ጥንቃቄ ስለ ባርት ኤህርማን

ጥንቃቄ ስለ ባርት ኤህርማን


ዶ/ር ባርት ኤህርማን የዘመናችን ስመ ጥር የምንባባዌ ሕየሳ ምሑር ሲሆን ክርስትናን በመተቸቱ ምክንያት ትልቅ ስም ያተረፈ ግለሰብ ነው። የዕውቁ ክርስቲያን የምንባባዌ ሕየሳ ሊቅ የብሩስ መዝገር ተማሪ ነበረ፤ በጋራም መጽሐፍ አዘጋጅተዋል። ይህ ሰው ያጠናው ምንባባዌ ሕየሳ (textual criticism) ቢሆንም ክርስቲያናዊ ነገረ መለኮት ላይ ያለው ዕውቀት የስሙን ያህል ትልቅ ሊባል የሚችል አይደለም። በምንባባዌ ሕየሳም ቢሆን ከእርሱ በፊት የማይታወቅ አዲስ ያገኘው ግኝትና ለዘርፉ ያበረከተው የተለየ አስተዋጽዖ የለም። የሚታወቀውንና ከክርስቲያን ሊቃውንት የተማራቸውን ጉዳዮች ነው አጏጊ ርዕሶችን እየሰጠ በመጽሐፍ የሚያሳትመው። ራሱን ሲያስተዋውቅ የታሪክ ምሑር በማስመሰል ቢሆንም በዘርፉ እንዲያ ያለ ማዕርግ ሊያሰጠው የሚችል የትምህርት ደረጃ የለውም። ገበያ ለመሳብ ለራሱ ያጎናፀፈው ማዕርግ ነው። ስለ textual criticism ከምሑራን ጋር አንድ መድረክ ላይ ሲቀርብና ስለ ጉዳዩ የማያውቅ ሕዝብ ፊት ሲቆም የሚናገራቸው ነገሮች በአንድ ራስ ሁለት ምላስ የሚያሰኙ የተለያዩ ነገሮች ናቸው:: ለትልልቅ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጽፋቸው ጽሑፎችና ለገበያ ሲል የሚያሳትማቸው መጻሕፍት በአቋም ደረጃ ፍፁም የማይገናኙ ናቸው። ለዚህ ነው በቅርበት የሚያውቁት ምሑራን the good Ehrman and the bad Ehrman, the scholar Ehrman and the popular Ehrman በማለት የሚጠሩት። ሰውየው በምሑራን ዓለምና በጎጋው ዓለም ሁለት እርስ በርሳቸው የተኳረፉ ገፅታዎች ያሉት ገበያ ተኮር ሰው ነው፤ ስለዚህ ጥንቃቄ ያሻል።

ለእስልምና ሙግቶች ምላሽ