የሰው ልጅ የዕድሜ ገደብ ስንት ነው?
ጥያቄው፡-
«እግዚአብሔርም። መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ።» (ዘፍ 6:3) ይህ አንቀጽ የሰው ልጅ የዕድሜ ገደብ 120 ዓመት እንደሆነ ይነግረናል። በሌላ አንቀጽ ደግሞ ከመቶ ሀያ አመት እድሜ በላይ የኖሩ ሰዎችን መልሶ ይጠቅስልናል። ለአብነትም፡- «ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ። አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ቃይንምንም ወለደ። አርፋክስድም ቃይንምን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሳላንም ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን ከወለደ በኋላ ሶስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።» (ዘፍ 11:11-12)
መልስ፦
እግዚአብሔር በሰዎች ላይ መንፈሱ እንዳይኖር ከወሰነ በኋላ እስከ ጥፋት ውሃ ድረስ 120 ዓመት ብቻ ዕድሜ እንዲኖረው ገልጿል። ይሄ ደግሞ የሰው ልጅን ዕድሜ ገደብ ይገልጻል። ነገር ግን በሌላ ቦታ ደግሞ በዘፍጥረት 6፥8 ላይ ኖኅ የተባለ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ እርሱና ቤተሰቡ መርከብ ከተረፉ በኋላ 11፥12-16 ሴም አርፋክስድን ወለደ፤ እርሱም ወለደ ይለናል ከወለደ በኋላ 500 ዓመት እንደኖረ ይነግረናል። ሌሎችም ልጆች እንደወለደ ከዛም ብዙ ዓመት እንደኖረ ይናገራል። ታዲያ 120 ዓመት የተባለው እዚህ ጋር ይጋጫልን? የሚለው በአጭሩ ሲመለስ፦ በዘፍጥረት 6፥3 ላይ የሥጋ ለባሽ ፍፃሜው ረጅም ሳይሆን 120 ዕድሜ ብቻ እንዲሆን የወሰነው። ይህም ከጥፋት ውሃ በፊት ላለው ህዝብ ነው እንጂ ከዚያ በኋላ ለተነሳው ለኖህና ከኖህ ቤተሰብ ለተገኙት ይሄ ቅጣት አይመለከታቸውም ማለት ነው። ህዝቡ አመፁ ተቀጡ፥ እግዚአብሔርም ማለ በቁጣ ውሃ እንደማያጠፋ። ስለዚህ በጥቅሶቹ ላይ ግጭት የለም አለ ከተባለ ከጥፋት ውሃ በፊት እና ከጥፋት ውሃ በኋላ ያለውን ታሪክ ማንበብ ይኖርብናል ማለት ነው።
