አሸባሪዎችና ሙስሊሞች ወይንስ ሽብርተኝነትና እስልምና? – የበኃይሉ ሚዴቅሳ ስሁት አመክንዮ

አሸባሪዎችና ሙስሊሞች ወይንስ ሽብርተኝነትና እስልምና?

የበኃይሉ ሚዴቅሳ ስሁት አመክንዮ

በኃይሉ ሚዴቅሳ የተሰኘ ጸሐፊ የረመዳንን ወር መጋመስ አስመልክቶ አንድ ጽሑፍ በድሬ ቲዩብ ላይ ለንባብ አብቅቷል፡፡ ይህ ጸሐፊ ሙስሊም ዐቃቤያነ እምነት እንደሚያደርጉት ሁሉ በዓለም ላይ እየደረሱ ለሚገኙት የሽብር ጥቃቶች ሰበቡ እስልምና አለመሆኑን ለማሳመን ጥረት አድርጓል፡፡ እንዲህ ያለ ጽሑፍ በአንድ ሙስሊም ቢዘጋጅ የተለመደ የሙስሊም ሰባኪያን ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ስለምንገነዘብ በቸልታ ባለፍነው ነበር፡፡ ዳሩ ግን ሙስሊም ያልሆነ ሰው በማሕበረሰቡ ዘንድ ያለውን ተደራሽነት ተጠቅሞ ከተጨባጩ እውነታ ጋር ሆድና ጀርባ የሆነ መሰል ጽሑፍ ሲያሰራጭ መዘዙ ብዙ በመሆኑ የተነሱትን ነጥቦች በአንክሮ ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡ ግምገማችንን ከመጀመራችን በፊት ከበኃይሉ ጋር የምንስማማባቸውን ሁለት ነጥቦች እንጠቁም፡- የመጀመርያው የሽብር ጥቃቶችን የሚፈፅሙት ፅንፈኞች ከጠቅላላው ሕዝበ ሙስሊም አንፃር አናሳዎች ናቸው፤ አብዛኛው ሕዝበ ሙስሊም ግን ሰላም ወዳድ ነው የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አብዛኞቹ የሽብር ጥቃት ሰለባዎች ሙስሊሞች ናቸው የሚል ነው፡፡ የኛ ተቃውሞ በሁለቱ ነጥቦች ላይ ሳይሆን ከነዚህ ሁለት ነጥቦች በመነሳት በተደረሰበት ስሁት ድምዳሜ ላይ ነው፡፡ ጸሐፊው እንዲህ በማለት ይጀምራል፡-

ረመዳን ተጋመሰ፡፡ ከ15 ቀናት በኋላ ይፈታል፡፡ ታላቁ ወር በቅንነትና ደግነት፣ በፆምና ፀሎት እየተከበረ 16ኛው ቀን ላይ ደርሷል-የምህረት ቀን ላይ!! ይህንን ታላቅ ሃይማኖት እኩይ ምግባር ከሆነው ሽብርተኝነት ጋር ማገናኘት በምዕራቡ ዓለም እየተለመደ መጥቷል፡፡ በተለይ በማዕከላዊ አውሮጳና በሰሜን አሜሪካ ስደተኛና ሙስሊም ጠል የፖለቲካ ኃይሎች ሥልጣን ይዘዋል፡፡ እዚህ ጋር እነ ትራምፕን፣ ማይክል ኦርባንን፣ በጀርመንም የነ ሲዲዩን ተቀናቃኞች ስታስተውል የሥልጣናቸው ምንጭ ጸረ ሙስሊም ርዕዮት ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛ ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት ከሙስሊሙ ዓለም የሚመነጭ ሽብርተኝነትን ምዕራቡን ክፍል እያጠቃ ነው የሚለውን ነው፡፡

ይሁን እንጂ ገለልተኛ ጥናቶች የሚያሳዩት ተቃራኒውን ነው፡፡ ዓለም ላይ፣ የሙስሊሞችን ያህል በሽብርተኞች የተጠቃ፣የሞተና የተፈናቀለ የለም፡፡ ደግሞም ምድራችን ላይ ሽብርተኞችን እንደሙስሊሞች የተዋጋቸው የለም፡፡ የሽብር አደጋዎችን ቀድሞ በማክሸፍም የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ያህል የሠራ መንግሥትና ሕዝብ የለም፡፡ ይህ በጥናት የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡

የምዕራቡን ዓለም ፖለቲካ የክርክር አጀንዳ የማድረግ ፍላጎት የለንም፤ ዳሩ ግን ጸሐፊው ነገሮችን በሚዛናዊነት ከማስቀመጥ ይልቅ ሙስሊሞችን ለማስደሰት አልሞ ብዕሩን ማንሳቱ ከአጻጻፉ ግልጽ ሆኖ ይታያል፡፡ የብዙ ሙስሊሞችና ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ንፁህ ደም በግፍ የሚፈስስበትን የረመዳንን ወር በዚህ መንገድ መግለፁና በአክራሪ ሙስሊሞች በዓለም ዙርያ የሚፈፀሙትን የሽብር ጥቃቶች ከሃይማኖቱ ጋር ማገናኘት የምዕራባውያን ሤራ እንደሆነ ለማስመሰል መሞከሩ ለዚህ እማኝ ነው፡፡

ሁለተኛው አንቀጽ በአመክንዮአዊ ተፋልሶ የተቀየደ ነው፡፡ የሙስሊሙ ዓለም በሽብር እየተናጠ መሆኑ በገሃድ የሚታይ ሃቅ ነው፡፡ ከዚህ ተነጥሎ ሊታይ የማይገባው ሌላው ነጥብ ምዕራባውያን ከሙስሊሙ ዓለም የሚመጡ ፅንፈኞች በሚያደርሷቸው ጥቃቶች ቁም ስቅላቸውን እያዩ የመሆናቸው እውነታ ነው፡፡ ስለዚህ “…ገለልተኛ ጥናቶች የሚያሳዩት ተቃራኒውን ነው” የሚለው የጸሐፊው አባባል ትርጉም አይሰጥም፡፡ “ገለልተኛ ጥናቶች” ከተባሉት ምንጮች የተገኙት መረጃዎች በመስከረም አሥራ አንዱ የሽብር ጥቃት ወቅት 3000 የሚሆኑ ንፁሃን ሰዎች በአንድ ቀን በምድረ አሜሪካ በግፍ መገደላቸውንና 6000 ያህል መቁሰላቸውን የመሳሰሉትን በምዕራባውያን ላይ የተፈፀሙ የሽብር ጥቃቶችን የሚያስተባብል መረጃ ይዘው እስካልወጡ ድረስ  “ከሙስሊሙ ዓለም የሚመነጭ ሽብርተኝነት የምዕራቡን ክፍል እያጠቃ ነው” የሚለው የቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች አባባል በስህተትነት የሚፈረጅበት ምክንያት የለም፡፡ በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ እየተቀነቀነ በሚገኘው የአክራሪ እስልምና አስተምሕሮ ምክንያት የምዕራቡም ሆነ የሙስሊሙ ዓለም እየተሸበረ ነው፡፡ “ገለልተኛ ጥናቶች የሚያሳዩት ተቃራኒውን ነው” በማለት የአንዱን ሠቆቃ አድበስብሶ ሙስሊሙን ዓለም ብቻ ተጠቂ ማስመሰል ሚዛን መሳት ነው፡፡

ሌላው የጸሐፊው ስህተት ሙስሊሞች የሽብርተኝነት ዋነኛ ተጠቂዎች መሆናቸው ሽብርተኝነት ከሃይማኖቱ ጋር ላለመገናኘቱ ማስረጃ ሊሆን አለመቻሉን አለማስተዋሉ ነው፡፡ የሽብር ዋና ምንጭና አስኳል የሙስሊሙ ዓለም እስከሆነ ድረስ የመጀመርያዎቹ ገፈት ቀማሾች ሙስሊሞች ቢሆኑ ምንም የሚደንቅ ነገር የለውም፡፡ ከአሸባሪ ሙስሊሞች ይልቅ ሰላም ወዳዶች ስለሚበዙ እነዚህ ሰላም ወዳድ ሙስሊሞች በአፍንጫቸው ስር የሚጠነሰሰውን የሽብር ተግባር ከማንም ይልቅ መዋጋታቸው የሽብርተኝነት ምንጭ የሙስሊሙ ዓለምና እስላማዊ አስተምሕሮ ላለመሆናቸው በማሳያነት ሊጠቀሱ አይችሉም፡፡ ይልቅ የሙስሊሙ ዓለም ራሱ ተሸብሮ ለሌላውም ዓለም የሽብር መንስዔ በመሆኑ እየተመራበት የሚገኘው ንፅረተ ዓለም ችግር ይኖርበት እንደሆን መጠየቅ ተገቢም ትክክልም ነው፡፡ ጸሐፊው ያቀረባቸውን አኃዛዊ መረጃች ከተመለከትን በኋላ ይህንን ሐሳብ እንመለስበታለን፡-

የሽብር ሰለባዎቹ አማኞች

ምድራችን ካስተናገደቻቸው የሽብር ጥፋቶች ሁሉ አብዛኞቹን የተቀበሉት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ቢቢሲ ‹‹Are most victims of terrorism Muslim?›› በሚል ርዕስ ከጥቂት ዓመታት በፊት አንድ አጭር ትንታኔ አስነብ አብዛኞቹ የሽብር ሰለባዎች ሙስሊሞች መሆናቸውንና ዓለም ለዚህ እውቅና የመሥጠት ፍላጎት እንደሌለው ገልፆ ነበር፡፡

የአሜሪካ የጸረ-ሽብር ማዕከልን (NCTC) እንደሚለው ደግሞ ከ2004 እስከ 2013 (እ.ኤ.አ) ከተጠመዱት የሽብር ፈንጂዎች መካከል 60 በመቶዎቹ የተተኮሱት ሙስሊሞች ላይ ነው፡፡ እስከ 2011 በነበሩት 5 ዓመታት ደግሞ ከ82-97 በመቶ የሚደርሱ ጥቃቶችም ኢላማ ያደረጉት ሙስሊሞችን ነው፡፡ የአልቃኢዳን ብቻ ነጥለን ብንወስድ የሽብር ቡድኑ በዘመቻ ዘመኑ ከገደላቸው ስምንት ሰዎች ሰባቱ ሙስሊሞች ናቸው፡፡

Max Roser ከባልደረቦቻቸው ጋር የፃፉትን Terrorism የተሰኘ ጥናት ስናነብም አብዛኞቹ የሽብር አደጋዎች የተከሰቱት በሙስሊም አገሮች እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በ2017 ብቻ ዓለም 26ሺህ 445 የሽብር ጥቃት አስተናግዳለች፡፡ ከዚህ ውስጥ በኢራቅ፣ 6ሺህ476፣ በአፍጋኒስታን 6ሺህ 97፣ በሶሪያ 2ሺህ 26 አደጋዎች ደርሰዋል፡፡ አሜሪካ የደረሰባት የሽብር ጥቃት ግን 68 ብቻ ነው፡፡ 83ቱ ደግሞ በምዕራብ አውሮጳ የተከሰቱ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ በሌሎች ክፍለ ዓለማት ተፈጽመዋል፡፡

የቀድሞው የዴይሊ ሜይል የፖለቲካ ጉዳዮች አርታኢ ማት ቾርሌይ በ2014 የተደረገን ጥናት ጠቅሶ ሲጽፍ፣ በዚያ ዓመት 32 ሺህ 658 ሕዝብ በሽብር መገደሉን ይገልፃል፡፡ ከዚህ ውስጥ አብዛኛው ሙስሊም ነው፡፡ ብዙ ዜጎቻቸውን በሽብር ከተነጠቁ አስሩ አገራት ውስጥ ሁሉም ሙስሊም አገራት ናቸው፡፡

Global Terrorism Data Base የሽብር መረጃዎችን በሚያጠናክር ተቋም ውስጥ የሚሠሩት ኤሪን ሚለር፣ አብዛኞቹ የሽብር ድርጊቶች ይከናወኑ የነበሩት ሙስሊም በሆኑ አገሮች ውስጥ መሆኑን ይጠቅሱና 95 በመቶው የሽብር ኢላማ በእስልምና አማኞች ላይ የደረሰነው ቢባል ከእውነታው መራቅ እንዳልሆነ ይጠቅሳሉ፡፡

አብዛኞቹ የሽብር ጥቃት ሰለባዎች ሙስሊሞች መሆናቸው እሙን ቢሆንም እነዚህን የተጋነኑ አኃዛዊ ሪፖርቶች ሙሉ በሙሉ እውነታን የሚወክሉ አድርጎ መውሰድ አይቻልም፡፡ የመጀመርያው ችግር እነዚህ ዘገባዎች የተወሰኑ ዓመታትንና አካባቢዎችን ብቻ መርጠው የሚያሳዩ መሆናቸው ነው፡፡ የዘገባዎቹ ምንጮች በአብዛኛው የዜና አውታሮች በመሆናቸውና ዜናዎቹ ደግሞ መርጠው የሚዘግቡና ከሞላ ጎደል የሟቾችን ሃይማኖት የማይገልፁ በመሆናቸው ትክክለኛውን ቁጥር ይቅርና እውነታን የሚወክል ቁጥር እንኳ ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ጸሐፊው የጠቀሰው የአሜሪካ የጸረ-ሽብር ማዕከል (NCTC) የ2011 ሪፖርት ይህንን ጉዳይ እንደ ዋና ችግር በመጥቀስ በመግቢያው ላይ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪም አነስተኛ መጠን ያላቸውን ጥቃቶችና ከመረጃ በተሰወሩ “ሩቅ” አካባቢዎች የሚፈፀሙ የሽብር ተግባራትን በተመለከተ የመረጃ እጥረት መኖሩን ይገልጻል፡፡[1] እነዚህ ከግምት ውስጥ ያልገቡ አኃዞች ቢደማመሩ በአጠቃላይ መረጃው ላይ የጎላ ተፅዕኖ በማስከተል ምስሉን ሊቀይሩት ይችላሉ፡፡

ጸሐፊው የጠቀሰውን የቢቢሲ ሪፖርት የተመለከትን እንደሆን በዐበይት የጥናት ተቋማት የተሰራጩ መረጃዎችን የሚገመግም ሲሆን በጥናቶቹ የተቀመጡት አኃዛዊ መግለጫዎች አስተማማኝ አለመሆናቸውን ያሳስባል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጸሐፊው የጠቀሰውን በአሜሪካ የጸረ-ሽብር ማዕከል (NCTC) የቀረበውን ሪፖርት አስመልክቶ የተሟላና ጥቅል አለመሆኑን እንዲህ ሲል አስቀምጧል፡- However, the report did not say in what proportion of cases it had been possible to determine the victims’ religious affiliation – or whether these cases were representative of the others. The answers are not easy to obtain, because the report is no longer produced.[2]

ጸሐፊው በ NCTC ሪፖርት ውስጥ ያልተባለን ሐሳብ ጽፏል፡-የአሜሪካ የጸረ-ሽብር ማዕከልን (NCTC) እንደሚለው ደግሞ ከ2004 እስከ 2013 (እ.ኤ.አ) ከተጠመዱት የሽብር ፈንጂዎች መካከል 60 በመቶዎቹ የተተኮሱት ሙስሊሞች ላይ ነው” በማለት የጻፈው የ the Global Terrorism Database (GTD) ማዕከል አባል የሆነችው ኤሪን ሚለር ከላይ በተጠቀሰው የቢቢሲ ዘገባ ውስጥ የተናገረችው እንጂ በ NCTC ሪፖርት ውስጥ የሚገኝ አይደለም፡፡ በተጨማሪም “እስከ 2011 በነበሩት 5 ዓመታት ደግሞ ከ82-97 በመቶ የሚደርሱ ጥቃቶችም ኢላማ ያደረጉት ሙስሊሞችን ነው” በማለት የጻፈው የሪፖርቱን ትክክለኛ ሐሳብ የሚወክል አይደለም፡፡ በ NCTC ሪፖርት መሠረት ከ82-97 በመቶ የተገመቱት የሽብር ሰለባዎች ሙስሊሞች ሆነው የተገኙት የተጠቂዎቹ ሃይማኖት በታወቀባቸው አጋጣሚዎች ብቻ እንጂ ሁሉንም የሽብር ጥቃት አጋጣሚዎች የሚገልፅ አይደለም፡፡ ሪፖርቱ እንዲህ ይላል፡- In cases where the religious affiliation of terrorism casualties could be determined, Muslims suffered between 82 and 97 percent of terrorism-related fatalities over the past five years.[3] የተጠቂዎች ሃይማኖት ተለይቶ የተመዘገበው ከሽብር ጥቃቶች አጋጣሚዎች በስንት እጅ እንደሆነ መረጃ አለመሰጠቱ ደግሞ “ከ82-97 በመቶ” የሚለውን ግምት በጥርጣሬ እንድናየው ያስገድደናል፡፡ በመስጊዶች ወይንም በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው ሲጸልዩ ሳሉ የሽብር ጥቃቶች ሰለባ የሆኑትን ወገኖች ሃይማኖት መናገር ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እንዲሁም በሙስሊም አገራት ውስጥ በአንድ ቦታ ተሰብስበው ባሉ ሰዎች ላይ ጥቃት ቢፈፀም ሁሉም ሙስሊሞች መሆናቸውን መናገር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሙስሊም ባልሆኑት አገራት ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ቦታዎች ላይ የጥቃት ዒላማ የተደረጉትን ሰዎች ሃይማኖት መናገር አዳጋች ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያሉት ሪፖርቶች የሙስሊሙን ቁጥር በማጋነን የሚያሳዩ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ እናም ይህ የተጋነነ ቁጥር እውነታን እንደማያንፀባርቅ መታወቅ አለበት፡፡ ይህንን ስንል ሙስሊሞች የሽብር ጥቃቶች ዋነኛ ሰለባዎች መሆናቸውን እየካድን እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ እንዲህ የተጋነኑ ቁጥሮች አስተማማኝ አለመሆናቸውን ብቻ እየገለፅን ነው፡፡ በማስከተል ጸሐፊው እንዲህ ይላል፡-

ሁሉም የሽብር ቡድኖች፣ ከአልቃኢዳ እስከ አልሸባብ፣ ከቦካሃራም እስከ አይ ኤስ አይ ኤስ… እስልምና ነው ቢሉም አብዝተው የገደሉት ግን ቆመንለታል የሚሉትን ማኅበረሰብ ነው፡፡ ጥናታዊ አሀዞቹ የሚያመለክቱት ይህንን ነው፡፡ ሆኖም አብዛኛው የዓለም መገናኛብዙሃን ሽብርተኝነት ምዕራባዊያኑንና ወዳጆቻቸውን ብቻ ለማጥቃት የመጣ አድርገው ይዘግቡታል፡፡ የዚህስ ምክንያቱ ምንድን ነው? የሚለውን እመለስበታለሁ፡፡

የሽብርተኝነት ዓላማና ግብ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን ማጥፋት ቢሆንም ሙስሊሞች ዋነኛ ተጠቂዎች መሆናቸው በገሃድ እየታየ ያለ እውነታ ነው፡፡ ይህ መሆኑ ግን የሽብርተኝነት ምንጭ እስልምና አክብሮ የያዛቸው የሃይማኖት መጻሕፍት ላለመሆናቸው ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ ሙስሊሞችም ቢሆኑ እንዲህ  እንዲሠቃዩ እያደረጓቸው የሚገኙት የገዛ ሃይማኖታቸው መመርያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት እስካልተወገዱ ድረስ የሙስሊሙ ዓለም ለራሱም ሆነ ለሌላው ዓለም የሽብርና የሰቆቃ ምንጭ መሆኑን ይቀጥላል፡፡ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኧል-ሲሲ በአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ሊቃውንት ፊት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር ይህንን እውነታ እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፡-

“… እዚህ ጋ እየተናገርኩ ያለሁት የእምነት አባቶችን ነው፡፡ እየተጋፈጥን ስላለነው ነገር በአንክሮ ማሰብ ያስፈልገናል – በእርግጥ ይህንን ጉዳይ ከዚህ ቀደም አንድ ሁለት ጊዜ አንስቻለሁ፡፡ በጣም ክቡርና ቅዱስ አድርገን የያዝነው አስተሳሰብ አጠቃላይ ኡማውን [እስላማዊውን ማሕበረሰብ] ለዓለም ማሕበረሰብ የጭንቀት፣ የአደጋ፣ የግድያና የጥፋት ምንጭ እንዲሆን ማድረጉ የማይታመን ነው፡፡ ይህ ሊሆን አይችልም!

ያ አስተሳሰብ – “ሃይማኖት” እያልኩ አይደለም ነገር ግን “አስተሳሰቡ” – ከእርሱ ማፈንገጥ የማይቻልበት ደረጃ ላይ እስክንደርስ ድረስ ለክፍለ ዘመናት አክብረን የያዝነው የመጻሕፍትና የአስተሳሰብ ስብስብ መላውን ዓለም እየተፃረረ ይገኛል፡፡ ዓለምን በሞላ እየተፃረረ ነው!

እነዚህን ቃላት እዚህ በአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ፣ በዚህ የሊቃውንትና የኡላማ ጉባኤ ፊት እየተናገርኩ ነው – አሁን እየተናገርኩ ያለሁትን ነገር በተመለከተ ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ በፍርዱ ቀን ስለ እውነተኛነታችሁ ምስክር ይሁንባችሁ፡፡

እየነገርኳችሁ ያለሁትን ይህንን ሁሉ ነገር በዚህ አስተሳሰብ ውስጥ ተጠምዳችሁ የምትኖሩ ከሆነ ልትረዱት አትችሉም፡፡ በትክክል መገምገም እንድትችሉና የበለጠ አብርሆት ካለው ፅንፍ ማየት እንድትችሉ የቀደመውን አስተሳሰብ መጣል ያስፈልጋችኋል፡፡

ደግሜ ደጋግሜ እላለሁ ሃይማኖታዊ አብዮት ያስፈልገናል፡፡ እናንተ ኢማሞች በአላህ ፊት ተጠያቂዎች ናችሁ፡፡ መላው ዓለም፣ እደግመዋለሁ መላው ዓለም የእናንተን ቀጣይ እርምጃ እየተጠባበቀ ይገኛል… ምክንያቱም ይህ ኡማ እየፈረሰ ነው፣ እየወደመ ነው፣ እየጠፋ ነው – እየጠፋ ያለው ደግሞ በገዛ እጃችን ነው፡፡[4]

ሙስሊም መሪዎች የሽብርተኝነትን ትክክለኛ መነሻ ተረድተው ሃይማኖታቸው ስር ነቀል ለውጥ እንደሚያስፈልገው እየተናገሩ ባሉበት ሁኔታ ቢቻል የችግሩ ምንጭ የሆኑትን መጻሕፍት በማጋለጥ ሙስሊም ሊቃውንት ለሰላም ስጋት በማይሆኑበት መንገድ እንዲተረጉሙ አለበለዚያ ደግሞ እንዲያስወግዷቸው ግፊት ማድረግ እንጂ እንዲህ ባሉ ጽሑፎች ሕዝብን ማዘናጋት ትክክል አይደለም፡፡ ካለማወቅም ይሁን ከፖለቲካዊ ትክክለኝነት (Political Correctness) በመነጨ አስተሳሰብ እስላማዊ መጻሕፍት ሰላምን እደሚያስተምሩ በመስበክ ለእስልምና ጥብቅና ሲቆሙ የነበሩ ወገኖች ይህንን ማድረጋቸው ምንም አልፈየደም፡፡ አንድን ከሥነ ምግባር የወጣ ሰው ሥነ ምግባሩ ጥሩ እንደሆነ ደጋግሞ በመንገር ፀባዩን እንዲያርም ማድረግ እንደማይቻል ሁሉ ሽብርን የሚሰብክ ሃይማኖት ሰላምን እንደሚሰብክ በመናገር ሰላማዊ ማድረግ አይቻልም፡፡ ይልቁኑ ስህተቱን ነቅሶ በማውጣት እንዲያስተካከል መንገር እንጂ መፍረግረግና መለማመጥ አጥፊው የልብ ልብ እንዲሰማው ማድረግ ነው፡፡ እውነትን ሸሽጎ ውሸትን በመናገር ችግሩን ማፈርጠም መፍትሄ አይሆንም፡፡ የፖለቲካዊ ትክክለኝነት ንግግሮች ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ ይቅርና ጊዜያዊ መፍትሄ እንኳ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ የሃይማኖት አባቶችና የፖለቲካ መሪዎች የእስልምናን ሰላማዊነት አጥብቀው ቢሰብኩንም ነገር ግን ችግሮች እየተባባሱ ሄዱ እንጂ ሲቀንሱ አልታዩም፡፡ እውነትን በመናገር ሊፈጠር የሚችለውን ጊዜያዊ ችግር በመፍራት ዝንተ ዓለም በሽብር እየተናጡ ከመኖር እውነቱን አፍረጥርጦ በመናገር ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ ይበጃል፡፡ “ጅቡ እግሬን እየበላው ነውና እንዳይሰማን ዝም በል” እንዳለው ሞኝ ሰው መሆን ይበቃናል፡፡  ጸሐፊው ይቀጥላል፡-

ከሽብርተኞች ጋር የሚዋጉ ሙስሊሞች ዓለም ላይ ከሽብር ቡድኖች ጋር ገጥመው ሲፋለሙ ከሚውሉት የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሙስሊሞችን የሚበልጥ የለም፡፡ አይ ኤስንም ሆነ አልቃኢዳን፣ አልሸባብንም ሆነ ቦኮሃራምን እኩይ ድርጊቱን አውግዘው ሲዋጉ የሚውሉት ሙስሊሞች ናቸው፡፡

በአሜሪካ ምድር ሊደርሱ የነበሩ ብዙ የሽብር ጥቃቶችን ለጸጥታ አካላት በመጠቆም ያከሸፉት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ ከአገሪቱ መንግሥት የበለጠ ተግባር በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ተሰርቷል በአሜሪካም ሆነ በአውሮጳ ከደረሱ የሽብር ተግባሮች አብዛኞቹ የተፈጸሙት ሙስሊም ባልሆኑ ዜጎች ነው፡፡ መገናኛ ብዙሃን ግን ይህንን ለመዘገብ የሚዛናዊነት አንደበት አጡ›› ይላል የረዥም ልቦለድ ደራሲውና የፖለቲካ ተንታኙ ዳኒሻዊው ሊዎን ዲ ዊንተር፡፡

የዚህን አውሮጳዊ ሰው ጥናት የሚመግብ ሌላ የምርምር ውጤት በCenter For strategic and International studies አለ፡፡ ‹‹አብዛኞቹ ሙስሊሞች እስላማዊ ጽንፈኝነትንም ሆነ እምነቱን ሽፋን የሚያደርግን አክራሪነት ይቃወማሉ፤ የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ የሃይማኖት እኩልነት፣ የሥራና የአስተዳደር ፍትህ ናቸው›› ይላል ጥናቱ፡፡

ጸሐፊው ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገባው እውነታ ቢኖር በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ሙስሊሞች መኖራቸውን ነው፡፡ እስላማዊ መጻሕፍት ሽብርን እንደሚያበረታቱ የሚያውቁ ነገር ግን ሰብኣዊነት የሚሰማቸውና እንዲህ ዓይነቱን ነውጠኛ ትምህርቶች የማይቀበሉ ከሙስሊሙ ማሕበረሰብ ጋር በጥልቀት ስለተቆራኙ ብቻ ሙስሊም የሆኑ “ሙስሊሞች” አሉ፡፡ እነዚህ “ሙስሊሞች” ተራማጅ አመለካከት ያላቸው ሲሆኑ ነውጠኛ የሆኑት የእስልምና ትምህርቶች በተሓድሶ መወገድ እንዳለባቸው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል የአውስትራሊያውን ኢማም ተውሒዲ፣ የእንግሊዙን መጂድ ነዋዝና የመሳሰሉትን ወገኖች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሌሎች ሙስሊሞች ደግሞ እነዚህ ነውጠኛ እስላማዊ ትምህርቶች ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን የጦርነት ታሪኮች ሁሉ በዚያ ዘመንና በዚያ ቦታ ብቻ የተወሰኑ እንደሆኑ ስለሚያምኑ የሽብር ድርጊቶችን ይቃወማሉ፡፡ ቁርአንና ሌሎች እስላማዊ ጽሑፎችን በዚህ መንገድ ተረድተው ሰላምን እየሰበኩ የሚገኙ ብዙ ሙስሊም ሊቃውንት በአገራችንም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በዚህ መንገድ ሊተረጎሙ የማይችሉ እስላማዊ ጽሑፎች መኖራቸው የነዚህን ወገኖች ጥረት የሚያደናቅፍ ይመስላል፡፡

የሽብር ተግባራትን የሚቃወሙ፣ እስላማዊ መጻሕፍት ምን እንደሚያስተምሩ የማያውቁና በነውጠኛ ትምህርቶች ያልተበከሉ ሙስሊሞች መኖራቸውም ልብ ሊባል ይገባል፡፡ የአገራችን አብዛኞቹ ሙስሊሞች በኢትዮጵያዊነት ሥነ ምግባር ያደጉና በእስላማዊ መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙትን የሽብር አስተምሕሮዎች በጥልቀት የማያውቁ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ሰለፎች (ወሃቢዮች) የኢትዮጵያን ሙስሊሞች “ከእንደገና የማስለም” ዘመቻ በመክፈት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት፡፡ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊ ሙስሊምና አረባዊ ሙስሊም እየተወያዩ ሳሉ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም “እኛ እስልምናን በሰይፍ ተገደን ሳይሆን በውድ ነው የተቀበልነው” በማለት በኩራት ሲናገር አረባዊው ሙስሊም መልሶ “እናንተ እስልምናን ያለሰይፍ እንደተቀበላችሁት ሁሉ ከእስልምና ስትወጡም ያለሰይፍ ነው” አለው ይባላል፡፡ አሁን እየተደረገ ያለው በአንፃራዊነት ሰላማውያን የሆኑትን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሰይፍ ወደሚያምኑ የሰለፊ (ወሃቢያ) ሙስሊሞች መቀየር ነው፡፡ ይህ ከሰዑዲ አረብያና ከኳታር ኤክስፖርት የሚደረግ የፅልመት አስተሳሰብ ተፅዕኖ በአገራችን ውስጥ እየጎላ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአንፃራዊነት በመቻቻልና አብሮ በመኖር የሚያምኑት እስላማዊ መጻሕፍት ሰላምን ስለሚያስተምሩ ሳይሆን በነዚህ ጽንፈኛ አስተምህሮዎች በሚገባ ስላልተጠመቁ ነው፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያዊነት ስሜትና ሥነምግባር በጣም ጠንካራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባሕላችንን የጥላቻና ሌሎችን የመግፋት ባሕል በሆነው የአክራሪ እስልምና ትምህርት እንዲለውጡ ለማድረግ እስላማውያን በብርቱ መጣር ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

“አብዛኞቹ ሙስሊሞች ሰላም ወዳድ ናቸው” ሲባል “አናሳ” የተባሉት ነውጠኞች የደቀኑትን አደጋ መዘንጋት የለብንም፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 95 ከመቶ የሚሆነውን የአጥፍቶ መጥፋት ተግባር የሚፈፅሙት እነዚህ ወገኖች ናቸው፡፡ ከሕዝበ ሙስሊሙ ብዛት አንጻር አሸባሪነትን የሚደግፉት 1 በመቶ ናቸው ቢባል እንኳ ይህ ቁጥር 16 ሚሊዮን ተብሎ እንደሚተረጎም ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሽብርተኝነትን የሚደግፉት ሙስሊሞች ቁጥር ከዚህ በእጅጉ የላቀ ነው፡፡ ማንኛውም ፍላጎቱ ያለው አንባቢ https://www.thereligionofpeace.com/pages/articles/opinion-polls.aspx ላይ በመግባት እነዚህን አስደንጋጭ ቁጥሮች ማየት ይችላል፡፡

ሽብርተኝነት ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የተቆራኘ ከሆነ አብዛኞቹ የሽብር ሰለባዎች ስለምን ሙስሊሞች ሆኑ?

በኃይሉም ሆነ ሌሎች የእስልምናን ነገረ መለኮትና ታሪክ በወጉ ያላጠኑ ወገኖች የተቸገሩበት ጥያቄ ይህ ነው፡፡ የሽብር ቡድኖች የእስልምና ፍሬዎች ከሆኑ ሙስሊሞችን ሊገድሉ አይችሉም ስለዚህ አሸባሪዎች ሙስሊሞች አይደሉም የሚለው አመክንዮ እስላማዊ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመረመረና የእስልምናን ታሪክ በቅጡ ላወቀ ሰው ሚዛን የሚደፋ አይደለም፡፡ ሊጠቀሱ ከሚችሉ በርካታ ምክንያቶች መካከል ጥቂቶቹን እናንሳ፡-

የመጀመርያው ምክንያት በቁርኣን መሠረት ክርስቲያኖችና አይሁዶችን የሚወዳጁ ሙስሊሞች ልክ እንደእነርሱ የሚቆጠሩ በመሆናቸው ነው፡-

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡” (የማእድ ምዕራፍ 5፡51)

“ካፊሮችን” የሚወዳጁ ሙስሊሞች ወደ ገሃነም ይወርዳሉ፡-

“ከእነሱ ብዙዎቹን እነዚያን የካዱትን ሲወዳጁ ታያለህ፡፡ በእነሱ ላይ አላህ የተቆጣባቸው በመኾኑ ለእነርሱ ነፍሶቻቸው ያስቀደሙት ሥራ በጣም ከፋ፡፡ እነሱም በቅጣት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡” (የማእድ ምዕራፍ 5፡80)

“ካፊር” የቤተሰብ አባላቶቻቸውን እንኳን ቢሆን የሚወዳጁ ሙስሊሞች በደለኞች ናቸው፡-

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነሱ በዳዮች ናቸው፡፡” (የንስሐ ምዕራፍ 9፡23)

አቡ ዳውድ እንዲህ ብሏል፡-

“ከሙሽሪክ (ከአላህ ውጪ ሌላ ነገር የሚያመልክ ሰው) ጋር የሚተባበርና አብሮት የሚኖር ሰው ልክ እንደ እርሱ ነው፡፡”[5]

ተመሳሳይ ዘገባዎችን በሌሎች ሐዲሳት ውስጥም እናገኛለን፡፡ ኢብን ከሢርና ኢብን ተይሚያን ጨምሮ ብዙ ሙስሊም ሊቃውንትም ይህንኑ ሐሳብ ያፀናሉ፡፡ ስለዚህ አይኤስን የመሳሰሉት እስላማዊ የሽብር ቡድኖች ሙስሊሞችን ሲገድሉ በዚህ መነሻ ነው፡፡ ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር፣ በተለይም ደግሞ ከምዕራባውያን ክርስቲያኖችና ከአይሁዶች ጋር የሚወዳጁ ሙስሊሞች ለሙስሊሙ ማሕበረሰብ (ኡማ) አደገኞች እንደሆኑ ይታሰባል፡፡ ስለዚህ እነዚህን ሰዎች መግደል ሙስሊሙን ማሕበረሰብ ከጉዳት መከላከል ነው የሚል አመክንዮ አላቸው፡፡ አላህ ደግሞ በቁርኣኑ ውስጥ “ካፊሮችን” የሚወዳጁ ሙስሊሞች እውነተኛ ሙስሊሞች አለመሆናቸውንና “ልክ እንደካፊሮች” መሆናቸውን በመናገር እርምጃውን ያፀድቀዋል፡፡ “ካፊሮች” መገደል ካለባቸው እነዚህ ሙስሊሞችም መገደል አለባቸው፡፡ ስለዚህ ሙስሊም አሸባሪዎች በቁርኣን ያልተደገፈና እስላማዊ ያልሆነ ነገር እየፈፀሙ አይደለም፡፡

ሌላው ደግሞ በእስልምና ውስጥ ብዙ አንጃዎች የመኖራቸው ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ አንጃዎች እርስ በርሳቸው የሚወነጃጀሉና አንዳቸው ሌላቸውን እንደ ካፊር የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ በተለይም የሺኣና የሱኒ ሙስሊሞች በፖለቲካዊ ጥቅም ከመጋጨታቸውም በላይ አንዳቸው ሌላቸውን እንደ እውነተኛ ሙስሊም አይቆጥሩም፡፡ ነገር ግን ሙስሊሞች የውስጥ ሽኩቻዎቻቸውን ለውጪው ዓለም በመግለጥ እስልምና እርስ በርሱ የተከፋፈለ መሆኑን ማሳወቅ ስለማይፈልጉ በእስላማዊ አንጃዎች መካከል ያለውን የጥላቻ ጥልቀት ለማወቅ ቀረብ ብሎ መመልከት ያሻል፡፡

እነዚህ ቡድኖች ሙስሊሞችን የሚገድሉበት ሦስተኛው ምክንያት ከራሱ ከእስልምና ተፈጥሮ የሚመነጭ ነው፡፡ እስልምና ከእግዚአብሔር የሆነ ሃይማኖት አይደለም፡፡ መሠረቱም ጥላቻና ትዕቢት ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር የሌለበት ዓለም ስለሆነ የሁከት ዓለም ነው፡፡ ሙስሊሞች የውጪ ጠላት ሲመጣባቸው ተባብረው የጋራ ጠላታቸውን ለመዋጋት ይሞክራሉ፡፡ የውጪው አየር ሰላም ሲሆንም ደግሞ ሥራ አይፈቱም፤ እርስ በርሳቸው ይዋጋሉ፡፡ የእስልምናን የመጀመርያዎቹን ዘመናት ስንመለከት መሪዎቹ እርስ በርሳቸው በመገዳደል ነበር ሥልጣን ሲነጣጠቁ የነበሩት፡፡ ከመሐመድ ጋር የነበሩት የመሐመድ ወዳጆች ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ በመካከላቸው የነበረው አንድነት ተናግቶ ነበር፡፡ ዑመር በጠላቶቻቸው ተገደሉ፡፡ ከዑመር በኋላ ስልጣን የተረከቡት ኡሥማንም ተገደሉ፡፡ ሦስተኛው ኸሊፋ አሊም እንደዚሁ ተገደሉ፡፡ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በሺኣና በሱኒ መካከል ለተፈጠረው የከረረ ክፍፍልና ጥላቻ መንገድ ጠረገ፡፡ የአሊ ልጅ ሁሴንም ተገደለ፡፡ ይህም ክፍፍሉን እስከ ወድያኛው አፀናው፡፡ ስለዚህ እስልምና መሠረቱ እንዲህ ከሆነ ሙስሊሞች ከሌላው ወገን ጋርም ሆነ እርስ በርሳቸው ተቻችለው ለመኖር መቸገራቸው ሊያስገርመን አይገባም፡፡

እነዚህ ሰዎች ሙስሊሞችን ለምን ይገድላሉ ለሚለው ጥያቄ ሊጠቀስ የሚችል አራተኛው ምክንያት እስልምና በሚከተለው ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እስልምና “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” ዓይነት ፍልስፍናን የሚከተል ሃይማኖት ነው፡፡ ይህም ማለት “ውጤቱ አካሄድህን ያፀድቃል (The end justifies the means)” በማለት ያምናል ማለት ነው፡፡ ሙስሊሞች የሚያደርጉት ነገር መልካም ውጤትን የሚያስገኝና እስልምናን የሚጠቅም ከሆነ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ሙስሊም ማሕበረሰቦችን ማዋከብ በረጅም ጊዜ እስላማዊ ዕቅድ ጠቃሚ የሆነን ውጤት የሚያስገኝ ከሆነ ያደርጉታል፡፡ አይ ኤስና አልቃኢዳን የመሳሰሉት የሽብር አንጃዎች ሙስሊሞችን ማወክና አስጨንቆ ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ በሁለት መልኩ እስልምናን የሚጠቅም እንደሆነ ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ የመጀመርያው ለክርስቲያኖች ከለላን የሚሰጡ መንግሥታዊ ተቋማትንና ማህበረሰባዊ አደረጃጀቶችን በማፈራረስ አካባቢውን ከክርስቲያኖች ማፅዳት ማስቻሉ ነው፡፡ ይህም ደግሞ በተሳካ ሁኔታ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ሙስሊሞች በብዛት መካከለኛውን ምስራቅ ለቀው እንዲወጡ በማድረግ ሙስሊም ወዳልሆኑ አገራት ተሰደው እንዲሰፍሩና በስብከትና በጦርነት ማግኘት ያልተቻለውን ውጤት በዚህ መልኩ ለማግኘት የተጠነሰሰ ሤራ የመኖሩ ሁኔታ ከፍተኛ ነው፡፡ በነዳጅ ኃብት የበለፀጉት አረብ አገራት ሙስሊም ወገኖቻቸው ሲሠቃዩ አለማስጠለላቸው ይህ ጉዳይ ከጥርጣሬም በላይ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ስደት እስልምና ከሚስፋፋባቸው መንገዶች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡[6] በአሁኑ ወቅት ከሦርያና ከሊብያ የሚጎርፉት ሙስሊም ስደተኞች የአውሮፓን ወደቦች እያጨናነቁ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ስደተኞች የእግር ማሳረፍያ ቦታ ካገኙ በኋላ እስላማዊ የሆነን ማሕበረሰብ ይመሠርታሉ፡፡ እስላማዊውን ተልዕኮ በሚገባ መፈፀም ይችሉ ዘንድ የሚያስተምሯቸውና የሚያደራጇቸው ለዚሁ ዓላማ የተሰለፉ ስልጡኖች ተዘጋጅተው ስለሚጠብቋቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፅዕኖን ማሳረፍ ወደሚችሉ ማሕበረሰቦች ያድጋሉ፡፡ እንዲሁ ከላይ ሲታይ ሙስሊሙን ማሕበረሰብ የሚጎዳ የሚመስለው ሁከትና ስደት በዚህ መልኩ የእስልምናን የረጅም ጊዜ ዕቅድ ለማሳካት መንገድ ከፋች ይሆናል ማለት ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል!

በኃይሉ ሚዴቅሳና መሰሎቹ ባላጠናችሁትና በማታውቁት ጉዳይ ገብታችሁ ሕዝባችንን በማዘናጋት የአክራሪ እስልምና ሰለባ እንዲሆን ከምታደርጉት በዕውቀታችሁና በሙያችሁ ብቻ ብታገለግሉ መልካም ነው፡፡


[1] https://fas.net/irp/threat/nctc2011.pdf

[2] https://www.bbc.com/news/magazine-30883058

[3] የጥናቱን ገፅ 14 ይመልከቱ፡፡

[4] በቪድዮ የተደገፈ ሙሉ ንግግራቸውን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል፡- http://www.raymondibrahim.com//from-the-arab-world/egypts-sisi-islamic-thinking-is-antagonizing-the-entire-world/

[5] Sunan Abu Dawud: 2787

[6] በእስልምና መስፋፋት ውስጥ ስደት ምን ዓይነት ሚና እንደሚጫወት ለማወቅ “Al-Hijra, Islamic Doctrine of Migration, Accepting Freedom or Imposing Islam” በሚል ርዕስ በዶ/ር ሳም ሶሎሞንና በኤልያስ አልመቅዲሲ የተጻፈውን ዓይን ከፋች መጽሐፍ አግኝታችሁ ታነቡ ዘንድ አበረታታችኋለሁ፡፡


እስልምናና ሽብርተኝነት