ሀላል ምግብ ምንድነው?
በሀገራችን ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ “ሀላል” የሚል ተቀፅላ ያላቸው ሉኳንዳዎችና ምግቦች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ የሀላል ምግቦችን ማምረትን በዕቅድ የያዙ ግዙፍ ካምፓኒዎችም ወደ ሀገራችን በመግባት አንዳንዶቹ ሥራ ጀምረዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ክርስቲያኖች ግራ ሲጋቡና ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ይታያል፡፡
“ሀላል” የአረብኛ ቃል ሲሆን “የተፈቀደ” የሚል አቻ ትርጉም አለው፡፡ ሙስሊሞች እንደ አሣማ ያሉ የምግብ አይነቶችን መብላት ወይም አልኮል መጠጥ መጠጣት አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ለምግብነት የሚታረድ እንስሳ መዘጋጀት የሚችለው በተወሰነ መልኩ ብቻ ነው፡፡ ይህም እንስሳው በሚታረድበት ጊዜ እስላማዊ ጸሎት ማካሄድን ያጠቃልላል፡፡ ሙስሊሞች እንዲበሉት የማይፈቀድላቸው የምግብ ዓይነት ሀራም (የተከለከለ) ይባላል፡፡ ሙስሊሞች እንዲበሉት የተፈቀደላቸው የምግብ ዓይነት ደግሞ ሀላል ይባላል፡፡
በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ሙስሊሞች ሁሉም የምግብ ዓይነት በተለይም ደግሞ ሥጋ ሀላል እንዲሆን በመንግሥትና በምግብ አምራቾች ላይ ግፊት የሚያደርጉ የሀላል ምክር ቤቶችን ያቋቁማሉ፡፡ አንዳንድ ሙስሊሞች ይህንን ድርጊት በሀገራትና በሕዝቦች ላይ መንፈሳዊ ኃይልን እንደማግኛ መንገድ ይቆጥሩታል፡፡ የሙስሊሞች ቁጥር ከጠቅላላው ህዝብ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር 1 በመቶ በሆነባት አፍሪካዊት ሀገር በቦትስዋና ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ አብዛኞቹ የሥጋና የምግብ ምርቶች ሀላል ናቸው፡፡ በሌሎች ብዙ ሀገራትም ተመሳሳይ ሁኔታ አለ፡፡
በክርስቲያኖች ዘንድ እንኳን ሳይቀር ሀላል ያልሆነውን ምግብ ከመብላት ሀላል የሆኑ ምግቦችን መብላት ጤናማ እንደሆነ የሚያሳስብ አመለካከት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህ ነገር እውነት አይደለም፡፡ እንዲያውም የሀላል እርድ በአብዛኛው ጊዜ ንፅህና የጎደለውና የሚታረዱትን እንስሳት ክፉኛ የሚያሰቃይ ሊሆን ይችላል፡፡
በብዙ ሀገራት ውስጥ አንድ ድርጅት ምግቡ የሀላል ሰርተፍኬት እንዲያገኝ ለእስላማዊ ተቋማት ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በመጨረሻ ይህንን ክፍያ እንዲከፍል የሚደረገው ያንን ምግብ የሚገዛው ተራ ተመጋቢ ነው፡፡ እንዲህ ባለ መልኩ የሚገኘው ክፍያ ሌሎች የእስልምና ፕሮጀክቶችን ለመደጎም ሊውልም ይችላል፡፡
ስናጠቃልል ክርስቲያኖች ሀላል ምግቦችን ገዝተው መጠቀማቸው በክርስቲያኖች ላይ መንፈሳዊ ድልን እንደ መቀዳጀት የሚቆጥሩትን የአክራሪ ሙስሊሞችን ሥነ ልቦና ከመገንባት በተጨማሪ አክራሪ እስልምናን በኢኮኖሚ ማጠናከር ይሆናል፡፡ የእንስሳትንም ሥቃይ የሚያበዛ የአስተራረድ ዘዴን ስለሚጠቀም (እንስሳው ቶሎ እንዳይሞት ጥረት ስለሚደረግ) ሥጋውን ገዝተን መጠቀማችን ተጨማሪ እንስሳት እንዲሠቃዩ ምክንያት ይሆናል፡፡ ሙስሊሞች እንደ ክርስቲያኖች ሁሉ ደም እንዳይበሉ ቢከለከሉም የሀላል እርድ አዘገጃጀት ደም ወጥቶ እንዳያልቅ የሚያደርግ በመሆኑ በሥጋ ውስጥ የሚቀር ደም የመመገብ ሁኔታም ይኖራል (የሀላል ሥጋ ብዙ ጊዜ አስከፊ ሽታ የሚኖረው አንዱ በዚህ ምክንያት ነው)። የሀላል ሥጋ አዘገጃጀት ንፅህናውን ያልጠበቀ በመሆኑም ለጤና እክል መዳረግን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለዚህ ሀላል ምግብን በተመለከተ አባቶቻችን ያሰመሩትን መስመር ማለፍ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እየታየ እንዳለው መዘዙ አደገኛ በመሆኑ ክርስቲያኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን፡፡