በፊየል የተበሉ የቁርአን ክፍሎችን በተመለከተ በወንድም ዳንኤልና በኡስታዝ የሕያ መካከል የተደረገ ውይይት
ተከታዩ ውይይት ጁን 2016 በፌስቡክ ገጻችን ላይ በወንድም ዳንኤልና የሕያ ኢብኑ ኑህ በተባለ ኡስታዝ መካከል የተደረገ ሲሆን ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው እዚህ አምጥተነዋል፡፡ ውይይቱ በፊየል የተበሉ የቁርአን አናቅፅን በተመለከተ የተደረገ ነው፡፡
አላህ ቁርአኑን ለምን ከፍየል መጠበቅ ተሳነው?
በተከታዩ እስላማዊ ምንጭ መሰረት በዝሙት የተያዙ ሴቶችን ስለ መውገርና ጎልማሳ ወንዶችን ጡት ስለ ማጥባት የሚናገሩ አንቀጾችን አላህ ለመሐመድ “ገልጦላቸው” ነበር ነገር ግን መሐመድ በሞቱበት ዕለት ሚስቶቻቸውና ወዳጆቻቸው እየተዋከቡ ሳሉ አንዲት ፍየል/ በግ ወደ አይሻ ቤት ሰተት ብላ በመግባት አንቀፆቹ የተጻፉበትን ወረቀት በላችው (ካፊር ፍየል!)። ከዚህም የተነሳ ቁርአን በአንድ ጥራዝ ሲሰበሰብ እነዚህ አንቀፆች ሳይካተቱ ቀሩ።
It was narrated that ‘Aishah said: “The Verse of stoning and of breastfeeding an adult ten times was revealed, and the paper was with me under my pillow. When the Messenger of Allah died, we were preoccupied with his death, and a tame sheep came in and ate it.”
Sunan Ibn Majah 3:9:1944
- Yahya Ibnu Nuhe እሽ ወገኔ ከታች ዘርዘር አድርጌ ምላሹን እሰጥሀለው፡፡ መልካም ንባብ፡፡
Yahya Ibnu Nuhe በፍየል የተበላ ቁርአን አለን?
ክፍል ሁለት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
መግቢያ
ሱነን ኢብን ማጃህ መጽሃፍ 9 ሃዲስ 2020
عَنْ عَائِشَةَ، . وَعَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ الْقَاسِمِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ لَقَدْ نَزَلَتْ آيَةُ الرَّجْمِ وَرَضَاعَةُ الْكَبِيرِ عَشْرًا وَلَقَدْ كَانَ فِي صَحِيفَةٍ تَحْتَ سَرِيرِي فَلَمَّا مَاتَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ وَتَشَاغَلْنَا بِمَوْتِهِ دَخَلَ دَاجِنٌ فَأَكَلَهَا
አይሻ እንደተረከችው፦ ስለ መውገር እና አስር ማጥባት ጥቅስ ወርዶ ነበር፣ በአላህ መልእክተኛ ሞት ጊዜ ውጥረት ላይ በመሆናችን ምክንያት ለማዳ የሆነች ፍየል እቤት ገብታ ያንን ወረቀት በላችው።
ፍየል በላቸው የተባለው የውግራት ጥቅስ ከአስር ጥቢ ጥቅስ ጋር ወوَ ‘’እና‘’በሚል ሃርፉል ዓጥፍ ማለትም አያያዥ መስተጻምር“copulative conjunction‘’ የተያያዘ ስለሆነ አስር የጥቢ ጥቅስ ሃዲስ ላይ ከሆነ የውግራትም ጥቅሱ ሃዲስ ላይ ነው ያለው፣ ይህን ሙግት ይዘን የጥቢ ጥቅስ ወደተባለበት ጥቅስ እንሂድ፦
ነጥብ ሁለት
ጥቢ
በቁርአን ላይ ስለ ጥቢ የሚናገሩ ሶስት አናቅጽ አሉ፣ እነርሱም፦
2:233 እናቶችም ልጆቻቸውን ሙሉ የኾኑን ሁለት ዓመታት ያጥቡ፡፡ ይህም ማጥባትን መሙላት ለሻ ሰው ነው፡፡
46:15 ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው በችግርም ወለደችው፥ *እርግዝናው* حَمْلُهُ እና ከጡት መለያውም ሠላሳ ወር ነው፤
31:14 ሰውንም በወላጆቹ በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው፤ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፤ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት *ውስጥ*فِي ነው፤
ነገር ግን ሶስቱም ስለ አስር ጥቢ የሚያወሩት ምንም ነገር የለም፣ ሚችነሪዎች አስር የጥቢ ጥቅስ ቁርአን ላይ ወርዶ ከነበረ የት ገባ? አላህ አውርጄ እጠብቀዋለው ያለውን ቁርአን እንዴት ፍየል በላቸው? ብለው ጥያቄ አቀረቡልኝ፣ እኔም ጥያቄያቸው ይዤ ወደ ኡስታዜ ወደ ሼህ ሙሃመድ ሃመዲን አመራው፣ እሳቸው አላህ ይጠብቃቸው ቁርአን ውስጥ አስር የጥቢ ጥቅስ ወርዶ ነበር የሚል የለም፣ ካለ ሃዲሱን አሳየኝ አሉኝ፣ እሺ ብዬ ከሚሽነሪዎች የለቀምቁትን ከነብጉሩ ላሳያቸው ስል በቃላቸው ያውቁት ነበርና በኦርጅኑ አርቢኛው እንዲህ አስቀመጡልኝ፦
ኢማሙል ሙስሊም መጽሃፍ 8 ቁጥር 3421:
حَدَّثَنَا يَحْيَى بْنُ يَحْيَى، قَالَ قَرَأْتُ عَلَى مَالِكٍ عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي بَكْرٍ، عَنْ عَمْرَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّهَا قَالَتْ كَانَ فِيمَا أُنْزِلَ مِنَ الْقُرْآنِ عَشْرُ رَضَعَاتٍ مَعْلُومَاتٍ يُحَرِّمْنَ . ثُمَّ نُسِخْنَ بِخَمْسٍ مَعْلُومَاتٍ فَتُوُفِّيَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهُنَّ فِيمَا يُقْرَأُ مِنَ الْقُرْآنِ .
አይሻ እንደተረከችው ከቁርአን *ጋር* فِيمَا አስር ግልጽ ጥቢ ጋብቻን ህገወጥ ማድረግ ወርዶ ነበር፣ ከዚያም በአምስት ጥቢ ተሻረ፣ የአላህ መልእክተኛ ሲሞቱ ከቁርአን *ጋር* فِيمَا ነበረ።
ችግሩን አሁን ተረዳሁት፣ ሃዲስ ላይ ያለው ቃል ከቁርአን ጋር እንጂ ቁርአን ውስጥ ወርዶ ነበር አይልም፣ ፊማ فِيمَا ጋር*with* እንጂ ፊ فِي ውስጥ*in* አይደለም፣ ነጥቡ ይህ ነው፣ ሃዲሰል ነበውይ ሆነ ሃዲሰል ቁድስይ ከቁርአን ጋር የወረዱ እንጂ ቁርአን አይደሉም፣ አስር የማጥባት ጥቅስ ከቁርአን ጋር ወርዶ በአምስት ጥቢ የተሻረ ነው፣ ነቢያችን ሃዲስ ላይ የሚመጡትን ህጎች በሌላ ሃዲስ ይሽሩት ነበር፦
ኢማሙል ሙስሊም መጽሃፍ 3 ቁጥር 675:
حَدَّثَنَا عُبَيْدُ اللَّهِ بْنُ مُعَاذٍ الْعَنْبَرِيُّ، حَدَّثَنَا الْمُعْتَمِرُ، حَدَّثَنَا أَبِي، حَدَّثَنَا أَبُو الْعَلاَءِ بْنُ الشِّخِّيرِ، قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَنْسَخُ حَدِيثُهُ بَعْضُهُ بَعْضًا كَمَا يَنْسَخُ الْقُرْآنُ بَعْضُهُ بَعْضًا
ቁርአን በሌላ አንቀጽ እንደሚሻር ሁሉ የአላህ መልእክተኛም ትዕዛዛቸውን በሌላ ትዕዛዝ ይሽሩ ነበር።
መደምደሚያ
ስለዚህ ፍየል በላችው የተባለው የውግራትና የአስር ጥቢ ቃላት ከመነሻው ደይፍ ቢሆንም ሙግቱን ለማጥበብ እንቀበለው ቢባል እንኳን የሃዲስ ክፍል እንጂ የቁርአን ክፍል አይደለም፣ ከዚያም ባሻገር ፍየሏ የበላችው ወረቀቱን እንጂ የሰሃባዎችን ቀልብ አይደለም፣ ቁርአን የአላህ ቃል ነው፣ የምናመልከው አላህ ደግሞ ቃሉ የመጨረሻ ወህይ ስለሆነ ይጠብቀዋል፣ የሰው ልጅ ቁርአንን መሰረዝና መደለዝ፣ መጨመርና መቀነስ፣ ማረምና ማስተካከል አይችልም፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
ወሰላሙ አለይኩም
- Yahya Ibnu Nuhe ተጨማሪ ከዚህ በፊት የተመለሰ ምላሽ ደግሞ ከታች አስቀምጥልሀለው፡፡
Yahya Ibnu Nuhe በወንድም አቡ ዩስራ
–
በሚሽነሪዎችና የነሱን ቅጥፈት እንደወረደ መቀበል እና ማሳራጨት እንደ እዉቀት የሚመስላቸዉ የሀገራችን አንዳንድ ክረስቲያን
ወገኖቻችን በተደጋጋሚ ከሚያነሱት ጥያቄዎች አንዱ ( ስለ ረጅም በተመለከተ ብቻ በሌላ ክፍል
ደግሞ ስለ ጥቢ እንመለስበታለን) የሆኑዉን ለዛሬ
በአላህ ፍቃድ ለማየት እንሞክራለን፡፡
ይኸዉም ‹ቁርአን › አልተጠበቀም የተወሰነ የቁርአን ክፍል በፍየል/በግ ተብልቷል እያሉ በተደጋጋሚ በተለያዩ የፌስ ቡክ ግሩፖች ላይ በጥያቄ መልክ ይቀርባል፡ ችግሩ ሁሉም የግንዛቤ
እጥረት እንጂ በነሱ ቤት እኛ ሙስሊሞቹ ያላወቅንዉ ነገር ወይንም የደበቀንዉ ነገር ያለ ለማስመሰል ይጥራሉ፡፡
–
በተደጋጋሚ የሚቀርበዉ ሀዲስ ሱነን ኢብን ማጃህ ነዉ እንደሚከተለዉ ይነበባል፡-
.
It was narrated that ‘Aishah said: “The Verse of stoning and of breastfeeding an adult ten times was revealed, and the paper was with me under my pillow. When the
Messenger of Allah died, we were preoccupied with his death, and a tame sheep came in and ate it.”
Sunan Ibn Majah Vol. 3, Book 9, Hadith 1944
–
በዚህ ሀዲስ መሰረት አኢሻ(ረአ) ከትራስ ስር ስለ ጥቢ እና ስለ ረጅም ( በድንጋይ ወግሮ ስለመግደል) የሚናገር ‹አንቀፅ› እንደነበረ እና
በነብዩ(ሰአወ) ሞት ምክንያት ቢዚ በመሆናቸዉ ምክንያት ለማዳ የሆነች በግ( ፍየል)እቤት ገብታ ያንን ወረቀት እንደበላችዉ እራስዋ አኢሻ(ረአ) ዘግባለች፡፡
እናም በአሁን ግዜ በቁርአን ዉስጥ ‹ረጅም› በተመለከተ በቀጥታ የተጠቀሰ ነገር የሌለዉ ይህች ፍየል ስለበላችዉ ነዉ እናም ስለዚህ ቁርአን
ተበርዟል የሚል ድምዳሜ ላይ ይደረሳሉ፡፡
–
አንደኛ፡- ይህ ሀዲስ በምንም መልኩ ስለ እነዚህ ጉዳዮች ( ስለ ጥቢ እና ረጅም) የሚያወራ ብቸኛ
ወረቀት ነዉ አይልም – ወይንም በሌላ አነጋገር ሌሎች ሰዎችም ጋር ይህ አንቀፅ አለመኖሩን አያመላክትም- ይህ ሀዲስ የሚለዉ አኢሻ ዘንድ
ስለነበረዉ ‹ወረቀት› #ብቻና #ብቻ ነዉ የሚያወራዉ እሱን በፍየል ስለመበላቱ ብቻ፡፡
–
ሁለተኛ፡- በሌላ ሀዲስ ዘገባ ኡመር(ረአ) ስለ በድንጋይ ተወግሮ ስለመገደል የሚናገረዉን አንቀፅ የ‹ቁርአን አካል› ተደረጎ እንዲቀመጥ
በመመኘኘት የነብዩን(ሰአወ) ፈቃድ ሲጠይቅ ነብዩ(ሰአወ) ከልክለዉታል፡ ለምን ቢባል- መጀመርያም የቁርአን አካል ሆኖ እንዲቆይ
አልነበረምና ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ ንባቡ ወይንም ቴክሰቱ የተሻረ ( በአሁን ባለዉ ቁርአን ላይ የማይገኝ ) ነገር ግን ህጉ የሚሰራ( በሀዲስ
ተጠብቆ የቆየ) አይነት ነዉ።
( Abrogation of
the recitation of the text, but not its legal ruling) ‘O Messenger of Allah,
let the verse about stoning be
written for me.’ He (the Prophet) said, ‘I can’t do this.’” (Sunan Al-
Kubra Baihiqi 8/211 & Sunan Al-Kubra
Nasai Hadith 7148. Albani (in Sahiha
6/412) said Baihiqi pointed to its authenticity)
–
ሶስተኛ፡- It is reported in a narration from Kathir bin Salt that: Zaid (b.Thabit) said: ‘I heard the Messenger
of Allah say, ‘When a married man or woman commit adultery stone them
both (to death)’, (hearing this) Amr said, ‘When this was revealed I came
to Prophet and asked if I could write it, he (the Prophet) disliked
it.’ (Mustadrik Al-Hakim, Hadith 8184.
Hakim called it Sahih. al-Dhahbi agreed with him) ከዚህ ሀዲስ የምንረዳዉ ደግሞ አሁንም ነብዩ(ሰአወ) እንዲፃፍ
አለመፍቀዳቸዉን ነዉ፡፡
–
አራተኛ፡- የነብዩ(ሰአወ) ባልደረቦች ይህንን ሀዲስ ያዉቁት እና በአእምሮዋቸዉ ይዘዉት እንደነበር
በተለያዩ ሀዲሶች ተናግረዋል ምሳሌ
‹‹……….among what Allah revealed, was the Verse of the Rajam (the stoning of married person (male &
female) who commits illegal sexual intercourse, and we did recite this Verse and #understood and #memorized it……..>>
ታዲያ ይህች ፍየል የነዚህንም ሰዎች አእምሮ አብራ አልበላች! አንደ
ሰዉ ( አኢሻ (ረአ) ) ጋር የነበረ ነገር ፍየል በላዉ ማለት ብቸኛ መረጃ እሱን ነበረ ማለትን አያመላክተም፡፡
–
ማጠቃሊያ፡- በፍየል ተበላ ማለት ብቸኛ ይህን የሚመለከት ኮፒ አኢሻ(ረአ) ጋር ብቻ ነዉ ማለትን አያመለክትም ሌሎችም ሰዎች ጋር ይኖራልና እንዲሁም ሰሃቦች ይህ ነገር በቀላቸዉ
ይዘዉት እንደነበር ተናግረዋል ፤ ስለዚህ አኢሻ (ረአ) ጋር ያለዉ እንኩዋን ቢጠፋ ሌሎች ጋር በቀላሉ ይገኛል፡፡ወሏሁ አእለም!!
https://ethioislamic.wordpress.com/…/ቁርአንን-አስመልክቶ-ለተነሱ…/
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe መጀመርያ በለጠፍከው ጽሑፍ ውስጥ የጥቢ ሐዲስ በፍየል የመበላቱ ታሪክ “ዶኢፍ” ነው የተባለው ቅጥፈት ነው፡፡ የሱናን ኢብን ማጃህ ጥራዝ ካለህ ቦታውን አውጥተህ ተመልከት፡፡ በሐዲስ ሊቃውንት የተሰጠው ደረጃ “ሐሰን” የሚል እንጂ “ዶኢፍ” የሚል አይደለም፡፡ ሌላው ሐዲሳትን ወደ እንግሊዘኛ የተረጎሙት ሙስሊም ሊቃውንት ሁሉ ይህ የውግረት አንቀፅ የቁርአን አካል እንደነበር በሚያመለክት ሁኔታ ተርጉመውታል፡፡ ስለ ሆነም ቫሂድ (?) ከአንድ ግለሰብ ሰማሁት ብሎ ከሰጠው ትርጓሜ ይልቅ ኦፊሴላዊውን ትርጉም እመርጣለሁ፡፡ የሐዲሳቱ አውድም ኦፊሴላዊውን ትርጓሜ የሚያፀና በመሆኑ የግለሰቡን ትርጓሜ መቀበል አግባብ አይመስለኝም፡፡
የአቡ ዩስራን መልስ እስኪ እንመዝን፡-
/////አንደኛ፡- ይህ ሀዲስ በምንም መልኩ ስለ እነዚህ ጉዳዮች ( ስለ ጥቢ እና ረጅም) የሚያወራ ብቸኛ ወረቀት ነዉ አይልም – ወይንም በሌላ አነጋገር ሌሎች ሰዎችም ጋር ይህ አንቀፅ አለመኖሩን አያመላክትም- ይህ ሀዲስ የሚለዉ አኢሻ ዘንድ ስለነበረዉ ‹ወረቀት› #ብቻና #ብቻ ነዉ የሚያወራዉ እሱን በፍየል ስለመበላቱ ብቻ፡፡/////
#መልስ፡- ኸሊፋ ኡመር ይህ አንቀፅ የቁርአን አካል እንደሆነ ያምኑ የነበረ ሲሆን ቁርአን ሲሰበሰብ አብሮ እንዲካተት ወደ ዘይድ አምጥተውት ነበር፡፡ ነገር ግን ዘይድ ከኡመር ውጪ ሌላ ምስክር የለም በሚል እንዳልተቀበለው አስ-ሱዩጢ ዘግበዋል (Al Suyuti. Al Itqan fi Ulum al-Qur’an; p. 385; Cited in: Qur’an, the Dillema; Vol. 1, p. 52)፡፡ በነቢዩ ዘመን በፍየል ከተበላው ሌላ ኮፒ ቢኖር ኖሮ ዘይድ ባገኘው ነበር፡፡ ኡመርም ማመሳከርያ ማቅረብ በቻሉ ነበር፡፡ ሳሂህ አል-ቡኻሪ ውስጥ እንደተዘገበው የሱራ አል-አሕዛብ 23ኛ አንቀፅ የተጻፈበት ቁስ በአንድ የነቢዩ ወዳጅ ዘንድ ብቻ ነበር የተገኘው፡፡ ይህ የሚያመለክተው በአንድ ቁስ ላይ ብቻ የተጻፉ አናቅፅ መኖራቸውን ነው፡፡ በፊየል የተበሉትም አናቅፅ ከዚያ ቁስ ውጪ በሌላ ላይ እንደተጻፉ ለመናገር የሚያስደፍር ማስረጃ የለም፡፡
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe //////ሁለተኛ፡- በሌላ ሀዲስ ዘገባ ኡመር(ረአ) ስለ በድንጋይ ተወግሮ ስለመገደል የሚናገረዉን አንቀፅ የ‹ቁርአን አካል› ተደረጎ እንዲቀመጥ በመመኘኘት የነብዩን(ሰአወ) ፈቃድ ሲጠይቅ ነብዩ(ሰአወ) ከልክለዉታል፡ ለምን ቢባል- መጀመርያም የቁርአን አካል ሆኖ እንዲቆይ አልነበረምና ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ ንባቡ ወይንም ቴክሰቱ የተሻረ ( በአሁን ባለዉ ቁርአን ላይ የማይገኝ ) ነገር ግን ህጉ የሚሰራ( በሀዲስ ተጠብቆ የቆየ) አይነት ነዉ።//////
#መልስ፡- ይህ እስላማዊ ምንጮች እርስ በርሳቸው እንደሚጣረሱ ከማመልከት የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ ከሳሂህ ሲታ መካከል አንዱ የሆነው ኢብን ማጃህ ነቢዩ በሕይወት እያሉ ተጽፎ በገዛ ቤታቸው ተቀምጦ ነበር ሲለን የጠቀስከስካቸው “ሐዲሳት” ደግሞ ነቢዩ እንዲጻፉ አልፈቀዱም ይሉናል፡፡ የቱ ነው ትክክል? (በርግጥ የጠቀስካቸው ሐዲሳት ከስድስቱ ስብስቦች ውጪ ስለሆኑ ምን ያህል እውነተኛና ተዓማኒ እንደሆኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡) ሰዎች ለመጻፍ ሲጠይቁ ነቢዩ አለመውደዳቸው የቁርአን አካል ሆኖ እንዲቆይ ስላልፈለጉ እንደሆነ “በሐዲሳቱ” ውስጥ አልተነገረም፡፡ ምናልባት የቁርአን ጽሑፎች ከርሳቸው ቁጥጥር ውጪ በግለሰቦች እጅ እንዲቀመጥ ስላልፈለጉ ይሆናል፡፡ የሰዎቹም አጠያየቅ እንደርሱ ይመስላል፡- ‘O Messenger of Allah,
let the verse about stoning be written #for_me.’//////አራተኛ፡- የነብዩ(ሰአወ) ባልደረቦች ይህንን ሀዲስ ያዉቁት እና በአእምሮዋቸዉ ይዘዉት እንደነበር በተለያዩ ሀዲሶች ተናግረዋል ምሳሌ ‹‹among what Allah revealed, was the Verse of the Rajam (the stoning of married person (male & female) who commits illegal sexual intercourse, and we did recite this Verse and #understood and #memorized it›› ታዲያ ይህች ፍየል የነዚህንም ሰዎች አእምሮ አብራ አልበላች! አንደ ሰዉ ( አኢሻ (ረአ) ) ጋር የነበረ ነገር ፍየል በላዉ ማለት ብቸኛ መረጃ እሱን ነበረ ማለትን አያመላክተም፡፡/////
#መልስ፡- ይህንን አንቀፅ የተናገሩት ኡመር ነበሩ፡፡ ይህ አባባላቸው ቀደም ሲል አጥንተውት የነበሩ ሰዎች ላለመርሳታቸው ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡ ከእሳቸው ውጪ ሌላ ምስክር ስላልነበረ ዘይድ አለመቀበሉን አስ-ሱዩጢ ጽፈዋል፡፡ ይህ የሚያመለክተው በሌሎች ሰዎች ዘንድ መረሳቱን ነው፡፡ የቁርአን አናቅፅን መርሳት ለነቢዩ ባልደረቦች አዲስ አይደለም፡፡ እንዲያውም ረጃጅም የቁርአን ምዕራፎች ተረስተው መቅረታቸውን የሚያመለክቱ ዘገባዎች በሳሂህ ሐዲሳት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ አንድ ምሳሌ ልስጥህ፡-
“አቡ ሀርብ ቢን አቡ አል-አስዋድ አባታቸውን ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት አቡ ሙሳ አል-ሸዐሪ የበስራ ቁርአን አነብናቢዎችን አስጠሯቸው፡፡ ቁጥራቸው ወደ ሦስት መቶ የሚሆኑቱ መጡ፡፡ ቁርአንን አነበነቡት፤ እርሳቸውም እንዲህ አሏቸው ‹‹እናንተ አነብናቢዎች እንደመሆናችሁ መጠን ከበስራ ነዋሪዎች ሁሉ ምርጦች ናችሁ፡፡ ማነብነባችሁን ቀጥሉ፡፡ (ነገር ግን) ለረጅም ጊዜ ማነብነባችሁ ከናንተ በፊት የነበሩትን ሰዎች ልቦች እንዳደነደነ ልቦቻችሁን እንዳያደነድን ተጠንቀቁ፡፡ በርዝመትና በጥንካሬ #ከሱራ_በረዓት ጋር የሚነፃፀር ሱራ እናነበንብ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተከታዩ ውጪ #የተቀረውን_ረስቼዋለሁ፡- ‹‹የአደም ልጅ በኃብት የተሞሉ ሁለት ሸለቆዎች ቢኖሩት ሦስተኛውን ይመኛል፡፡ ከአፈር ውጪ የአደምን ልጅ ሆድ የሚሞላ ምንም ነገር የለም፡፡›› #ከሱረት_ሙሰቢሃት መካከል ከአንዱ ጋር የሚመሳሰል ሌላ ሱራም እናነበንብ ነበር ነገር ግን ከተከታዩ ውጪ #የተቀረውን_ረስቼዋለሁ፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ የማትፈፅሙትን ነገር ስለምን ትናገራላችሁ? እርሱም በናንተ ላይ ምስክር እንዲሆንባችሁ በአንገቶቻችሁ ላይ ተጽፏል፤ በዕለተ ትንሣኤም ከእርሱ ትጠየቃላችሁ፡፡››” (Sahih Muslim 5:2286; Jalal al Din `Abdul Rahman b. abi Bakr al Suyuti. Al Itqan fi `ulum al Qur’an; Halabi, Cairo, 1935/1354, part 2, p. 25)
#ማጠቃለያ፡- ጥቅሱ በፊየል፣ በግመል ወይም በውኀ ተበልቶ ቢጠፋ ቁምነገሩ ያለው በአጠፋፉ ሁኔታ ላይ ሳይሆን በመጥፋቱ ላይ በመሆኑ የፊየሊቷ ታሪክ እውነት አይደለም ቢባል እንኳ ከቁርአን መሰረዙ በሳሂህ ሐዲሳት እስከተረጋገጠ ድረስ ቁርአን ሐሰተኛ ሰነድ መሆኑ ሊታበል የሚችል አይደለም፡፡View 1 more reply
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net //////// ምልክት ውስጥ የሚገኘው የኔ ሳይሆን Yahya ያቀረበው ሙግት ነው። የኔ #መልስ ከሚለው በኋላ የተቀመጠው ነው።
- Yahya Ibnu Nuhe እሽ ወገናችን መልሶቹን ከተመለከትክ በኋላ ማስተባበያ ለመስጠት ያደረግከውን ጥረት አደንቃለሁ፡፡ መልካም ነው ነጥቦቹን አይተን እውነት ለማስተባበየነት ይመጥናሉ ወይንስ ዝም ከማለት ይሻላል በሚል የተሰጡ ናቸው የሚለውን ከዚህ በታች አንድ ባንድ እንፈትሻቸዋለን፡፡ ከመጀመሪያው የወንድም Wahid Umar Negash መልስ እንጀምር ስለጥቢ የሚያወራው የሱነን ኢብን ማጃህ ሀዲስ ደኢፍ ነው መባሉ ቅጥፈት ያልከው ገርሞኛል፡፡ እንዴው በደፈናው ካለማስረጃ ‹‹ሐሰን›› በሚል ደባብሰኽው አለፍክ፡፡ ደኢፍ መባሉ አንተ እንዳልከው ግለሰብ ያለው የግል አስተያየት ሳይሆን ኦፌሴላዊ ነው፡፡ ማስረጃውን ከታች ልስጥህ
–
የሀዲሱ ደረጃ
–
የሀዲሱን ደረጃ በምንመለከትበት ሰዓት ከዘጋቢ ሰንሰሎቶቹ አንዱ ሙሀመድ ኢብን ኢስሀቅ ዘገባውን ሲያስተላልፉ የተጠቀሙት ቃል ‹‹ዓን›› ይህ ከተለመደው አዘጋገብ ወጣ ያለ በመሆኑ በሀዲስ ጥናት መስክ አንኳር ዘርፍ የሆነውን ‹‹ተድሊስ›› (የሀዲስ ሰንሰለቱ መቋረጥ) ሳቢያ ሀዲሱ ደዒፍ ወይንም ደካማ ነው፡፡ ይህን ሀዲስ አስመልክቶ ዝርዝር በሆነ ትንታኔ ሸይኽ ሙሀመድ ጣቂ ኡስማኒ ‹‹ታክማል ፈትሁል ሙሂም›› በተሰኘ ድርሳናቸው ጥራዝ 1 ገጽ 69 ላይ አስቀምጠውታል፡፡ Yahya Ibnu Nuhe ቀጣይ የተመከትከው የወንድም Abu Yusra ጹሁፍ ነው፡፡ እስኪ በተራ እንዳሰው
–
አንደኛ ፡- በመጀመሪያው ነጥብ ዙሪያ ያነሳሀው ነጥብ ጭራሽ ከቀረበው ማስረጃ አንጻር ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ምክንያቱን ላስረዳህ!! ነጥቡ እያለ ያለው ይህ ሰነድ ብቸኛ የመረጃ ምንጭ ነበር የሚል ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡ የሚያወራውም ስለአኢሻ እንጅ ጥቅል አይደለም አንተ ደግሞ እያልክ ያለኸው ሌሎችም ጋ ለመኖሩ በቂ ማስረጃ የለም ነው፡፡ አርጊውመነትህን በሁለት መንገድ ውድቅ ማድረግ ይቻላል፡፡1- ብቸኛ የሰነድ ማስረጃ ነው ለሚለው አገላለጽ ምንም ማስረጃ የለህም ያንተም አርጉመንት የተንጠለጠለው ሌሎችም ጋ የለም በሚል እንጅ ራሱን ችሎ አይደለም በሚለው ነጥብ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ
2-ሌሎች ጋ እንደነበር ማስረጃ በመስጠት ብቻ መከራከሪያ ነጥብህ በቀላሉ ይፈርሳል፡፡ ተከተለኝ ጥቂቶችን ልስጥህ
ሀ) በሰሂህ ሱነነል ኩብራ አለ በይሀቂይ 8/211 እንዲሁም አንነሳኢይ ሀዲስ ቁጥር 7148 በተጨማሪም አልባኒ በሲሂህ የስብስብ ጥራዛቸው ውስጥ ጥራዝ 6/412 ላይ በተመሳሳይ እንደገለጹት በነዚህ አንቀጾች ዙሪያ ዘይድ ኢብን ሳቢትና መርዋን ቢን ሀኪም በሚገባ ያውቋቸውና ይወያዩባቸው አንደነበር ተጠቅሷል፡፡
ለ) በሙስተድረክ አል ሀኪም ሀዲስ ቁጥር 8184 ሰሂህ በሆነ ሀዲስ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት(ረ.ዐ) አንቀጹን በትክክል ከረሱል (ሰዐወ) እንደሰማው ገልጸዋል፡፡
Yahya Ibnu Nuhe ሁለተኛ ፡- ለሶስተኛው የሰጠኸው መልስ ስሜታዊነት የተቀላቀለበትና ምክንያታዊነት የራቀው ነው፡፡ ቀጥሎ የገለጽከው ‹‹ሰሂህ ሲታ›› አመለካከትህ ላይ ብዙ እርግጠኛ ያለሆኑ አንዳንድም ከግንዛቤ እጥረት ስህቶችን አይቻለሁ፡:፡ የመጀመሪያው እንዴው በደፈናው ከስድስቱ መጽሀፍት ውስጥ ኢብን ማጃህ አለ ብሎ መናገር ለኢስላማዊ ድረሳናት እንግዳ መሆንህን ያሣያል፡፡ በዚህ ዙሪያ አንዳንድ የሀዲስ ሊቃውንት ናቸው ኢማም ማሊክ ሙወጣዕ ቦታ ለስድስቶቹ ኢብነ ማጃህን የሚጠቀሙት እንጅ ጥቅል አይደለም ስንገልጽ ስፕሲፊክ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
በሁለተኛ የፈጸምከው ግን ገራሚ ስህተት ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ከስድስቶቹ የሀዲስ ጥራዝ ውስጥ አይገኝም የሚል አንደምታ ያለው ቃል ሰንዝረሀል፡፡ ይሄ ስድስቶችን ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ ስህተት ነው፡፡ ከላይ ከጠቀስኩት ውስጥ ነሳዒ ይገኛል ነሳኢ ደግሞ ከአብይ የሀዲስ ጥራዛት መካከል ነው፡፡ ስለዚህም በሀዲስ ውስጥ በሚገባ ተጠቅሷል፡፡
Yahya Ibnu Nuhe አራተኛ፡- በአራተኛ ደረጃ የተነሳው አንቀጹ በቃል ተሸምዶ እንደነበር ሲገለጽ ውስጣችን በፈጠረው ሀሳብ ‹‹ተረስቶ›› ሊሆን ይችላል ብሎ ካለምንም ማስረጃ መሞገት አስቂኝ ነው፡፡ ሙግቱ ካስፈለገም ይህው አንቀጽ ለመረሳቱ ማስረጃ ማቅረብ እንጅ እያወራን ያለንበት አንቀጽ ትቶ ተረሳ የሚል ሀሳብ እየፈለጉ ማስረጃ መጠገኛ መዳከር አይጠበቅብንም፡፡
ከተረሳ ይሄ አንቀጽ ተረስቷል ብሎ ማስረጃ ማቅረብ ነው፡፡ ሌሎችን አንቀጾች አስመልክቶ የራሳቸው ምክንያት ያላቸውና ውይይቱ ለብቻ የሚደረግባቸው ሲሆን ጥርጣሬው እውነት ይሆን ዘንድ ግን ማስረጃ የሚያስፈልገው ለርዕሳችን ነው፡፡
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe ከሱናን ኢብን ማጃህ ላይ የተጠቀሰው ሐዲስ “ደኢፍ” ነው ማለትህን በተመለከተ እንደርሱ አለመሆኑን ገልጬልህ የሐዲሱ ጥራዝ ካለህ ቦታውን አውጥተህ እንድትመለከት ነግሬህ ነበር፡፡ አንተ ግን መጽሐፉን ከማየት ይልቅ ከድረ-ገፅ ላይ ያገኘኸውን “ምላሽ” በግርድፉ ተርጉመህ አስቀምጠሃል፡፡ እኔንም ካለማስረጃ እንደተናገርኩ በማስመሰል በሀሰት ከሰኸኛል፡፡ ኦፊሴላዊው የሐዲስ ምደባ በመጽሐፉ ውስጥ ተቀምጦልሃል፡፡ ወዳጄ ድርቅናው ይቅርብህና መጽሐፉ በእጅህ ካለ ቦታውን ገልጠህ እየው፡፡ ከሌለህ ደግሞ የኢብን ማጃህ ሐዲስ ኦንላይን በነፃ ስለሚገኝ ድረ-ገፁን ጎብኘው፡፡ http://sunnah.com/urn/1262630 “ሐሰን” የሚል በግልፅ ተቀምጦልሃል፡፡ ደረቅ ክርክር አያዋጣህም፡፡
የኢብን ማጃህ ሐዲስ በአይሻ ዘንድ የነበረው ወረቀት ብቻ በፊየል መበላቱን እንጂ አንቀፁ በሌሎች ሰዎች እጅ አለመገኘቱን እንደማያመለክት አቡ ዩስራ ላቀረበው ሙግት ሁለት ምላሾችን ሰጥቻለሁ፡፡ የመጀመርያው፤ ኡመር አንቀፁ በቁርአን ውስጥ እንዲካተት ወደ ዘይድ ባመጡ ጊዜ ተጨማሪ ማስረጃ የለም በሚል ሰበብ ዘይድ አለመቀበሉና ኡመርም የጽሑፍ ማስረጃ አለማቅረባቸው ነው፡፡ አንቀፁ በሌላ ቁስ ላይ ተፅፎ ቢሆን ኖሮ ኡመር የጽሑፍ ማስረጃውን እንደ ምስክር በማቅረብ ባስረዱ ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ማድረግ አልቻሉም፡፡ ሁለተኛው ምላሽ ደግሞ በአንድ ቁስ ላይ ብቻ የተጻፉ የቁርአን አንቀፆች እንደነበሩ ማሳየት ሲሆን ይህም የአቡ ዩስራ ቅድመ ግንዛቤ ደካማ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ የሱራ አል-አሕዛብ ሃያ ሦስተኛ አንቀፅ የተጻፈበት ቁስ በአንድ ሰው እጅ ብቻ መገኘቱን በዋቢነት ጠቅሻለሁ፡፡ ስለዚህ ኡመር የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ ካልቻሉና በአንድ ቁስ ላይ ብቻ የተጻፉ አንቀፆች መኖራቸው ከተረጋገጠ በፊየል የተበላው አንቀፅ በሌላ ቁስ ላይ ተጽፎ መኖሩን ለመናገር የሚያበቃ ማስረጃ የለም ማለት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የሰጠኸው ምላሽ ፊየል ወዲህ ቁርአን ወዲያ ዓይነት ሆኖብኛል፡፡
የጠቀስካቸው ሁለቱ “ሐዲሶች” ግለሰቦች ሐዲሱን በጆሯቸው መስማታቸውንና በአፋቸው መወያየታቸውን እንጂ በአይሻ ዘንድ ከነበረው ቁስ ሌላ በተለየ ቁስ ላይ መስፈራቸውን የሚያረጋግጡ አይደሉም፡፡ እየተወያየን ያለነው ከአንድ በላይ በሆኑ ቁሶች ላይ ስለመስፈር አለመስፈሩ መስሎኝ!
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe ለሦስተኛው ነጥብ የሰጠሁትን መልስ በተመለከተ ስሜታዊ የሆንከው አንተ ነህ፡፡ እንዲህ ብለሃል፡-
////በዚህ ዙሪያ አንዳንድ የሀዲስ ሊቃውንት ናቸው ኢማም ማሊክ ሙወጣዕ ቦታ ለስድስቶቹ ኢብነ ማጃህን የሚጠቀሙት እንጅ ጥቅል አይደለም ስንገልጽ ስፕሲፊክ ማድረግ ይኖርብናል፡፡////
ኢብን ማጃህ ከስድስቱ ስብስቦች መካከል አንዱ መሆኑ በስፋት ተቀባይነት ያገኘ ስለመሆኑ በሐዲሱ ኦፊሴላዊ ድረ-ገፅ ላይ በግልፅ ሰፍሮልሃል፡፡ ይኸው አንብበው፡- “Sunan Ibn Majah is a collection of hadith compiled by Imam Muhammad bin Yazid Ibn Majah al-Qazvini (rahimahullah). #It_is_widely_considered_to_be_the_sixth of the six canonical collection of hadith (Kutub as-Sittah) of the Sunnah of the Prophet (ﷺ). It consists of 4341 ahadith in 37 books.” http://sunnah.com/ibnmajah
አንተ ግን አንዳንድ ሊቃውንት ብቻ እንደተቀበሉት ነው እየተናገርክ ያለኸው፡፡ ምናልባት ሐዲሱን ከስድስቱ መካከል በማይቆጥሩት አንዳንድ ሊቃውንት ላይ አንተ ተደምረህ ሚዛኑ ወደዚያ አጋድሎ እንደሆን አላውቅም፡፡ ከስድስቱ ስብስቦች መካከል አንዱ መሆኑ በስፋት ተቀባይነት ያገኘውን ሐዲስ በእርግጠኛነት መንፈስ መጥቀሴ ትክክል ካልሆነ ሐዲሱን ከስድስቱ መካከል የሚቆጥሩት ሙስሊም ሊቃውንትም ተሳስተዋል ማለት ነው! ስለዚህ ከዚህ አጠቃላይ ግንዛቤ በመነሳት እንጂ ሐዲሳትን በተመለከተ በሙስሊሞች መካከል ጭቅጭቅ መኖሩን ዘንግቼ አይደለም፡፡
እንዲህ ብለሃል፡- ////በሁለተኛ የፈጸምከው ግን ገራሚ ስህተት ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ከስድስቶቹ የሀዲስ ጥራዝ ውስጥ አይገኝም የሚል አንደምታ ያለው ቃል ሰንዝረሀል፡፡ ይሄ ስድስቶችን ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ ስህተት ነው፡፡ ከላይ ከጠቀስኩት ውስጥ ነሳዒ ይገኛል ነሳኢ ደግሞ ከአብይ የሀዲስ ጥራዛት መካከል ነው፡፡////
ነሳዒ መጠቀሱን ልብ ባለማለቴ እርሱን እንደ ስህተት ልትቆጥረው ትችላለህ፡፡ ነገር ግን የሐዲስ ዝርዝሮችን ከማወቅ አንድ ደረጃ ከፍ ብለን እየተወያየን መሆናችንን አትርሳ፡፡ እንደርሱ ባይሆን ኖሮ አንተም እንዲህ ጊዜህን ሰውተህ መልስ ለመስጠት ባልጣርክ ነበር፡፡ እንዲህ ያለውን ጥልቅ ርዕሰ ጉዳይ እየተወያየን ባለንበት ሁኔታ ኤለመንተሪ የሆነውን የሐዲስ ዝርዝር እንደማያውቅ ሰው ልትቆጥረኝ አይገባም፡፡ የነሳዒ ስድስቱም ቅፆች በእጄ ይገኛሉ፡፡ አንተ የጠቀስከውን ሐዲስ ለማግኘት መጻሕፍቱን ባገላብጥም የጠቀስከውን ሐዲስ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ አሁን በእጄ የያዝኩት የነሳዒ ሐዲስ የመጨረሻ ጥራዝ የሆነው ስድስተኛው ቅፅ 5761ኛ ሐዲስ ላይ ነው የሚዘጋው፡፡ አንተ የጠቀስከው ደግሞ ሐዲስ ቁጥር 7148 ነው፡፡ ከየት አመጣኸው? ይህ ሐዲስ መኖሩን በማስረጃ እንድታረጋግጥልኝ እፈልጋለሁ፡፡
አራተኛውን ነጥቤን በተሳሳተ መንገድ ነው የተረጎምከው፡፡ የተረሱ የቁርአን አንቀፆች መኖራቸውን የጠቀስኩት የተረሱትን እነዚያን አንቀፆች በተመለከተ መልስ እንድትሰጠኝ አይደለም፤ ነገር ግን የነቢዩ ባልደረቦች አንቀፁን በአእምሯቸው ሸምድደውት እንደነበር የሚገልፀውን ሐዲስ በመጥቀስ በጽሑፍ የሰፈረው አንቀፅ በፊየል መበላቱ አንቀፁ እንዲጠፋ አያደርግም የሚለውን የሙግት ሐሳብ ደካማነት ለማሳየት ብቻ ነው፡፡ ነጥቤ፡- ግለሰቦቹ በአንድ ወቅት ሸምድደውት ነበር ማለት ቁርአንን በማሰባሰብ ሂደት ወቅት ሊረሱት አይችሉም ማለት አይደለም የሚል ነው፡፡ ለዚህ ነው የነቢዩ ባልደረቦች ሌሎች የቁርአን ጥቅሶችን መርሳታቸውን የጠቀስኩልህ፡፡ ሌሎቹን ከረሱ ይኸኛውን ላለመርሳታቸው ዋስትና የለም፡፡ ኡመር በቁርአን ውስጥ እንዲካተት ለዘይድ ባሳሰቡት ጊዜ ሌላ ምስክር ያልተገኘውና ጥያቄያቸው ውድቅ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡Yahya Ibnu Nuhe እሽ ወገኔ ነጥቦችህን ተመልክቻቸዋለሁ ብዙዎቹ ከጅማሬው ጀምሮ የሚያተኩሩት በአርዕስቱ ዙሪያ ሳይሆን በሀዲሳት ዙሪያ አንስተህው በነበረውና ምላሽ በሰጡሁባቸው አጀንዳዎች ላይ ነው፡፡እውነት ለመናገር በርዕሱ ዙሪያ ምንም አላልክም ማለት ይቻለል፡፡ ያስቀመጥኩልህን ምላሾች ቢያንስ በነጥብ ታስተባብላለህ ብየ ጠብቄ ነበር፡፡ ነጥቦቸቹን ከመዳጋገም በዘለለ ምንም አዲስ ነገር አላመጣህም፡፡ ትንሽየ የተናገርካት ላይ አስተያየት ልስጥና ወደ ሀዲሶቹ ሀሳብህ እመጣለሁ፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ያቀረብከው ከዚህ በፊት ካነሳነው መወያያ ትንሽ ተንሸራተህ በቃል ያለውን ሳይሆን በጹሁፍ ያለውን እንዳልከኝ ለመግለጽ ሞክረሀል፡፡ ተው እንጂ ወዳጄ የአቡ ዩስራ ጹሁፍን መሰረት አድረገን እየተወያየን መሆኑንማ አትርሳ! ታዲያ የአቡ ዩስራ ጹሁፍ በአራተኛ ደረጃ ምን እንዳለ አላየኀውም?
በአጭሩ ሲገልጽ‹‹ታዲያ ይህች ፍየል የእነኝህንም ሰዎች አእምሮ አልበላች ›› ብሎ ግልጽ አድርጎታል፡፡
አንተም ጥያቄ አንስተህ ምላሽ የሰጠውህ በዚህ ዙሪያ ነበር፡፡ ታዲያ እንደማያስኬድ ከላይ ስገልጽ ይሆን መንሸራተቱ የመጣው?
በሁለተኛ ደረጃ ደግመህ ያነሳሀው ተረስቶ ሊሆን ይችላል የሚለው ፍራቻ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ለዛ አንቀጽ መረሳት ምንም አይነት ማስረጃ አሁንም አላቀረብክም፡፡ ስለዚህ አንቀጽ አያወራን አንተ የምታቀርበው ግን ሌሎች ተረስተው ያውቃሉና ይህን ተረስቷል ነው፡፡ ይሄ አመክኗዊ ውይይት አይደለም አበበ በሶ በልቷል ተብሎ ሲነገረን ማርም በልቷል ብሎ መከራከር ጉንጭ ከማልፋት የዘለለ ፋይዳ የለውም ስለራሱ አንቀጽ ማስረጃ ካለህ ይዘህ ና ካልሆነ በመሰለኝ ጊዜያችንን ማቃጠል አይኖርንብንም፡፡
- Yahya Ibnu Nuhe ወደ ሀዲሶቹ ስገባ በመጀመሪያ ያነሳሀው የሰጠህውን የሀዲሱን ደረጃ አስመልክቶ ነው፡፡ በርግጥ በኢብን ማጃህ አተያይ ሀዲሱ ሀሰን ነው (ልብ በል! አሁንም ሀሰን እንጅ ሰሂህ አይደለም) ነገር ግን ከላይ እኔ እንዳቀረብኩልህ የሸይኽ ጣቂ ኡስማን ገለጻ ሰንሰለቱ የተበጠሰ በመሆኑ ሪዋያው ላይ ችግር በመኖሩ ሀዲሱ ደካማ ነው፡፡ በሀዲስ ጥናት መስክ አንድ ሀዲስ ሰንሰለቱ ላይ ችግር ኖሮም የሀዲሱ ገለጻ ከሌሎች ሰሂህ ሀዲሶች ጋር የሚጣጣም ከሆነ ‹‹ሀሰን›› የመሆን እድል አለው፡፡ በዚህ አካሄድ ሀዲሱ ከሌላ ዘጋቢ ሀዲሶች ጋር በመገኘቱ ሀዲሱ ‹‹ምንም አይልም›› የሚባለውን ደረጃ ያዘ፡፡ ግን እንዲያም ሆኖ ለጥንቃቄ ሀዲሱን በደኢፍነት(ለመረጃ ደካማ የሆነ) የፈረጁ ኡለሞች እንዳሉ ከላይ አስቀምጫለሁ፡፡ ቅጥፈት ነው ላልከው እንዳልሆነና በዚህም መስክ ደጋፊ ማስረጃ እንዳለ በትክክልም አሳይቻሀለው፡፡
Yahya Ibnu Nuhe በሁለተኛ ደረጃ ያነሳሀው ኢብን ማጃህ ከስድስቱ ነው አይደለም የሚለው ሀሳብ የተሳሳትከው አንተ እንጅ እኔ አይደለሁም፡፡ መጀመሪያውኑ ያቀረብከው አቀረራረብ ከዛ ውስጥ እንዳለ ድፍን ባለ አገላለጽ ነበር፡፡ ይህ ትክክል እንዳልነበር ማስረጃዎችን አቀረብኩ አንተም ከዛ በኋላ አንተም ባልሞት ባይ ተጋዳይነት አብዛኛው አይደለም ወደሚል ሌላ ክርክር አዞርከው ለሱም ቢሆን ከታች ማስረጃ እሰጥሀለው፡፡
በርግ…See More
- ISLAM-FYI.COMThe Six Authentic Books of Hadith (Sihah Sitta صحاح ستہ) | Islam For…
The Six Authentic Books of Hadith (Sihah Sitta صحاح ستہ) | Islam For Your Information
- Muhammed Hayat temesasay wuyiyitochin lemeketatel www.facebook.com/groups/Why.I.am.not.Christian/
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe ወዳጄ ቀደም ሲል ላነሳሃቸው ነጥቦች በሙሉ አንድ በአንድ መልስ ሰጥቻለሁ፡፡ ከርዕሱም ፈፅሞ አልወጣሁም፡፡ ምናልባት ልብ ብለህ አልተከታተልከኝ ይሆናል፡፡ ግልፅ ላድርግልህ፡፡ የመጀመርያው የአቡ ዩስራ ሙግት የኢብን ማጃህ ሐዲስ በአይሻ እጅ የነበረው ወረቀት “ብቻና ብቻ” መበላቱን እንጂ በሌሎች ሰዎች ዘንድ የነበረው መበላቱን አያመለክትም የሚል ነበር፡፡ እኔም ቁርአንን በማሰባሰብ ሂደት ወቅት ኡመር በጽሑፍ የሰፈረውን በዋቢነት አለመጥቀሳቸውንና በአንድ ቁስ ላይ ብቻ የተጻፉ የቁርአን አንቀፆች መኖራቸውን በመግለፅ በፊየል የተበላው አንቀፅ ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደማይችል አፅንዖት ሰጥቼ የራሴን መልስ አስቀምጫለሁ፡፡ በሌላ ቁስ ላይ በጽሑፍ ሰፍሯል የሚለው የአቡ ዩስራ ጥርጣሬ በነዚህ ሁለቱ ነጥቦች ውድቅ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ አንተ ደግሞ እነዚህን ሁለቱን ነጥቦች ወደጎን በማድረግ በቃል የሸመደዱ ሰዎች መኖራቸውን የሚገልፁ “ሐዲሳትን” በማስረጃነት አቀረብክልኝ፡፡ ልብ በል፡- የአቡ ዩስራ የመጀመርያው መልስ የአይሻ ጽሑፍ ብቸኛው እንዳልሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ የኔ መልስ ቁርአንን በአንድ ጥራዝ በማሰባሰብ ሂደት ወቅት የጽሑፍ ማስረጃ አለመቅረቡንና በአንድ ቁስ ላይ ብቻ የተጻፉ አንቀፆች መኖራቸውን በመጥቀስ ይህንን አባባል የሚያስተባብል ነው፡፡ አንተ የሰጠኸኝ መልስ ደግሞ በቃል የሸመደዱ ሌሎች ሰዎች ነበሩ የሚል ነው፡፡ ለዚህ ነው መልስህ ፊየል ወዲህ ቁርአን ወዲያ ዓይነት ሆኖብኛል ያልኩህ፡፡ “ፊየል የሸምዳጆችን አእምሮ አልበላችም” የሚለው የአቡ ዩስራ ምፀታዊ ምላሽ አራተኛ ነጥብ ላይ የተቀመጠና ከአንደኛው ሙግት የተለየ ነው፡፡ ለርሱም ቢሆን መልስ ሰጥቻለሁ፡፡ የውይይቱን መስመር የለቀቀከው አንተ ነህ፡፡ ከሐሳቤ የተንሸራተትኩ የመሰለህ የአቡ ዩስራን የሙግት ነጥቦችና የኔን ምላሾች ባለማገናዘብህ ነው፡፡
“ላለመረሳቱ ምንም ዓይነት ማስረጃ አላቀረብክም” ላልከው ቁርአን ሲሰበሰብ ኡመር አንቀፁ በቁርአን ውስጥ እንዲካተት ዘይድን በጠየቁት ጊዜ ዘይድ ከኡመር ውጪ ሌላ ምስክር ባለመኖሩ ምክንያት ለማካተት ፍቃደኛ አለመሆኑን፤ እንዲሁም የነቢዩ ባልደረቦች የቁርአንን አናቅፅ የመርሳት ችግር እንደነበረባቸው የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በማቅረብ መልስ ሰጥቻለሁ፡፡ ጥቅሱ ስለመረሳቱ ከዚህ የተሻለ ማረጋገጫ የሚያሻህ አይመስለኝም፡፡ ማስረጃዎቹን ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆንክ ላስገድድህ አልችልም፡፡
የኢብን ማጃህ ሐዲስ ደኢፍ መሆኑን ገልፀህ ሐሰን መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለመቻሌን በአፅንዖት ከተናገርክ በኋላ ማስረጃ ሲቀርብልህ ሐሳብህን ቀይረህ “ሐሰን” መሆኑን መቀበልህ ጥሩ ነው፡፡ በእጃችን የሚገኘው ኦፊሴላዊ ጥራዝ ሐዲሱ “ሐሰን” መሆኑን እስከተናገረ ድረስ ደኢፍ እንደሆነ የሚናገሩ ምሑራን መኖራቸው ምንም ለውጥ አያመጣም፡፡ በዚህች ዓለም ላይ የተለየ አቋም የሚያንፀባርቁ ምሑራንን መጥቀስ የማይቻልበት ርዕሰ ጉዳይ ያለ አይመስለኝም፡፡ የፈለግነውን አቋም የሚደግፉልንን ሊቃውንት ፈልገን ማግኘት እንችላለን፡፡ ነገር ግን እኔና አንተ ሊቃውንት እስካልሆንን ድረስ በተረጋገጠው አቋም ላይ ተመስርተን ነው መነጋገር ያለብን፡፡ በሳሂህ ሐዲሳት ውስጥ የሚገኙ ከአቋማቸው ጋር የማይሄዱ ሐዲሳትን እንኳ “መውዱእ” እንደሆኑ በድፍረት የሚናገሩ ምሑራን መኖራቸውን አትርሳ፡፡ የቁርአንን አናቅፅ እንኳ አውጥተው የጣሉ ሙስሊም ምሑራን ነበሩ፡፡ የትኛውንም አቋም የሚያራምዱ ምሑራንን ፈልጎ ማግኘት ቀላል ነው፡፡- Azanu Metka እግዚአብሄር እዉቀቱንና ፀጌዉን ያብዛልህ

Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net ኢብን ማጃህ ከስድስቱ መካከል ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ የውይይቱን አቅጣጫ ከማስለወጥ የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ከስድስቱ መካከል እንደሆነ ስለሚቀበሉ “አይደለም” ብለው የሚጨቃጨቁትን ሙስሊሞች አቋም የመጥቀስ ግዴታ የለብኝም፡፡ አቋሙ የጥቂት ሰዎች ብቻ ቢሆንና ለግል አቋሜ ድጋፍ ፍለጋ ጉዳዩን “ድፍን” በሆነ መንገድ ባቀርበው ነበር ስህተት የሚሆነው፡፡ ኢብን ማጃህ ከስድስቱ የሚቆጠረው በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ ብቻ እንደሆነ በስህተት ማሰብህ ነው የኔን አቀራረብ እንድትቃወም ያደረገህ እንጂ በስፋት ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ መረጃ ቢኖርህ ኖሮ ተቃውሞ ባላሰማህ ነበር፡፡ ያንተ አቋም ስህተት መሆኑን ደግሞ በማስረጃ አረጋግጬልሃለሁ፡፡ ስለዚህ የኔን “ስህተት” ፍለጋ የፈጠርከውን ስህተት አርመህ “ተራ የሐዲስ ሊቃውንት አመለካከት ልዩነት” የሆነውን ጉዳይ በመተው በውይይቱ ፍሬ ሐሳብ ላይ ብታተኩር የተሻለ ይመስለኛል፡፡
የነሳዒ ስድስቱም ቅፆች ጥራዞች አሉኝ፡፡ በኢንተርኔት ላይ ያለውን አይደለም እየጠቀስኩልህ ያለሁት፡፡ ነሳዒ ሱናን አል-ኩብራ የተሰኘ ስብስብ እንደነበረውና ሁሉም ሐዲሶች ተዓማኒ ባለመሆናቸው ምክንያት ተዓማኒ እንደሆኑ ያመነባቸውን ብቻ ለይቶ በሌላ ጥራዝ ማዘጋጀቱን አውቃለሁ፡፡ ሁለተኛው ኤዲሽን ዛሬ “ሱናን ነሳዒ” ብለን የምናውቀው ባለ 6 ቅፅ መጽሐፍ መሆኑንም አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን አል-ኩብራ በዚህ ዘመን በህትመት ላይ መኖሩን አላውቅም (የመረጃ እጥረት ሊሆን ይችላል)፡፡ ቢኖር እንኳ የጠቀስከው ሐዲስ በራሱ በነሳዒ ተዓማኒ እንደሆነ ስላልታመነበት በሁለተኛው ኤዲሽን ውስጥ አላካተተውም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ለሙግትህ የሚጠቅም አይደለም፡፡ ለማንኛውም መጽሐፉ ካለህ ማረጋገጥ እንድችል ቦታውን ፎቶ አንስተህ ብትልክልኝ፤ ወይም ሙሉ መጽሐፉ በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ ከሆነ አውርጄ ማየት እንድችል ብትጠቁመኝ ደስ ይለኛል፡፡ መረጃውን ከሌላ ምንጭ ልታገኝ እንደምትችል ስለማምን የግድ ጥራዙን እንድታሳየኝ አልልም፡፡ ለማንኛውም ያልከውን ለመቀበል ጠንካራ ማስረጃ ያስፈልገኛል፡፡
በመጨረሻም፡ ግንዛቤህንና መልካም ሥነ ምግባርህን እንደማደንቅ ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡ አንዳንድ የክርክር ቃላትን ባትጠቀም ደግሞ የበለጠ መልካም ይሆናል፡፡ ጠንካራ የሙግት ሐሳብ እንደሌላቸው የሚያምኑ ሰዎች ናቸው እንደርሱ የሚያደርጉት፡፡Yahya Ibnu Nuhe እሽ ወገኔ ሀሳቦችህን ተመልክቻቸዋለሁ በተቻለ መጠን ያለተደጋገሙትና አዲስ ናቸው የምላቸው ላይ አስተያየት ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡
በመጀመሪያ ያነሳሀው በአኢሻ ዘንድ ያለው ብቻና ብቻ እንደሆነ አይገልጽም በሚለው አንተ ሌላ ቦታ ላይ በአንድ ቁስ የተጻፈ የቁርዓን አንቀጽ እንደነበር ገልጸህ ይህም ከዛ እንደማይለይ ለማስረዳት ሞክረሀል፡፡ ወዳጄ ነጮቹ ይህንን ኢ-አመክኖአዊ አቀራረብ Hasty Generalization ይሉታል ሁሉንም አንቁላሎች አንድ ቅርጫት ውስጥ መጨመር እንደማለት ነው፡፡ ይህ ለውይይት የሚቀርብ አፕሮች ሳይሆን መጀመሪያውኑ መታረም ያለበት የተሳሳተ ፋላሲ ነው፡፡ቀድሜ እንደገለጽኩልህ በአንቀጹ ዙሪያ ማስረጃ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ግን የለህም በሌለ ነገር መወያየት ደግሞ የሁለታችንንም ጌዜ ማቃጠል ነው፡፡
- Yahya Ibnu Nuhe በሁለተኛ ደረጃ ያነሳሀው የኢብን ማጃህን ጉዳይ ነው፡፡ ወዳጄ ይህ ሀሳብ ለምን እንደተነሳ የዘነጋህው መሰለኝ ሀሳቡን እኮ መጀመሪያ ደኢፍ መባሉ ቅጥፈት ነው በማለትህ ይህ እንዳልሆነ ማስረጃ እያቀረብኩልህ ነበር፡፡ ለዚህ አያይዘህ ያቀረብከው ሰዎች ከፍላጎታቸው አለመጣጣም ሀዲሳትን ላይቀበሉ እንደሚችሉ ጭመር ነው ይህም ምን ጥርጥር አለው እኔ ግን ያቀረብኩት በሙስሊሙ አለም እውቅ የሖኑትን ሀዲስ ምሁር ሸይኽ ጣቂ ኡስማኒን ነው፡፡ ሸይኹ እስከማውቀው ለስሜታቸው ስላልተመቻቸው ሀዲሳትን ‹‹ መውዱዕ›› እንደሚሉ ‹‹አዋቂዎች›› ወይንም ለመመለስ የሚያስጨንቋቸውን የመጽሀፍ ‹‹ቅዱስ›› አንቀጾች ፎርጅሪ/ፍብረካ/ እና አፖክሪፋ/ጭማሪ/ መጽሀፍት ናቸው እንደሚሉ የባይብል ምሁራን አይደሉም፡፡ እንደነዛ አይነት ሰዎች የሚያመጧቸውን ማስረጃች ብቀበልማ ውይይታችን እዚህ ድረስ ሳይመጣ ከላይ ይቋጭ ነበር፡፡
- Yahya Ibnu Nuhe ሌላው በሶስተኛ ደረጃ ያነሳሀው ኢብን ማጃህ ከስደስቱ ነው አይደለም የሚለውን አጀንዳ ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ከላይ በሚገባ አስቀምጫለሁ ይህንን ነጥብ ያነሳንበት ምክንያትም ከላይ አንተ ከስድስቱ እንደሚገኝ ድፍን አድርገህ መግለጽህ ተገቢ እንዳለሆነ ላማሳየት ነው፡፡ አነሰም በዛም በዚህ ዙሪያ ለወደፊቱ ጥቆማውን ሰጥቸሀለው፡፡ የውይይት ዋና አላማው መማማር አስከሆነ ድረስ መወቃቀስን ሙጥኝ ማለቱ ብዙም ጠቃሚ መስሎ አልታየኝም፡፡ ተሳስተሀል አልተሳሳትኩም ክርክር ኮሜንት ከማርዘምና ስሜታዊ ከማድረግ የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡
Yahya Ibnu Nuhe ሌላው በመጨረሻ ላይ ያነሳህው የኢማም ነሳዒ ጉዳይ ነው መጽሀፉ በህትመት መኖሩን እንደማታውቅ ገልጸህ መረጃውን ጠይቀህኛል፡፡መልካም ነው ግን ከዛ በፊት የገረመኝ መጽሀፉን ሳታውቀው ስለመጽሀፉ የሰነዘርከው ሀሳብ ነው፡፡ በርግጥ እንዳልከው አንዳንድ ጸረ-ኢስላም ድህረገጾች ጋ ያልከው ሀሳብ ሊኖር ይችላል፡፡ እውነታውን ግን ያ አይደለም እሱን እዚህ እነግርሀለው በመጀመሪያ ደረጃ አሱነነል ኩብራ አልሙጅተባ ወይም አል ሙጅተና ሁለቱም ቃላት ትርጉማቸው በጥንቃቄ የተመረጡ ማለት ነው፡፡ ሀዲሶቹ ሰሂህ ለመሆናቸው እራሳቸው ኢማም ነሳኢ ምስክርነቱን ሰጥተዋል የተቀነሰበት ምክንያት በወቅቱ የነበረው ንጉስ ሀዲሶቹ ሰሂህ ቢሆንም ዘገባውም ጭምር አስተማማኝ የሆኑት ለብቻቸው እንዲመረጡ በመሻቱ ነበር፡፡
መረጃውን በጥያቄህ መሰረት በእፕ ያለውን ስክሪን ሹት አድርጌ ከታች አስቀምጥልሀለው ከራሱ ከእትሙ ሄደህ እንድታረጋግጥ ደግሞ መክተበተ ሻሚላ ውስጥ ታገኘዋለህ፡፡ ምናልባት አሁንም መክተባው ከሌለህ ፒዲኤፉን ዳውንሎድ እንድታደርግ ወይንም ኦንላይን እንድትመለከተው ከታች ሊንኩን እሰጥሀለው፡፡
–
http://read.kitabklasik.net/2009/06/sunan-al-nasai.html?m=1
READ.KITABKLASIK.NETSunan al-Kubra (al-Nasai) – Abu…Sunan al-Kubra (al-Nasai) – Abu ‘Abdirrahman Ahmad bin Syu’aib al-Nasa’i ~ ONLINE LIBRARY ~…
- Yahya Ibnu Nuhe ወዳጄ ፎቶውን ላስቀምጥልህ ስል ፔጅህ ይህንን አክሰስ ገድቦታል በውስጥ እልክልህና አንተው እዚህ ትለጥፈዋለህ፡፡
- Merigeta Kedame Tsega አሁንም ት/ት ላይ ነኝ ተመችቶኛል የቀጥል በውስጥ መስመር አትረብሹኝ
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe ሙግቶቼን በተሳሳተ መንገድ መተርጎምህን ለማረም ያህል አንድ ዙር መቀጠል የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ በአንድ ቁስ ላይ የተጻፈ ሌላ የቁርአን ጥቅስ መኖሩን ጠቅሼ በፊየል የተበላውም ብቸኛ ቁስ ሊሆን መቻሉን መናገሬን በተሳሳተ መንገድ ነው የተረጎምከው፡፡ ይህ ሙግት Hasty Generalization የማይሆንበት ምክንያት የፊተኛው ሙግት ደጋፊ ማስረጃ እንጂ ብቻውን የቆመ ባለመሆኑ ነው፡፡ ዋናው የሙግት ሐሳብ ቁርአንን በማሰብሰብ ሂደት ወቅት ኡመር አንቀፁ በቁርአን ውስጥ እንዲካተት ጥያቄ ባቀረቡ ጊዜ ሌላ አስረጅ ባለመኖሩ ምክንያት ዘይድ ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጓል የሚለው ነው፡፡ በአንድ ቁስ ላይ ብቻ የተጻፈ የቁርአን አንቀፅ እንዳለ መጠቀሱ ሁሉም የቁርአን ጥቅሶች ከአንድ በላይ በሆኑ ቁሶች ላይ ተጽፈዋል የሚለውን የተሳሳተ ቅድመ ግንዛቤ ውድቅ የሚያደርግ የዋናው ሙግት መጋቢ ነው፡፡ የሚገርመው ነገር በመልስህ ጅማሬ ላይ ነቢዩ አንቀፁ ተጽፎ እንዲቀመጥ አለመፍቀዳቸውን የሚያሳዩ ሐዲሳት ናቸው ያልካቸውን ሁለት “ማስረጃዎች” ከጠቀስክ በኋላ ከአንድ በላይ በሆኑ ቁሶች ላይ ተጽፏል ብለህ መሟገትህ ነው፡፡ ተጽፏል ወይስ አልተጻፈም? ለሚለው ጥያቄ የሰጠኸው መልስ እርስ በርሱ የሚጠፋፋ ነው፡፡
የኢብን ማጃህ ሐዲስ ደኢፍ መሆኑን የተናገሩ ምሑራን መኖራቸውን ጠቅሰሃል፡፡ በየትኛውም ርዕሰ ጉዳይ ላይ ልዩ አቋም ያላቸውን ምሑራን መጥቀስ እንደሚቻል ነግሬሃለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ማለት ከብዙሃኑ ሊቃውንት አመለካከት አንጻር ጥግ ላይ የተቀመጠውን አመለካከታቸውን አንስተህ ማራገብ አለብህ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ምሑር በዘርፉ ሊቅ መሆኑ ብቻውን ትክክለኛ አቋም ለመያዙ ዋስትና ስለማይሆን ኡስማኒን ማወደስ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም፡፡ እኔና አንተ የሐዲስ ሊቃውንት አይደለንም፡፡ ስለዚህ ኦፊሴላዊ በሆኑ አቋሞች ላይ ተመስርተን ነው መነጋገር ያለብን፡፡ የኢብን ማጃህ ሐዲስ ሐሰን መሆኑን ሊቃውንት ስለተስማሙበት ይመስለኛል የገዛ ሃይማኖትህ መመርያዎች ከሆኑት መጻሕፍት መካከል በአንዱ ውስጥ ሰፍሮ የተገኘው፡፡ ከዚህ አመለካከት በተፃራሪ የቆመውን ሐሳብ ጠቅሰህ ብትሞግት አመለካከቱን ከማይቀበሉት ምሑራን አንፃር አቋምህ ውድቅ ነው፡፡
የኢብን ማጃህ ሐዲስ ከስድስቱ መካከል መቆጠሩን መግለፄን የተቃወምክበትን ትክክለኛ ምክንያት አድበስብሰህ ለማለፍ ጥረት እያደረክ ነው፡፡ መጀመርያ እኮ ከስድስቱ መካከል የሚቆጥሩት ጥቂት ምሑራን ብቻ እንደሆኑ ነበር የገለፅከው! አብዛኞቹ ከስድስቱ መካከል እንደሚቆጥሩትና ከስድስቱ የማይቆጥሩት አናሳ መሆናቸውን ማስረጃ ሳቀርብልህ ስህተትህን አርመህ ከማለፍ ይልቅ እኔ መሳሳቴን ለማረጋገጥ ጥረት አደረክ፡፡ ግን አልተሳካልህም፡፡ ውዱ ወዳጄ በመማማር የምታምን ከሆነ ትምህርት ከአንተ ወገን ብቻ የሚመጣ አለመሆኑንና አንተም ከሌሎች መማር እንዳለብህ መቀበል ይኖርብሃል፡፡ ለማንኛውም ኢብን ማጃህ ከስድስቱ መካከል መቆጠሩን በደፈናው የገለፅኩት አንተ እንዳልከው ሐዲሳትን በተመለከተ በሙስሊሞች መካከል ያለውን ጭቅጭቅ ዘንግቼ አለመሆኑን በድጋሜ ላረጋግጥልህ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ጉዳይ ሰፊ ተቀባይነት ያለው ከመሆኑ አንፃር የአናሳዎችን አመለካከት ጠቅሶ ማለፍ አስፈላጊም ግዴታም አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በኔ የተጀመረ ሳይሆን ሙስሊም ሊቃውንት ሳይቀሩ የሚያደርጉት ነው፡፡ ልክ እኔ እንዳደረኩት ኢብን ማጃህ ከስድስቱ ስብስቦች መካከል አንዱ መሆኑን በደፈናው የጠቀሰ አንድ እስላማዊ መጽሐፍ በዋቢነት ልስጥህ፡-
Among these the most famous are the six collections which are known as Kutub sittah, these are: Sahih Al-Bukhari, Sahih Muslim, Sunan Abu Dawud, Sunan An-Nasa’i, Al-Jami’ lit-Tirmidhi and SUNAN IBN MAJAH. (Sahih Muslim: Arabic English, Vol. 1, Publishers Note: p. 9) በተጨማሪም English Translation of Jami’ At-Tirmidhi, Vol. 1, Publisher’s Forward: p. 21 ተመልከት፡፡
ስለዚህ አንተ እያልክ እንዳለኸው በደፈናው መጥቀስ ስህተት ከሆነ የሳሂህ ሙስሊምና የአት-ትርሚዚ አሳታሚዎችም ተሳስተዋል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ይህንን ነጥብ በማንሳት በማይረባ ሙግት ጊዜያችንን እንድናባክን እንደማታደርገን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net የነሳዒ ሱነን አል-ኩብራ መጽሐፍ በሕትመት ስለመገኘቱ የሰጠኸኝን መረጃ በጥንቃቄ ካየሁት በኋላ ሐሳቤን እገልጻለሁ፡፡ ነገር ግን ነሳዒ የመጀመርያ ጥራዙን አርሞ ከስድስቱ መካከል የተቆጠረውን ሐዲስ ያዘጋጀበትን ምክንያት በተመለከተ የተናገርከው ነገር ከዚህ ቀደም ካለኝ መረጃ ጋር ተጣርሶብኛል፡፡ እርገጠኛ ለመሆን ስለ ሐዲሱ በሙስሊም ምሑራን የተጻፉ መጻሕፍትንና የሐዲሱን ድረገፅ በማየት ያገኘሁት መረጃ አንተ እዚህ ከጻፍከው ጋር የሚጋጭና የኔን የቀደመ መረጃ የሚያረጋግጥ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በድረገፁ ላይ የሚገኘውን መግቢያና አንድ መጽሐፍ ልጥቀስልህ፡-
In reality when the Imam had finished compiling Sunan Al-Kubra he presented to the governor of Ramalah so the governor asked him “Is it all sahih?” He replied in the negative, thus the governor suggested and requested that he compile another book and gather in there the Sahih Hadith. So then he did this and named his book Sunan Al-Sughra (the small Sunan) and Al-Mujtaba and Mujtana (both mean carefully chosen) and this is the Sunan which we know as Sunan An-Nasa’i.” http://sunnah.com/nasai/about
“In his large work on Sunan (which he confessed contained a fair number of weak and dubious traditions), Nasa’i compiled the legal traditions which he considered to be either fairly reliable or of possible reliability. At the request of some of his friends, he also produced a synopsis of the sunan, called al-Mujtaba, or sa-sunan as-Sughura. This later work, which he claimed contained only reliable traditions is now accepted as one of the six canonical collections.” (Dr. Abu Ameenah Bilal Philips; Usool al-Hadeeth: the Methodology of Hadith Evaluation, p. 187)
ከላይ በተቀመጡት መረጃዎች መሠረት ነሳዒ ሐዲሱን ወደ ረማላህ ገዢ ባመጣው ጊዜ ሁሉም ሳሂህ ስለመሆኑ ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ “አይደለም” የሚል ነበር “when the Imam had finished compiling Sunan Al-Kubra he presented to the governor of Ramalah so the governor asked him “Is it all sahih?” He replied in the negative”፡፡ ይህ ጥራዝ ደካማና አጠራጣሪ የሆኑ ሐዲሳትን መያዙንም ተናዟል “he confessed contained a fair number of weak and dubious traditions”፡፡ ስለዚህ ሳሂህ የሆኑትን ብቻ ለይቶ እንዲጽፍ በተነገረው መሠረት አሁን ከስድስቱ መካከል ለመቆጠር የበቁትን ሐዲሳት አዘጋጅቷል፡፡ ይህ አንተ ከተናገርከው ጋር ፍፁም የሚጋጭ ነው፡፡ የቱን ልቀበል?Yahya Ibnu Nuhe እሽ ወዳጄ ድጋሜ መመለስህ መልካም ነው፡፡ እኔም ካንተ ጹሁፍ አንጻር አሁን ላይ የታዩኝን የቀሩ ብየ የማስባቸውን አንኳር ነጥቦች እንድዳስሳቸው እድለን ሰጥተህኛል፡፡ በዋናነት ማየት የምፈልገው ነገር የኢብን ማጃህን ሀዲስ አስመልክቶ ደኢፍ መባሉ እንዴው ዝም ብሎ ተራ የሀሳብ ልዩነት አድርገህ መውሰድህ ነው፡፡ ሀዲሶችን ከላይ ስታነሳቸው የሀዲስ ጥናት መስክ ላይ ቢያንስ ኢንትሮደክሽን ይኖራሀል ብየ አስቤ ነበር ዲቴል መግባቱ ያላስፈለገኝ ፡፡ ምንም ችግር የለውም ለምን ይህ እንደሆነ ከታች ዝርዝር የሆነውን የሀዲስ ጥናት መስክ ምሁራን አስተያየት አስቀምጥልሀለው፡፡
ሲጀመር የሀዲሱ ዘጋቢ አንድን ሀዲስ የሰጠው ደረጃ ሁሌም ቋሚ መመዘኛ ተደርጎ አይወሰድም ይህ ተራ የሀዲስ ተማሪ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ሀዲሱን ለመወሰን ሙስጠለሀል ሀዲስ ወይንም የሀዲስ ጥናት መስክ የሚያሟላቸውን ክራይቴሪያዎች ሊያልፍ ግድ ነው፡፡
አሁን ተከተለኝ
ሀዲሱ በዘጋቢነት ደረጃ የተወሰደው በተለያዩ ዘጋቢዎች ከአብደላህ ኢብን አቡበክር ነው፡፡
1- ይህ ሀዲስ ከያህያ ኢብን ሰዕድ አልአንሳሪ ተዘግቦ ነበር፡፡ በዚህ ዘገባ ውስጥ ግን ሙሉ ሀዲሱ በተመሳሳይ ተቀምጦ በፍየል መበላቱን የሚገልጸው ክፍል የለም፡፡ ይህ ሀዲስ በኢማም ሙስሊም የሰሂህ ጥራዝ ሀዲስ ቁጥር 1452 ላይ ይገኛል፡፡
2- ይህ ሀዲስ በተመሳሳይም በኢማም ማሊክ ተዘግቦ ነበር፡፡ ይህ ሀዲስ እንዴውም የሚዘግበው ኢብን ማጃህ ከወሰዱበት አብደላህ ኢብን ኢስሀቅ ምንጭ አብደላህ ኢብን አቡበክር ነው፡፡ አሁንም ይህ ዘገባ ሙሉ ሀዲሱን ይዞ በኢብን ማጃህ ስላለው የፍየል መበላት ርዕስ ግን ምንም የሚለው ነገር የለውም፡፡ ሀዲሱ የኢማም ማሊክ ሙወጣዕ ኪታቡ ሪዳ ሀዲስ ቁጥር 17 ላይ ይገኘል፡፡
ለሀዲስ ጥናት መስክ ምሁራን በአንድ ሀዲስ ዙሪያ ሰሂህ ከሆኑ ሌሎች ሀዲሶች የተለየ ጭማሪ መኖር ለደኢፍነቱ በቂ ነው፡፡ በዚህም በሙሀመድ ኢብን ኢስሀቅ በኩል የተላለፈውን ይህን ሀዲስ የሀዲስ ጥናት መስክ ምሁራኖች ያለምንም ልዩነት ለደኢፍነቱ መስክረዋል፡፡ ዝርዝር መረጃውን ታህዚብ አተህዚብ ሙጀለድ/ጥራዝ/ 11 ገጽ 223 ላይ መመልከት ይቻላል፡፡ ኢማም አጠሀዊይ በሙሽኪለል አሳር ጥራዝ 11 ገጽ 486 ላይም ሀዲሱን አስመልክቶ ዝርዝር ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡ ሙሉ ጹሁፋቸውን ከማስቀምጥ ሪፈረንሶችን ከታች ልስጥህ፡፡ተዕዊል ሙኽተሊፉል ሀዲስ አረብኛው ጥራዝ ገጽ 443፤ ሙዐሳሳት አሪሳላ ጥራዝ 43/343 እንዲሁም አልአሉሲ በሩሁል ማዕኒ 11/140 ወዘተ …..
- Yahya Ibnu Nuhe ሌላው የኢብን ማጃህን አንስተህ አንዳንድ ምሁራንም በደፈናው ለመግለጽ የሞከሩ እንዳሉ በመግለጽ ሞግተሕኛል፡፡ በርግጥ በዚህ ርዕስ ዙሪያ ማውራት ለሁላታችንም መውረድ ነው ብየ ስላሰብኩ ላልመለስበት አቅጄ ነበር፡፡ ግን ያመጣሀው መረጃና የአንተ ሀሳብ ለየቅል ነውና መናገር ስለሚኖርብኝ ልግለጸው፡፡ እኔ ለዚህ ሀሳቤ የመረጃ ችግር የለብኝም ባለፈውም ሰጥቼሀለው ካነሰህ አሁንም እጨምርለሀለው፡፡ አሁን ግን ካንተው መረጃ ላየ እራሱ የሚለውን ስንመለከት Most/አብዛኛው/ በሚል አገላለጽ ነው ያስቀመጠው እንጅ ድፍን አድርጎ አላስቀመጠውም ይህም አንተ ካልከው ጋር ይጣረሳል፡፡
Yahya Ibnu Nuhe ሌላው ያነሳሀው የነሳኢን ጉዳይ የሰጠውህን መረጃ አስመልክቶ ነው፡፡ ወገኔ ጹሁፌን በደንብ እንዳላነበብከው ወይንም ያልኩት እንዳልገባህ ይሰማኛል፡፡ ለማንኛውም ጹሁፌ እንዱህ ይል ነበር
‹‹ሀዲሶቹ ሰሂህ ለመሆናቸው እራሳቸው ኢማም ነሳኢ ምስክርነቱን ሰጥተዋል የተቀነሰበት ምክንያት በወቅቱ የነበረው ንጉስ ሀዲሶቹ ሰሂህ ቢሆንም ዘገባውም ጭምር አስተማማኝ የሆኑት ለብቻቸው እንዲመረጡ በመሻቱ ነበር፡፡››
በሀዲስ ጥናት መስክ ውስጥ አንድ ሀዲስ የሚታየው እራሱ ሀዲሱና ሰንሰለቱ ሁለቱ ነው፡፡ ሀዲሱ ሰሂህ ሆኖ ሰንሰለቱ ግን አስተማማኝ ሰሂህ ላይሆን ይችላል፡፡ የተቀነሱት ሀዲሶችም በሀዲስ ረገድ ጠንካራ ሆነውም ቢሆን በዘገባ ረገድ ደካማ መሆናቸውን ንጉሱ ስላልወደደው ነበር፡፡ እንጂ እንዳለ የተቀነሱት ደኢፍ ሀዲስ ናቸው ማለት አይደለም፡፡
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net እኛ ክርስቲያኖች እስልምና እውነት አለመሆኑን ለማሳየት የሚችሉ ሐዲሳትን መዘን ባወጣን ቁጥር ሊቃውንቶቻችሁ እስልምናን ከትችት ለመታደግ ሳሂህ ሐዲሳትን “ደኢፍ” ወይም “መውዱዕ” በማለት ከመፈረጅ ወደ ኋላ እንደማይሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ሐሰን ታጁ የተባለው የአገራችን ሙስሊም ጸሐፊም የኢብን ማጃን የፊየል ታሪክ “የመጨረሻ አስከፊ ቅጥፈት (መውዱዕ) ነው” በማለት ቅጥፈት ፈፅሟል፡፡ (ሐሰን ታጁ፣ የሐመረ ተዋሕዶን ቅጥፈት፣ ገፅ 27-28)፡፡ ስለዚህ አንተ እንዳልከው ለሐዲሳት የምትሰጡት ደረጃ ሁሌም ቋሚ አለመሆኑ አያስገርምም፡፡ ቋሚ ካልሆነ ደግሞ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ የቆመበት አስተምሕሮ ረግረጋማ ነው ማለት ነው፡፡ ሌላው ሙስሊም ሊቃውንት አንድን ሐዲስ “ደኢፍ” ብሎ ለመፈረጅ በሳሂህ ሐዲሳት ውስጥ የሌለ አዲስ ሐሳብ መጨመሩን እንደመመዘኛ እንደሚጠቀሙ ተናግረሃል፡፡ እንደርሱ ከሆነ በሳሂህ ሐዲሳት መካከል ግጭትና የሐሳብ ልዩነት እያለ እንኳን ለሁለቱም “ሳሂህ” የሚል ደረጃ ስለምን ይሰጣሉ? ለዚህ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ሐዲሳትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ያንተ መረጃ ትክክል ከሆነ ሚዛኑ ለሁሉም ሐዲሳት የማይሠራ አባይ ሚዛን በመሆኑ እስልምና የተናጋ አቋም እንዳለው ያረጋግጣል፡፡
የፊየሊቱን ታሪክ ማስተባበል ሐዲሱ የሚያስከትለውን ችግር ማስወገድ መስሎ ታይቶሃል፡፡ ነገር ግን ቁምነገሩ እርሱ አይደለም፡፡ በመጀመርያው ዙር ምላሼ ላይ የተናገርኩትን አንድ ነገር ላስታውስህ፡፡ እንዲህ ብዬ ነበር፡- “ጥቅሱ በፊየል፣ በግመል ወይም በውኀ ተበልቶ ቢጠፋ ቁምነገሩ ያለው በአጠፋፉ ሁኔታ ላይ ሳይሆን በመጥፋቱ ላይ በመሆኑ የፊየሊቷ ታሪክ እውነት አይደለም ቢባል እንኳ ከቁርአን መሰረዙ በሳሂህ ሐዲሳት እስከተረጋገጠ ድረስ ቁርአን ሐሰተኛ ሰነድ መሆኑ ሊታበል የሚችል አይደለም፡፡”
አንቀፁ መውረዱንና በቁርአን ውስጥ አለመካተቱን የሚናገረው ሐዲስ ሳሂህ መሆኑን ማመንህ ትልቅ ነገር ነው፡፡ የኔ ሙግት “የፈጣሪ ቃል ያለበት መጽሐፍ በፊየል ሊበላ አይችልም” የሚል ሳይሆን “ቁርአን አልተጨመረበትም ከላዩ ላይም አልተቀነሰም የሚለው የሙስሊሞች እምነት ከሐዲሱ አንፃር ትክክል አይደለም” የሚል በመሆኑ የፊየሊቱ ታሪክ ወሳኝ አይደለም፡፡ ስለዚህ አንቀፁ ከቁርአን ውስጥ መጥፋቱን የሚናገሩት ሐዲሳት ትክክል መሆናቸውን ካመንክ በቂ ነው፡፡
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net ኢብን ማጃህ ከስድስቱ ጋር መቆጠሩን በደፈናው ስለመናገር በተመለከተ እኔው ራሴ የጠቀስኩትን ምንጭ በመጠቀም ሐሳቤን ለማስተባበል ሞክረሃል፡፡ ነገር ግን Most የምትለዋ ቃል የት ጋር እንደገባች አላስተዋልክም፡፡ አውዱን በተሻለ ሁኔታ ማየት እንድትችል ከፊት የሚገኘውን አንድ አረፍተ ነገር ጨምሬ ደግሜ ልጥቀስልህ፡- There are many collections and compilations of Ahadith. Among these the most famous are the six collections which are known as Kutub sittah, these are: Sahih Al-Bukhari, Sahih Muslim, Sunan Abu Dawud, Sunan An-Nasa’i, Al-Jami’ lit-Tirmidhi and SUNAN IBN MAJAH.
ትርጉም፡- “ብዙ የሐዲሳት ስብስቦችና ጥራዞች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በጣም ታዋቂ የሆኑቱ ኩቱብ ሲታህ በመባል የሚታወቁት ስድስቱ ስብስቦች ናቸው፤ እነርሱም፡- ሳሂህ አል-ቡኻሪ፣ ሳሂህ ሙስሊም፣ ሱናን አቡ ዳውድ፣ ሱናን አን-ነሳዒ አል-ጃምዒ ሊት-ትርሚዚ እና ሱናን ኢብን ማጃህ ናቸው፡፡”
“ከእነዚህም መካከል” ሲል ከአረፍተ ነገሩ በፊት ከተወሱት ብዙ ሐዲሳት መካከል ለማለት እንጂ ኢብን ማጃን ለብቻው የሚነጥል አይደለም፡፡ ኢብን ማጃህ ከስድስቱ መካከል በደፈናው ተቆጥሯል፡፡ የእንግሊዘኛ ችግር ያለበት ሰው ካልሆነ በስተቀር ይህንን ለመረዳት የሚቸገር ማንም የለም፡፡ አንተ ደግሞ የእንግሊዘኛ ችግር ያለብህ አይመስለኝም፡፡ ሆነ ብሎ ከሚጠም ሰው ጋር እንደመሟገት ያለ አስቀያሚ ነገር የለም፡፡
Authorለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net ነሳዒን በተመለከተ ያለ ማስረጃ ነው እያወራህ ያለኸው፡፡ እኔ ግን ማስረጃ ሰጥቼሃለሁ፡፡ የሰጠሁህ ማስረጃ በግልፅ እንደሚያመለክተው ነሳዒ የመጀመርያው ስብስቡ ደኢፍ ሐዲሳትን በማካተቱ ምክንያት ሳሂህ ሐዲሳትን ብቻ የያዘ ሌላ ስብስብ አዘጋጅቷል፡፡ ሰውየው ራሱ የደኢፍ ሐዲሳት ድብልቅ እንደሆነ አምኖ መጽሐፉን ኤዲት አድርጎት ሳለ ከመጀመርያው መጽሐፍ ውስጥ ደኢፍ ተብሎ የተጣለውን ክፍል መጥቀስ ምን ማለት ነው? አንዱ የሐዲስ ሊቅ ሐሰን መሆኑን የመሰከረለትን ሐዲስ ደኢፍ ነው ትላለህ፡፡ ሌላው የሐዲስ ሊቅ ደግሞ ደኢፍ ነው ብሎ የጣለውን ሳሂህ ነው ትላለህ፡፡ ወዳጄ ግራ ተጋብተሃል እኮ፡፡ አስተውል እንጂ፡፡
አንድ ሐዲስ ሳሂህ ለመሆን አንዱና ዋነኛው መስፈርት የዘገባ ሰንሰለቱ (ኢስናዱ) አስተማማኝ መሆኑ ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ ታዋቂው የሐዲስ ሊቅ ኢብን አል-ሳላህ እንዲህ ብሏል፡- “A Sahih hadith is the one which has a continuous isnad, made up of reporters of trustworthy memory from similar authorities, and which is found to be free from any irregularities (i.e. in the text) or defects (i.e. in the isnad).” http://www.islamic-awareness.net/Hadith/Ulum/asb7.html
ኢብን አል-ሳላህ እንደተናገረው አንድ ሐዲስ ሳሂህ ለመባል ያልተቋረጠ ኢስናድ ሊኖረው ይገባል እንዲሁም ኢስናዱ እንከን የለሽ መሆን አለበት፡፡ አንተ ግን እያልከን ያለኸው ኢስናዱ ደኢፍ ሆኖ ሐዲሱ ሳሂህ ሊሆን ይችላል ነው፡፡ የአንድ ሐዲስ ሳሂህ መሆን መሠረቱ የኢስናዱ አስተማማኝነት ሆኖ ሳለ አስተማማኝ ያልሆነ ኢስናድ ያለው ሐዲስ ሳሂህ ሊሆን የሚችለው እንዴት ሆኖ ነው?ISLAMIC-AWARENESS.ORG1 ReplyYahya Ibnu Nuhe እሽ ወገኔ የዛሬውን ጹሁፎችህ ብተዋቸው ለዚህ ተራ መስክ እንግዳ ለሆነው አማኝ ብዥታን የሚፈጥሩ ናቸው ብየ ስላመንኩ ተራነታቸውን አንድ ባንድ ማሳየት ያስፈልጋል በሚል ተመልሻለሁ በአንተ በኩል ላለው አማኝም ካለእውቀት የልብ ልብ ሊሰጥ ስለሚችል ልጓም ማበጀቱ ግድ ነው፡፡
በመጀመሪያ ያነሳሀው የሀዲስ ሊቃውንት ጥያቄ ሲፈጠርባቸው የሀዲሳትን ደረጃ እንደሚቀያየሩ የገለጸው ስሜታዊ አገላለጽ በጣም ነው የደነቀኘ፡፡ ምናልባት የሀዲስ ሊቃውነንት ቢሰሙ ከፈገግታም በዘለለ ሊስቁም ይችሉ ይሆናል፡፡ እኔ የምለው የትኛው የክርስቲያን አዋቂ ነው የሙስሊም ሊቃውንትን የሀዲስ ደረጃ የማስቀየር አቅም ያለው? እንዴው ከነመፈጠራቸውስ የሚታወቁ ጥሩ የንጽጽር አዋቂ አሉ እንዴ? እኔ እንጃ፡፡አሉ የሚባሉትን አቃቸዋለሁ ለዚህ የሚመጥኑ አይደሉም፡፡ በነገራችን ላይ የማወራህ በአለም አቀፍ ዙሪያ ስላሉት ነው ሀገር ውሰጥ የነሱን ጹሁፎች እንደወረደ ከመተርጎም በዘለለ የግል ጥናት የሚያደርግ ሰው በግሌ አላገጠመኝም እሱ ጭራሽ ግምት ውስጥ የሚገባም አይደለም፡፡አለም አቀፍ ተብለው የማውቃቸው አይደለም ሀዲስ ለማስቀየርና ይቅርና የሀዲስ ሊቃውንት ጋ እንኳን ሊደርስ የሚችል የረባ አርጊውመንት እንዳላቸው አላውቅም፡፡ በተራ የሙስሊም አፖሎጂስቶች ተመልሰው በእንጭጭ የሚቀሩ ናቸው፡፡ እና እባክህን በማይረባ ነገር አንከራከር ህይወት አይሆነነም፡
- Yahya Ibnu Nuhe ሌላው ሀዲሱ ላይ የቀረበው የደኢፍ ውሳኔ ታሪኩን ለማስተባበል የተፈጠረ እንደሆነ የሞት ሞትህ ለመሞገት ሞክረሀል፡፡ ተውንጂ ወገኔ መጀመሪያውኑ ሀዲሱ የሚገኘው እኮ መጽሀፍ ‹‹ቅዱስ›› ውስጥ አይደለም ያገኘኽውም ኢስላማዊ ድርሳናት ውስጥ ነው ይህንን ነገር ደብዛውን ማጥፋት ቢፈለግ መጀመሪያው መጻፍና ማስተላለፍ አይኖርም ነበር፡፡ ትንሽ አእምሯችንንማ እናሰራው እንጅ!!!
- Yahya Ibnu Nuhe የቁርዓን ክፍል ነው እያልክ በተደጋጋሚ የተናገርከው ፍጹም ትክክል እነዳልሆነ ከላይ አስረደቻሀለው፡፡ ሀዲሱ ላይ የተገለጸው የጥቢ አንቀጽ ከቁርዓን ጋር ወርዶ የነበረ ትእዛዝ እንጅ የቁርዓን አካል አይደለም ቢሆንማ የአላህ መልክዕክተኛ ኡመር ሲያመጣው ከላይ እንዳየነው ባልከለከሉት ነበር፡፡ ክፍተት ያገኘን እየመሰለን ስለእንትና ክብር እያልን ባንዋሽ እንደመንፈሳዊ ሰው ያስከብራል፡፡
ከዚህ ውይይት እንደምንታዘበው ኡስታዝ የሕያ ምላሽ ብሎ ያቀረበው በሁለት ጓደኞቹ የተጻፉ መጣጥፎችን ነበር፡፡ ወንድም ዳንኤል በመጀመርያዎቹ ምላሾቹ ጠንካራ ሙግቶችን ያቀረበ ቢሆንም ኡስታዙ የውይይቱን ርዕስ ማስለወጥ የሚመስል አካሄድ በመጠቀም፣ የወንድም ዳንኤልን ሐሳብ በማጣመም፣ መልስ የተሰጠባቸውን ሐሳቦች ያለ ምንም ማሻሻያ በመደጋገም (ለምሳሌ ያህል በመዝጊያ አስተያየቱ ወንድም ዳንኤል ገና በሁለተኛው ዙር በቂ ምላሽ የሰጠበትን የኡመርን ክልከላ ጉዳይ ምላሹን ችላ በማለት እንደደገመው ማለት ነው)፣ አላስፈላጊ ቃላትን በመወርወር፣ ራሱን ከልክ በላይ ከፍ ከፍ በማድረግና ሌላውን ወገን በማንኳሰስ፣ ወዘተ. ደካማ ምላሾቹን ለመደጋገፍ ሲሞክር ይታያል፡፡ ጠንካራ ማስረጃዎች ሲቀርቡበት የቀደሙ ሐሳቦቹን የሚያፋልሱ ሙግቶችን እያቀረበ ለማምለጥ የሚያደርገው ሙከራ ሙስሊሙ ወገን ሙግቶችን ለመርታት እንጂ ለእውነት ግድ እንሌለው ያሳያል፡፡ የመጨረሻዎቹ ሦስት አስተያየቶቹ ከዚህ የተለዩ አይደሉም፡፡ እንዲህ ያሉ የሙግት ስልቶች በሙስሊም ተሟገቾች ዘንድ በእጅጉ የተለመዱ ናቸው፡፡ ወንድም ዳንኤል ከሙስሊሙ ወገን ሲወረወሩ ለነበሩት እርባና የሌላቸው ቃላት አፀፋ ባለመስጠት የውይይቱን ሰላማዊ አካሄደ ለማስጠበቅ ያደረገው ጥረት የሚደነቅና ለሌሎቻችንም ምሳሌ የሚሆነን ነው፡፡ ከውይይቱ ብዙ ጠቃሚ ቁምነገሮችን ተምራችኋል ብለን እናምናለን፡፡







