የእስላማዊ ስነ-ፅንስ ተረክ በዘመናዊ ሳይንስ መነፅር [ክፍል አምስት]

የእስላማዊ ስነ-ፅንስ ተረክ በዘመናዊ ሳይንስ መነፅር [ክፍል አምስት]

ዶ/ር ሻሎም መኮንን


ሙድጋ

በቁርአን ተረክ መሰረት ” የረጋ ደም ” የሆነው  የፍትወት ጠብታ ወደ ቁራጭ ሥጋነት ይለወጣል ። በጽሑፉ መግቢያ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የቁርአንን የስነ-ፅንስ ሀተታዎች ከዘመናዊ የስነ-ፅንስ ጥናት ግኝት ጋር እያነፃፀሩ ለመተቸት ከመጣረሳቸውም በላይ ከመራራቃቸው የተነሳ አዳጋች ነው። እንደሌሎቹ የቁርአን ሀተታዎች በተመሳሳይ ይህም ክፍል ፈፅሞ ስህተት ነው። የሰው ልጅ በማህፀን ቁራጭ ሥጋ የሚሆንበት የፅንስ ደረጃ የለም።

ይህ የቁርአን ክፍል ስህተት እንደሆነ የተረዱ የሙስሊም ዐቃቤያን የተለመደው የአረብኛ ቋንቋ ትንተና ውስጥ ይገባሉ። የአረቢኛ ቋንቋ ትንተናቸው እንዲሁም የሚሰጡት ትርጓሜዎች ለማጭበርበር የሚጠቀሟት መሆኑን በእስልምና ዙርያ ላሉ ሰዎች አዲስ ነገር አይደለም። እንግዲህ በዚህ የቁርአን ክፍል ላይ ለሰፈረው “ሙድጋ የሚለው የአረብኛ ቃል ቁራጭ ሥጋ ሳይሆን ” የታኘከ ሥጋ የሚመስል ” ተብሎ መተርጎም እንዳለበት ያስረዳሉ። ነገር ግን ከሳይንሳዊ ግኝቶች ተረኩን ለማቀራረብ በሚል ካልሆነ ከየት ያመጡት ትርጉም እንደሆነ እነሱም የሚያውቁት አይመስለኝም። የቁርአንን ሀተታ ለማስረዳትም በስፋት ከሚጠቀሙበት ውስጥ ይህ የማስቲካ ስዕል እና ማስቲካ እንዲመስል ተደርጎ የተሳለ የፅንስ ስዕል በዋነኝነት ይገኝበታል። ኪይት ሙርም በተመሳሳይ ከሼይክ ዚንዳኒ ጋር ባሳተመው መፅሀፍ የታኘከ ማስቲካ እና ፅንስን (ምስሉ ሌላም ቢሆን) አነፃፅሯል።

እንዲህ ያለ ስላቅ የሚመስል አቀራረብ ሰውን ከሸወደልን ለእውነታነቱ ግድ አይሰጠንም በሚል ካልሆነ በቀር እውነተኛውን ሃይማኖትን እሰብካለው የፈጣሪን መንገድ ልጠቁም ከሚል ሰባኪ አይጠበቅም። እንደሚሉን ሙድጋ የታኘከ ሥጋ ይሁን ቢባል እንኳን “ማስቲካ እና ሥጋ ሲታኘኩ የሚያስቀሩት የጥርስ ምልክት” አንድ አይደለም። “የታኘከ ማስቲካ” እና “የታኘከ ሥጋን” አይቶ ለማያውቅ ሰው ካልሆነ ይህንን ምስል ማስረጃ ከማድረግ የሚተርፈው ትዝብት ብቻ ነው።

በቁርአን ክፍሉ ላይ ያለውን “ሙድጋ” የሚለውን ቃል  የዚህ ዘመን ዘመነኛ ሰባኪዎች ብቻ በሚያውቁት ትርጉም ተጠቅመን በመፍታት አውደ ክፍሉን እንዲሁም ከሳይንስ ጋር ለማቀራረብ የሄዱበት መንገድ እንደማያስኬድ እንይ:- 

① ይህ የታኘከ ነገር (በተለይ ማስቲካ) የሚሉን ከረጋ ደም ነው የሚፈጠረው?

ከዚያም ጠብታዋን የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን። (ሱራ23:14)

② ቁርአን የታኘከ ማስቲካ የሚመስለው(ሙድጋ) በቀጣይ አጥንት ተደርጎ እንደተፈጠረ ይገልፃ ወደ አጥንትነት ይቀየራል?ከዚያም ስጋ ይለብሳል ?  በጭራሽ።

ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን ፤ አጥንቶቹንም ሥጋ አለበስናቸው (ሱራ 23:14)

③ የታኘከ ነገር ማለት ከሆነ በሆድ ውስጥ ያለው ፅንስ የታኘከ ነገር ነው እንዴ? በክፍሉ “እንደሚሆን እንጂ እንደሚመስል” የሚያመለክት ቃል የለም።

ይህ በእንዲህ ሳለ የእስልምና ሰባኪያን “ሙድጋ”  ለሚለው የአረብኛ ቃል “የታኘከ ማስቲካ” ወይንም “የታኘከ ሥጋ” የሚል ትርጉም ከየትኛው ጥንታዊ የአረብኛ መዝገበ ቃላት እንዳመጡት ቢጠየቁ መልስ ያላቸው አይመስለኝም። ሙድጋ ለመታኘክ የተዘጋጀ መጠን ያለው፣ ወይንም ቁራጭ ስጋ ማለት ነው። የታኘከ ማለት ሳይሆን ሊታኘክ የተዘጋጀ የአንድ ጉርሻ መጠን ያለው ማለት ነው። The Hans Wehr Dictionary እንዲሁም  Lane’s lexicon ቃሉን በዚሁ መንገድ ይፈቱታል።

በተመሳሳይ በእዛው በኢስልምና መዛግብት ሙሐመድ ” ሙድጋ” የሚለውን ቃል ለልብ [ሳሂህ ሙስሊም መጽሐፍ 22፣ ሀዲስ 133] እንዲሁም ለወንድ ልጅ መራብያ አካል [ሱናን አቡ ዳውድ 181] ተጠቅሞታል። ሁለቱ ጃለሎች በተፍሲራቸው “ለመታኘክ የተዘጋጀ መጠን ያለው” የሚለውን ትርጓሜ አስቀምጠዋል፦ [https://quranx.com/tafsirs/23.14]።  ቁርአን በስነ-ፅንስ ረገድ የሰጠው ሀተታ በየትኛውም መልኩ ከስህተት ሊወጣ የሚችል ዓይነት አይደለም።

ሙድጋ የሚለውን ቃል “ልም አፅም” ብለው የሚፈቱት የእስልምና ሰባክያን አሉ። የእነዚኞቹ መሠረታቸው የእስልምና መዛግብትም ሆነ የአረብኛ ቋንቋ ሳይሆኑ ዘመናዊ ሳይንስ መሆኑ ነው። የቁርአን ሀተታ “ቁራጯን ሥጋ አጥንት አድርገን ፈጠርን” ስለሚል፤ በዘመናዊው ስነፅንስ ሳይንስ ደግሞ አጥንት ከልም-አፅም የሚጀምር ስለሆነ ቁርአን በክፍሎቹ ላይ ቁራጭ ሥጋ ያለው ልም አፅሙን ለማመልከት ነው የሚል ማብራርያ ይሰጣሉ። እንግዲህ የቁርአንን ንግግር ትክክል ለማድረግ ሙድጋህ የሚለው ቃል ትርጉሙ ልም አፅም መሆን አለበት።

የእስልምና ሰባኪዎች ንጥል ቃላትን በማይታወቅ ትርጉም መፍታት ይህ አንዱ አይደለም። እንደሌሎች ክፍሎችም ይህንን ክፍል የእስልምና ታላላቅ ሙፈሲሮች፣ ይህ ሳይንሳዊ ግኝት እስኪታወቅ የኖሩ ሙስሊሞች ሌሎች የእስልምና መዛግብቶች የተረዱት ቁራጭ ሥጋ ብለው ነው። ልም አፅም (cartilage) በአረብኛ የእራሱ “ገድሩፍ” غضروف የሚል ቃል አለው[https://hamariweb.com/dictionaries/cartilage+_arabic-meanings.aspx]። እውነት የቁርአን ደራሲ ገድሩፍ ለማለት ፈልጎ “ሙድጋ” ይላል ከተባለ በሌላ አገላለፅ ማለት የፈለገውን በአግባቡ መግለፅ አይችልም እያልን ነው። ይህ ደግሞ ቁርአን የሰው እጅ ሥራ መሆኑን ይገልፃል።

ቢሆንም ከላይ እንዳደረግነው ሁሉ ለዚህም ክፍል ክፍት መንገድ ብንሰጣቸው እንደሌሎቹ ችግር ያለበትና የትም የማይሄድ ነው። ሁለት ነጥቦችን እናስከትል

① ፅንሱ ልም አፅም የሚሆንበት የፅንስ ደረጃ አለ ? የለም ! አጥንት የሚሆነው ክፍሉ ብቻ እንጂ ፅንሱ ልምአፅም (cartilage) አይሆንም።

② አጥንት የሚሆነው ልም አፅምና አጥንቱን የሚያለብሱት ስጋዎች በእኩል ሰአት የሚፈጠሩ ናቸው። በእነዚኞቹ ትርጉም ሙድጋን  ልም አፅም ብለን ብንፈታው ቁርአን የሚለን ልም አፅሙ አጥንት ይሆናል አጥንቱ ደግሞ ስጋ ይለብሳል። ይፈፅሞ ስህተት ነው!

ሙድጋ “ልም አፅም” ተብሎ ቢተረጎም እንኳን ክፍሉ ከስህተት ባይፀዳም ከላይ እንዳየነው “ሙድጋ” ትርጉሙ ልም አፅም አይደለም። ቁርአን በቦታው ልም አፅም ማለት ፈልጎ ቢሆን ኖሮ ቁራጭ ሥጋ (ሙድጋ) ከማለት ይልቅ ልም አፅም (ገድሩፍ) ይል ነበር።

ጥያቄ ለህሊና

ፕሮፌሰር ኪይት ሙር ለማስተማርያነት ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ካሳተመው መጽሐፍ እስከ10 ሳምንት ያለን የፅንስ እድገት በጥንቃቄ  እንድትመለከቱ በመጋበዝ ከዚያም በቀና ልብ ለእራስ የሚመለሱ ጥያቄዎችን አቀርባለው። የኪይት ሙርን መጽሐፍ የመረጥኩት በሙስሊም ወገኖቻችን ዘንድ የቁርአንን ስነ-ፅንስ ልከኝነት ለመደገፍ በቀዳሚነት ስሙ የሚጠራው ሳይንቲስት በመሆኑ ነው።  “THE DEVELOPING  HUMAN CLINICALLY ORIENTED EMBRYOLOGY” 10ኛ ዕትም ከገፅ 2-3 ምስሎቹን ወስጃለው

  • የቱ ጋር ነው አለቅት ወይንም የረጋ ደም የሚሆንበት ደረጃ ያለው?
  • የቱ ጋር ነው የፍትወት ጠብታ የሚሆነው?
  • የቱ ጋር ነው ቁራጭ ሥጋ የሚሆነው?
  • የቱ ጋር ነው ቁራጭ ሥጋው አጥንት የሚሆነው?
  • የቱ ጋር ነው ወደ አጥንትነት የተቀየረው ቁራጭ ሥጋ፤ ሥጋ ለብሶ አዲስ ፍጥረት የሆነው?

መልሱ ቀላል ነው። በቁርአን የአላህ ዕውቀት ብቻ እንደሆነ ተነግሮ አላህ እንዲህ እንዲህ አድርጎ ፈጥሯል የተባለው በአምላክ ስም የተነገረ ስሁት የሆነ ንግግር ነው።

ዘመናዊ ስነ-ፅንስ ምን ይላል?

በዘመናዊ ስነ-ፅንስ ጥናት ውስጥ ኑጥፋ፣ ኑጥፈቲን አምሻጂን፣ አለቃህ፣ ሙድጋህ፣ ኢዛምን ምናምን የሚባል የጽንስ ደረጃ የለም። እንደ ዘመናዊ ስነ-ፅንስ አስተምህሮ የወንዴ ዘር ህዋስ እና ከሴቴ እንቁላል ሕዋስ ጋር የሚገናኙት የማህፀን ቱቦ ላይ ነው። ፅንስ “ሀ” ብሎ የሚጀምረው የማህፀን ቱቦ ላይ ሲሆን ከታች በምስሉ እንደምታዩት በክፍያ ንቃዮት ሁለት፥ አራት፥ ስምንት እያለ አስራ ስድስት ሲሞላ ሞሩላ ይሆናል።  የመጀመርያ ሳምንት ተገባዶ የሁለተኛ ሳምንት ጅማሮ ላይ በአማካይ ከስምንት እስከዘጠኝ ቀን ሲሞላ ጥባቄ ፅንስ ይፈፀማል።

ጥባቄ ፅንስን እንዲፈፀም ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥ አንደኛው የውስጠ ማህፀን ምቹ መሆኑና ሁለተኛው ኳሰ-ፅንሱ እንዲለጠፍ የሚያግዙት ውጫዊ አካሎቹ (ሲይንሲሺዮ ትሮፎብላስት እና ሳይቶትሮፎብላስት) ናቸው። የሲይንሲሺዮ ትሮፎብላስት ህዋሶች ጥባቄ ፅንስ የሚከናወንበት ውስጠ ማህፀን ጋር የሚገኙ ህዋሶችን አስወግደው በእነርሱ ቦታ ይተካሉ። የተለያዩ ሆርሞኖች በዚህ ሂደት ተሳታፊ ሲሆኑ እናትየዋ በዚህ ሂደት ውስጥ ቁርጠትን ጨምሮ ሌሎች ምልክቶችን ልታይ ትችላለች። ቀጣይ የሚከወነው አቢይ ግብር ሰርጓዴ ፅንስ ነው። ስርጓዴ ፅንስ ልጅ የሚሆነውን ፅንስ የሰውነት ክፍሎች ምስረታ ጅማሮ ነው።

ሰርጓዴ ፅንስ ሶስት ክፍሎች ሲኖሩት

Ⅰ) ውስጠኛው ገላፅንስ (endoderm)

Ⅱ) መሀከለኛው ገላፅንስ (mesoderm)

Ⅲ) ውጨኛው ገላፅንስ (ectoderm)

የውጨኛው ገላፅንስ (ectoderm) በውጪ በኩል ያሉ አካላትን ማለትም  ጥፍር፣ ቆዳ፣ ፀጉር እንዲሁም ጥርስ፣ ሰርን የመሳሰሉትን የሰውነት አካላት የሚፈጥር ሲሆን  የውስጠኛው ገላ-ፅንስ ደግሞ የውስጠኛውን የሳንባ  ንብር፣ ጉበት፣ ጣፊያ፣ ስርአተ ቅንባሮ ልመት፣ ጉሮሮ እና የመሳሰሉትን የሚፈጥረው ክፍል ነው። የመሀከለኛው ገላፅንስ (mesodem) የፅንሱን አፅመ-ክፍል፣ ሳምባ፣ ስርአተ-ደም ዝውውር፣ ደም፣ መቅኔ፣ ኩላሊት እና የመሰሳሰሉትን ይፈጥራል። እንግዲህ የእስልምና ትርክት በአጥንት አፈጣጠር ዙርያ ያስቀመጡት ድምዳሜ ከዘመናዊው የህክምና ሳይንስ  ጥናት ጋር በተፃራሪው የቆመ ነው። ቁርአን እንዲህ ያስቀምጣል፦

በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ ጠብታ አደረግነው

ከዚያም ጠብታዋን የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን ፤ የረጋውንም ደም ቁራጮች አድርገን ፈጠርን

ቁራጯንም ስጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን ፤ አጥንቶቹንም ስጋ አለበስናቸው

ከዚያም አዲስ ፍጥረት አድርገን አስገኘነው ፤ ከሰአሊዎች ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ።

ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ ናችሁ

ከዚያም በትንሳኤው ቀን ትቀሰቀሳላችሁ።    (ሱራ 23:13-16)

በዚህ የቁርአን ክፍል እንደምናነበው የቁርአን ደራሲ የሽል አፈጣጠር ቅደም ተከተል ብሎ ያመነውም እያስቀመጠ ነው። እንደክፍሉ ቅደም ተከተል አላህ ጠብታዋን የረጋ ደም ፤ የረጋውን ደም ቁራጭ ሥጋ፤ ቁራጩን ሥጋ በመቀጠል አጥንት ያደርግና አጥንቱንም ደግሞ ሥጋ በማልበስ ወደ አዲስ ፍጥረትነት ይቀይረዋል ። ቁርአን ያስቀመጠው ይህ ቅደም ቅደም ተከተል ሙሉ በሙሉ እና አንድ በአንድ ምንም ማስተባበል የማያሻው ግልፅ ስህተት ነው።  በውስጡ አንድም ትክክለኛ ሀሳብ ባይኖርበትም በሰው ልጅ ስነፍጥረት ውስጥ ሽሉ አጥንት የሚሆንበትና፣ አጥንቱ ደግሞ ስጋ የሚለብስበት ደረጃ የለም።

የፅንሱን አፅመ ስርአት እና በዙርያው የሚገኙ ጡንቻዎችን የሚያዋቅረው የሰርጓዴፅንስ ክፍል ውስጠ-ገላፅንስ ሲሆን በቅድሚያ ልምአፅም ይፈጥርና ልምአፅሙ ወደ አጥንትነት ይቀየራል።ልም አፅሙ እና እርሱን የሚሸፍነው ጡንቻ  የሚሰሩት በእኩል ለእኩል ነው። የኢስልምና ሰባኪዎች እንደሚሉን ቁርአን ወደ አጥንትነት ይቀየራል ያለው “ልምአፅምን ቢሆን እንኳን ” አጥንት የሚሆነው ልምአፅም ” እና “አጥንቱን የሚሸፍኑት ጡንቻዎች” የሚፈጠሩት በእኩል ጊዜ ስለሆነ  ቁርአን ከስህተት አይወጣም።  እንግዲህ በስምንተኛው ሳምንት መገባደጃ ላይ ልም አፅሙ ሙሉ በሙሉ ሳይጠነክር ፅንሱ በተወሰነ መልኩ መንቀሳቀስ የሚችልበት ደረጃ ይደርሳል።

ይህ በዘመናዊ ጥናት ግኝት እንዲህ ቢሆንም በቁርአን ክፍል ገለፃ መሰረት ግን ቁራጭ ስጋ አጥንት ይሆናል  ፣ በመቀጠል አጥንቱ ስጋ ይለብሳል ፣ ከዚያም ፅንሱ ይወት የሚዘራው አጥንቱ ስጋ ከለበሰ በኋላ ነው። ይሄ ተረክ ሊዛመድ ቀርቶ ከዘመናዊው የህክምና ሳይንስ አስተምህሮ አራምባ እና ቆቦ ነው። ይህ የቁርአን “ገለፃ “

መለኮታዊ ነው ሊያስብለው ቀርቶ ፈገግም የሚያስብል ነገር አለው።

በሙሐመድ “የቁርአን ፍቺ እንዲሰጠው” የተጸለየለት ዕውቁ ሙፈሲር ኢብን አባስ ባዘጋጀው ተፍሲር ላይ እንደተመሠረት የሚነገርለት ተፍሲር ክፍሉን እንዲህ ያብራራዋል፦

በእናቱ ማህፀን ውስጥ በመልካም ማረፊያ ቦታ ለአርባ ቀን የዘር ጠብታ ሲሆን ያስቀምጠዋል። ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡ https://quranx.com/tafsirs/23.14

ይህ ፈጽሞ ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም።


ቁርኣንና ሳይንስ?

ቁርኣን