28)

በዕብ 1:8-9 እና በሐዋ 4:27-28 ላይ “ቀባህ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ኤኽሪሴን/ἔχρισέν” የሚለው ቃል ሲሆን መቀባትን ያመለክታል። “ኽሪስቶስ” የሚለውም ቃል የመጣው ከዚሁ ቃል ነው። ስለዚህ በኤፌ 4:7 ሆነ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ “ክርስቶስ” ተብሎ የተጠራው አብ ነው ማለት አይቻልም። አብ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቷል ከተባለ አብ ተቀብቷል ማለት ይሆናል። አብ ተቀብቷል የሚል አስተምህሮ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሌለ ሁሌም ክርስቶስ የሚባለው ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ ብቻ ነው። አብ አንድም ቦታ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቶ አያውቅም። ስለዚህ በኤፌ 4:7-10 ላይ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ መሆኑን ከመላው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እናረጋግጣለን። እንደውም ከላይ በጠቀስናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ አብ ከክርስቶስ በማንነት ተለይቶ ተጠርቷል። ይህ በእርግጥም በኤፌ 4:7-10 ክርስቶስ የተባለው ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል

➢ በዚህ ክፍል ክርስቶስ የተባለው ወልድ መሆኑን የምናውቅበት ሌላው መንገድ በአውዱ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ ነው፦

“10 ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው። 11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ 12-13 ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ ማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ” (ኤፌ 4:10-13)

✍️ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል ከወረደ በኋላ ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ እንደወጣ ከተናገረ በኋላ ለምን የጸጋ ስጦታዎችን እንደሰጠ ይናገራል። አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌል ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ክርስቶስ እንደ ስጦታው መጠን እንደሰጠ ይናገራል (ኤፌ 4:11)

ከዚያም በቁ.12-13 እነዚህን የጸጋ ስጦታዎች የሰጠበትን ምክንያት ይናገራል። እርሱም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ነው። ክርስቶስ ለክርስቲያኖች የጸጋ ስጦታዎችን የሰጠበት ምክንያት እነዚህ ናቸው።

▶️ በአፌ 4:12-13 ላይ ክርስቶስ የጸጋ ስጦታዎችን ከሰጠበት ምክንያቶች አንዱ የእግዚአብሔርን በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት እንድንደርስ ነው። ታዲያ በዚህ ክፍል ላይ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ማነው?

በኤፌ 4:7-13 ላይ የተጠቀሰው የእግዚአብሔር ልጅ ልናምነውና ልናውቀው የሚገባው የእግዚአብሔር ልጅ ወይም ወልድ ነው። ታዲያ ይህ ልናምነውና ልናውቀው የሚገባው የእግዚአብሔር ልጅ ማነው ስንል ከላይ ከቁ.7-10 ሁሉን የሚሞላው ክርስቶስ መሆኑን እናረጋግጣለን። በአውዱ ክርስቶስ የተባለው ማንነት ነው ከስር ወረድ ብሎ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው። ይህ ከአውዳዊ ንባቡ ግልጽ የሆነ እውነታ ሲሆን፥ በእርግጥም ወልድ/ክርስቶስ ሁሉን የሚሞላ መንፈስ እንደሆነ ያረጋግጣል።

ሲቀጥል በኤፌ 4:12-13 የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ሁሉን ይሞላል የተባለለት ክርስቶስ መሆኑን የምናውቅበት ሌላው መንገድ ስለ እርሱ የተባለው ነገር ነው።

በዚህ ክፍል ላይ የእግዚአብሔርን ልጅ ማወቅና ማመን እንዳለብን ተገልጿል። በተቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ደግሞ ማመንና ማወቅ ያለብን ክርስቶስን እንደሆነ ተገልጿል። ይህ በእርግጥም ሁሉን ይሞላ ዘንድ የተባለለት ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ያረጋግጣል፦

“8-9 አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ 10-11 እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ” (ፊሊ 3:8-11)

“ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ” (ቆላ 2:2)

“ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን” (2ጴጥ 3:18)

“በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና” (1ቆሮ 2:2)

“በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል” (2የጴጥ 2:20)

“እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና” (2ጴጥ 1:8)

➢ ከማወቅም ባሻገር ማመንም ያለብን በክርስቶስ እንደሆነ ተገልጿል። ስለዚህ በኤፌ 4:12-13 ማመንና ማወቅ ያለብን የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው ማለት ነው፦

“ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል” (ገላ 2:16)

“እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና” (ሮሜ 3:22)

“ትእዛዚቱም ይህች ናት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ” (1ዮሐ 3:23)

“እነርሱም። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት” (ሐዋ 16:31)

ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል” (1ዮሐ 5:1)

“ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል” (2ኛጢሞ 3:15)

በኤፌ 4:12-13 ላይ የእግዚአብሔርን ልጅ ማመንና ማወቅ እንዳለብን ተገልጿል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በኤፌ 4:7-10 ሁሉን ይሞላል የተባለለት “ክርስቶስ” በመሆኑ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ክርስቶስን ማወቅና ማመን እንዳለብን ተገልጿል። ስለዚህ በኤፌ 4:12-13 የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ክርስቶስ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ሁሉን የሞላው፥ መንፈስ የሆነው ክርስቶስ ልናውቀውና ልናምነው የሚገባው ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ይህ ከምንም በላይ ወልድ መንፈስ መሆኑን ያረጋግጣል።

ማስረጃ ስድስት

“ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው” (የዮሐንስ ወንጌል 3:13)

በዚህ ስፍራ ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኒቆዲሞስ ጋር ያደረገውንን ንግግር እንመለከታለን። ከውኃና ከመንፈስ ስለመወለድ፥ ስለ ዳግም ውልደት አስፈላጊነት ከነገረው በኋላ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም እንደሌለና ያም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ መሆኑን ነገረው።

በዮሐንስ 3:13 ላይ “በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ” ያለው በpresent tense ነው። ማለትም ያ ንግግር በተደረገበት ሰዓት የሰው ልጅ በሰማይ ነበር። በክፍሉ ላይ በfuture tense የሰው ልጅ ወደፊት በሰማይ ይኖራል እየተባለ ሳይሆን ይህ ንግግር በተደረገበት በዚያኑ ሰዓት እንኳ በሰማይ እንደሚኖር እየተገለጸ ነው።

ለዚህም ነው የኢንግሊዝኛ ትርጉሞች በትክክል “The Son of Man which is in heaven” ብለው በpresent tense የተረጎሙት፦

“And no man hath ascended up to heaven, but he that came down from heaven, even the Son of man which is in heaven” (John 3:13) KJV

“And no one hath ascended into heaven, but he that descended out of heaven, even the Son of man, who is in heaven” (John 3:13) ASV

“and no one hath gone up to the heaven, except he who out of the heaven came down the Son of Man who is in the heaven” (John 3:13) YLT

ጌታ ኢየሱስ ይህን ንግግር ከኒቆዲሞስ ጋር ሲያደርግ በስጋ ተገልጦ በምድር ነበር። ነገር ግን በምድር በነበረበት በዚያኑ ሰዓት ራሱን “በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ” ብሎ በመጥራት በሰማይም እንደነበር ተናግሯል። ስለዚህ በአንድ ጊዜ ወይም simultaneously በሰማይም በምድርም ነበር ማለት ነው።

በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም መኖር ማለት ምን ማለት ነው?

በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም መኖር በሁሉ ቦታ መገኘት ወይም omnipresence ነው። በቦታ አመገደብና አለመወሰን ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ተገልጦ በምድር በነበረበት ጊዜ እንኳ በዚያኑ ሰዓት በሰማይም እንደሚኖር መግለፁ በአንድ ጊዜ በሁሉ ቦታ እንደሚገኝ ያረጋግጣል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደግሞ በሰማይም በምድርም ያለው ወይም በሁሉ ስፍራ የሚገኘው እግዚአብሔር እንደሆነ በግልጽ ተጽፏል፦

“23 እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። 24 ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር” (ኤር 23:23-24)

እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ (ዮሐ 4:23-24) በመንፈሳዊው ባህርይው አማካኝነት በሰማይም በምድርም አለ። የእግዚአብሔር ባህርይ ቁስ (matter) ስላልሆነ ቁስ ያለውን ውስንነቶች የሉበትም። ስለዚህ በዚህ መንፈስ በሆነው ባህርይው በሁሉ ስፍራ ይገኛል። እግዚአብሔር በሁሉ ስፍራ ይገኛል ማለት ወይንም omnipresent ነው ማለት ይህ ነው

መንፈስ ያልሆነ ቁስ በአንድ ጊዜ በሰማይም በምደርም ሊኖር አይችልም! ከላይ እንዳየነው ሰማይንና ምድርን የሞላው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ ቁስ አይደለም። ስለዚህ በሁሉ ቦታ የሚገኘው መንፈስ የሆነ አካል እንደሆነ ከዚህ እንረዳለን። ሁሉን ሞልቶ በሁሉም ስፍራ ለመገኘት መንፈስ መሆን ያስፈልጋል። ቁስ ሁሉን ሊሞላ እንደሚችል የሚያሳይ አንድም ማስረጃ የለም

ስለዚህ በዮሐ 3:13 እንደተገለጸው ክርስቶስም በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ሊኖር የቻለው መንፈስ ስለሆነ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በመሆኑ በሁሉ ቦታ ሊኖር ችሏል። ይህ ወልድ መንፈስ ለመሆኑ ሊታበል የማይችል ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

በዮሐ 3:13 በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም የሚኖረው ወልድ ለመሆኑ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጥያቄ የሌለው እውነታ ነው። ለሐዋርያት እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ግን ይህ አወዛጋቢ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ለእነርሱ ኢየሱስ አብም ወልድም ነው። ኢየሱስ ሲል ሁሌም ወልድን ነው የሚያመለክተው የሚል ክርስቲያናዊ አረዳድ የላቸውምና። ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ መሆኑን በማስረጃ ማስረዳት አለብን

✏️ በዮሐንስ 3:13 እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ መሆኑን በምን እናውቃለን?

በዮሐንስ 3:13 ላይ በሁሉ ስፍራ በአንድ ጊዜ ይገኛል የተባለው ለወልድ መሆኑን የምናውቀው በዚህ ክፍል ላይ ለእርሱ የተባሉት ነገሮች በሙሉ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ለወልድ በመባላቸው ነው። ይህ በእርግጥም በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም አለ የተባለለት ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል። እንየው፦

ሀ) የሰው ልጅ ተብሏል

በዮሐ 3:13 በምድር እያለ እንኳ በሰማይም እንዳለ የተነገረለት የሰው ልጅ ነው። ስለዚህ በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም የሚገኘው ይህ የሰው ልጅ ነው ማለት ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የሰው ልጅ የተባለው ወልድ ነው፦

የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል” (ማቴ 16:27)

“በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል” (ማር 8:38)

“በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ በክብሩ በአባቱና በቅዱሳን መላእክቱ ክብርም ሲመጣ በእርሱ ያፍርበታል” (ሉቃ 9:26)

በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰው ልጅ የተባለው ወልድ እንደሆነ ከዚህ በላይ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ወልድ አለም ሳይፈጠር ከአባቱ ከአብ ጋር የነበረ (ዮሐ 17:5) በኋላ በአባቱ ላኪነት በስጋ የመጣው (ሮሜ 8:3) አምላክ (ዕብ 1:8 1ዮሐ 5:20) በመሆኑ ከዚያ ከመጣበት ሰዋዊ ባህርይ የተነሳ “የሰው ልጅ” ተብሎ ተጠርቷል።

አስተውሉ! ዮሐንስ 3:13 ላይ የሰው ልጅ/ወልድ ራሱ እንጂ በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይኖራል የተባለው በሰው ልጅ ውስጥ ያለው አይደለም! ክፍሉ “በሰው ልጅ ውስጥ ሆኖ በሰማይ የሚኖረው” አይልም። በሁሉ ስፍራ ያለው ራሱ የሰው ልጅ/ወልድ ነው። ስለዚህ በሁሉ ስፍራ ያለው በወልድ ውስጥ ያለ ግን ወልድን ያልሆነ ሌላ ማንነት ነው ማለት አይቻልም።

ሌላው ሊስተዋል የሚገባው ነጥብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ አብ የሰው ልጅ ተብሎ ተጠርቶ አያውቅም። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በተደጋጋሚ የሰው ልጅ ተብሎ የተጠራው ወልድ ብቻ ነው። ይህ በዮሐ 3:13 በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይኖራል የተባለለት የሰው ልጅ ወልድ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

የሰው ልጅ የሚለው ስያሜ በስጋ የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ስያሜ ነው። መለኮታዊውም ሰዋዊውም ባህርይ ያለው ያ አንድ አካል/person በስጋ ከመጣ በኋላ የተጠራበት ስሙ ነው። አንዱን ባህርይ ብቻ ነጥሎ ሳይሆን የሚያመለክተው ሁለቱም ባህርያት ያሉትን አንዱን አካል/person ነው።

ስለዚህ ወልድ/የሰው ልጅ የራሱ ያደረገው ሰዋዊ ባህርይ በቦታ ቢወሰንም በዘላለማዊ ሕልውናው የኖረበት መለኮታዊ ባህርይው ግን በሁሉ ቦታ አለ። በዮሐ 3:13 የምንመለከተው ይህንን ነው። “የሰው ልጅ” የሚለው ስም ልክ “ኢየሱስ” እንደሚለው ስም የአንዱ ስግው-መለኮት ስም ስለሆነ መለኮትነቱንም (በሁሉ ቦታ መገኘቱን) ሰውነቱንም (የሰው ልጅ መባሉ) የሚያመለክት ስም ሆኖ ለእርሱ ጥቅም ላይ ውሏል።

መግቢያው ላይ ለማየት እንደሞከርነው ደግሞ በሁሉ ስፍራ ያለው (ኤር 23:23-24) መንፈስ የሆነው (ዮሐ 4:23-24) አምላክ ነው። ስለዚህ ዮሐንስ 3:13 ላይ እንደሚለው የሰው ልጅ ወይም ወልድ በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ሊኖር የሚችለው በባህርይው መንፈስ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ ወልድ መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

ለ) ከሰማይ ወርዷል

በዮሐንስ 3:13 በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይኖራል የተባለለት የሰው ልጅ ወልድ መሆኑን የምናውቅበት ሌላኛው መንገድ ከሰማይ ወርዷል መባሉ ነው። ከሰማይ ወርዷል ማለት ሰው ሆኖ ለመወለድ ወደ ምድር መጥቷል፥ በስጋ ተገልጦ ወደ ዓለም ገብቷል ማለት ነው። ታዲያ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከሰማይ የወረደው ማነው?

➢ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከሰማይ የወረደው ወልድ ነው፦

“ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና” (ዮሐ 6:38)

በዚህ ስፍራ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአይሁዳውያን ጋር ሲነጋገር እንመለከታለን። የሕይወት እንጀራ እርሱ እንደሆነና፥ አብ የሚሰጠው ሁሉ ወደ እርሱ እንደሚመጣ ከነገራቸው በኋላ የላከውን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ እንደወረደ ነገራቸው። ይህ ከሰማይ የወረደው ወልድ እንደሆነ ያሳያል።

ምክንያቱም ከሰማይ የወረደው እርሱን የላከውን (የአብን) ፈቃድ ለመፈጸም ነው። አብ የላከው ደግሞ ልጁን ነው፦

“በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና” (1ዮሐ 4:9)

“ፍቅርም እንደዚህ ው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም” (1ዮሐ 4:10)

“እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን” (1ዮሐ 4:14)

“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና” (ሮሜ 8:3-4)

“ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4:4)

ክርስቶስ ኢየሱስን የላከው እግዚአብሔር አብ መሆኑ በቀጣዩ ጥቅስ ላይም ተገልጿል፦

“ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው” (ዮሐ 6:39)

ስለዚህ በዮሐ 6:38 የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወረድኩ ሲል ወልድ መሆኑን እያመለከተ ነው። የላከውን የአብን ፈቃድ ለመፈጸም የወረደው ወልድ ነው። በዮሐ 3:13 ግን ያ ከሰማይ የወረደው ወልድ በሁሉ ቦታ እንደሚገኝ ተገልጿል። ስለዚህ ወልድ በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይገኛል ማለት ነው። በሁሉ ቦታ የሚኖረው መንፈስ በመሆኑ ይህ ወልድ በሁሉ ቦታ የሚገኝ መንፈስ መሆኑን ያረጋግጣል።

“31 ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው። 32 ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም” (ዮሐ 3:31-32)

በዚህ ስፍራ ላይ በመጥምቁ ዮሐንስ እና በአይሁድ መካከል የተደረገውን ንግግር እንመለከታለን። ጌታ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጥቶ ከእነርሱ ጋር ያጠምቅ ስለነበር (ዮሐ 2:22) አይሁድ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ መጥተው ከእርሱ ጋር የነበረው፥ እርሱም የመሰከረለት በዮርዳኖስ ማዶ እያጠመቀ እንደሆነ ሲነግሩት (ዮሐ 3:26) እርሱ ክርስቶስ እንዳልሆነና ከእርሱ በፊት እንደተላከ (ዮሐ 3:28) በሙሽራው ድምጽ ደስ የሚለው ሚዜው እንደሆነ (ዮሐ 3:29) ከነገራቸው በኋላ ከቁ.31-32 ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ እንደሆነና ያየውንና የሰማውን እንደሚመሰከር ነገራቸው።

✍️ ይህ ከሰማይ የወረደው ወልድ እንደሆነ ያሳያል። ምክንያቱም ያየውንና የሰማውን የመሰከረው ወልድ ነውና፦

“እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ” (ዮሐ 8:38)

“ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና” (ዮሐ 5:19)

“26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው። 27 ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም” (ዮሐ 8:26-27)

“ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና” (ዮሐ 15:15)

ስለዚህ በዮሐ 3:31-32 ከሰማይ የመጣው ከሁሉ በላይ ነው፥ ያየውንና የሰማውንም ይመሰክራል ሲል ይህ ከሰማይ የመጣው ወልድ መሆኑን እያመለከተ ነው። የሰማውንና ያየውን የሚመሰክረው ወልድ ነውና። ስለዚህ ከሰማይ መጣ የተባለለት ወልድ ነው። በዮሐ 3:13 ግን ያ ከሰማይ የወረደው ወልድ በሁሉ ቦታ እንደሚገኝ ተገልጿል። ስለዚህ ወልድ በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይገኛል ማለት ነው። በሁሉ ቦታ የሚኖረው መንፈስ በመሆኑ ወልድ በሁሉ ቦታ የሚገኝ መንፈስ መሆኑን ይህ ቃል በሚገባ ያረጋግጣል።

“እናንተ ከታች ናችሁ፥ እኔ ከላይ ነኝ፤ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፥ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም” (ዮሐ 8:23)

በዚህ ስፍራ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአይሁዳውያን ጋር ያደረገውን ንግግር እንመለከታለን። ጌታ ኢየሱስ እንደሚሄድ፥ እነርሱም እንደሚፈልጉት፥ ነገር ግን እርሱ ወዳለበት መምጣት እንደማይችሉና በኃጢአታቸው እንደሚሞቱ ሲነግራቸው (ዮሐ 8:21) አይሁዳውያን እኔ ወዳለሁበት አትመጡም ሲላቸው ራሱን ይገድላል ማለቱ እንደሆነ በመሰላቸው ጊዜ (ዮሐ 8:22) እነርሱ ከታች እንደሆኑና እርሱ ከላይ እንደሆነ፥ እነርሱ ከዚህ ዓለም እንደሆኑና እርሱ ከዚህ ዓለም እንዳልሆነ ነገራቸው (ዮሐ 8:23) ስለዚህ እርሱ ወደ ዓለም የመጣው ከላይ ነው ማለት ነው።

✍️ በዚህ ክፍል ላይ “ከላይ” ተብሎ የተተረጎመው “ανω/አኖው” የሚለው የግሪክ ቃል ሰማይን ለማመልከት በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው (ቆላ 3:1) ስለዚህ ክርስቶስ እኔ ከላይ ነኝ ሲል ከሰማይ መጥቻለሁ ማለቱ ነው። ይህ ከሰማይ የወረደው ወልድ እንደሆነ በሚገባ ያሳያል።

ምክንያቱም በዮሐ 8:23 አውድ ከላይ መጣሁ ያለው ወልድ ነው፦

የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው” (ዮሐ 8:16)

“ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል” (ዮሐ 8:18)

“እንግዲህ። አባትህ ወዴት ነው? አሉት። ኢየሱስ መልሶ። እኔንም ወይም አባቴንም አታውቁም፤ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር አላቸው” (ዮሐ 8:19)

“26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው። 27 ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም” (ዮሐ 8:26-27)

“ስለዚህም ኢየሱስ። የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ” (ዮሐ 8:28)

የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም አላቸው” (ዮሐ 8:29)

➢ በጠቅላላው የዮሐንስ 8:23 አውድ “እኔ” እያለ ያለው አብን አባቴ ብሎ የሚጠራውና በአብ መላኩን በመግለፅ፥ የላከው አብ ከእርሱ ጋር መሆኑን በመናገር፥ “እኔንም ወይም አባቴንም” በማለት ራሱን በማንነት ደረጃ የለየው ወልድ ነው። ስለዚህ በዮሐ 8:23 ላይ ከላይ ነኝ በማለት ከሰማይ መምጣቱን የገለጸው ወልድ ነው።

በዮሐ 3:13 ግን ያ ከሰማይ የወረደው ወልድ በሁሉ ቦታ እንደሚገኝ ተገልጿል። ስለዚህ ወልድ በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይገኛል ማለት ነው። በሁሉ ቦታ ለመኖር ደግሞ መንፈስ መሆን ስለሚያስፈልግ፥ ወልድ በሁሉ ቦታ የሚገኝ መንፈስ መሆኑን ይህ ቃል በሚገባ ያረጋግጣል።

አስተውሉ! በመጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ አንድም ቦታ ከሰማይ ወርዶ ወደ ዓለም የገባው አብ ነው አልተባለም። ወይንም ደግሞ በዮሐ 3:13 ላይ ከሰማይ የወረደው “በሰው ልጅ ውስጥ ያለው” ነው አልተባለም። በብዙ ማስረጃዎች እንዳየነው ከሰማይ የወረደው ራሱ የሰው ልጅ/ወልድ እንጂ አብ አይደለም። ይህ በሁሉ ቦታ አለ የተባለለት ወልድ መሆኑን ያሳያል። በሁሉ ቦታ ያለው ደግሞ መንፈስ ስለሆነ ይህ እውነት ወልድ መንፈስ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

ማስረጃ ሰባት

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል” (ዮሐ 4:24)

በዚህ ስፍራ ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውሃ ልትቀዳ የመጣችው ሳምራዊቷ ሴት ለጠየቀችው ጥያቄ የሰጣትን መልስ እንመለከታለን። የእነርሱ አባቶች በዚያ ተራራ እንደሰግዱና እነርሱ (አይሁዳውያን) ግን ሰው ሊሰግድ የሚገባው በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ ስትለው (ዮሐ 4:20) በዚህ ተራራ ሆነ በኢየሩሳሌም የማይሰግዱበት ጊዜ እንደሚመጣና (ዮሐ 4:21) እግዚአብሔር መንፈስ እንደሆነ፥ የሚሰገድለትም በእውነትና በመንፈስ እንደሆነ ነገራት።

ስለዚህ ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተነስተን እግዚአብሔር ወይም በባህርይው መንፈስ እንደሆነ እንረዳለን። እግዚአብሔር መንፈስ ነው ማለት በባህርይው የማይታይ፥ የማይዳሰስ፥ የማይጨበጥ፥ ረቂቅ ነው ማለት ነው። ቁስ አይደለም ወይም ደግሞ ግዙፍ አካል የለውም ማለት ነው። የመንፈስ ትርጉም ይህ ነውና (ሉቃ 24:39) በዮሐ 4:24 መንፈስ የሚለው ቃል ገላጭ/adjective ሆኖ ሲሆን የገባው እግዚአብሔር በምንነቱ ምንድነው የሚለውን የሚመልስ ነው።

አምላክ በባህርይው መንፈስ መሆኑ ወልድ መንፈስ መሆኑን የሚያረጋግጠው እንዴት ነው?

አምላክ በባህርይው መንፈስ መሆኑ ወልድ መንፈስ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል። ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ወልድ አምላክ ነው! ከላይ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ለማየት እንደሞከርነው አምላክ በባህርይው መንፈስ ከሆነ አምላክ የሆነው ወልድ በባህርይው መንፈስ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ወልድ አምላክ መሆኑ ተረጋገጠ ማለት በባህርይው መንፈስ መሆኑ ተረጋገጠ ማለት ነው። በባህርይው መንፈስ ያልሆነ አምላክ የለምና። እንየው፦

“7 ስለ መላእክትምመላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ 8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግንአምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (ዕብ 1:7-8)

በዚህ ስፍራ ላይ የዕብራዊያኑ ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ ብሉይ ኪዳን ስለ እግዚአብሔር ልጅ የሚለውን ቃል ሲጠቅስ እንመለከታለን። በቁ.7 ላይ ብሉይ ኪዳን ፍጡራን መላእክት በባህርያቸው አገልጋዮች የተደረጉ መሆናቸውን እንደሚናገር ከመዝ 104:4 ከጠቀሰ በኋላ ስለ ልጁ ግን ምን እንደሚል ከመዝ 45:6 በመጥቀስ ይናገራል። እርሱም ልጁ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እንደሆነና የመንግሥቱም በትር የቅንነት በትር እንደሆነ ነው። ስለዚህ ወልድ አምላክ ነው።

በዕብ 1:7-8 ላይ በግልጽ የተገለጸውን እውነት አንዳንዶች ሊያስተባብሉ ሲሞክሩ እናያለን። በክፍሉ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር አምላክ በተባለበት በዚያው መንገድ አምላክ አልተባለም፥ እውነተኛ መለኮት መሆኑን አያሳይም ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ግን ፈጽሞ ሀሰት ነው። በክፍሉ ላይ ወልድ አብ አምላክ በተባለበት በዚያው መንገድና አውድ አምላክ መሆኑ ተገልጿልና። አንድ በአንድ እንየው፦

ሀ) ወልድ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ ተብሏል

በዕብ 1:8 ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ እውነኛ አምላክ መሆኑን በሚገባ የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም እንደ አዲስ ኪዳን አስተምህሮ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው፦

“ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም። የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል” (ራዕይ 11:15)

ዕብ 1:8 በተጻፈበት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እግዚአብሔር መሆኑ ተገልጿል። ነገር ግን በብሉይ ኪዳንም የተረጋገጠ ነው። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው በዕብ 1:8 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እየጠቀሰ የነበረው በመዝሙረ ዳዊት የሚገኘውን መሲሃዊ መዝሙር ነው (መዝ 45:6)

✏️ እንደ ኦሪትና እንደ ራሱ የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ አስተምህሮ ደግሞ ለዘላለም የሚነግሰው፥ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እግዚአብሔር ነው፦

እግዚአብሔር ለዘላለሙ እስከ ፍጻሜ ይነግሣል” (ዘጽ 15:18)

እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤ አሕዛብ ከምድሩ ይጠፋሉ” (መዝ 10:16)

“እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል” (መዝ 29:10)

መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው” (መዝ 145:13)

እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤ ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው። ሃሌ ሉያ” (መዝ 146:10)

በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ የተባለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ለየትኛውም ፍጡር ይህ አልተባለም። ፍጡራን በራሳቸው አውድ አምላክ/ኤሎሂም ተብለው ቢጠሩም፥ ዘላለማዊ ንግስናና ዙፋን ያላቸው አምላክ ተብለው ግን አያውቁም። አምላክ መባላቸው በዘላለማዊ ንግስና አልተገለጸም ወይም qualified አልተደረገም።

ደግሞም ከዚህ በሚለይ አውድ ለዘላለም ይነግሳሉ የተባሉ ፍጡራን ቢኖሩም ማናቸውም ለዘላለም የሚነግሱ አምላክ አልተባሉም። ዘላለማዊው ንግስናቸው በጌታ በመዋጀታቸው ያገኙት የጸጋ ንግስና እንጂ ከአምላክነት ጋር ተጫፍሮና ተያይዞ አልመጣም። ወይም ይህንን አይነት (ለዘላለም የሚነግስ) አምላክ ናቸው አልተባለላቸውም።

ወልድ ግን ዘላለማዊ ንግስና ወይም ዙፋን ያለው አምላክ መሆኑ ተገልጿል። ይህ ማለት በብሉይም በአዲስም ኪዳን የእግዚአብሔር ብቻ የሆነው መለኮታዊ ባህርይ አለው ማለት ነው። ይህ ወልድ የባህርይ አምላክ ለመሆኑ ግልጽና ሊታበል የማይችል ማስረጃ ነው። ስለዚህ አብ አምላክ በተባለበት በዚያው አውድ አምላክ አልተባለም ማለት አይቻልም።

ለ) ልጁን ከመላእክት ጋር ያነጻጽረዋል

ሐዋርያው ጳውሎስ በዕብ 1:7 ላይ የመላእክትን ማንነትና ባህርይ ከብሉይ ኪዳን በመጥቀስ ከገለጸ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ ከእነርሱ ጋር ያነጻጽረዋል፦

“7 ስለ መላእክትም። መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ 8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግንአምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (ዕብ 1:7-8)

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ባህርይ የሚናገረውን ነገር ከገለጸ በኋላ፥ ስለ ልጁ ግን ምን እንደሚል በቁ.8 ላይ ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት አገልጋይ መናፍስት እንዲሆኑ የተደረጉ የሚል ሲሆን፥ ስለ ልጁ ግን አምላክ ሆይ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ይኖራል ይላል

በዕብ 1:8 ላይ “..ስለ ልጁ ግን..” የሚለው። ለምን ግን አለ?

በዕብ 1:8 ላይ “..ስለ ልጁ ግን..” ያለበት ምክንያት ልጁ ከመላእክት በባህርይው እንደሚለይ ለመግለጽ ነው። ስለ መላእክት በባህርያቸው ፍጡራን አገልጋዮች እንደሆኑ ሲናገር፥ ስለ ልጁ ግን አምላክ መሆኑን ነው የተናገረው። ስለ መላእክት አዎ፥ ፍጡራን አገልጋዮች መሆናቸውን ተናገረ። ስለ ልጁ ግን አምላክ መሆኑን ነው የገለጸው። መላእክቱ በባህርያቸው አገልጋይ እንዲሆኑ የተደረጉ/የተፈጠሩ ናቸው። ልጁ ግን በባህርይው አምላክ ነው።

በዕብ 1:7-8 ባህርያዊ ንጽጽር (ontological contrast) እየተደረገ ነው። የመላእክቱ ባህርይና የልጁ ባህርይ ምን እንደሆነ በተነጻጻሪነት ቀርቧል። በዕብ 1:7 “መላእክቱን መናፍስት የሚያደረግ” ሲል እየተናገረ የነበረው ስለ ባህርያቸው (ontology) ነው። በባህርያቸው የተፈጠሩ መናፍስት ናቸው። ይህንን እውነታ በቁ.7 ላይ ከገለጸ በኋላ በቁ.8 ላይ “..ስለ ልጁ ግን..” በማለት ከመላእክት ባህርይ የሚለይ ባህርይ ስላለው ልጁ መናገር ይጀምራል። የልጁን ከመላእክት ባህርይ ጋር contrast በማድረግ ልጁን አምላክ በማለት ይጠራዋል።

ወልድ የባህርይ አምላክ (ontologically deity) ባይሆን ኖሮ የእርሱ ባህርይና የመላእክቱ ባህርይ በንጽጽሮሽ ባልቀረበ ነበር። መላእክቱ አገልጋይ መናፍስት የተደረጉ እርሱ #ግን አምላክ ነው ባልተባለለት ነበር። በእርሱና በመላእክቱ መካከል ባህርያዊ ንጽጽሮች ባልተደረገ ነበር። በእርሱና በመላእክቱ መካከል ባህርያዊ ንጽጽሮሽ ሊደረግ የቻለው እነርሱ በባህርያቸው ለማገልገል መናፍስት የተደረጉ/የተፈጠሩ ፍጡራን ሲሆኑ እርሱ ግን በባህርይው አምላክ በመሆኑ ነው።

የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ከመላእክት በባህርይው የተለየ ባህርየ-መለኮት በመሆኑ መላእክቱ ራሱ ሲያመልኩትና ሲሰግዱለት እንመለከታለን፦

“ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ። የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል” (ዕብ 1:6)

“መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች #በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ” (ራዕይ 5:8)

“መንፈስም አነሣኝ፥ በኋላዬም። የእግዚአብሔር ክብር ከቦታው ይባረክ የሚል የጽኑ ንውጥውጥታ ድምፅ ሰማሁ” (ሕዝ 3:12)

(በሕዝ 3:12 ላይ በኪሩቤል እየተመለከ ያለው የእግዚአብሔር ክብር በስጋ ከመምጣቱ በፊት የነበረው ወልድ ኢየሱስ ነው። ሊመሰገን፥ ሊባረክ የሚችለው አካላዊው የእግዚአብሔር ክብር እርሱ ነውና (ዕብ 1:3 ኢሳ 40:5))

መላእክት የእግዚአብሔርን ልጅ ሊያመልኩና ሊሰግዱለት የቻሉት እርሱ በባህርይ ከእነርሱ የተለየ መለኮት፥ እነርሱ ደግሞ ለማገልገል የተፈጠሩ ፍጡራን መናፍስት በመሆናቸው ነው። ይህ በተጨባጭ ወልድ አምላክ መሆኑንና አብ መለኮት በሆነበት በዚያው አውድ እውነተኛ መለኮት መሆኑን ያረጋግጣል።

አስተውሉ! ዕብ 1:7-8 ላይ አምላክ የተባለው ራሱ ወልድ እንጂ በውልድ ውስጥ ያለ ግን ወልድን ያልሆነ ሌላ ማንነት አይደለም። ክፍሉ ራሱ ወልድ አምላክ መሆኑን ይናገራል እንጂ “በልጁ ውስጥ ስላለው ግን እንዲህ ይላል..” አይልም። ስለዚህ ወልድ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ ነው ማለት ነው።

በዮሐ 4:24 ላይ ግን አምላክ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። የአምላክ ባህርይ ቁስ ያልሆነ መንፈስ እንደሆነ በዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተገልጿል። ወልድ ደግሞ ከመላእክት የተለየ፥ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ስለዚህ ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ ነው ማለት ነው! መንፈስ ያልሆነ አምላክ የለምና። ለዚህ ነው ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ በመሆኑ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ለዚህም ነው ስጋ ባልነበረበት ቅድመ-ዓለም እንኳን ነበር የተባለው (ዕብ 1:2 ዮሐ 17:5) በሁሉ ስፍራ ይገኛል የተባለው (ዮሐ 3:13 ኤፌ 4:10) ይህ ሁሉ ወልድ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

ማስረጃ ስምንት

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

በዚህ ስፍራ ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ ላይ የእግዚአብሔርን ልጅ የክርስቶስ ኢየሱስን ማንነት በመግለፅ መልእክቱን ሲያጠናቅቅ እንመለከታለን። እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነተኛ የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቦናን እንደሰጠን ከገለጸ በኋላ፥ እውነተኛ በሆነው በእርሱ እንዳለንና እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ይገልጽና ይህን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት እንደሆነ በመናገር ወልድን አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል።

ነገር ግን አንዳንዶች በ1ዮሐ 5:20 ላይ የተረጋገጠውን እውነት ሊያስተባብሉ ይሞክራሉ። በክፍሉ ላይ እውነተኛ አምላክ የተባለው ወልድ አይደለም ብለው ሊከራከሩ ሲሞክሩ እናያለን። ይህ ግን ፍጹም ሀሰት ነው። በክፍሉ ላይ የተባሉት ነገሮች በሙሉ ለወልድ የተባሉ ነገሮች ናቸው። አንድ በአንድ እንመልከተው፦

ሀ) የእግዚአብሔር ልጅ መጥቷል

በክፍሉ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ ተገልጿል። ይህ ማለት በክፍሉ ላይ የተባሉት ነገሮች በሙሉ የተባሉት ለዚህ መጥቷል ለተባለው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ የክፍሉ ተደራሲ ወልድ አይደለም ብሎ መከራከሪያ አይቻልም። በተጨማሪም የወልድ ወደ ዓለም መምጣት በሌሎች ስፍራዎች ተረጋግጧል፦

“እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ” (ዮሐ 5:43)

“ኢየሱስም አላቸው። እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና” (ዮሐ 8:42)

“በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ” (ዮሐ 12:46)

ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ” (ዮሐ 16:28)

“ጲላጦስም። እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው” (ዮሐ 18:37)

ወደ አለም የመጣው ወልድ መሆኑን የሚያረጋግጡ ከዚህ የበለጡ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። በዮሐ 5:20 ላይ የተባሉት ነገሮች በሙሉ የተባሉት ስለ ወልድ እንደሆነ የምናውቅበት የመጀመሪያው ማሳያ ይህ ነው። የመልእክቱን መዝጊያ የሚጀምረው የእርሱን መምጣት በመናገር ነውና።

ለ) እውነተኛ የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቦናን ሰጥቶናል

ሐዋርያው ዮሐንስ የእግዚአብሔር ልጅ መምጣቱን ከገለጸ በኋላ፥ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ እውነተኛ የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቦናን እንደሰጠን ይናገራል። የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ እናውቀው ዘንድ ልቦናን የሰጠን እውነተኛ አብ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጌታ ኢየሱስ አባት እግዚአብሔር አብ በተደጋጋሚ እውነተኛ ተብሎ ተጠርቷል፦

“እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ እርሱ እውነተኛና ቅን ነው” (ዘዳ 32:4)

“በእጅህ ነፍሴን እሰጣለሁ፤ የእውነት አምላክ አቤቱ፥ ተቤዥተኸኛል” (መዝ 31:5)

“እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፥ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአልና፥ ከዓይኔም ተሰውሮአልና” (ኢሳ 65:16)

“ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ” (ዮሐ 3:33)

“እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር። እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው” (ዮሐ 7:28)

“ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው” (ዮሐ 8:26)

እውነተኛ የሆነውን አምላክ እግዚአብሔርን እናውቅ ዘንድ ልቦና የሰጠን ደግሞ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ሐዋርያው ተናግሯል። ይህ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተረጋገጠ እውነት ነው፦

“ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም” (ማቴ 11:27)

“ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ” (ሉቃ 10:22)

“መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው” (ዮሐ 1:18)

ይህ በክፍሉ ላይ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ ያሳያል። እውነተኛ የሆነውን (አብን) እናውቅ ዘንድ ልቦናን የሰጠን መምጣቱ የተነገረለት ወልድ ነው። ስለዚህ አሁንም እየተወራ ያለው ስለ ወልድ ነው። እንደመጣ፥ ልቦናን እንደሰጠ የተነገረለት እርሱ ነውና። ስለዚህ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ አይደለም ማለት አይቻልም።

ሐ) እውነተኛ በሆነው በእርሱ አለን

ሐዋርያው ዮሐንስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነተኛ የሆነውንም እናውቅ ዘንድ ልቦናን እንደሰጠን ከተናገረ በኋላ እውነተኛ በሆነው በእርሱ እንዳለን ይናገራል። በዚህ ቦታ ላይ እውነተኛ ብሎ የሚጠራው ራሱ ወልድን ነው። ቀደም ብሎ ወልድ እናውቀው ዘንድ ልቦና የሰጠንን አብን እውነተኛ ብሎ ከጠራው በኋላ፥ ቀጠል አድርጎ እርሱን እናውቅ ዘንድ ልቦና የሰጠንን ወልድንም እውነተኛ ብሎ ይጠራዋል። ይህም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተረጋገጠ ነው፦

“ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ 14:6)

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን” (ዮሐ 1:14)

“በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል” (ራዕይ 3:7)

“በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል” (ራዕይ 3:14)

“ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም” (ራዕይ 19:11)

“በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል” (ኤፌ 4:21)

“ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ” (ዮሐ 1:17)

ሐዋርያው እውነተኛ በሆነው በእርሱ አለን ሲል እውነተኛ ያለው ወልድን መሆኑን የምናውቅበት ተጨማሪ ማሳያ አማኞች ያሉት በወልድ እንደሆነ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመረጋገጡ ነው፦

በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም” (ዮሐ 15:4)

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል” (ዮሐ15:5)

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል” (ዮሐ 15:7)

– በዮሐንስ 15 አውድ የወይን ግንድ እኔ ነኝ ገበሬውም አባቴ ነው ያለው ወልድ መሆኑን ልብ ይሏል (ዮሐ 15:1)

“እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ” (ዮሐ 14:20)

“ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ” (ዮሐ 6:56)

“ነገር ግን። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው” (1ቆሮ 1:30-31)

አስተውሉ! ቀደም ብሎ እውነተኛ የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቦናን የሰጠን ሲል እውነተኛ ያለው አብን ነው። ልቦናን የሰጠን ያለው ደግሞ ልጁን ነው። ቀጠል አድርጎ ግን እውነተኛ በሆነው በእርሱ አለን ሲል እውነተኛ ያለው ራሱ ወልድን ነው። አሁን እየተባሉ ያሉት ነገሮች የተባሉት ለወልድ ነው። መምጣቱ፥ ልቦናን መስጠቱ፥ እውነተኛ መሆኑ፥ እኛም በእርሱ መሆናችን የተነገረው ለወልድ ነው።

ሐዋርያው “..እውነተኛ በሆነው በእርሱ አለን..” ሲል እውነተኛ ያለው ወልድን እንደሆነ የምናውቀው፥ ያን ካለ በኋላ በቀጥታ ይህ እውነተኛ የሆነው ማን እንደሆነ በመግለጹ ነው፦

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

እውነተኛ በሆነው በእርሱ አለን ካለ በኋላ ያ በእርሱ እንዳለን የተናገረለት እውነተኛ ወልድ መሆኑን በቀጥታ “..እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው..” በማለት ገልጿል። ይህ በሁለተኛው ረድፍ ላይ በእርሱ አለን የተባለው እውነተኛ ወልድ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል። ስለዚህ የመጣው፥ አብን እናውቅ ዘንድ ልቦናን የሰጠን፥ በእርሱ ያለነው እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ነው ማለት ነው። ከላይ ጀምሮ እየተወራ ያለው ስለ እርሱ ነውና።

መ) እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው

ሐዋርያው ዮሐንስ የእግዚአብሔር ልጅ መምጣቱን፥ አብን እናውቅ ዘንድ ልቦናን እንደሰጠን፥ በእርሱ ዘንድ ያለነው እውነተኛ እርሱ መሆኑን ከገለጸና እነዚህ ነገሮች ሁሉ እየተነገሩ ያሉት ስለ እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ቀጠል አድርጎ ከተናገረ በኋላ፥ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት መሆኑን ይናገራል።

ከላይ እያየን እንደመጣነው ከመጀመሪያው ጀምሮ እየተናገረ የነበረው ስለ ወልድ በመሆኑ በዚህ ቦታ ላይ እውነተኛ አምላክ የተባለው ወልድ አይደለም ማለት አይቻልም። እውነተኛ አምላክ ያለውን ወልድን ነው። ሲቀጥል በዚህ ቦታ ላይ የተገለጸው የወልድ አምላክነት በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተረጋግጧል፦

“ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት” (ዮሐ 20:28)

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” (ዮሐ 1:1)

“ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (ዕብ 1:8)

“አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን” (ሮሜ 9:5)

“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ 9:6)

አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (መዝ 45:6)

“5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው” (ኤር 23:5-6)

✍️ በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው እውነተኛ አምላክ ያለው ወልድን መሆኑን የምናውቅበት ሌላኛው መንገድ፥ እውነተኛ አምላክ ካለው በኋላ እርሱን የዘላለም ሕይወት ብሎ በመጥራቱ ነው። ወልድ በተቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የዘላለም ሕይወት ተብሏልና፦

“እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም” (ዮሐ 10:28)

“በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች” (ዮሐ 1:4)

“ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ 14:6)

“ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል” (ዮሐ 11:25)

“ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን” (1ዮሐ 1:2)

ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ” (ቆላ 3:4)

✍️ 1ዮሐ 5:20 በጻፈበት በዚያው አውድ እንኳን የዘላለም ሕይወት የሆነው ወልድ መሆኑን ሐዋርያው ዮሐንስ ገልጿል፦

“11 እግዚአብሔርም የዘላለምን_ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። 12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም” (1ዮሐ 5:11-12)

ስለዚህ በአውዱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ያለው የእግዚአብሔርን ልጅ ነው። ስለዚህ ሐዋርያው በ1ዮሐ 5:20 ላይ መምጣቱን፥ ልቦናን መስጠቱን፥ በእርሱ ያለነው እውነተኛ እርሱ መሆኑን፥ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት መሆኑን የተናገረለት ለእግዚአብሔር ልጅ ለክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ይህ ወልድ አምላክ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

አስተውሉ! በ1ዮሐ 5:20 ላይ እውነተኛ አምላክ የተባለው ራሱ ወልድ እንጂ በውልድ ውስጥ ያለ ግን ወልድን ያልሆነ ሌላ ማንነት አይደለም። ክፍሉ ራሱ ወልድ አምላክ መሆኑን ይናገራል እንጂ “..በልጁ #ውስጥ ያለው እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” አይልም። እውነተኛ አምላክ የሚለው ራሱን ወልድን ነው።

በዮሐ 4:24 ላይ ግን አምላክ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። የአምላክ ባህርይ ቁስ ያልሆነ መንፈስ እንደሆነ በዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተገልጿል። አሁን እንዳየነው ደግሞ ወልድ እውነተኛ አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ስለዚህ ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ ነው ማለት ነው! መንፈስ ያልሆነ አምላክ የለምና። ለዚህ ነው ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ በመሆኑ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ለዚህም ነው ስጋ ባልነበረበት ቅድመ-ዓለም እንኳን ነበር የተባለው (ዕብ 1:2 ዮሐ 17:5) በሁሉ ስፍራ ይገኛል የተባለው (ዮሐ 3:13 ኤፌ 4:10) ይህ ሁሉ ወልድ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

ማስረጃ ዘጠኝ

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” (ዮሐ 1:1)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ዮሐንስየ የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ ኢየሱስን ማንነት በመግለፅ ሲጀምር እናያለን። በመጀመሪያ እንደነበር፥ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደነበር፥ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር እንደነበር ይገልጻል። በዮሐ 1:1 ላይ ቃል እግዚአብሔር የተባለበት ሰዋሰዋዊ አወቃቀር እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን አምላክ ከተባለበት አወቃቀር ጋር አንድ አይነት ሲሆን (መዝ 118:27) ይህ ቃል/ወልድ አምላክ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

አንዳንዶች ግን ዮሐ 1:1 ላይ ያለው ቃል ራሱ ወልድ አይደለም ሲሉ ይሰማሉ። እንደነርሱ አረዳድ እግዚአብሔር የተባለው ቃል ራሱ ወልድ ሳይሆን የአብ ንግግር ወይም ደግሞ ራሱ አብ ነው ሲሉ ይሰማሉ። ይህ ግን ፈጽሞ ስህተት ነው። በዮሐንስ 1:1 ላይ ለቃል የተባሉት ነገሮች በሙሉ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለወልድ የተባሉ ነገሮች በመሆናቸው ቃል ራሱ ወልድ ነው። እንየው፦

ሀ) በመጀመሪያ ነበር

በዮሐንስ 1:1 ላይ ለቃል ተብለው ከምናያቸው የመጀመሪያ ነገሮች አንዱ በመጀመሪያ እንደነበር ነው። ከጥንት ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረው እግዚአብሔር ሲሆን (መዝ 55:19 ኢሳ 43:13 ኢሳ 41:4) ከመጀመሪያው ጀምሮ ነበር ማለት ከፍጥረት ጅማሬ ጀምሮ ነበረ ማለት ነው። ዘላለማዊነት የሚገልጽ ቃል ጽንሰ ሀሳብ ነው። ስለዚህ ቃል በመጀመሪያ ነበር ማለት ከፍጥረት ጅማሬ ጀምሮ ነበር ማለት ነው። ይህ ቃል ራሱ ወልድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ምክንያቱም ወልድ ከፍጥረት ሁሉ በፊት ነበር፦

“ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን” (ዕብ 1:2)

በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር በብዙ ጎዳና ለአባቶቻቸው በነቢያት ተናግሮ (ዕብ 1:1) በዚህ ዘመን መጨረሻ ላይ ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ እንደተናገረ ይናገራል። ዓለማት ማለት ጠቅላላ የተፈጠረው ፍጥረት ሲሆን (ዕብ 11:3) በዕብ 1:2 መሰረት እነዚያ ዓለማት የተፈጠሩት በልጁ ነው። ስለዚህ ልጁ ዓለማት ሲፈጠሩም ነበር ማለት ነው። ያኔም ባይኖር ኖሮ ዓለማት በእርሱ ባልተፈጠሩ ነበርና። ወልድ ዓለማት ሲፈጠሩም የነበረ መሆኑ በመጀመሪያ የነበረው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

“አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል” (ሚክ 5:2)

በዚህ ስፍራ ላይ እግዚአብሔር አምላክ አወጣጡ ከቀድሞ ከዘላለም የሆነ ገዢ ከቤተልሔም እንደሚወጣለት ሲናገር እንመለከታለን። ይህ ለእግዚአብሔር የሚወጣለት ገዢ ከቀድሞ ከዘላለም ጀምሮ የነበረ ነው። በዚህ ስፍራ የገቡት “ከቀድሞ” እና “ከዘላለም” የሚሉት ቃላት አንድ ላይ ሲገቡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን እውነታ የሚገልጹ ቃላት ናቸው (ምሳ 8:23) ስለዚህ ይህ ገዢ/መሲሁ ከዘላለም ጀምሮ የነበረ አካል ነው ማለት ነው።

ሚክ 5:2 ላይ ያለው መሲሃዊ ትንቢት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ተጠቅሷል (ማቴ 2:5-6) በተጨማሪም ይህ የሚወለደው ዘላለማዊ ገዢ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በዚያው አውድ ላይ ተገልጿል (ማቴ 2:14-15) ስለዚህ ከቀድሞ ከዘላለም ጀምሮ የነበረውው ወልድ ነው ነው ማለት ነው። ወልድ ከቀድሞ ከዘላለም ጀምሮ መኖሩ በመጀመሪያ የነበረው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

ሚክ 5:2 ላይ ከቀድሞ ከዘላለም ጀምሮ ነበር የተባለለት ገዢ አብ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ይህ ገዢ “ይወጣልኛል” ነው ያለው። ለአባቱ በስጋ ከቤተልሔም ተወልዶ የወጣለት/የተነሳለት ልጁ ነው። አብ ነው ከተባለ ግን አብ ለአብ ወጣ ወደሚል absurdity ሊያመራ ነው። ስለዚህ ከቀድሞ ከዘላለም ጀምሮ የነበረው፥ ለእግዚአብሔር የወጣው ገዢ ወልድ እንጂ አብ አይደለም።

አልፋና ዖሜጋ ፊተኛውና ኋለኛውመጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” (ራዕ 22:13)

በዚህ ቦታ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛና ኋለኛ፥ መጀመሪያና መጨረሻ መሆኑን ሲናገር እንመለከታለን። እነዚህ ቃላት በሙሉ ቅድመ-ሕልውናን (pre-existence) የሚገልጹ ቃላት ሲሆኑ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ የእግዚአብሔርን ቅድመ-ሕልውና ለመግለጽ ገብተዋል (ራዕ 21:6 ኢሳ 48:12 ኢሳ 44:6) ወልድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእነዚሁ ቃላት ራሱን መግለጹ በመጀመሪያ የነበረው ቃል መሆኑን ያሳያል።

በዚህ ቦታ ላይ ተናጋሪ ራሱ ወልድ መሆኑን የምናውቀው፥ ወረድ ብሎ በቀጥታ እርሱ ኢየሱስ እንደሆነና የዳዊት ስርና ዘር የሚያበራም ኮኮብ እንደሆነ በመግለጹ ነው (ራዕ 22:16) ስለዚህ አልፋና ኦሜጋው፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ራሱ ወልድ ነው ማለት ነው። ወልድ እነዚህን ነገሮች በሙሉ መሆኑ በመጀመሪያ የነበረው ቃል መሆኑን ያሳያል።

በራዕይ 22:13 ላይ የተባለው ነገር የተባለው ለአብ ነው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም በቀ.13 ላይ ያለው ራሱ ተናጋሪ በቁ.16 ላይ የዳዊት ዘር መሆኑን ተናግሯል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የዳዊት ዘር የሆነው ወልድ እንጂ አብ አይደለም (ሮሜ 1:1-3 ሐዋ 13:22-23) ስለዚህ በቁ.13 ቀደምሞ እንደነበር የተነገረለት ወልድ እንጂ አብ አይደለም።

“ኢየሱስም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው” (ዮሐ 8:58)

በዚህ ስፍራ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አብርሃም ሳይወለድ እንደነበር ሲናገር እንመለከታለን። ይህ ቅድመ-ሕልውናን (pre-existence) የሚያመለክት ንግግር ሲሆን በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ከፍጥረት አስቀድሞ እንደነበር ለማሳየት ጥቅም ላይ ቃል ነው (መዝ 90:2) ወልድ ክርስቶስ ኢየሱስ ይህንን መናገሩ በመጀመሪያ የነበረው ቃል መሆኑን ያሳያል

በዚህ ክፍል ላይ ተናጋሪው ወልድ መሆኑን የምናውቀው ይህን ቃል ከማለቱ በፊት ከፍ ብሎ አባት እንዳለው በመናገሩ ነው (ዮሐ 8:54) እርሱን የሚያከብረው አምላካችን የሚሉት አባቱ እንደሆነ በመናገሩ አብርሃም ሳይወለድ በፊት የነበረው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ማረጋገጥ እንችላለን። ይህ ወልድ በመጀመሪያ የነበረው ቃል እንደሆነ ያሳያል።

በዮሐ 8:58 ላይ አብርሃም ሳይወለድ በፊት እኔ አለሁ ያለው አብ ነው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አብርሃም ሳይወለድ በፊት የነበረው ማንነት አባት አለው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ አባት ያለው ወልድ ነው (ሮሜ 15:6 2ዮሐ 1:3) ስለዚህ ይህን የተናገረው አብ ነው ከተባለ አብ አባት አለው ወደሚል absurdity ያመራል። ሲቀጥል በዮሐ 8:58 አባቴ ያለው ማንነት አብርሃም ሳይወለድ እንደነበር ተናገረ እንጂ “..በእኔ ውስጥ ያለው አብርሃም ሳይወለድ ነበር..” አላለም። ስለዚህ በቁ.58 ላይ የተነገረለት ማንነት ወልድ እንጂ አብ አይደለም።

ለ) በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር

ሐዋርያው ዮሐንስ ቃል በመጀመሪያ እንደነበር ከገለጸ በኋላ ያው ራሱ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ እንደነበር ይናገራል። ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ማለት ቃል አለም ከመፈጠሩ በፊትም እንኳን ቃል ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ነበር ማለት ነው። በቃልና በእግዚአብሔር መከካል የነበረው አብሮነት የሚያሳይ ነው። ይህ በመጀመሪያ የነበረው ቃል ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

ምክንያቱም ወልድ አለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር ነበርና፦

“አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ” (ዮሐ 17:5)

በዚህ ስፍራ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ አባቱን እግዚአብሔር አብን ዓለም ሳይፈጠር በእርሱ ዘንድ በነበረው ክብር እንዲያከብረው ሲጠይቀው እናያለን። ይህ ማለት ወልድ ክርስቶስ ኢየሱስ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር ክብር ኖሮት ነበር ማለት ነው። ያኔ በነበረው በዚያው ክብር አሁን በስጋ ከመጣ በኋላ እንዲያከብረው ሊጠይቀው የቻለው ለዚህ ነው። ከአለም መፈጠር በፊት ከእርሱ ጋር ነበርና።

በዮሐ 17:5 ተናጋሪው ወልድ መሆኑን የምናውቀው አብን “..አባት ሆይ..” ብሎ በመጥራቱ ነው። አብን አባት ሆይ ብሎ ከጠራው እርሱ ልጁ ነው ማለት ነው። ሲቀጥል ደግሞ በዚያው አውድ ራሱን “..ልጅህን..” ብሎ በመጥራቱ (ዮሐ 17:1-2) ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር የነበረው እርሱ ወልድ መሆኑን ገልጿል። ወልድ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር የነበረ መሆኑ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

“1 ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ 2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን” (ዕብ 1:1-2)

በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ለአባቶቻቸው በነቢያት ተናግሮ በዚህ በዘመን መጨረሻ ግን ሁሉ ወራሽ ባደረገው ደግሞም አለማትን በፈጠረበት በልጁ እንደተናገረን ሲናገር እናየዋለን። ዓለማትን ሲባል መላው የተፈጠረው ፍጥረት ሲሆን (ዕብ 11:3) በዕብራውያን 1:2 አውድም የመላውን ፍጥረት መፈጠር ያመለክታል (ዕብ 1:8-12)

ዓለማት ሲፈጠሩ እግዚአብሔር ከነበር፥ ደግሞም ዓለማትንም የፈጠረው በልጁ ከሆነ፥ ልጁ ከእርሱ ጋር ነበር ማለት ነው። ያኔም ቢሆን ልጁ ከእርሱ ጋር ባይኖር ኖር እግዚአብሔር በእርሱ (በልጁ) ዓለማትን ባልፈጠረ ነበር። አብ ዓለማትን በልጁ ሊፈጥር የሚችለው ልጁ ያኔም ከእርሱ ጋር ከነበር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ዓለማትን በልጁ መፍጠሩ፥ ልጁ/ወልድ ያ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

“ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን” (1ዮሐ 1:2)

በዚህ ስፍራ ሐዋርያው ዮሐንስ ከአብ ዘንድ የነበረውን፥ ለእኛም የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት እናወራላችኋለን ሲል እንመለከታለን። ይህ ሐዋርያት ያዩት፥ ለእነርሱም እንደተገለጠ የሚመሰክሩለት የዘላለም ሕይወት የእግዚአብሔር ልጅ ሲሆን በዚህ ክፍል ላይ ከአብ ጋር እንደነበር ተገልጿል። ይህ ወልድ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

ሕይወት ነኝ ያለው ወልድ ነው (ዮሐ 14:6 ዮሐ 11:25) የተገለጠው ወልድ ነው (1ዮሐ 3:9 1ዮሐ 3:5) ሐዋርያት ያዩት ወልድን ነው (ዮሐ 1:14 2ጴጥ 1:16-18) ሐዋርያት በስጋ እንደተላከ የመሰከሩትም ለወልድ ነው (1ዮሐ 4:10 1ዮሐ 4:14 1ዮሐ 4:1-2 ሮሜ 8:3) በአጠቃላይ በ1ዮሐ 1:2 የተባሉት ነገሮች በሙሉ የተባሉት ለወልድ ነው። ስለዚህ በክፍሉ ከአብ ዘንድ ነበር የተባለው የዘላለም ሕይወት ወልድ ነው ማለት ነው። ወልድ ከአብ ዘንድ የነበረ መሆኑ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

“5 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። 6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም” (ፊል 2:5-6)

በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖችን ስለ ትህትና ሲያስተምር (ፊል 2:3) የመጨረሻውን የትህትና አርዓያ የሆነውን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ምሳሌ ያነሳላቸዋል። በኢየሱስ ዘንድ የነበረ ሀሳብ በእነርሱ ዘንድ እንዲሆን ከነገራቸው በኋላ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር እንዳልቆጠረው ይነግራቸዋል።

በፊል 2:6 ላይ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ነበር የተባለው ወልድ ነው። ምክንያቱም በቁ.5 ላይ “በኢየሱስ ክርስቶስ” የነበረ ሀሳብ ይላልና። በመላው መጽሐፍ ቅዱስ “ኢየሱስ ክርስቶስ” የሚለው ስም የወልድ ስም ሆኖ ነው ጥቅም ላይ የዋለው (1ዮሐ 3:23 ሉቃ 1:31-32) አንድም ጊዜ የአብ ስም ሆኖ አያውቅም። ስለዚህ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር የነበረውና በቁ.6 ላይ “እርሱ” የተባለው ወልድ ነው።

በፊል 2:6 ላይ “መልክ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ሞርፊ/μορφή” የሚለው ቃል ሲሆን “ባህርይ/nature” ወይም “ሕላዌ/essence” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ነው። ይህ ማለት በፊሊ 2:6 መሰረት ወልድ በአብ ባህርይ ሲኖር ነበር ማለት ነው። ወልድ ሲኖርበት የነበረው መልክ/ባህርይ ራሱ የአብ ባህርይ ነው። የመለኮታዊ ባህርይ አንድነት አለ። ልጁ ምንም እንኳ በአባቱ ባህርይ ሲኖር የነበረ ቢሆንም ከእርሱ ጋር መቀማትን እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም።

ወልድ በአባቱ ባህርይ ሲኖር ነበር ማለት ከአባቱ ጋር ነበር ማለት ነው። ከአባቱ ጋር ስለነበር ነው፥ በእርሱ ባህርይ ሊኖር የቻለው። ከእርሱም ጋር መቀማትን እንደማይገባ ነገር ላይቆጥር የቻለው ያኔም ቢሆን አብሮት ስለነበር ነው። ያኔ ከእርሱ ጋር ባይሆን ኖሮ እነዚህ ነገሮች በሙሉ ሊባሉለት ባልተቻለ ነበር። ይህ ሁሉ የሆነው ያኔም ከእርሱ ጋር ስለነበር ነው። ይህ ወልድ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

ሐ) ቃልም እግዚአብሔር ነበር

ሐዋርያው ዮሐንስ ቃል በመጀመሪያ እንደነበር፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ እንደነበር ከገለጸ በኋላ እሱ ራሱ እግዚአብሔር እንደነበር ይገልጻል። በዮሐ 1:1 ላይ ቃል እግዚአብሔር የተባለበት ሰዋሰዋዊ አወቃቀር እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን አምላክ ከተባለበት አወቃቀር ጋር አንድ አይነት ሲሆን (መዝ 118:27) እውነተኛ አምላክነትን ይገልጻል። ይህ ወልድ ራሱ ቃል መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ምክንያቱም ወልድ አምላክ/እግዚአብሔር ነውና፦

“ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (ዕብ 1:8)

በዚህ ስፍራ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ወልድን ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እንደሆነ ሲናገር እናያለን። በቁ.7 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ መላእክትን አገልጋይ መናፍስትና የእሳት ነበልባል እንደሆነ እንደሚል ከገለጸ በኋላ ልጁ ግን ከእነርሱ በተለየ ሁኔታ አምላክ መሆኑን ሲገልጽ እንመለከታለን። ልጁ ከመላእክት ጋር በባህርይው ተነጻጽሮ እንኳ ከእነርሱ በመለየት አምላክ የተባለው በባህርይው አምላክ በመሆኑ ነው።

በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን (ዘጽ 15:18 መዝ 10:16 መዝ 29:10 መዝ 145:13 መዝ 146:10 ራዕ 11:15) ልጁ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ መባሉ እውነተኛ መለኮት መሆኑን ያረጋግጣል። የእግዚአብሔር ልጅ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ መሆኑ ራሱ እግዚአብሔር የነበረው ቃል መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

ይኸው መሲሃዊ ትንቢት በብሉይ ኪዳንም የሚገኝ መሲሃዊ ትንቢት ሲሆን (መዝ 45:6-7) የሚመጣው መሲህ አምላክ መሆኑን በሚገባ ይናገራል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የሚመጣው ቅቡዕ/መሲህ ወልድ ነው (1ዮሐ 3:23 ሐዋ 10:38 ሉቃ 1:32) ስለዚህ በዚህ መሲሃዊ ትንቢት አምላክ የተባለው አብ ሳይሆን ልጁ ነው።

“5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው” (ኤር 23:5-6)

በዚህ ስፍራ ላይ እግዚአብሔር አምላክ የሚመጣውን መሲህ እግዚአብሔር ጽድቃችን ብሎ ሲጠራው እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሲሁ ከተጠራባቸው ስሞች አንዱ “ቁጥቋጥ” ሲሆን (ዘካ 3:8 ኤር 33:15-16 ኢሳ 11:1) ይህ ከዳዊት ዘር የሚመጣው መሲህ/ቁጥቋጥ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” ተብሎ ተጠርቷል። በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሙ “እግዚአብሔር/ያሕዌ” የሆነ አካል/person እግዚአብሔር ብቻ ነው (ዘጽ 6:3 ዘጽ 15:3 ዘዳ 28:58 ኤር 10:16 ኤር 51:19 ኤር 50:34) መሲሁ በቀጥታ ስሙ ያሕዌ መባሉ አምላክ መሆኑን ያሳያል።

ከተሞች፥ መሰዊያዎች በገዢያቸው ስምና dedicate በተደረጉለት አምላክ ስም የተጠሩ ቢሆንም በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእግዚአብሔር በቀር ያሕዌ ተብሎ የተጠራ person የለም። ሲቀጥል በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስም ባህርይን ይወክላል (ምሳ 18:10/መዝ 61:3 መዝ 20:1/መዝ 91:14) ስለዚህ ስሙ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው ማለት ይህ መሲሁ በባህርይው ያሕዌ ነው ማለት ነው። በባህርይው የሆነው ነገር እየተነገረ ነው። መሲሁ ወልድ በባህርይው እግዚአብሔር ጽድቃችን መሆኑ ያ እግዚአብሔር የነበረው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለው አብ ነው ብሎ መከራከር አይቻልም። ምክንያቱም ቁጥቋጥ የሆነውን መሲሁ አስነሳዋለሁ ያለው አብ ነው (ቁ.5) ስለዚህ እግዚአብሔር የሆነው ቁጥቋጥ አብ ነው ከተባለ አብ አብን አስነሳ የሚል absurdity ይሆናል። አብ ያስነሳው ልጁን ነውና

ሲቀጥል ይህ የሚነሳው መሲህ ለዳዊት እንደሚነሳ ተገልጿል (ቁ.5) እግዚአብሔር አምላክ ለዳዊት አስነሳለሁ ሲል ቀድሞ ለዳዊት የገባውን ኪዳን እፈጽማለሁ ማለት ነው (1ዜና 17:11-14) እርሱም ከዘሩ በዙፋኑ ለዘላለም እንደሚያስቀምጥ ነው። ይህም መሐላ በመዝ 132:11 ተደግሟል፥ በአዲስ ኪዳንም ለክርስቶስ ኢየሱስ ተጠቅሷል (ሐዋ 2:30-31)

በመላው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከዳዊት ዘር የተወለደው ወልድ እንጂ አብ አይደለም (ሮሜ 1:1-3 ሐዋ 13:22-23) ስለዚህ በኤር 23:5-6 ላይ ለዳዊት ይነሳል የተባለው ቁጥቋጥ ወይም መሲህ ወልድ እንጂ አብ አይደለም። አብ የዳዊት ዘር አይደለምና። ስለዚህም በዚያ ስፍራ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ አምላክ መሆኑ የተገለጸው ወልድ እንጂ አብ አይደለም።

“ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት” (ዮሐ 20:28)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ቶማስ ከሞት የተነሳውን ክርስቶስ ኢየሱስን ካየ በኋላ የመለሰለትን መልስ እንመለከታለን። ክርስቶስ ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ከአብርሃም በፊት እንደነበር (ዮሐ 8:58) ከሰማይ እንደወረደ (ዮሐ 6:38 ዮሐ 8:23) ከአብ ጋር አንድ እንደሆነ (ዮሐ 10:27-30) ሕይወት እንደሚሰጥ (ዮሐ 5:19) ራሱን ከሞት እንደሚያስነሳ (ዮሐ 10:17) ቀድሞም ከአብ ጋር እንደነበር (ዮሐ 6:62) በሰማይም በምድርም በአንድ ጊዜ እንደሚገኝ (ዮሐ 3:13) በመጨረሻው ቀን የሚመጣው ጌታ እንደሆነ (ማቴ 24:42-44) ተናግሮ ነበር።

እነዚህን ነገሮች ስለ ራሱ ሊናገር የሚችለው በስጋ የመጣው አምላክ ብቻ ነው። ፍጡር ሰው ይህን ስለ ራሱ ሊናገር አይችልም። ታዲያ ግን ክርስቶስ የምርም እነዚህን ነገሮች እንደሆነ በምን ተረጋገጠ? በትሳኤው! ሞቶ ሲነሳ የእውነትም ከዚያ ቀደም ስለ ራሱ የተናገራቸውን ነገሮች እንደሆነ ተረጋገጠ። ስለዚህም ቶማስ ከሞት እንደተነሳ በዓይኑ ሲመለከት አምላኬና ጌታዬ ብሎ መለሰለት። የምርም ከዚያ ቀደም ነኝ ያለውን ወደ ምድር የመጣው መለኮት እንደሆነ በትንሳኤው አረጋገጠ። ወልድ ጌታና አምላክ መሆኑ ያ እግዚአብሔር የነበረው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

በዮሐ 20:28 “ጌታና አምላክ” የተባለው አብ አይደለም። ምክንያቱም በቁ.28 ላይ አምላክ የተባለው አካል በዚያው አውድ አባት እንዳለው ተገልጿል (ዮሐ 20:17) በአብ እንደተላከም ተገልጿል (ዮሐ 20:21) ስለዚህ አብ ነው ከተባለ፥ አብ በአብ ተላከ፥ አብ የአብ ልጅ ነው ወደሚል absurdity ያመራል። ከምንም በላይ ደግሞ ያው ጌታና አምላክ የተባለው አካል ወልድ መሆኑ በዚያው አውድ መገለጹ (ዮሐ 20:31) አምላክ የተባለው ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል።

መ) ሁሉ በእርሱ ሆኗል

ሐዋርያው ዮሐንስ ቃል እግዚአብሔር እንደነበር ከገለጸ በኋላ ሁሉ በእርሱ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን፦

ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም” (ዮሐ 1:3)

“ሁሉ በእርሱ ሆነ” የሚለው ሀረግ የአብን ፈጣሪነት ለመግለጽ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የዋለ ሲሆን (ሮሜ 11:36) ቃል የሁሉ ፈጣሪ እንደሆነ ያሳያል። ይህ ቃል ራሱ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

ምክንያቱም ወልድ የሁሉ ፈጣሪ ነው፦

“8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ 10 ይላል። ደግሞ። ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ 11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ 12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም” (ዕብ 1:8-12)

በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰማይና ምድር የወልድ የእጅ ስራ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን። በቁ.8-9 ላይ ልጁ አምላክ መሆኑን፥ በእግዚአብሔር መቀባቱን ከገለጸ በኋላ ይቀጥልና ራሱኑ ወልድን ምድርን ከጥንት እንደመሰረተ፥ ሰማያትም የእጆቹ ስራ እንደሆኑ ይናገራል። ይህ ማለት ሰማይና ምድርን የሰራው ወልድ ነው ማለት ነው። በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ለወልድ እየጠቀሰ ያለው መዝ 102:25-27 ሲሆን የጠቀሰውም ክፍል የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት የሚገልጽ ክፍል ነው። ይህ ወልድ ሁሉ በእርሱ የሆነው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል

ዕብ 1:8-12 ልጁ የሰማይና የምድር ሰሪ ነው ይላል እንጂበልጁ ውስጥ ያለው የሰማይና የምድር ሰሪ ነውአይልም። የአብ ፈጣሪነት በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተነገረ ቢሆንም በዚህ ቦታ ላይ እየተነገረ ያለው ግን የራሱ የወልድ ፈጣሪነት ነው። በመፍጠር ረገድ ወልድ ከአብ ጋር አንድነት ያለው ሲሆን፥ ይህ ከአብ ጋር በአንድነት ያለው ፈጣሪነቱ ከተገለጸባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንዱ ዕብ 1:8-12 ነው።

“1 ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ 2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን” (ዕብ 1:1-2)

በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር አምላክ ዓለማትን በልጁ እንደፈጠረ ሲናገር እንመለከታለን። እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው በተለያየ ጎዳና በነቢያት ተናግሮ በዚህ ዘመን መጨረሻ ላይ ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ሲናገር እንመለከታለን። በዕብ 1:2 ላይ ዓለማት የሚለው ቃል መላው ፍጥረትን የሚያመለክት ቃል ነው (ዕብ 11:3) ስለዚህ አብ ሁሉን ፍጥረት የፈጠረው በልጁ ነው ማለት ነው።

ይህ ወልድ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን ያረጋግጣል። ለዚያም ነው በአውዱ ላይ የሰማይና የምድር ሰሪ የተባለው (ዕብ 1:8-12) አብ ዓለማትን ሁሉ የፈጠረው በእርሱ ነውና። እግዚአብሔር አለማትን በልጁ መፍጠሩ ፈጣሪነት የአብም የልጁም እንደሆነ ያሳያል። ስለዚህ ዓለማት በእግዚአብሔር ልጅ መፈጠራቸው እርሱ ያ ሁሉ በእርሱ የሆነው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

“13-14፤ እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። 15-16፤ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል” (ቆላ 1:13-16)

በዚሁ ስፍራ ላይም ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጅ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን ሲናገር እንመለከታለን። በቆላ 1:13-14 እግዚአብሔር አምላክ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት እንዳፈለሰን ከገለጸ በኋላ እርሱ (የፍቅሩ ልጅ) የማይታየው አምላክ ምሳሌ እንደሆነና የሚታዩትና የማይታዩት፥ ዙፋናት፥ ጌትነት፥ አለቅነትና ስልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ እንደተፈጠሩና ሁሉም በእርሱና ለእርሱ እንደተፈጠረ ይናገራል።

በቆላ 1:13-16 ሳይጠቀስ የቀረ ፍጥረት የለም። ቁሳዊው ምድር ወይም ዓለም የሚታዩት ከሚባለው ምድብ ውስጥ ይካተታል፥ ይታያልና (ዘፍ 13:15) መንፈሳዊው አለም መንግስተ ሰማይ ደግሞ የማይታዩት ከሚባለው ምድብ ውስጥ ይካተታል፥ አይታይም ተብሏልና (2ቆሮ 4:17-18) ሲቀጥል በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል ይላል። መላእክት የተፈጠሩ ፍጡራን ሲሆኑ (ዘፍ 2:1 ነህ 9:6) መኖሪያቸውም በሰማይ ነው (1ነገ 22:19)

ሰዎችም እንዲሁ ፍጡራን ሲሆኑ (ዘፍ 1:26) መኖሪያቸውም በምድር ነው (መዝ 115:16) በቆላ 1:13-16 መሰረት እነዚህን ሁሉ የፈጠረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የሚታየውንም ምድር፥ የማይታየውንም ሰማይ በየደረጃቸው ያሉትንም መላእክት፥ በሰማይና በምድር ያሉትንም ፍጥረታት ሁሉ ሰውንም ጨምሮ የፈጠረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ወልድ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑ ያ ሁሉ በእርሱ የሆነውን ቃል እንደሆነ ያረጋግጣል።

“ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን” (1ቆሮ 8:6)

በዚህ ቦታ ላይም ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጅ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን ሲገልጽ እናያለን። በ1ቆሮ 8:5 ላይ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩም ለእኛ ክርስቲያኖች ግን ሁሉ ነገር ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ እንዳለንና ሁሉ በእርሱ የሆነ እኛም ከእርሱ የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን ሲናገር እናያለን።

“ሁሉ በእርሱ የሆነ” የሚለው አገላለጽ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የአብን ፈጣሪነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ አገላለጽ ሲሆን (ሮሜ 11:36) ስለ የመላውን ፍጥረት መፈጠር ያመለክታል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሁሉ በእርሱ ሆነ” የሚለው አገላለጽ የፍጥረትን መፈጠር ከማመልከት ውጪ ሌላን ነገር አመልክቶ አያውቅም። ሁሌም ቢሆን የፍጥረትን መፈጠር የሚገልጽ አገላለጽ ነው። ስለዚህ ሁሉ በክርስቶስ ሆነ ማለት ሁሉ በእርሱ ተፈጠረ ማለት ነው

በ1ቆሮ 8:6 ላይ ያለው “ሁሉ በእርሱ የሆነ” የሚለው አገላለጽ በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የወልድን ፈጣሪነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ አገላለጽ ሲሆን (ቆላ 1:16) በዮሐ 1:3 ላይ ካለው አገላለጽ ጋርም በቃላት ሆነ በሰዋሰው ፍጹም አንድ አይነት ነው። ወልድን አስመልክቶ በ1ቆሮ 8:6 ላይ ያለው ቃል በመልእክትም ሆነ በአገላለጽ ከዮሐ 1:3 ጋር ፍጹም አንድ አይነት መሆኑ ወልድ ያ ሁሉ በእርሱ የሆነው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

በ1ቆሮ 8:6 ሁሉ በእርሱ በኩል የሆነ የተባለለት ወልድ አይደለም ብሎ መከራከር አይቻልም። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቷል። በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ እንጂ (1ዮሐ 3:23 ሉቃ 1:31-32) አብ አይደለም። ሲቀጥል በክፍሉ አንድ ጌታ የተባለው አካል የቀረበው አንድ አምላክ ከተባለው አካል ተለይቶ ነው። አንድ ጌታ ኢየሱስ አለን ያለው ነጥሎ አንድ አምላክ አብ አለን ካለ በኋላ ነው።

በ1ቆሮ 8:6 ላይ አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይላል። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው “ክርስቶስ” የሚለው ቃል በግሪክ “ኽሪስቶስ/Χριστός” የሚለው ሲሆን ትርጉሙም “የተቀባ” ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ስያሜ የሚጠራው አካል የተቀባ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ ነው (ዕብ 1:8-9 ሐዋ 4:27-28) ስለዚህ በ1ቆሮ 8:6 ሆነ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ “ክርስቶስ” ተብሎ የተጠራው አብ ነው ማለት አይቻልም። አብ ተቀብቷል የሚል አስተምህሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሌለ ይህ ሁሌም ክርስቶስ የሚባለው ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል።

ከዚያ በተጨማሪም በዚያው በ1ቆሮንቶስ መጽሐፍ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ” የተባለው ወልድ ነው (1ቆሮ 1:9) ስለዚህ አንድ ጌታ አለን ሲል እያመለከተ ያለው ያንኑ ጌታችንን ወልድን ነው። በቀጣዩ የቆሮንቶስ መጽሐፉ ላይም ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ የጠራው ወልድን ነው (2ቆሮ 1:19) ስለዚህ በ1ቆሮ 8:6 ሁሉ በእርሱ የሆነ የተባለለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ እንጂ አብ አይደለም። ይህ ያለ ምንም ጥርጥር ወልድ ያ ሁሉ በእርሱ የሆነው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

ሠ) በእርሱ ሕይወት ነበረች

ሐዋርያው ዮሐንስ ሁሉ በቃል እንደሆነ ከገለፀ በኋላ በእርሱ (በቃል) ሕይወት እንደነበረችና ያቺ ሕይወትም የሰው ብርሃን እንደነበረች ይናገራል፦

በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች” (ዮሐ1:4)

በቃል ውስጥ የሰው ብርሃን የነበረችው ሕይወት ነበረች ማለት ለሰው ልጆች ሕይወትን የሚሰጠው ቃል እንደሆነና የሰው ልጆችም ከጨለማ የሚወጡት ይህን ብርሃን የሆነውን ሕይወት ከቃል ሲቀበሉ እንደሆነ ያሳያል። እንደ ብሉይ ኪዳን አስተምህሮ ሕይወትን የሚሰጠው እግዚአብሔር ሲሆን (ዘዳ 30:20 ዘዳ 32:39 1ሳሙ 2:6 ነህ 9:6 መዝ 36:9) ቃል የሕይወት ምንጭ ነው መባሉ መለኮት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ከዚህ ባሻገር ግን ሕይወት በቃል የነበረ መሆኑ ወልድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም ሕይወት በወልድ ነበረችና፦

“11 እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። 12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም” (1ዮሐ 5:11-12)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ሲናገር እንመለከታለን። እግዚአብሔር የሰጠን ይህ የዘላለም ሕይወት በልጁ ያለ መሆኑ ደግሞም ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ያለው ሕይወት እንዳለው የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ደግሞ ሕይወት እንደሌለው መገለጹ የእግዚአብሔር ልጅ ራሱ ቃል እንደሆነ ያረጋግጣል። በዮሐ 1:4 ላይ በቃል ሕይወት ነበረች እንደተባለው በ1ዮሐ 5:11-12 የዘላለም ሕይወት በልጁ አለ ተብሏልና። ይህ ቃል ራሱ ወልድ ለመሆኑ አንዱ ማስረጃ ነው።

ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን” (1ዮሐ 1:2)

በዚህ ቦታ ላይም ሐዋርያው ዮሐንስ ሕይወት እንደተገለጠ ይህ የተገለጠውም ሕይወት ከአብ ዘንድ የነበረው ሕይወት እንደሆነ ሲናገር እናያለን። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከአብ ዘንድ የነበረውና (ዮሐ 17:5) ጊዜው ሲደርስ የተገለጠው (1ዮሐ 3:9 1ዮሐ 3:5 ሮሜ 8:3 1ጴጥ 1:20) የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ሐዋርያትም ያዩት ወልድን ነው (ዮሐ 1:14 2ጴጥ 1:16-18) ስለዚህ በዚህ ስፍራ ላይ ከአብ ዘንድ የነበረው ደግሞም ለእኛ የተገለጠው ሕይወት የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ወልድ ይህ ለእኛ የተገለጠው ሕይወት መሆኑ በዮሐ 1:4 ላይ ሕይወት በእርሱ የነበረችው ቃል ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

በ1ዮሐ 5:20 ላይ የመጣው እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቦናን የሰጠን፥ እርሱ እራሱ እውነተኛ የሆነው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ተብሎ ተጠርቷል። በ1ዮሐ 5:20 ላይ ከጅምሩ ጀምሮ በወጥነት እየተነገረለት ያለው የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ የዘላለም ሕይወት የተባለው እርሱ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የዘላለም ሕይወት ተብሎ መጠራቱ ያ በእርሱ ሕይወት የነበረችው ቃል መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል። ይህ ቃል ራሱ ወልድ ለመሆኑ ሌላኛው ማስረጃ ነው።

“ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐ 14:6)

በዚህ ስፍራው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት እንደሆነና በእርሱ በቀር ወደ አብ የሚመጣ እንደሌለ ሲናገር እንመለከታለን። ወደ አብ መግቢያው ልጁ ሲሆን (ዕብ 7:24-25) በዚያው በአውዱም ሕይወት ነኝ ያለው አካል አባት ያለው አካል መሆኑን ገልጿል (ዮሐ 14:7) ስለዚህ ሕይወት የሆነው ልጁ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ሕይወት መሆኑን መናገሩ በዮሐንስ ወንጌል መግቢያ ላይ በእርሱ ሕይወት ነበረች የተባለለትን ቃል መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው።

“አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል” (ዮሐ 5:21)

በዚህ ቦታ ላይም ወልድ ሕይወት ሰጪ እንደሆነ ራሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ተናግሯል። አብ ሙታንን እንደሚያስነሳ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው ወልድም እንዲሁ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል ይላል። የእግዚአብሔር ልጅ ልክ እንደ አባቱ ሰዎች ሕይወትን የሚሰጥ ከሆነ በዮሐ 1:4 ላይ ሕይወት በእርሱ ነበረች የተባለለትን ቃል ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው። ዮሐ 1:4 ላይ የሰዎች ብርሃን የተባለው፥ በቃል የነበረው ሕይወት ይህ ወልድ ለሰዎች የሚሰጠው ሕይወት ነው። ቃል ራሱ ወልድ ነውና።

ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ” (ቆላ 3:4)

በዚህ ቦታ ላይም ወልድ የክርስቲያኖች ሕይወት እንደሆነ ተገልጾ እንመለከታለን። ሕይወታችን የሆነው ክርስቶስ ሲገለጥ እኛም አብረነው በክብር እንደምንገለጥ ተጽፏል። በቆላ 3:4 ሕይወታችን የተባለው ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ክርስቶስ መሆኑ በአውዱ ላይ ተገልጿል (ቆላ 3:1) በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ወልድ ነው (ዕብ 1:1-3) ስለዚህ ወልድ ሕይወታችን ነው። ወልድ ሕይወታችን መሆኑ ያ በእርሱ ሕይወት የነበረችው ቃል ለመሆኑ ግልጽ ማስረጃ ነው። ስለዚህ ቃል ራሱ ወልድ ነው።

ረ) ቃልም ስጋ ሆነ

ሐዋርያው ዮሐንስ በቃል ሕይወት እንደነበረች ከገለጸ በኋላ ወረድ ብሎ ቃልም ስጋ እንደሆነ ይናገራል፦

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን” (ዮሐ 1:14)

ቃልም ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ ማለት ያ እግዚአብሔር የነበረው ቃል ከመለኮታዊው ባህርይው ባሻገር ሰዋዊን ባህርይ የራሱ በማድረግ በመካከላችን መገኘቱን የሚያመለክት ነው። ይህ ቃል ራሱ ወልድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት በስጋ የመጣው ወልድ ነው፦

“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ” (ሮሜ 8:3-4)

በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር ከሥጋ የተነሳ ስለደከመ፥ ለሕግ ያልተቻለውን የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ እንደላከ ሲናገር እንመለከታለን። ስለዚህ በሮሜ 8:3 መሰረት በስጋ የመጣው፥ የስጋ ባህርይን የራሱ ያደረገው ልጁ ነው ማለት ነው። ስለዚህ በዮሐ 1:14 ላይ ቃልም ስጋ ሆነ ሲል ያ ስጋ የሆነው ቃል ይህ በኃጢአተኛ ስጋ ምሳሌ የተላከው ልጁ ነው ማለት ነው። ይህ ወልድ ራሱ ቃል ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ነው

አስተውሉ! ሮሜ 8:3 ላይ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን “” ኃጢአተኛ ስጋ ምሳሌ ላከ ይላል እንጂ “” ኃጢአተኛ ስጋ ምሳሌ የሆነውን ልጁን ላከ አይልም። ስለዚህ ልጁ “” ስጋ የመጣው አካል እንጂ መገለጫ ስጋ አይደለም ማለት ነው። ወልድ መገለጫ ስጋ ነው ከተባለ ሮሜ 8:3 ልጁ በኃጢአተኛ ስጋ ምሳሌ ላከ ስለሚል ስጋ በስጋ ተላከ ወደሚል absurdity ያመራል። ስለዚህ ወልድ በስጋ የመጣው አካል እንጂ መገለጫ ስጋ አይደለም።

“13 ስለዚህም ምክንያት። ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም። እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም። እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። 14-15 እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። 16 የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” (ዕብ 2:13-16)

በዚህ ስፍራ ላይ የዕብራዊያኑ ጸሐፊ ስለ ክርስቶስ ስጋዌ ሲናገር እንመለከታለን። በቁ.13 ላይ ጸሐፊው በመንፈስ ቅዱስ ጠንሳሽነት “እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች” የሚለውን የክርስቶስን ንግግር ከዘገበ በኋላ ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው እንደማያፍር ይገልጻል። ስለዚህ በቁ.14-15 #እርሱ እየተባለ ያለው ወንድሞች ያሉት ማንነት ነው ማለት ነው። በቀጣዩ ቁጥር እየተወራ ያለው እግዚአብሔር ልጆቹን ስለ ሰጠው፥ ልጆቹም ወንድሞቹ ስለ ሆኑለት አካል ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ወንድሞች ያሉት ወልድ እንደሆነ ይናገራል፦

ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና” (ሮሜ 8:29)

ስለዚህ በዕብ 2:13-16 እየተወራ ያለው ስለ ወልድ ነው ማለት ነው። ለዚያም ነው ቁ.13 ላይ ራሱን በማንነት ከእግዚአብሔር/ከአብ ነጥሎ “እግዚአብሔር የሰጠኝ” ያለው። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ወልድ ነውና። ስለዚህ በቀጣዮቹ ቁጥሮች ላይ የተባለው ነገር በሙሉ ስለ ወልድ የተባለ ነገር እንደሆነ በዚህ እናረጋግጣለን።

ቀጥለው ባሉት በቁ.14-15 ላይ ይህ ወንድሞች ያሉት ማንነት ወይም ወልድ፥ ልጆቹ በስጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ በተጨማሪም በሞት ላይ ስልጣን ያለውን እርሱም ዲያቢሎስን ሊሽር፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በስጋና በደም ተካፈለ ይላል። ወይንም ስጋና ደም ያለው ሰው ሆነ

ስለዚህ ከዕብ 2:14-15 እንደምንረዳው ስጋና ደምን በመካፈል ሰው የሆነው ወንድሞች ያሉት ወልድ ነው። ይህ በዮሐ 1:14 ላይ ስጋ መሆኑ የተነገረለት ቃል ይህ ራሱ ወንድሞች ያሉት ወልድ ለመሆኑ ማስረጃ ነው። በዮሐ 1:14 ላይ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ ከዕብ 2:14-15 መረዳት እንችላለን። በዕብ 2:13-16 ላይ በስጋና በደም የተካፈለው ወልድ መሆኑ ተገልጿልና።

✍️ ይህ እውነታ ደግሞ በዕብ 2:16 አጽንኦት ተሰጥቶት ተነግሯል

“የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” (ዕብ 2:16)

ከቁ.14 ጀምሮ ስጋና ደምን ስለመካፈል ወይም በስጋ ስለመምጣት በተነገረበት በዚያው አውድ ቁ.16 ላይ ያው ራሱ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃምን ዘር እንደያዘ ተገልጿል። አውዱ ስጋና ደምን ስለመካፈል ስለሆነ የሚናገረው፥ የአብርሃምን ዘር ይዟል ሲል ስለዚያ ስጋና ደም መካፈል ወይንም በስጋ ስለመምጣት እየተናገረ እንደሆነ ግልጽ ነው። ያ ወንድሞች ያሉት ወልድ የአብርሃምን ዘር በመያዝ ስጋና ደምን ተካፍሏል።

➢ ለእኛ ለክርስቲያኖች ይህ ምንም ጥርጥር የሌለበት እውነታ ቢሆንም ለሐዋርያት እምነት ተከታዮች ግን አይደለም። እንደ እነርሱ አረዳድ ዕብ 2:16 የሚያመለክተው ስጋዌን ከሚያመለክተው አውዱ ተገንጥሎ ርዳታን ወይም እገዛን ነው። አውዱ ግን ይህን አይፈቅድም። በአውዱ እየተነገረ ያለው በስጋና በደም ስለ መካፈል ስለሆነ፥ ወንድሞች ያሉት ወልድ የአብርሃምን ዘር መያዙ ሰው ሆኖ መምጣቱ እንደሆነ እንረዳለን።

“5 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። 6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ 7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ 8 በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” (ፊል 2:5-8)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ትህትና ሲያስተምር እንመለከታለን። እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር (ቁ.3) ካለ በኋላ ለትህትና ታላቁን ምሳሌ ያነሳል። እርሱም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ሀሳብ በእናንተ ዘንድ ይሁን ካለ በኋላ (ቁ.5) ስለ ክርስቶስ ዘላለማዊ አኗኗር መናገር ይጀምራል።

እርሱም በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ፥ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም። ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ ይላል።

በዚህ ክፍል ላይ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ የምናውቅበት የመጀመሪያው መንገድ በቁ.5 ላይ ይህን ያደረገው ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ መገለጹ ነው። በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ክርስቶስ ኢየሱስ” የሚለው ስም የወልድ ስም ነው (1ዮሐ 3:23 ሉቃ 1:32-33) እንደ መጠሪያም ያገለገለው ለወልድ ነው (1ቆሮ 1:9 2ቆሮ 1:19)

በፊሊ 2:5 ላይ “በክርስቶስ” ኢየሱስ የነበረ ሀሳብ ይላል። በተደጋጋሚ ለማየት እንደሞከርነው “ክርስቶስ” የሚለው ቃል በግሪክ “ኽሪስቶስ/Χριστός” የሚለው ሲሆን ትርጉሙም “የተቀባ” ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ስያሜ የሚጠራው አካል የተቀባ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ ነው (ዕብ 1:8-9 ሐዋ 4:27-28) ስለዚህ በፊሊ 2:5 ሆነ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ “ክርስቶስ” ተብሎ የተጠራው አብ ነው ማለት አይቻልም። አብ ተቀብቷል የሚል አስተምህሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሌለ ይህ ሁሌም ክርስቶስ የሚባለው ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል።

ሲቀጥል በቁ.6 ላይ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ይላል። በፊል 2:6 ላይ “መልክ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ሞርፊ/μορφή” የሚለው ቃል ሲሆን “ባህርይ/nature” ወይም “ሕላዌ/essence” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ነው። ስለዚህ በዚህ ክፍል መሰረት ክርስቶስ ኢየሱስ ሲኖር የነበረው በአብ ባህርይ ነው ማለት ነው።

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ ከአብ ጋር የባህርይ አንድነት ያለው ወልድ ነው (ዮሐ 10:27-30 ዕብ 1:3 ቆላ 1:15) ስለዚህ በፊሊ 2:5-7 እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ ነው። በተጨማሪም በፊሊ 2:8 እስከ መስቀል ሞት ታዘዘ ይላል። እንደ እግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ ደግሞ በመስቀል ሞት የሞተው ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ነው (ሮሜ 5:10 ገላ 2:20)

✍️ ስለዚህ በፊሊ 2:7 ላይ የባሪያን መልክ ያዘ ሲል ያን የባሪያ መልክ ይዞ ሰው ሆኖ የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው።

በፊሊ 2:7 ላይ “መልክ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ሞርፊ/μορφή” የሚለው ቃል ሲሆን “ባህርይ/nature” ወይም “ሕላዌ/essence” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ነው። ስለዚህ የባሪያን መልክ ይዞ በምስሉ እንደ ሰው ተገኘ ማለት የባሪያን ባህርይ ወይም አገልጋይነት የሚስማማውን ባህርይ ይዞ ሰው ሆነ ማለት ነው።

ከላይ በብዙ ማስረጃ እንዳየነው ደግሞ በፊሊ 2:5-7 ያሉትን ነገሮች በሙሉ ያደረገው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የባሪያን መልክ በመያዝ በሰው ምስል መገኘቱ ያ ስጋ የሆነው ቃል መሆኑን ያሳያል። ቃልም ስጋ ሆነ ሲል ይህ የባሪያን መልክ ይዞ ሰው ስለ ሆነው ወልድ እየተናገረ ነው።

አስተውሉ! በስጋ የተላከው፥ በስጋና በደም የተካፈው፥ ሰዋዊን ባህርይ የራሱ ያደረገው ወልድ ነው። ስለዚህ የሐዋርያት ቤተ እምነት ወገኖች እንደሚሉት ወልድ ራሱ ስጋ ከሆነ ስጋ በስጋ ተላከ፥ ስጋ በስጋና በደም ተካፈለ፥ ስጋ ሰዋዊን ባህርይ የራሱ አደረገ ወደሚል absurdity ሊያመራ ነው። ሲቀጥል በክፍሉ “ልጁን በስጋ ላከ” ይላል እንጂ “ቃሉን/ንግግሩን በስጋ ሲልክ ልጅ ሆነ” አይልም። በስጋ የላከው ራሱ ወልድን ነው። ስለዚህ በመጀመሪያ የነበረው ቃል ንግግር ሳይሆን ራሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

ሰ) ተመልሶ ይመጣል

ሐዋርያው ዮሐንስ በወንጌሉ ላይ ቃል ስጋ እንደሆነ ከተናገረ በኋላ በተመለከተው ራዕይ ላይ ተመልሶ የሚመጣው እርሱ መሆኑን ተናግሯል፦

“11 ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም። 12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ 13 በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል” (ራዕይ 19:11-13)

ዮሐንስ ባየው ራዕይ ውስጥ ሰማይ ተከፍቶ (ራዕ 19:11) በነጭ ፈረስ የተቀመጠ፥ በጽድቅ የሚፈርድ፥ እውነተኛና ተዋጊ ይመለከታል። ነጭ የለበሱ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ይከተሉት ነበር። ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህ ቃል ራሱ ወልድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ምክንያቱም በዳግም ምጽአት ወቅት ተመልሶ የሚመጣው ወልድ ነው፦

“እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ” (1ተሰ 1:9-10)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በዳግም ምጽአት ወቅት የሚመጣው ወልድ መሆኑን ሲናገር እንመለከታለን። ሐዋርያው ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር አምላክ ሕያውና እውነተኛው አምላክ መሆኑን ከገለጸ በኋላ፥ ከሙታን ያስነሳውን ከሚመጣውም ቁጣ የሚያድነውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማይ ይጠብቁት ዘንድ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዳሉ ይገልጽላቸዋል። ስለዚህ ከሰማይ የሚመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ከሰማይ የሚመጣው ወልድ መሆኑ ያ ሐዋርያው ሲመጣ ያየው ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።

“በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል” (ሉቃስ 21:27)

“እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው_ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና” (ሉቃስ 12:40)

“ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው_ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና” (ማቴ 24:44)

የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” (ማቴ 25:31)

“በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል” (ማር 13:26)

መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ክፍሎች በሙሉ በዳግም ምጽዓት ወቅት ተመልሶ የሚመጣው የሰው ልጅ መሆኑን ይናገራል። የሰው ልጅ የሚለው ስያሜ በብሉይ ኪዳን መሲሁ የተጠራበት ስያሜ ሲሆን (ዳን 7:13-14) ጌታ ኢየሱስ በተደጋጋሚ ራሱን በዚህ ስያሜ ጠርቷል። በዳግም ምጽዓት ወቅት ከሰማይ የሚመጣው ቃል ሆኖ ሳለ በእነዚህ የወንጌል ክፍሎች ውስጥ የሰው ልጅ እንደሚመጣ መገለጹ ቃል ራሱ ወልድ ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

በእነዚህ የወንጌል ክፍላት ውስጥ “የሰው ልጅ” የተባለው ወልድ ለመሆኑ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጥርጥር የለውም። ነገር ግን የሐዋርያት ቤተ እምነት ተከታዮች ይህ ክርስቲያናዊ አረዳድ የላቸውም። ስለዚህ በእነዚህ ክፍሎች ላይ “የሰው ልጅ” የተባለው ራሱ ወልድ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለብን።

የሰው_ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል” (ማቴ 16:27)

“በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል” (ማር 8:38)

“በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ በክብሩ በአባቱና በቅዱሳን መላእክቱ ክብርም ሲመጣ በእርሱ ያፍርበታል” (ሉቃ 9:26)

በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደተገለጸው የሰው ልጅ አባት አለው። አባት ያለው ደግሞ ወልድ በመሆኑ (ሮሜ 15:5-6) ይህ የሰው ልጅ ራሱ ወልድ እንደሆነ እናረጋግጣለን። ወልድ አለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር የነበረ (ዮሐ 17:5) ሁሉን የፈጠረ (ዕብ 1:8-12) አምላክ (ዕብ 1:8 1ዮሐ 5:20) ቢሆንም በስጋ በመምጣቱ (ሮሜ 8:3) ከዚያ ከመጣበት ሰዋዊ ባህርይ የተነሳ የሰው ልጅ ተብሎ ተጠርቷል።

የሰው ልጅ የሚለው ስያሜ በስጋ የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ስያሜ ነው። መለኮታዊውም ሰዋዊውም ባህርይ ያለው ያ አንድ አካል/person በስጋ ከመጣ በኋላ የተጠራበት ስሙ ነው። አንዱን ባህርይ ብቻ ነጥሎ ሳይሆን የሚያመለክተው ሁለቱም ባህርያት ያሉትን አንዱን አካል/person ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ” የሚለው ስም ልክ “ኢየሱስ” እንደሚለው ስም የአንዱ ስግው-መለኮት ስም ነው ማለት ነው።

“እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?” (ዮሐ 6:62)

በዚህ ስፍራ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ ሲናገር እንመለከታለን። የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት እንደሚወጣ ለሐዋርያቱ ነግሯቸዋል። በዚህ ስፍራ መውጣት ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል ወደ ሰማይ ማረግን ሊያመለክት የሚችል ቃል ሲሆን (ሐዋ 2:34) ለሰው ልጅ ይህ ቃል መዋሉ ወደ ሰማይ እንደሚያረግ የሚያመለክት ነው። ይህ የሰው ልጅ ራሱ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

ምክንያቱም ወደ ሰማይ ያረገው ወልድ ነው፦

“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ” (ዕብ 4:14)

“ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት” (ዮሐ 20:17)

“ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ” (ዮሐ16:28)

“ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው” (ዮሐ 17:11)

“32 ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤ 33 ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው” (ሐዋ 2:32-33)

በዮሐ 6:62 ላይ ወደ ሰማይ ያርጋል የተባለለት የሰው ልጅ ራሱ ወልድ መሆኑን በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንረዳለን። ስለዚህ ወደ ሰማይ ያርጋል የተባለለት የሰው ልጅ ራሱ ወልድ ከሆነ በዳግም ምጽአት ወቅትም ተመልሶ ይመጣል የተባለለት የሰው ልጅ ራሱ ወልድ ነው። ይህ የሰው ልጅ/ወልድ ራሱ ተመልሶ ይመጣል የተባለለት ቃል እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

“እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ” (ሐዋ 7:56)

በዚህ ስፍራ የመጀመሪያው ሰማዕት እስጢፋኖስ ያየውን ራዕይ እንመለከታለን። አይሁድ በሀሰት ከስሰውት ወደ ሸንጎ ካቀረቡት በኋላ ከጥንት ከአብርሃም ዘመን ጀምሮ እስከ ክርስቶስ መሰጣት ድረስ የነበረውን ሁኔታ ተረከላቸው። ያኔም የሚነገርበትን ቃልና መንፈስ መቋቋም ስላቃታቸው ሊወግሩት ተነሱ። ያኔም ሰማይ ተከፍቶ የሰውን ልጅ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየው። ይህ የሰው ልጅ ራሱ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል

ምክንያቱም በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ወልድ ነው፦

“2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ 3 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብ 1:2-3)

ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል” (ኤፌ 1:20-21)

“የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው” (ሮሜ 8:34)

“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና” (ዕብ 12:1-2)

“እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብ 10:12)

“ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን” (ዕብ 8:1)

“እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ” (ቆላ 3:1)

“21 ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤ 22 እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ” (1ኛጴጥ 3:21-22)

በሐዋ 7:56 ላይ ወደ በእግዚአብሔር ቀኝ ነው የተባለለት የሰው ልጅ ራሱ ወልድ መሆኑን በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንረዳለን። ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ነው የተባለለት የሰው ልጅ ራሱ ወልድ ከሆነ በዳግም ምጽአት ወቅትም ተመልሶ ይመጣል የተባለለት የሰው ልጅ ራሱ ወልድ ነው። ይህ የሰው ልጅ/ወልድ ራሱ ተመልሶ ይመጣል የተባለለት ቃል እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

አስተውሉ! ወልድ የሰው ልጅ ተብሎ የተጠራው በስጋ ስለመጣ ነው። ወልድ አምላክ መሆኑ በተደጋጋሚ የተገለፀ ሲሆን (ዕብ 1:8 1ዮሐ 5:20) የሰው ልጅ ተብሎ የተጠራው የራሱ ካደረገው ሰዋዊ ባህርይ የተነሳ ነው (ሮሜ 8:3 ዕብ 2:13-16)

በዮሐ 1:1 ላይ ያለው ቃል ራሱ ወልድ መሆኑን በብዙ ማስረጃዎች አይተናል። በመጀመሪያ የነበረ መሆኑ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረ መሆኑ፥ እግዚአብሔር መሆኑ፥ ሁሉ በእርሱ መሆኑ፥ ስጋ መሆኑ፥ በዳግም ምጽዓት ወቅት ተመልሶ መምጣቱ ሁሉ ያ ቃል ራሱ ወልድ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ይህ በመጀመሪያ የነበረው ቃል ወይም ወልድ ደግሞ እግዚአብሔር መሆኑ በዚያው ዮሐ 1:1 ላይ ተገልጿል። ስለዚህ ቃል/ወልድ እግዚአብሔር ነው። ከላይ ስንጀምር ለመግለጽ እንደሞከርነው ደግሞ በዮሐ 4:24 መሰረት እግዚአብሔር/አምላክ መንፈስ ነው። የአምላክ ባህርይ ቁስ ያልሆነ መንፈስ እንደሆነ በዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተገልጿል። ስለዚህ አምላክ የሆነው ይህ ቃል/ወልድ መንፈስ ነው ማለት ነው! መንፈስ ያልሆነ አምላክ የለምና። ለዚህ ነው ይህ አምላክ የሆነው ቃል/ወልድ መንፈስ በመሆኑ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ለዚህም ነው ስጋ ባልነበረበት ቅድመ-ዓለም እንኳን ነበር የተባለው (ዕብ 1:2 ዮሐ 17:5) በሁሉ ስፍራ ይገኛል የተባለው (ዮሐ 3:13 ኤፌ 4:10) ይህ ሁሉ ወልድ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

ማስረጃ አስር

“ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት” (ዮሐ 20:28)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ቶማስ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬም አምላኬም ብሎ ሲመልስለት እንመለከታለን። ቶማስ ይህን የመለሰው ለክርስቶስ በመሆኑ ጌታም አምላክም የተባለው ክርስቶስ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ቶማስ ለክርስቶስ ኢየሱስ የተናገረው ቃል ለየትኛውም ፍጡር ተብሎ የማያውቅ ቃል ሲሆን፥ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሰዎች እግዚአብሔር አምላካቸው መሆኑን ለመግለጽ የተናገሩት ቃል ነው፦

አምላኬ ጌታዬም፥ ወደ ፍርዴ ተነሥ፥ አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ” (መዝ 35:23)

አንዳንዶች ግን በዮሐ 20:28 ቶማስ ጌታዬም አምላኬም ያለው ወልድን አይደለም ሲሉ ይሰማሉ። እንደ እነርሱ የተሳሳተ አረዳድ በዚህ ስፍራ ጌታም አምላክም የተባለው አብ እንጂ ልጁ አይደለም። ይህ ግን ፈጽሞ ስህተት ነው። በዮሐ 20:28 ቶማስ ጌታዬም አምላኬም ያለው የእግዚአብሔርን ልጅ ነው። አንድ በአንድ እንመለከተው፦

1) በአውዱ እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ ነው

በዮሐንስ 20 አውድ ተደራሲ የሆነውና እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ ነው። ስለዚህ በቁ.28 ላይ ቶማስ ጌታዬም አምላኬም ሲል ያንኑ የእግዚአብሔርን ልጅ እንጂ ሌላን አካል ሊሆን አይችልም።

ሀ) ወደ አብ አርጓል

“ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት” (ዮሐ 20:17)

በዮሐ 20:28 ላይ ጌታም አምላክም የተባለው ማንነት በዮሐ 20:17 ላይ ወደ አባቱ እንደሚያርግ ተናግሯል። ስለዚህ ይህ ጌታም አምላክም የተባለው አካል አባት ያለው፥ ደግሞም ወደ አብ ያረገው አካል ነው። እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ይህ በዮሐ 20:28 ላይ ጌታም አምላክም የተባለው ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል፦

“2፤ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ 3፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብ 1:2-3)

“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ” (ዕብ 4:14)

“ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ” (ዮሐ16:28)

“ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው” (ዮሐ 17:11)

“32 ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤ 33 ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው” (ሐዋ 2:32-33)

ለ) በአብ ተልኳል

“ኢየሱስም ዳግመኛ። ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው” (ዮሐ 20:21)

በዮሐ 20:28 ጌታም አምላክም የተባለው ማንነት በዮሐ 20:21 ላይ በአብ እንደተላከ ተናግሯል። ስለዚህ ይህ ጌታም አምላክም የተባለው አካል ራሱ አብ ሳይሆን በአብ የተላከው አካል ነው ማለት ነው። አንድ አካል ራሱን መላክ አይችልምና በአብ የተላከው ይህ አካል ወልድ ነው። ስለዚህ በዮሐ 20:28 ላይ ጌታም አምላክም የተባለው ወልድ ነው ማለት ነው፦

“በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና” (1ዮሐ 4:9)

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም” (1ዮሐ 4:10)

“እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን” (1ዮሐ 4:14)

“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና” (ሮሜ 8:3-4)

“ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4:4)

“ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው” (ዮሐ 6:39)

ሐ) ሰዋዊ ባህርይ አለው

“ይህንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው” (ዮሐ 20:20)

በዮሐ 20:28 ላይ ጌታም አምላክም የተባለው ማንነት በዮሐ 20:20 ላይ ለደቀመዛሙርቱ እጆቹንም ጎኑንም ሲያሳያቸው እንመለከታለን። ይህ ማለት ሰዋዊ ባህርይ ወይም human nature አለው ማለት ነው። ስለዚህ ጌታም አምላክም የተባለው ማንነት ሰውነት አለው ማለት ነው። ይህ ጌታም አምላክም የተባለው ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። በስጋ የመጣው ወልድ ነውና፦

“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ” (ሮሜ 8:3-4)

“11-12 የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና፤ 13 ስለዚህም ምክንያት። ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም። እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም። እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። 14-15 እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። 16 የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” (ዕብ 2:11-16)

“5 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። 6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ 7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” (ፊል 2:5-7)

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን” (ዮሐ 1:14)

አስተውሉ! በዮሐ 20:28 ጌታም አምላክም የተባለው ሰውነት ያለው ማንነት (ወልድ) ራሱ እንጂ በእርሱ ውስጥ ያለ ሌላ ማንነት አይደለም። ቶማስ “..ጌታም አምላክም #በውስጥህ አለ” አላለውም። ያን ሰዋዊ ባህርይ ያለውን ራሱኑ ማንነት ነው ጌታዬም አምላኬም ያለው። ስለዚህ ጌታም አምላክም እየተባለው ያለው በስጋ የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

መ) ሞቶ ነበር

“ሌሎቹም ደቀ መዛሙርቱ። ጌታን አይተነዋል አሉት። እርሱ ግን። የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም አላቸው” (ዮሐ 20:25)

በዮሐ 20:28 ላይ ጌታም አምላክም የተባለው ማንነት በዮሐ 20:25 ላይ ተቸንክሮ እንደነበር ተገልጿል። ይህ ማለት ጌታም አምላክም የተባለው አካል በመስቀል ላይ ሞቶ ነበር ማለት ነው። ይህ ጌታም አምላክም የተባለው አካል ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። በስጋው ሞቶ የነበረው የእግዚአብሔር ልጅ ነውና፦

“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን” (ሮሜ 5:10)

“ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” (ገላ 2:20)

“7 እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት 8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ” (ዕብ 5:7-8)

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም” (1ዮሐ 4:10)

ለገዛ_ልጁ_ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?” (ሮሜ 8:32)

“17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። 18 እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ” (ዮሐ 10:17-18)

“37 በኋላ ግን። ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከባቸው። 38 ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው። ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። 39 ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት” (ማቴ 21:37-39)

አስተውሉ! በዮሐ 20:28 ላይ ጌታም አምላክም የተባለው በስጋ ሞቶ የነበረው ወልድ ራሱ እንጂ በወልድ ውስጥ ያለ ሌላ ማንነት አይደለም። ቶማስ “..በተቸነከረው ውስጥ ያለው ጌታዬ አምላኬ ነው” አላለም። ጌታዬም አምላኬም ያለው ራሱ የተቸነከረውን ወልድን ነው። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታም አምላክም መሆኑን ያረጋግጣል።

ሠ) ጌታም አምላክም የተባለው ወልድ መሆኑ ተገልጿል

በዮሐ 20:28 ላይ ጌታም አምላክም የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በዚያ በዮሐንስ 20:20 አውድ ተገልጿል። ስለዚህ ቃሉን ከአውዱ ገንጥሎ ፍጹም በተሳሳተ አኳሃን ለመተርጎም ካልተሞከረ በስተቀር ጌታም አምላክም የተባለው ወልድ መሆኑን መካድ አይቻልም፦

“ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል” (ዮሐ 20:31)

ቶማስ ጌታ ኢየሱስን ጌታም አምላክም ካለው በኋላ እሱ ስላየው እንዳመነና ሳያዩት የሚያምኑ ብጹዓን እንደሆኑ ይነግረዋል (ዮሐ 20:29) ከዚያ ሐዋርያው ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ ጥንሳሴ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ብዙ ተአምራትን እንዳደረ ከተናገረ በኋላ (የሐ 20:30) ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ሰዎች አምነው አምነውም በስሙ ሕይወት ይሆንላቸው ዘንድ ይህ እንደተጻፈ በቁ.31 ላይ ይናገራል።

ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ ስለ ኢየሱስ የተጻፉት ነገሮች በሙሉ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድናምን የተጻፉ ናቸው ማለት ነው። ስለዚህ ቶማስ “ጌታዬም አምላኬም” ብሎ የመለሰለት ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ስለ እርሱ የተጻፉት ነገሮች በሙሉ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድናምን የተጻፉ ናቸውና። ይህ ጌታም አምላክም የተባለው ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል።

አስተውሉ! ቶማስ ጌታዬም አምላኬም ብሎ የመለሰለት ለኢየሱስ ነው። ይህ ጌታም አምላክም የተባለው ኢየሱስ ደግሞ ራሱ ወረድ ብሎ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ተገልጿል። ስለዚህ ማንም ጥቅሱን ያለ አውዱ ገንጥሎ ጌታም አምላክም የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም ሊል አይችልም።

2) በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተረጋግጧል

በዮሐ 20:28 ላይ ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተባለው ነገር በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተረጋግጧል። ሐዋርያው ቶማስ ወልድን ጌታም አምላክም ብሎት ነበር። ስለዚህ በእርግጥም ወልድ ጌታም አምላክም ከሆነ አምላክነቱና ጌትነቱ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይረጋገጥ ነበር፥ ደግሞም ተረጋግጧል። እንመልከተው፦

1) ጌትነቱ

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (1ቆሮ 1:9)

“8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ 10 ይላልደግሞጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ 11 እነርሱ ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ 12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል” (ዕብ 1:8-12)

“በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፥ ታከብሩ ዘንድ፥ የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ፈቃድ እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ መሆንን ይስጣችሁ” (ሮሜ 15:5-6)

“18 በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል። 19 ሥራህንና ፍቅርህን እምነትህንም አገልግሎትህንም ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ። 20 ዳሩ ግን። ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ” (ራዕይ 2:18-20)

“በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ” (ዕብ 13:20)

“እነዚያም ጌታን ኢየሱስን ደግሞ ገደሉ ነቢያትንም እኛንም አሳደዱ፥ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፥ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ” (1ተሰ 2:15)

በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከተጻፈው የሐዋርያት መልእክት ባሻገር ራሱ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስም ጌታ መሆኑን መስክሯል፦

“42 ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። 43 ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። 44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና” (ማቴ 24:42-44)

– የሰው ልጅ ወልድ ነው (ማቴ 16:27)

“እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ” (ዮሐ 13:13)

– በዮሐንስ 13 አውድ ኢየሱስ ወልድ መሆኑ ስለተገለጸ (ዮሐ 13:3) በዚህ ክፍል ላይ ጌታ ነኝ ያለው ወልድ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን።

የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ መሆኑን ከዚህም በላይ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ስለዚህ በዮሐ 20:28 ላይ ጌታ የተባለው ራሱ ወልድ ለመሆኑ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመረጋገጡ በዚያ ክፍል ላይ ጌታም አምላክም የተባለው ራሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያረጋግጣል

2) አምላክነቱ

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” (ዮሐ 1:1)

“ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (ዕብ 1:8)

“አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን” (ሮሜ 9:5)

“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ 9:6)

አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (መዝ 45:6)

“5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው” (ኤር 23:5-6)

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ #አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

➢ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከተጻፈው የሐዋርያትና የነቢያት መልእክትና ትንቢት ባሻገር ራሱ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስም አምላክ መሆኑን መስክሯል፦

እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ” (ኢሳ 61:8)

– ኢሳ 61 ላይ ተናጋሪው ወልድ ነው (ሉቃ 4:17-19)

[ በኢሳ 61:8 ዙሪያ ሰፊ ንባብ ለማድረግ፦ https://t.me/TheTriune/1289 ]

“17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ። አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ 18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ” (ራዕይ 1:17-18)

“12 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። 13 አልፋና ዖሜጋፊተኛውና ኋለኛውመጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። 14 ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው። 15 ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ። 16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ” (ራዕይ 22:12-16)

የእግዚአብሔር ልጅ አምላክ መሆኑን ከዚህም በላይ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ስለዚህ በዮሐ 20:28 ላይ አምላክ የተባለው ራሱ ወልድ ለመሆኑ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመረጋገጡ በዚያ ክፍል ላይ ጌታም አምላክም የተባለው ራሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያረጋግጣል።

አስተውሉ! ከላይ በተጠቀሱት የጌታ ኢየሱስ ንግግሮች ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎቹ አምላክነቱ እየተገለጸ ያለው ራሱ ወልድ እንጂ በወልድ ወስጥ ያለ ሌላ ማንነት አይደለም። ስለዚህ ቃላቱን ካለ አውዳቸው ገንጥሎ አምላክ የተባለው ወልድ አይደለም ማለት አይቻልም። በእነዚህ ቦታዎች አምላክ እየባለ ያለው ወልድ ነው

በዮሐ 4:24 ላይ ግን አምላክ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። የአምላክ ባህርይ ቁስ ያልሆነ መንፈስ እንደሆነ በዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተገልጿል። አሁን እንዳየነው ደግሞ ወልድ አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ስለዚህ ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ ነው ማለት ነው! መንፈስ ያልሆነ አምላክ የለምና።

ለዚህ ነው ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ በመሆኑ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ለዚህም ነው ስጋ ባልነበረበት ቅድመ-ዓለም እንኳን ነበር የተባለው (ዕብ 1:2 ዮሐ 17:5) በሁሉ ስፍራ ይገኛል የተባለው (ዮሐ 3:13 ኤፌ 4:10) ይህ ሁሉ ወልድ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

ማስረጃ አስራ አንድ

“ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤ እርሱም ከክፋት ሊቤዠን መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ሕዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለ እኛ ሰጥቶአል” (ቲቶ 2:13-14) አ.መ.ት

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ታላቁ አምላካችን” በማለት ሲጠራው እንመለከታለን። ከላይ በቁ.11 ሰዎችን የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተገለጠ ከተናገረ በኋላ ያም ጸጋ ዓለማዊ ምኞትን ክደን በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት በጽድቅ ራሳችንን እየገዛን የታላቁን አምላካችንና አዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ መገለጥ እንድንጠባበቅ እንደሆነ በቁ.12-13 ይናገራል። ከዚያም በቁ.14 ላይ እርሱ ከክፋት ሁሉ እንደተቤዠንና መልካም የሆነውን ሁሉ ለማድረግ የሚተጋን ሕዝብ ለራሱ ለማንጻት ራሱን ስለ እኛ እንደሰጠን ይናገራል።

በቲቶ 2:13 የግሪክ ሰዋሰው መሰረት “ታላቁ አምላካችን” እየተባለ ያለው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ግልጽ ነው። “ታላቁ አምላካችንና አዳኛችን” በሚለው ሀረግ ውስጥ አንድ ውስን መስተጻምር/definite article ያለ ሲሆን እንዲህ አይነቱ አወቃቀር የአንድ አካል መገለጫዎችን ያመለክታል። ያ አንዱ አካል የሆናቸውን ነገሮች ያሳያል። ለዚህ አይነቱ የግሪክ ሰዋሰው ሌሎች ምሳሌዎችን ማቅረብ የሚቻል ሲሆን በቲቶ 2:13 ላይ ታላቅ አምላክም አዳኝም የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

በቲቶ 2:13 ታላቁ አምላካችን ተብሎ የተጠራው ወልድ መሆኑ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጥያቄ የሌለው እውነታ ነው። ለሐዋርያት እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ግን ይህ አወዛጋቢ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ለእነርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራው አብም ወልድም ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሲል ሁሌም ወልድን ነው የሚያመለክተው የሚል ክርስቲያናዊ አረዳድ የላቸውምና። ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ ክርስቶስ የተባለው ወልድ መሆኑን በማስረጃ ማስረዳት አለብን

በቲቶ 2:3 ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ወልድ መሆኑን እንዴት እናውቃለን?

በቲቶ 2:13 ታላቁ አምላካችንና አዳኛችን የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ መሆኑን የምናውቀው በዚህ ክፍል ላይ ለእርሱ የተባሉት ነገሮች በሙሉ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ለወልድ በመባላቸው ነው። ይህ በእርግጥም ታላቁ አምላካችንና አዳኛችን የተባለለት ክርስቶስ ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል። እንየው፦

1) ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሏል

ቲቶ 2:13 ላይ ታላቁ አምላካችንና አዳኛችን የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ መሆኑን የምናውቅበት የመጀመሪያው መንገድ በዚያ ክፍል ላይ ያ ታላቁ አምላካችንና አዳኛችን “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ በመጠራቱ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የወልድ ስም ነውና፦

“በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል” (2 ቆሮ 1:19)

“ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (1ቆሮ 1:9)

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው” (1ዮሐ 1:3)

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7)

“ትእዛዚቱም ይህች ናት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ” (1ዮሐ 3:23)

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

“ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ” (2ዮሐ 1:3)

“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ” (ዕብ 4:14)

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” (ገላ 2:20)

“ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ፥ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው” (ዕብ 3:5)

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሌም ቢሆን “ኢየሱስ ክርስቶስ” የሚለው ስም ጥቅም ላይ የዋለው የወልድ ስም ሆኖ ነው። አንድም ጊዜ አብ ሆነ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብለው ተጠርተው አያውቁም። ስለዚህ ቲቶ 2:13 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው።

በቲቶ 2:13-14 ላይ የታላቁ አምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ይላል። ከላይ ለማየት እንደሞከርነው “ክርስቶስ” የሚለው ቃል በግሪክ “ኽሪስቶስ/Χριστός” የሚለው ሲሆን ትርጉሙም “የተቀባ” ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ስያሜ የሚጠራው አካል የተቀባ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ የተቀባው ወልድ ነው (ዕብ 1:8-9 ሐዋ 4:27-28) ስለዚህ በቲቶ 2:13-14 ሆነ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ “ክርስቶስ” ተብሎ የተጠራው አብ ነው ማለት አይቻልም። አብ ተቀብቷል የሚል አስተምህሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሌለ ይህ ሁሌም ክርስቶስ የሚባለው ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል።

2) ታላቅ ተብሏል

በቲቶ 2:13 ላይ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከተባሉት ነገሮች አንዱ ታላቅ መሆኑ ነው። “ታላቁ” አምላካችንና አዳኛችን ተብሏል። ይህ በቲቶ 2:13 ላይ እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው። ምክንያቱም ወልድ ታላቅ ነው ተብሏልና፦

“እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል” (ሉቃ 1:32)

በዚህ ስፍራ ላይ ከድንግል ማርያም የሚወለደው የልዑል ልጅ ታላቅ እንደሚሆን ተገልጾ እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልዑል ወይም The Most High God የተባለው እግዚአብሔር ሲሆን (ሐዋ 7:48) በሉቃ 1:32 ታላቅ እንደሚሆን የተነገረለት የልዑል ልጅ ደግሞ ልጁ ወልድ ነው። ስለዚህ በቲቶ 2:13 ላይ ታላቅ የተባለው ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

“በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ” (ዕብ 13:20)

በዚህ ስፍራ ላይ ከሞት የተነሳው ክርስቶስ ኢየሱስ ታላቁ የበጎች እረኛ ተብሎ ሲጠራ እንመለከታለን። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ሞቶ የተነሳው ወልድ ሲሆን (ዮሐ 10:17-18 ሮሜ 1:3-4 1ተሰ 1:9-10 1ጴጥ 1:3-5) ይህ ታላቁ የበጎች እረኛ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት የተነሳው እንደሆነ መገለጹ በእርግጥም ታላቅ እየተባለ ያለው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በማያሻማ አኳሃን ያረጋግጣል።

3) አዳኛችን ተብሏል

በቲቶ 2:13 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ወልድ መሆኑን የምናውቅበት ሌላው መንገድ በዚያ ክፍል ላይ አዳኛችን ወይም መድሃኒታችን እንደሆነ በመገለጹ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ አዳኛችን ነውና፦

“እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን” (1ዮሐ 4:14)

“ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና” (ዮሐ 3:17)

“24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ 25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” (ዕብ 7:24-25)

– ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ነው (ዕብ 4:14)

“ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ” (1ጢሞ 1:15)

– ወደ ዓለም የመጣው ወልድ ነው (1ዮሐ 4:9)

“ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ” (ማቴ 1:21)

– ከድንግል/ከሴት የተወለደው ወልድ ነው (ገላ 4:4)

“አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል” (2ጢሞ 1:10-11)

– በስጋ የተገለጠው ወልድ ነው (ሮሜ 8:3)

“20 እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ 21 እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል” (ፊሊ 3:20-21)

– ስጋ ያለው ወልድ ነው (ማቴ 26:26-29)

4) አምላካችን ተብሏል

በቲቶ 2:13 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ወልድ መሆኑን የምናውቅበት ሌላው መንገድ በዚያ ክፍል ላይ አምላካችን እንደሆነ በመገለጹ ነው። ይህ በቲቶ 2:13 ላይ እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል። ወልድ አምላክ ተብሏልና፦

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” (ዮሐ 1:1)

“ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (ዕብ 1:8)

“አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን” (ሮሜ 9:5)

ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል_አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ 9:6)

አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (መዝ 45:6)

“5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው” (ኤር 23:5-6)

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ” (ኢሳ 61:8)

– ኢሳ 61 ላይ ተናጋሪው ወልድ ነው (ሉቃ 4:17-19)

[ በኢሳ 61:8 ዙሪያ ሰፊ ንባብ ለማድረግ፦ https://t.me/TheTriune/1289 ]

በቲቶ 2:13 ላይ የተባሉት ነገሮች በሙሉ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በጠቅላላ ለእግዚአብሔር ልጅ የተባሉ ነገሮች ናቸው። በተቃራኒው በዚህ ክፍል ላይ የተባሉት አንዳንድ ነገሮች በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከወልድ በቀር ለማንም ያልተባሉ ነገሮች መሆናቸው በእርግጥም በዚህ ቦታ ላይ አምላክ የተባለው ልጁ ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

5) ተመልሶ ይመጣል

በቲቶ 2:13-14 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር እንደሚገለጥ ተገልጿል። የክብሩ መገለጥ ማለት ዳግም ምጽአት ማለት ሲሆን (2ተሰ 1:9-10) በዚህ ክፍል ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። ምክንያቱም ተመልሶ የሚመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ነውና፦

“እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ” (1ተሰ 1:9-10)

“20 እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ 21 እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል” (ፊሊ 3:20-21)

– ስጋ ያለው ወልድ ነው (ማቴ 26:26-29)

“በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል” (ሉቃስ 21:27)

“እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው_ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና” (ሉቃስ 12:40)

“ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና” (ማቴ 24:44)

የሰው_ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” (ማቴ 25:31)

“በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል” (ማር 13:26)

– የሰው ልጅ ወልድ ነው (ማቴ 16:27)

“እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን” (ራዕይ 1:7)

– የተወጋው ወልድ ነው (ሮሜ 5:10)

“12 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።..16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ” (ራዕይ 22:12-16)

– በሰውነቱ የዳዊት ዘር የሆነው ወልድ ነው (ሮሜ 1:3-4)

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ተመልሶ የሚመመጣው ወልድ ነው። በቲቶ 2:13-14 ላይ ደግሞ ያ ተመልሶ የሚመጣው ክርስቶስ ኢየሱስ ታላቁ አምላካችን ተብሏል። በዚያ ክፍል ላይ ለእርሱ ከተባለው ከዚህና ከሌሎች ነገሮች ተነስተን በእርግጥም ታላቁ አምላካችን የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

6) ተቤዥቶናል

በቲቶ 2:13-14 ስለ ታላቁ አምላካችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተባሉት ሌሎች አንዱ እኛን መቤዠቱ ነው። “..ከአመጻ ሁሉ እንዲቤዠን..” በማለት ይህ ታላቁ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተቤዠን ይናገራል። ይህ በቲቶ 2:13-14 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ወልድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም እንደ እግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ የተቤዠን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፦

“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን” (ቆላ 1:13-14)

“እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” (ማቴ 20:28)

“እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” (ማር 10:45)

– የሰው ልጅ ወልድ ነው (ማር 8:38)

“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልናበደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ” (ራዕይ 5:9-10)

– የታረደው ወልድ ነው (ዕብ 5:7-8)

“በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት” (ኤፌ 1:7)

“24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። 25 እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው” (ሮሜ 3:24-25)

“ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ” (1ጴጥ 1:18-19)

– ደም ያለው ወልድ ነው (1የሐ 1:7)

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የተቤዠን ወልድ ነው። በቲቶ 2:13-14 ላይ ደግሞ ያ የተቤዠን ክርስቶስ ኢየሱስ ታላቁ አምላካችን ተብሏል። ቲቶ 2:13-14 ላይ ለእርሱ ከተባለው ከዚህ ነገርና ከሌሎች ነገሮችም ተነስተን በእርግጥም ታላቁ አምላካችን የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

አስተውሉ! ከላይ በተጠቀሱት ክፍሎች በሙሉ ራሱ ልጁ ተቤዠን ይላል እንጂ በልጁ #ውስጥ ያለ ነገር ግን ራሱ ወልድን ያልሆነ አካል ተቤዠን አይልም። በልጁ ደም እንደተቤዠን ይናገራል እንጂ አብ በደሙ ተቤዠን አይልም። ስለዚህ ቲቶ 2:13-14 ላይ ተቤዠን የተባለው ታላቁ አምላክ ወልድ አይደለም ብሎ መከራከር አይቻልም።

7) አንጽቶናል

በቲቶ 2:13-14 ስለ ታላቁ አምላካችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተባሉት ሌሎች ነገሮች አንዱ ገንዘቡ የሆነን ሕዝብ ለራሱ ማንጻቱ ነው። ይህ በእርግጥም በቲቶ 2:13-14 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እኛን ያነጻን የእግዚአብሔር ልጅ ነውና፦

“2 ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ 3 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብ 1:2-3)

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” (1ዮሐ 1:7)

“እኔም። ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም። እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ” (ራዕይ 7:14)

“ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ” (ኤፌ 5:25-26)

– ራሱን አሳልፎ የሰጠን ወልድ ነው (ገላ 2:20)

“ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?” (ዕብ 9:14)

“ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን” (ራዕይ 1:4-5)

– ደም ያለው ወልድ ነው (1ዮሐ 1:7)

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ያነጻን ወልድ ነው። በቲቶ 2:13-14 ላይ ደግሞ ያ ያነጻን ክርስቶስ ኢየሱስ ታላቁ አምላካችን ተብሏል። ቲቶ 2:13-14 ላይ ለእርሱ ከተባለው ከዚህና ከሌሎች ነገሮች ተነስተን በእርግጥም ታላቁ አምላካችን የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

8) ራሱን ሰጥቶናል

በቲቶ 2:13-14 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱን ስለ እኛ አሳልፎ መስጠቱን በዚያ ክፍል ላይ ተገልጿል። ራሱን ስለ እኛ አሳልፎ ሰጥቷል ማለት ስለ እኛ ሞቶልናል ማለት ነው። ይህ በቲቶ 2:13-14 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። ራሱን ስለ እኛ የሰጠው የእግዚአብሔር ልጅ ነውና፦

“ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” (ገላ 2:20)

ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ” (ኤፌ 5:2)

– መስዋዕት የሆነው ወልድ ነው (ዕብ 10:12/ዕብ 1:1-3)

“23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። 25-26 ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ” (ኤፌሶን 5:23-26)

– ቤተክርስቲያን የወልድ አካል ናት (ቆላ 1:13-14/ቆላ 1:18)

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል” (ዮሐ 10:11)

– ነፍሱን ለበጎች ያኖረው እረኛ ወልድ ነው (ዕብ 13:20)

“እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” (ማቴ 20:28)

“እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” (ማር 10:45)

– የሰው ልጅ ወልድ ነው (ሉቃ 9:26)

“እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል” (1ዮሐ 3:16)

– ስለወደደን ራሱን አሳልፎ የሰጠን ወልድ ነው (ገላ 2:20)

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ስለ እኛ ራሱን የሰጠው ወልድ ነው። በቲቶ 2:13-14 ላይ ደግሞ ያ ራሱን አሳልፎ የሰጠን ክርስቶስ ኢየሱስ ታላቁ አምላካችን ተብሏል። ቲቶ 2:13-14 ላይ ለእርሱ ከተባለው ከዚህና ከሌሎች ነገሮች ተነስተን በእርግጥም ታላቁ አምላካችን የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

አስተውሉ! በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አብ ራሱን አሳልፎ ሰጠን የሚል አንድም ትምህርት የለም። አብ የአለም ኃጢአት ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ላከ እንጂ (1ዮሐ 4:10) ራሱን አሳልፎ ለሞት አልሰጠም። ስለዚህ ቲቶ 2:13-14 ላይ ታላቁ አምላካችን የተባለው አብ እንጂ ወልድ አይደለም ብሎ መከራከር አይቻልም። ታላቁ አምላካችን የተባለው ራሱን የሰጠን ወልድ እንጂ አብ አይደለምና። ታላቁ አምላክ የተባለው ወልድ ነው።

በዮሐ 4:24 ላይ ግን አምላክ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። የአምላክ ባህርይ ቁስ ያልሆነ መንፈስ እንደሆነ በዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተገልጿል። አሁን እንዳየነው ደግሞ ወልድ አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ስለዚህ ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ ነው ማለት ነው! መንፈስ ያልሆነ አምላክ የለምና። ለዚህ ነው ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ በመሆኑ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ለዚህም ነው ስጋ ባልነበረበት ቅድመ-ዓለም እንኳን ነበር የተባለው (ዕብ 1:2 ዮሐ 17:5) በሁሉ ስፍራ ይገኛል የተባለው (ዮሐ 3:13 ኤፌ 4:10) ይህ ሁሉ ወልድ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

አስተውሉ! ወልድ መንፈስ ነው ማለት በስጋ አልመጣም ማለት አይደለም። ወልድ መንፈስ የሆነው በመለኮታዊው ባህርይው ነው። በባህርይው መንፈስ የሆነው ወልድ ሰዋዊን ባህርይ ወይም ስጋን የራሱ በማድረግ ወደ ምድር መጣ (ፊሊ 2:7-8) ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት ወልድ በመለኮቱ መንፈስ በሰውነቱ ደግሞ ስጋ ነው።

ማስረጃ አስራ ሁለት

“5 እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው” (ኤር 23:5-6)

በዚህ ስፍራ ላይ እንደሚመጣ የተተነበየለት መሲህ ስሙ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ እንደሚጠራ ተተንብዮ እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር/ያሕዌ ተብሎ የተጠራው አካል/person እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ከእግዚአብሔር ውጪ የትኛውም አካል/person እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቶ አያውቅም። ለመለኮት ብቻ exclusive በሆነ ስያሜ መሲሁ መጠራቱ መሲሁ በእርግጥም መለኮት መሆኑን ያሳያል

በብሉይ ኪዳን ስም ማለት ባህርይ ማለት ነው። ከመጠሪያ ባሻገር ማንነትን እና ምንነትን ያመለክታል። የእግዚአብሔርን ስም ማስቆጣት (መዝ 74:18) እግዚአብሔርን ማስቆጣት ነው፥ የእግዚአብሔርን ስም መውደድ (መዝ 69:36) እግዚአብሔርን መውደድ ነው፥ ለእግዚአብሔር ስም መዘመር (መዝ 7:17) ለእግዚአብሔር መዘመር ነው፥ የእግዚአብሔርን ስም ማወቅ (መዝ 9:10) እግዚአብሔርን ማወቅ ነው።

ለዚያ ነው በኦሪት መጻሕፍት ውስጥ ያሕዌ/እግዚአብሔር የሚለው ስም እንደ ስም ጥቅም ላይ የዋለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው (ዘጽ 6:3 ዘጽ 15:3 ዘዳ 28:58) በመዝሙር መጽሐፍም ሆነ በራሱ በትንቢተ ኤርምያስ መጽሐፍ ውስጥም ስሙ እንደ ስም የዋለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው (መዝ 68:4 ኤር 10:16 ኤር 51:19 ኤር 50:34) ይህ ሊሆን የቻለው በስሙ/በባህርይው እግዚአብሔር የሆነው እግዚአብሔር በመሆኑ ነው።

በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለው ወልድ መሆኑን በምን እናውቃለን?

በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለው ወልድ መሆኑን የምናውቀው በዚህ ትንቢት ላይ ስለ እርሱ የተባሉት ነገሮች በሙሉ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለ እርሱ በመባላቸው ነው።

1) ለዳዊት ይነሳል

በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ስለሚመጣው መሲህ ሲናገር “ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጦን አስነሳለሁ” ብሏል። ይህ ጻድቅ ቁጥቋጥ የሚነሳ ለዳዊት ነው። ለዳዊት ይነሳል ማለት ምን ማለት ነው። ይህ ጻድቅ ቁጥቋጥ ለዳዊት ይነሳል ማለት እግዚአብሔር ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን ይፈጽማል ማለት ነው። እርሱም ከሆዱ ፍሬ በዙፋኑ እንደሚያስቀጥ የገባለት ኪዳን ነው (1ዜና 17:11-15 2ሳሙ 7:12-16) ስለዚህ ለዳዊት አስነሳለታለሁ ማለት ይህን መኀላ እፈጽምለታለሁ ማለት ነው።

ይህ የሚነሳው ጻድቅ ቁጥቋጥ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። ምክንያቱም ለዳዊት በተገባው ኪዳን መሰረት የተነሳው/የመጣው ወልድ ነው፦

“29 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው። 30 ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፥ 31 ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ” (ሐዋ 2:29-31)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጴጥሮስ ከእርሱ ለነበሩ አይሁዳውያን ስለ ክርስቶስ ሲሰብክላቸው እንመለከታለን። ዳዊት ነብይ ስለሆነና እግዚአብሔር ከወገቡ ፍሬ በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀመጥ መሐላ እንደማለለት ስላወቀ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ አስቀድሞ አይቶ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ስጋውም መበስበስን እንዳላየ አስቀድሞ እንደተናገረ ሰበከላቸው።

እግዚአብሔር ለዳዊት ከወገቡ ፍሬ በዙፋኑ እንደሚያስቀምጥ መሐላ የማለለት በመዝ 132:11 ነው። የክርስቶስ ስጋ እንደሚሰበሰብ ደግሞ የተናገረው በመዝ 16:10 ነው። አሁን ጥያቄው እግዚአብሔር ከዳዊት የወገብ ፍሬ በዙፋኑ እንደሚያስቀምጥ መማሉና የክርስቶስ ትንሣኤ ምን ያገናኛቸዋል? የሚለው ነው። ምንድነው ግንኙነታቸው?

እግዚአብሔር ለዳዊት እንደማለለት የሆዱ ፍሬ የሆነው መሲሁ በእርሱ ዙፋን የሚቀመጥ ከሆነ ሞቶ ሊቀር አይችልም። ሞቶ ከቀረ በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጣል የሚለውን መሐላ ሳይፈጽም ቀረ ማለት ነው። ስለዚህ ያ መሐላ አለመፈጸም አይችልምና ክርስቶስ በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጥ ዘንድ ከሞት ተነስቷል። ለዚያ ነው ሐዋርያት ጳውሎ መሐላውንና ትንሳኤውን ያገናኛቸው።

ለዳዊት የተማለውን መሐላ ይፈጽም ዘንድ ከሞት የተነሳው ወልድ ነው፦

“እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ” (1ተሰ 1:9-10)

“17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። 18 እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ” (ዮሐ 10:17-18)

በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ” (ዕብ 13:20)

– ደም ያለው ወልድ ነው (1ዮሐ 1:7)

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1:3-4)

ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል” (ኤፌ 1:20-21)

– በአብ ቀኝ ያለው ወልድ ነው (ዕብ 1:2-3)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል” (1ጴጥ 1:3-5)

– አባት ያለው ወልድ ነው (2ዮሐ 1:3)

በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት” (ገላ 1:1-2)

✍️ አምላክ ሆኖ ሳለ በስጋ የመጣው ወልድ በመጣበት ስጋ አማካኝነት ሞቶ ከሞት ተነስቷል። ከሞት በመነሳቱ እግዚአብሔር ለዳዊት የማለውን መሐላ መፈጸም ይችላል። ሞቶ ስላልቀረ በዳዊት ዙፋን ላይ መቀመጥ ይችላል። ስለዚህ ለዳዊት ለተማለተው መሐላ ፍጻሜው ወልድ ነው ማለት ነው። ይህ በኤር 23:5-6 ላይ እንደተተነበየው ለዳዊት የተነሳው ጻድቅ ቁጥቋጦ ወልድ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

“22 እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም። እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ። 23 ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ” (ሐዋ 13:22-23)

በዚህ ቦታ ላይም ሐዋርያው ጳውሎስ በዙሪያው ለነበሩ የእስራኤል ሰዎች ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ሲሰብክ እንመለከታለን። እግዚአብሔር ሳዖልን ከሻረው በኋላ ዳዊትን እንዳነገሰው፥ ካነገሰውም በኋላ ከእርሱ ዘር እንደ ተሰፋው ቃል ለእስራኤል መድሃኒት እርሱም ኢየሱስን እንዳመጣ ነገራቸው።

ይህ የኤር 23:5-6 ትንቢት ፍጻሜ ነው። በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥን እንደሚያስነሳ ተናግሮ ነበር። ይህንኑ የተስፋ ቃል ሲፈጽም ከራሱ ከዳዊት ዘር መድሃኒትን እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን አመጣ። ይህ በኤር 23:5-6 እየተነገረ ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል። እግዚአብሔር ወደ አለም ያመጣው ወልድን ነውና፦

“በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና” (1ዮሐ 4:9)

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም” (1ዮሐ 4:10)

“እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን” (1ዮሐ 4:14)

“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ” (ሮሜ 8:3-4)

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐ 3:16)

“ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4:4)

የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን። ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?” (ዮሐ 10:36)

✍️ ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ አለም የላከው፥ ወደ አለም ያመጣው ልጁን ነው። ከዳዊት ዘር ወደ ምድር የላከው ወልድን ነው። ስለዚህ በኤር 23:5-6 ላይ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥን አስነሳለሁ ሲል እየተናገረ የነበረው ስለ ልጁ ነበር ማለት ነው። ይህ በኤር 23:5-6 እንደተተነበየው ለዳዊት የተነሳው ጻድቅ ቁጥቋጦ ወልድ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

2) ጻድቅ ነው

በኤር 23:5-6 ላይ እንደተተነበየው እግዚአብሔር ለዳዊት የሚያስነሳው ይህ ቁጥቋጥ ጻድቅ ነው። ጻድቅ መሆኑ ወልድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ወልድ ጻድቅ ነው፦

“13 የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው። 14 እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ” (ሐዋ 3:13-14)

“ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም” (ሐዋ 7:52-53)

– ወደ አለም የመጣው ወልድ (ዮሐ 16:28)

“እርሱም አለኝ። የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን ታውቅ ዘንድና ጻድቁን ታይ ዘንድ ከአፉም ድምፅን ትሰማ ዘንድ አስቀድሞ መርጦሃል” (ሐዋ 22:14)

– ሐዋርያው ጳውሎስ ያየው ወልድን ነው (ሐዋ 9:20)

“1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። 2 እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ” (1ዮሐ 2:1-2)

– የኃጢአታችን ማስተሰረያ ወልድ ነው (1ዮሐ 4:9)

ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም” (ራዕ 19:11)

“ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም” (2ጢሞ 4:8)

– በዳግም ምጽአቱ የሚገለጠው ወልድ ነው (1ተሰ 1:9-10)

“8 ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ” (ዕብ 1:8-9)

ይህ እውነታ በአዲስ ኪዳን ብቻ ሳይሆን በብሉይ ኪዳንም ተረጋግጧል። የሚመጣው መሲህ ወይንም የእግዚአብሔር ልጅ ጻድቅ መሆኑ ያኔም ተገልጿል፦

“6 አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 7 ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ” (መዝ 45:6-7)

– የተቀባው ወልድ ነው (ሐዋ 4:27-28)

“ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል” (ኢሳ 53:11)

– ኃጢአታችንን የተሸከመው ወልድ ነው (1ጴጥ 2:24)

“4 ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል። 5 የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፥ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል” (ኢሳ 11:4-5)

– ከእሰይ ግንድ የወጣው ይህ መሲህ (ኢሳ 11:1) ወልድ ነው (ሮሜ 1:3-4)

“አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች” (ኢሳ 61:10)

– በኢሳ 61 ላይ እየተናገረ ያለው ወልድ ነው (ሉቃ 4:17-19)

“አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ #ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያምበአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል” (ዘካ 9:9)

– በአህያ ውርንጭላ የመጣው ወልድ ነው (ማቴ 21:7)

ስለዚህ በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ለዳዊት የሚያስነሳውና ስሙም “እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሆነው ይህ ጻድቅ ቁጥቋጥ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ማለት ነው። ጻድቅ መሆኑ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነውና።

3) ቁጥቋጥ ነው

በኤር 23:5-6 ላይ ስለሚመጣው መሲህ ከተባሉት ነገሮች አንዱ ቁጥቋጥ መሆኑ ነው። ቁጥቋጥ ማለት ከአንድ ግንድ የሚያድግ እጽዋት ሲሆን መሲሁም ቁጥቋጥ ተብሏል። ቁጥቋጥ የተባለበት ወይም ደግሞ በቁጥቋጥ የተመሰለበት ምክንያት ከዳዊት የዘር ግንድ ስለሚወለድ ነው። ይህ አሁንም በኤር 23:5-6 ላይ እየተወራ ያለው ስለ ወልድ መሆኑን ያረጋግጣል። በብሉይ ኪዳን አስተምህሮ ቁጥቋጥ የተባለው ልጁ ነውና፦

“ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፤ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ” (ዘካ 3:8)

– የአብ ባሪያ ልጁ ነው (ፊሊ 2:7)

“12 እንዲህም በለው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ስሙ ቍጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የእግዚአብሔርንም መቅደስ ይሠራል። 13 እርሱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይሸከማል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይነግሣል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፥ የሰላምም ምክር በሁለቱ መካከል ይሆናል” (ዘካ 6:12-13)

– በዳዊት ዙፋን ላይ የሚነግሰው ወልድ ነው (ሉቃ 1:31-32)

ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል” (ኢሳ 11:1)

– ከእሰይ ልጅ ከዳዊት ዘር የሆነው ወልድ ነው (2ጢሞ 2:8)

“በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ለጌጥና ለክብር ይሆናል፥ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱን ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል” (ኢሳ 4:2)

በኢሳ 4:2 ላይ ልክ እንደ ሌሎቹ ስፍራዎች ቁጥቋጥ የተባለው መሲሁ ሲሆን በማንነት ከእግዚአብሔር ተለይቶ ተገልጿል። “የ” እግዚአብሔር ቀጥቋጥ ከተባለ ራሱ እግዚአብሔርን/አብን አይደለም ማለት ነው። ይህ ቁጥቋጥ የተባለው መሲሁ ወይንም ወልድ እንደሆነ በሚገባ ያሳያል።

በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ለዳዊት አስነሳዋለሁ ያለው ንጉስ ቁጥቋጥ ተብሎ መጠራቱ መሲሁን ወይንም የእግዚአብሔርን ልጅ መሆኑን ያረጋግጣል። የሚመጣው መሲህ ወይም ወልድ ቁጥቋጥ መባሉ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተገልጿልና።

4) እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሏል

በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ለዳዊት አስነሳዋለሁ ያለው ይህ ጻድቁ ቁጥቋጥ ስሙ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በፊት እንደተነጋገርነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር/ያሕዌ ተብሎ የተጠራው አካል/person እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ከእግዚአብሔር ውጪ የትኛውም አካል/person እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቶ አያውቅም። በኦሪት መጽሐፍ ሆነ (ዘዳ 28:58) በዚያው በኤርምያስ መጽሐፍ (ኤር 50:34) ስሙ የእግዚአብሔር የሆነው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ይህ በኤር 23:5-6 ላይ እየተተነበየለት ያለው ስለ ወልድ እንደሆነ ያረጋግጣል። ወልድ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷልና፦

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” (ዮሐ 1:1)

– ቃል ወልድ ነው (ራዕ 19:13)

“ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (ዕብ 1:8)

“አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን” (ሮሜ 9:5)

– ክርስቶስ/የተቀባው ወልድ ነው (ሐዋ 4:27-28)

ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ 9:6)

– የተወለደው ወልድ ነው (ገላ 4:4)

አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው” (መዝ 45:6)

– መዝ 45:6 ስለ ወልድ የተነገረ ቃል ነው (ዕብ 1:8)

“ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤  እርሱም ከክፋት ሊቤዠን መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ሕዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለ እኛ ሰጥቶአል” (ቲቶ 2:13-14)

– ስለ እኛ ራሱን የሰጠው ወልድ ነው (ገላ 2:20)

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው” (1ዮሐ 5:20)

እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ” (ኢሳ 61:8)

– በኢሳ 61 ላይ ተናጋሪው ወልድ ነው (ሉቃ 4:17-19)

[ በኢሳ 61:8 ዙሪያ ሰፊ ንባብ ለማድረግ፦ https://t.me/TheTriune/1289 ]

አስተውሉ! በኤር 23:5-6 ላይ እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለው ራሱ ቁጥቋጡ እንጂ በቁጥቋጡ #ውስጥ ያለው አይደለም! በክፍሉ ላይ “..በቁጥቋጡ #ውስጥም ያለው ስሙ እግዚአብሔር ጽድቃችን ይባላል..” አይልም! እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለው #ራሱ ቁጥቋጡ ወይም መሲሁ/ወልድ ነው።

በተጨማሪም ይህ እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለውን አካል እግዚአብሔር እንደሚያስነሳው በኤር 23:5 ላይ ገልጿል። እግዚአብሔር ለዳዊት ያስነሳው ደግሞ ልጁን ነው (ሐዋ 13:23 1ዮሐ 4:9) ስለዚህ እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለው ራሱ አብ ከሆነ አብ አብን አስነሳ ወደሚል absurdity ያመራል። ስለዚህ እግዚአብሔር ጽድቃችን የተባለው አብ ያስነሳው ልጁ ነው። ስለዚህ ወልድ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው።

በዮሐ 4:24 ላይ ግን አምላክ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ ተገልጿል። የአምላክ ባህርይ ቁስ ያልሆነ መንፈስ እንደሆነ በዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተገልጿል። አሁን እንዳየነው ደግሞ ወልድ አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ስለዚህ ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ ነው ማለት ነው! መንፈስ ያልሆነ አምላክ የለምና።

ለዚህ ነው ይህ አምላክ የሆነው ወልድ መንፈስ በመሆኑ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ መንፈስ የተባለው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ለዚህም ነው ስጋ ባልነበረበት ቅድመ-ዓለም እንኳን ነበር የተባለው (ዕብ 1:2 ዮሐ 17:5) በሁሉ ስፍራ ይገኛል የተባለው (ዮሐ 3:13 ኤፌ 4:10) ይህ ሁሉ ወልድ በባህርይው መንፈስ እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

ወልድ መንፈስ ነው ማለት በስጋ አልመጣም ማለት አይደለም። ወልድ መንፈስ የሆነው በመለኮታዊው ባህርይው ነው። በባህርይው መንፈስ የሆነው ወልድ ሰዋዊን ባህርይ ወይም ስጋን የራሱ በማድረግ ወደ ምድር መጣ (ፊሊ 2:7-8 ሮሜ 8:3) ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት ወልድ በመለኮቱ መንፈስ በሰውነቱ ደግሞ ስጋ ነው

ማስረጃ ከቤተክርስቲያን አባቶች

የወልድ በመለኮቱ መንፈስ መሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ትምህርት ብቻ ሳይሆን ከ451 AD የቤተክርስቲያን ክፍፍል በፊት የነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶችም ያስተማሩት ትምህርት ነው። መግቢያው ላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የወልድ በመለኮቱ መንፈስ መሆን ከመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ጀምሮ የታመነ ክርስቲያናዊ እምነት ሲሆን የቤተክርስቲያን አባቶች እሱን ማስተማራቸው ለዚህ ተጨባጭ ማረጋገጫ ነው። እንመልከተው፦

1) ቅዱስ አትናቴዎስ/ St. Athanasius (296 AD – 373 AD)

“For this purpose, then, the incorporeal and incorruptible and immaterial Word of God comes to our realm, howbeit he was not far from us Acts 17:27 before. For no part of Creation is left void of Him: He has filled all things everywhere, remaining present with His own Father.” (On The Incarnation, chapter 8)

“ስለዚህ ለዚህ አላማ ቁስ ያልሆነው እና [በኃጢአት] ሊወድቅ የማይችለው መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኛ አለም መጥቷል፥ ነገር ግን በፊት ከእኛ ርቆ የነበረ አልነበረም (ሐዋ 17:27) ምክንያቱም እርሱ ያልነበረት የፍጥረት ክፍል አልነበረም። በሁሉ ስፍራ የሞላ ነው፥ ከአባቱ ጋር በሁሉ ስፍራ አለ። (ስለ ስጋዌው ምዕራፍ 8)

በዚህ ስፍራ ላይ እውቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወልድ መንፈስ መሆኑን ይናገራል። የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ወልድ (ራዕ 19:13) ቁስ እንዳልሆነ (incorporeal) መንፈስ እንደሆነ (immaterial) ከተናገረ በኋላ ወደ እኛ አለም እንደመጣ ተናግሯል። ወደ አለም የመጣው ደግሞ ወልድ ነው (1ዮሐ 4:9) ከዚያም ባሻገር ይህ ወልድ ከአባቱ ጋር በሁሉ ስፍራ እንዳለና በሁሉም ስፍራ እንደሞላ ተናግሯል። አባት ያለው ወልድ ሲሆን (ሮሜ 15:6) ይህ ወልድ በሁሉ ስፍራ እንደሞላም መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (ኤፌ 4:7-10) ስለዚህ ወልድ መንፈስ ነው የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ብቻ ሳይሆን ጥንት በነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶችም የታመነ ትክክለኛ እና እውነተኛ የክርስትና አስተምህሮ ነው።

2) ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/St. John Chrysostom (347 AD – 407 AD)

“The Image of the Invisible is itself also invisible, and invisible in like manner, for otherwise it would not be an image” (Homily 3, On Colossians)

የማይታው ምሳሌ የሆነው እርሱ ራሱ የማይታይ ነው። የማይታይ የሆነውም በዚያው በራሱ መንገድ ነው። እንደዚያ ካልሆነ ምሳሌው አይሆንም ነበር” (ድርሳን 3, ቆላሲስ ላይ)

የቆላሲስ መጽሐፍን በተረጎመበት ድርሳኑ ላይ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የማይታየው አምላክ ምሳሌ የሆነው ወልድ እርሱ ራሱ የማይታይ እንደሆነ ይናገራል። በቆላሲስ 1 ላይ የማይታይ አምላክ የተባለው አብ ሲሆን (ዮሐ 6:46) የእርሱ ምሳሌ የተባለው ደግሞ የፍቅሩ ልጅ የሆነው ወልድ ነው (ቆላ 1:13-14) ወልድ አይታይም ሊባል የቻለው መንፈስ በመሆኑ ነው። ምክንያቱም የማይታየው መንፈስ ነው (ሮሜ 1:20) አለመታየት የመንፈስ አንድ መገለጫ ነው። ወልድ የአብ ምሳሌ የተባለው ከአብ ጋር ካለው የመለኮታዊ ባህርይ አንድነት የተነሳ ሲሆን (ዮሐ 10:27-30 ፊሊ 2:6) ከእርሱ የተነሳ የማይታይ ተብሏል። ይህ ወልድ መንፈስ ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

3) የአሌክሳንደሪያው ቅዱስ ቄርሎስ/St. Cyril of Alexandria (376 AD – 444 AD)

“On this account we say that he suffered and rose again; not as if God the Word suffered in his own nature stripes, or the piercing of the nails, or any other wounds, for the Divine nature is incapable of suffering, inasmuch as it is incorporeal, but since that which had become his own body suffered in this way, he is also said to suffer for us; for he who is in himself incapable of suffering was in a suffering body” (The Epistle of Cyril to Nestorius) (Intelligio quosdam meae)

“ከዚህ የተነሳ መከራን ተቀብሎ ተነሳ እንላለን። እግዚአብሔር ቃል በራሱ ባህርይ ግርፋትን ሆነ በሚስማር መቸንከርን ሆነ ሌላ አይነት ቁስልን ተቀበለ ማለት አይደለም። መለኮታዊው ባህርይ መንፈስ ስለሆነ ሊሰቃይ አይችልምና። ነገር ግን የእርሱ ሰውነት የሆነው በዚህ መንገድ መከራን ስለ ተቀበለ ስለ እኛ መከራን ተቀበለ እንላለን። በራሱ መከራን ሊቀበል የማይችለው መከራን ሊቀበል በሚችል ሰውነት ነበርና። (የቄርሎስ ደብዳቤ ለንስጥሮስ)

ለንስጥሮስ በጻፈው ደብዳቤው ላይ ቅዱስ ቄርሎስ ወልድ መንፈስ መሆኑን ይናገራል። በደብዳቤው ላይ ወልድን “እግዚአብሔር ቃል” ብሎ ይጠራዋል። ወልድን “እግዚአብሔር ቃል” ብሎ መጥራት በአባቶች የተለመደ ሲሆን ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ቃል የሆነው ወልድ (ራዕ 19:13) እግዚአብሔር ነበር ስለተባለ ነው (ዮሐ 1:1) ይህ እግዚአብሔር የነበረው ቃል/ወልድ መለኮታዊው ባህርይው መንፈስ (incorporeal) በመሆኑ የእርሱ በሆነው መለኮታዊ ባህርይ መከራን ሊቀበል እንደማይችልና ከዚህም የተነሳ ሰውነትን የራሱ በማድረግ በዚያ ሰውነት መከራን እንደተቀበለ ቅዱስ ቄርሎስ ይናገራል። ስለዚህ ከጥንትም በነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶ በታመነው ትምህርት መሰረት ወልድ መከራን ለመቀበል የሰውነት ባህርይን የራሱ ባህርይ ያደረገው መንፈስ ነው።

4) የደማስቆው ዮሐንስ/John of Damascus (675 AD -749 AD)

“We hold then that the divine subsistence of God the Word existed before all else and is without time and eternal, simple and uncompound, uncreated, incorporeal, invisible, intangible, uncircumscribed, possessing all the Father possesses, since He is of the same essence with Him” (An Exposition of the Orthodox Faith (Book III) chapter 7)

“የእግዚአብሔር ቃል መለኮታዊ ሕልውና ከሁሉ በፊት የነበረ፥ ያለ ጊዜና ዘለዓለማዊ የሆነ፥ የሰውነት ክፍሎች ስብስስ ያልነበረ፥ ያልተፈጠረ፥ መንፈስ (incorporeal)፥ የማይታይ፥ የማይዳሰስ፥ ያልተገደበ፥ አብ ያለውን ነገር ሁሉ ያለው መሆኑን እናምናለን። ከእርሱ [ከአብ] ጋር በባህርይ አንድ ነውና” (ስለ ኦርቶዶክሳዊው እምነት የተሰጠ ማብራሪያ መጽሐፍ 3፥ ምዕራፍ 7)

ስለ ኦርቶዶክሳዊው እምነት በሰጠው ማብራሪያው ላይ የደማስቆው ዮሐንስ እግዚአብሔር ቃል ከጥንት ጀምሮ የነበረ፥ በባህርይው መንፈስ የነበረ፥ ያልተፈጠረ፥ ዘለዓለማዊ፥ በምንም ያልተገደበ፥ ከአብ ጋር ካለው የባህርይ አንድነት የተነሳ አብ ያለውን ሁሉ ያለው መሆኑን ገልጿል። በቤተክርስቲያን አባቶች ዘንድ “እግዚአብሔር ቃል” የሚለውን አገላለጽ ለወልድ ማዋል የተለመደ ነው። ምክንያቱም ቃል የነበረው ወልድ (ራዕ 19:13) እግዚአብሔር እንደነበር ተገልጿልና (ዮሐ 1:1) ይህንኑ ወልድ ይህ የቤተክርስቲያን አባት መንፈስ መሆኑን ገልጿል። ይህ ወልድ መንፈስ ነው የሚለው ትምህርት ከጥንት ጀምሮ የታመነው እውነተኛ ክርስቲያናዊ ትምህርት መሆኑን ያረጋግጣል።

5) የሳይረሱ ቲኦዶሬት/Theodoret of Cyrus (393 AD – 457 AD)

“It [Scripture] calls both the Father and the Son “Spirit” signifying by this term the incorporeal illimitable character of the divine nature” (Dialogue with Eranistes, Dialogue 1)

“መጽሐፍ ቅዱስ የመለኮታዊውን ባህርይ ኢ-ቁሳዊነት እና አይገደብነት ለማመልከት አብንም ወልድንም “መንፈስ” ብሎ ይጠራል” (ከኤራኒስቲስ ጋር በነበረው ውይይት፥ ውይይት 1)

የሳይረስ ጳጳስ የነበረው ቴኦዶሬት ከኤራኒስቲስ ጋር በነበረው ውይይት መጽሐፍ ቅዱስም የአብም የወልድም የሆነው አንዱ መለኮታዊ ባህርይ ቁስ አለመሆኑን እና የማይገደብ መሆኑን ለማመልከት አብንም ወልድንም መንፈስ ብሎ እንደሚጠራ ሲናገር እንመለከታለን። በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ አብንም (ዮሐ 4:23-24) ወልድንም (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) መንፈስ ብሎ ይጠራል። የአብም የወልድም የሆነው አንዱ መለኮታዊ ባህርይ መንፈስ ስለሆነ ከዚህ የባህርይ አንድነት የተነሳ አብ መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል ወልድም እንዲሁ መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ወልድ መንፈስ ነው የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊም በጥንት የቤተክርስቲያን አባቶችም የታመነው ትክክለኛው የክርስትና ትምህርት እንደሆነ በሚገባ ያረጋግጣል።

6) የእስክንድርያው ኦሪጅን/ Origen of Alexandria (185 AD – 254 AD)

“And from this it is distinctly shown that the divinity of the Son of God was not shut up in some place; otherwise it would have been in it only, and not in another. But since, in conformity with the majesty of its incorporeal nature, it is confined to no place” (De Principiis (Book IV))

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮት በአንድ ቦታ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፥ ካለዚያማ መለኮቱ በዚያ ቦታ ብቻ ያለ እንጂ በሌላ ቦታ የሌለ ይሆናል። ነገር ግን ከከበረው መንፈስ ከሆነው ባህርይው ጋር በሚስማማ መልኩ በየትኛውም ቦታ የተገደበ አይደለም” (ዴ ፕሪንሲፒስ መጽሐፍ 4)

እውቁ የቤተክርስቲያን ጸሐፊ የሆነው ኦሪጆን በዚህ መጽሐፉ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ መለኮቱ በሆነ ቦታ የተገደበ እንዳልሆነ እና መንፈስ ከሆነው ባህርይው ጋር በሚስማማ መልኩ በሁሉ ቦታ ያለ ምንም ውስንነት እንሚገኝ ጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ አምላክ እንደሆነ (ዕብ 1:8 1ዮሐ 5:20) በባህርይው መለኮት እንደሆነ (ፊሊ 2:6) ደግሞም በሁሉ ስፍራ እንደሚገኝ (ኤፌ 4:7-10) ይናገራል። እነዚህ ነገሮች በሙሉ ሊባሉ የሚችሉት እና የሚስማሙት መንፈስ ለሆነ አካል በመሆኑ የቤተክርስቲያን ጸሐፊ የሆነው ኦሪጅን የወልድ መለኮት መንፈስ ነው ሊል ችሏል። ይህ ወልድ መንፈስ ነው የሚለው ትምህርት ጥንታዊው የቤተክርስቲያን ትምህርት መሆኑን ያሳያል።

7) የእንዚናዙው ጎርጎርዮስ/Gregory of Nazianzus (329 AD – 390 AD)

The very Son of God, older than the ages, the invisible, the incomprehensible, the incorporeal, the beginning of beginning, the light of light, the fountain of life and immortality, the image of the archetype, the immovable seal, the perfect likeness, the definition and word of the Father he it is who comes to his image and takes our nature for the good of our nature” (The Wonder of The Incarnation)

“ከዘመናት ሁሉ በፊት የነበረው የእግዚአብሔር ልጅ፥ የማይታየው፥ ከመመርመር በላይ የሆነው፥ መንፈስ የሆነው፥ የመጀመሪያው ጀማሪ፥ የብርሃን ሁሉ ብርሃን፥ የሕይወትና የኢ-መዋቲነት ምንጭ፥ የፈጣሪ [የአብ] ምሳሌ፥ የማይነቃነቀው ማህተም፥ የአብ ፍጹም ምሳሌና ቃል ለእኛው ባህርይ ጥቅም ሲል ወደ አምሳሉ [በአምሳሉ ወደ ፈጠረን ወደ እኛ] መጥቶ የእኛን ባህርይ የያዘው እርሱ ነው” (የስጋዌው ተአምር)

እውቁ የቤተክርስቲያን አባት የእንዚናዙው ጎርጎርዮስ “የስጋዌው ተአምር” በተሰኘው ስብከቱ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ከዘመናት ሁሉ በፊት የነበረ፥ የማይታይ፥ መንፈስ የሆነ የሁሉ ጀማሪ መሆኑን ይናገራል። ይህ የቤተክርስቲያን አባት ስለ ወልድ የተናገረው ነገር ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ወልድ ከጥንት ጀምሮ ነበር (ዕብ 1:1-3 ዮሐ 1:1) የሁሉ ጀማሪ ነው (ዕብ 1:8-12 1ቆሮ 8:6 ቆላ 1:13-17 ዕብ 1:2 ዮሐ 1:1) የሕይወት ምንጭ ነው (ዮሐ 5:21 ዮሐ 14:6) ብርሃን ነው (ዮሐ 9:4-5) የአብ ምሳሌ ነው (ዕብ 1:3 ቆላ 1:15) የእኛን የሰውነት ባህርይ የያዘው እርሱ ነው (ፊሊ 2:7 ዮሐ 1:14 ሮሜ 8:3 ዕብ 2:12-16) ደግሞም መንፈስ ነው (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) ይህ ወልድ በመለኮቱ መንፈስ ነው የሚለው ትምህርት ከጥንትም የታመነ እውነተኛ ትምህርት መሆኑን ያሳያል።

አስተውሉ! ከላይ የተጠቀሱት አባቶች የቤተክርስቲያን አባቶች በሙሉ (ከደማስቆው ዮሐንስ በስተቀር) ከ451 ዓ.ም ክፍፍል በፊት የነበሩ አባቶች ናቸው። ይህ ማለት እነርሱ የነበሩባት ቤተክርስቲያን ያቺ አንዷ በጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ የተመሰረተችውና እስከዚያ ዘመን ድረስ ሳትከፋፈል የቀጠለችው ቤተክርስቲያን ናት ማለት ነው። እነዚህ አባቶች በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ በመሆናቸው ያቺ ቤተክርስቲያን ታምን የነበረውን ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን ትክክለኛ ትምህርት አስተምረዋል ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ በታሪክ የነበረችው አንዷ የክርስቶስ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የምታምነው እንዲህ ነበር ማለት ነው። በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ አባቶች የሰጡት ምስክርነት የሚያረጋግጠው ይህንን ነው።

ማጠቃለያ

ወልድ መንፈስ መሆኑን በብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ለመመልከት ሞክረናል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ባሻገርም ከጥንት ጀምሮ የታመነ የክርስትና ትምህርት መሆኑን ከቤተክርስቲያን አባቶች ማስረጃ ጠቅሰን ለማየት ሞክረናል። ወልድ በቀጥታ መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል፥ መንፈስ ብቻ ሊኖረው የሚችለውን መገለጫዎችና ባህርያት አሉት፥ መንፈስ ብቻ ሊጠራ በሚችለው ስያሜ ተጠርቷል። መለኮታዊው ባህርይው መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ስጋ የሆነን ሰዋዊ ባህርይ የራሱ በማድረግ ሊያድነን ወደ ምድር መጥቷል። ይህ ከመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች አስንቶ እስከ አሁን ድረስ የታመነው ትክክለኛ የክርስትና ትምህርት ነው።

ስለዚህ ይህን የማይቀበለው የሐዋርያት ቤተ-እምነት አስተምህሮ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝኖ ውድቅ ሆኗል። “ወልድ አብ የተገለጠበት ስጋ እንጂ መንፈስ አይደለም” የሚለው ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል መነጽር ታይቶ ከክርስትና ውጪ የሆነ ኑፋቄ መሆኑ ተረጋግጧል። ኑፋቄ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግስት የሚያሳጣ ስለሆነ (ገላ 5:21) በፍጥነት ከዚህ ኑፋቄ ወጥታችሁ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን እንድትድኑ ጥሪ እናቀርባለን!


ለሐሰት ትምህርቶች ምላሽ