ለምን ሒጃብ? ክፍል ሁለት

ለምን ሒጃብ

ክፍል ለት

ዶ/ር ሻሎም መኮንን


በሒጃብ ዙርያ የሰጠሁትን አጭር ትንታኔ በተመለከተ አንድ [ደካማ] ኂስ እንደቀረበብኝ፣ እኔም መልስ ያስፈልገዋል ብዬ  የማምን ከሆነ ምላሽ ለማቅረብ በሩ ክፍት እንደሆነ የሚገልፅ መልዕክት ከወንድም ዳንኤል ከትችቱ ጽሑፍ ጋር ደርሶኝ ነበር።

በርግጥ ኂሱም፣ መጣጥፌም ዘግየት ቢሉም፣ ከኹሉ በላይ ደግሞ የቀረበው ኂስ ከአመክኖአዊ ሕግጋት ጋር ቀርቶ እርስ በእርሱ እንኳ የማይስማማ፣ ጨዋነት የጎደለው ከፊል ስድብ በመሆኑ ማለፍ ነበረብኝ። ይህ በእንዲህ ቢሆንም በኹለት ምክንያቶች ማለትም አንድ፦ ሂስ አቅራቢውም ሆነ መሰሎቹ ትምህርት ይወስዱበት ዘንድ፤ ሁለት፦ ሒጃብ በምን ምክንያት እንደታዘዘ ሊያሳይ የሚችል ሐሳብ በዚህ ጽሑፍ ለማካተት በማሰብ እጆቼን ወደ መተየቢያው ዘርግቻለሁ። ከኂሱ ጎን ለጎን ብዙዎቻችሁ ይኾናል ብላችሁ የማትጠብቁት “ሒጃብ የደፋሪዎች መግባቢያ ኮድ” መሆኑን “ለምን ሒጃብ?” በሚል ንዑስ ርዕስ ስር ታገኙታላችሁ። መልካም ንባብ።US school demands 'letter from clergy' to allow students in hijab

ወደ ኂሱ ከመግባቴ በፊት ለዚህ ግለሰብ የምናገራቸው ሁለት የምክር ሐሳቦች ይኖሩኛል። አንደኛ አንድ ጽሑፍ ላይ ምላሽ መስጠት ካስፈለገ፣ ምላሽ ስለሚሰጠ’ው ጽሑፍ በቂ ዝግጅት ማድረግ መሠረታዊ ነገር ነው። ነገር ግን እንዲህ መሆን ሲገባው ኅያሲው (ተሳዳቢው ብንለው ይበልጥ ተገቢ ይሆናል) በርዕሱ ላይ በቂ ዝግጅት ማድርግ ቀርቶ የእኔን ጽሑፍ እንኳ አንብቦ በቅጡ አልተረዳውም። ታድያ ይህ ሃይማኖታዊም ኾነ ዓለማዊ የውይይት ምልልሶችን ለማድረግ ግዙፍ ችግር ነው። ኂስ አቅራቢው አሁንም ቢኾን ጽሑፉን ከንዴት፣  ከስሜታዊነትና ከአውቃለሁ ባይነት በመውጣት ተመልሶ ቢያነበው ለማወቅ እና ለመረዳት ጊዜው አይረፍድበትም። ለዚህ ግለሰብ የማቀርብለት ብቸኛው ምላሼ በመረጋጋት ዳግመኛ ተመልሰህ “ጽሑፉን አንብበው” የሚል ነው። አጉል አውቃለሁ ባይነት አይጠቅምም። ቅዱስ ቃሉ እንደሚለው፦ “ለራሱ ጠቢብ የሆነ የሚምስለውን ሰው አየኸውን? ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው።” (ምሳሌ 26:12)

ሁለተኛው ሐሳብ፦ በአንድ ጉዳይ ላይ ኂስ ወይንም እርማት ማቅረብ ማለት በራስ ጫማ፣ በእራስ መነፅር ተቸክሎ በሕይወት ዘመን ሁሉ ያጠራቀሟትን ስድብ ማዝነብ ማለት አይደለም የሚል ነው። ይህ ወንድማችን ወደፊት ሲያድግ እንደ መምህራኖቹ መሆን እንደሚፈልግ ገጹን ስቃኝ ከሌሎች ልጥፎቹ ተረድቻለው። ይህ ግለሰብ ክርስትናን በደከሙ ምክንያት አቀራረቦች፣ በወረደ የአጻጻፍ ስልት፣ በ “ጓ” ጀምሮ በ “ጣ” የሚጨርስ ጽሑፍ እያስነበበ ይወርፋል። በርግጥ የእርሱን ጽሑፎች ጊዜውን ሰጥቶ በነፃ [ሳይከፈለው] የሚያነብለት ቢገኝ፣ ማኅበራዊ ሚድያም ቢኾን ጽሑፎቹን በነፃ [ሳይከፍል] ካስተላለፈለት ለእርሱ ትልቅ ትብብር ነው። በየትኛውም ጽሑፍ ላይ አንባቢ ከጽሑፉ ምንም የሚያኘው አዲስ ነገር ከሌለ ጊዜ ማጥፋት ነው።  ታድያ ግን ይህ ወዳጃችን በክፍያ መገኘት ያለባቸውን መጣጥፎች በነፃ ያለድካም ስላገኘ ብቻ ሁሉንም አካላት በእራሱ ሚዛን ለክቶ “በነፃ ሚድያ መጻፍ ስለቻልን… ” በሚል ሽሙጥ አስቀምጧል። ይህ ግለሰብ ደረጃውን የተወሰነ ያወቀ አይመስልም። ሁሉን በእራስ ጫማ መለካት አግባብ አይደለም።

ከሁለተኛው ነጥቤ ሳልወጣ ይህ ግለሰብ እንዲህ በማለት «የሚኖርበት አካባቢ ሴቶች የአኗኗር ዘይቤ» ያስቃኘንና በሚያስተዛዝብ ሁኔታ «ለሁሉም ሴቶች» በነፍስ ወከፍ ያከፋፍላቸዋል። [ከዚህ በመለጠቅ በሰማያዊ ቀልሞ ያለው ጽሑፍ የኂስ አቅራቢው ነው]

እንደው ለሰውነታችን የሚያስፈልገውን በቂ ቫይታሚን D ለማግኘት ግዴታ ሒጃብ መውለቅ አለበት ራሱ ቢባል ምነው ! ከተፈለገው 15 ደቂቃ  በላይ ሙስሊም ሴቶች ውዱዕ ሲያደርጉም ሆነ ፀጉር ለመሰራት ሲፈልጉ ወይ ደግሞ ግቢ ውስጥ አጂነቢይ ካሌላ ከዚያም በላይ ያለ ሻርፕ ይቀመጡ የለንዴ !? “

እንደ ግለሰቡ አመለካከት ሙስሊም ሴቶች ሁሉ “ግቢያቸው” ውስጥ ፀጉራቸውን ቁጭ ብለው ይሠራሉ፣ እዚያው ግቢያቸው ውስጥም ውዱዕ (ትጥበት) ያደርጋሉ።  ስለዚህ እንደ ጸሐፊው ድምዳሜ ፀሐይ በዚህ ወቅት ይነካቸዋል። የእርሱ አካባቢ ሴቶች ቀን በቀን ጸጉራቸውን ይሠራሉ ብለን ወስደንለት ሐሳቡን እንቀጥል፦

ግቢ  የሌላቸው ሴቶች፣ ግቢ ኖሯቸውም ቤታቸው ውስጥ የሚታጠቡ ሴቶች፣ ቤት ውስጥ ለብቻው መታጠቢያ ክፍል ያላቸው ሴቶች፣ ፀጉራቸውን ቤታቸው ውስጥ  የሚሠሩ ሴቶች፣ የውበት ሳሎን በመሄድ የሚሰሩ ሴቶች፣ ጭራሽ ፀጉር መሠራት ምን እንደሆነ የማያውቁ ሴቶች፣ ወዘተ. በዚህ ግለሰብ መሠረት ሙስሊሞች አይደሉም። በሚያሳዝን ሁኔታ  “ሙስሊም ሴት ማለት” በእርሱ የኑሮ ደረጃ የምትኖር፣ ፀጉሯን ግቢዋ ውስጥ በርጩማ ላይ ተቀምጣ የምትሠራ፣ ውዱዕ ስታደርግ “ከግቢዋ የተተከለ ቧንቧ ስር” አልያ “በጆግ ወይንም በኮዳ” የምትታጠብ ማለት ነች።

በእርግጥ ባቀረበው ሂስ ውስጥ ብዙ የሚተቹ፣ አስቂኝና የማሰብ አቅሙን የሚያስገምቱ ነገሮች አሉበት። ይህ በእንዲህ ቢሆንም ከላይ ነቅሼ ያወጣኋቸው ሁለት ነጥቦች “ነገን አላሚ ነኝ” ብሎ የሚያስብ ወገን ስለሆነ የተወሰነ የአካሄድ ትምህርት ለመስጠት ነው። በተጨማሪም ግለሰቡ በእድሜም፣ በመረጃም፣ በማመዛዘንም ያላደገ በመሆኑ ወደፊት እነዚህ ነገሮቹ ሲለወጡ ምናልባት ልቡን “ግልፅ ሆኖ” ለሚታየው እውነት የሚከፍት ከሆነ በአንድ ጠረቤዛ እናገለግል እንችል ይሆናል በሚል እሳቤ ነው። የኾነው ቢኾን እንኳ እርሱ በጻፈበት መንገድ ለመጻፍ እድሜዬም፣ ደረጃዬም ከሁሉም በላይ ደግሞ ክርስትናዬ አይፈቅድልኝም። ከሁለቱ አስተያየቶቼ በመቀጠል በዚሁ አንድ ምክር ለማስተላለፍ እወዳለው። እንኳንስ “በቅጡ ባልተረዱት ጉዳይ ዙርያ” ይቅርና በደንብ በተረዱት ጉዳይ ላይ እንኳ እንደዚህ ሰውን እያቃለሉና እየዘለፉ መጻፍ አግባብ አይደለም። ኃይለ-ቃል ያለባቸውን ጽሑፎች ባልቃወምም እንዲህ ቀጥተኛ ዘለፋና ግላዊ ስድብ ውስጥ መግባት ለውይይት አስፈላጊ አይደለም።

ይህ ወገናችን ሙስሊም ሴቶች በቂ የፀሐይ ብርሃን ያገኛሉ በሚል ሞግቷል። የባለቤቱ የመረዳት ችግር እንጂ “ሂስ አቀረብኩበት” ባለው ጽሑፍ ውስጥ በቂ ምላሽ ስላለው እዚህ መድገሙ አስፈላጊ አደለም። ይህ ወዳጃችን በሚገርም ሁኔታ “ሒጃብ ነጠላ ጨርቅ ስለሆነ የፀሐይ ብርሃንን አይከልልም” ብሎ ሞግቷል። በዚህ ብቻም ሳያበቃ “ከህፃን እንኳ የማይጠበቅ…ቂልነት” በሚል ያልተገባ አገላለጽ ወርፎኛል። 

ኂስ አቅራቢው ቫይታሚን ዲ በሰውነታችን እንዲመረት “ቀጥተኛ የፀሐይ ብርሃን” እንደሚያስፈልግ አልተረዳም፤ ነገር ግን “ስለ ቫይታሚን ዲ” ትንታኔ ይሰጣል፣ ይሞግታልም።

ለምን ሒጃብ?

ከዚህ ቀደም ባለው ክፍል ሴቶች ለምን ሒጃብ ይለብሳሉ? የሚል ምላሻዊ-ጥያቄ ጠይቄ ነበር። አሁን ደግሞ ሒጃብ ከምን መነሻ እንደታዘዘ በቀናነት፣ እውነትን በሚጋፈጥ ልቦና ለማሳየት ልሞክር። ከታሪካዊ ዳራ እንጀምር።

ሒጃብን ግዴታ ያደረገው ሱራ 33 (ሱረቱል አሕዛብ) የወረደው በኡሁድ ጦርነት እና በምሽጎች ጦርነት መካከል ባሉት ሁለት ዓመታት እንደሆነ የእስልምና መዛግብት ይጠቁማሉ። ታድያ በዚያን ዘመን ሙሐመድ እና ተከታዮቹ በመካ ሕዝብ ላይ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ከማድረጋቸው በፊት ሥልጣናቸውን ለማጠናከር በማሰብ መዲና ውስጥ ሰፍረው ነበር። ሙስሊም ጸሐፍት ይህንን ጊዜ “ማሕበራዊ ተሓድሶ” ይሉታል። ሙስሊም ሴቶችን “ሒጃብ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ማሕበራዊ ትዕዛዞች የወረዱት በዚህ ጊዜ ነው። ይህ ወቅት አይሁዶች የመካ ባሕልን የሚከተሉ እንዲሁም የተለያየ ዓይነት “ባሕል” እና “አመለካከት” የነበረበት ጊዜ ነበር።

ሙስሊም ሴቶች ብቻ “ሒጃብ አድርጉ” የሚል ቁርአናዊ ትዕዛዝ ሴቶች አስገድደው እንዳይደፈሩ የሚከለክል ሳይሆን ደፋሪዎችን የሚያበረታታ፣ ተደፋሪዎችን የሚከስ ከሰብአዊነት እጅግ የወረደ መጥፎ ትዕዛዝ ነው። የቁርአኑን ክፍል እንጥቀስና በጥንቃቄ ምርመራችንን እንቀጥል።

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁ እና እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ (33:59)

“ባለጌዎች” የሚለው ቃል የአማርኛ መተርጉማን በቅንፍ ያከሉበት፣ የአረብኛው ቁርኣን ውስጥ የማይገኝ ስለሆነ አላካተትኩትም። በቁርአኑ ክፍል ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው ሒጃብ “ለሙስሊም ሴቶች የተሰጠ ኮድ” ነው። በቁርአኑ ክፍል ላይ ሙስሊም ሴቶች እንዲታወቁ እና እንዳይደፈሩ የሚል ምክንያት በአፅንኦት ተቀምጦ እናገኛለን። ይህ ኢ-ሰብአዊ ትዕዛዝ ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶችን  በሙስሊም ወንዶች (ወይንም ባልሆኑ) እንዲደፈሩ የይሁንታ ትእዛዝ በተዘዋዋሪ እየሰጠ ነው።

ከላይ እንደተመለከትነው ይህ የቁርአን ትዕዛዝ በሚወርድበት ጊዜ በመካ የተለያዩ አመላካከቶች ነበሩ። የአይሁድ ሴቶች፣ ያላመኑ የመካ ሴቶች፣ ባርያዎች እንዲሁም እስላማዊ መዛግብት የጃሂልያ ዘመን ሴቶች ብለው የሚያስቀምጧቸው ሴቶች ይገኙ ነበሩ። በአሳዛኝ ሁኔታ ሒጃብ ማድረግ ትዕዛዝ የታዘዘው ሙስሊም ሴቶች ከእነርሱ በገፅታ እንዲለዩና እንዳይደፈሩ ለማድረግ ነው። ቀንደኛ ደፋሪዎቹም የተለያዩ ማሕበረሰቦችን ሲያጠቁ የነበሩት ሙስሊም ጂሃዳውያን መሆናቸውን የሚያሳይ ክፍል እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ምክንያቱም ሙስሊም ያልሆነ ደፋሪ የኮዱን ምንነት ሊረዳ አይችልምና።

ኢብኑ ከቲር የተሰኘ ሙፈሲር “አማኝ ሙስሊሞች ሒጃብ ካደረጉ ከመሃይማን ሴቶች ወይንም ከባሮች” በገጽታ ይለያሉ” በሚል በወቅቱ በዑመር ሐሳብ አመንጪነት በሙሐመድ አፅዳቂነት የተቀመጠውን “የኮዱን ምንነት” ያብራራል። ኢብኑ ከቲር ክፍሉን ሲያብራራ እንዲህ የሚልም አክሎበታል፦

እንደታዘዙት(ሒጃብ/ጂልባብ) ካደረጉ ነፃ መሆናቸው እንዲሁም ባርያ ወይንም ጋለሞታዎች እንዳልሆኑ ይታወቃል።

በኢብኑ ከቲር እንደተገለጸውም ሆነ በቁርአን ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው “ትዕዛዙ” ሴቶችን ከአስገድዶ ደፋሪ ለመከላከል ሳይሆን ለደፋሪዎች ስራቸውን ለማቅለል ይመስላል። እስላማዊ መዛግብትን ካገላበጥን ሒጃብ የሚያደርጉ ሙስሊም ሴቶች ጥሩና መልካም፣ ሒጃብ ምርጫቸው ካልሆነ ደግሞ እንደከፈሩ (እንደካዱ) እና ሴተኛ አዳሪዎች ተደርገው ይወሰዳሉ። በሚያሳዝን ሁኔታ ደግሞ እስልምና ከሴት ባሮች ጋር ግንኙነት ማድረግ (መድፈር)፣ ጋለሞታዎችንም በመህር (በክፍያ) ግንኙነት ማድረግ ይፈቅዳል። የሒጃብ ኮድ በትንሹ ግልፅ የሆነላችሁ ይመስለኛል።

ሳይንሱ ምን ይላል?

በመጨረሻም ግለሰቡ ያልተረዳቸውን ነገሮችን በማቅረብ ጽሑፌን ልደምድም። እዚህ ጋር  “ያልተረዳቸው” ብዬ ያስቀመጥኩት “የሳታቸው” ለማለት አስቸጋሪ ሆኖ ተሰምቶኝ ነው። መሳት ማለት የተወሰነ ሲሆን ኂሱ ላይ የተመለከትነው ግን ኃያሲው ጭራሽ ነገሩን እንዳልተረዳው ነው።

የፀሐይ ጨረር በቆዳችን ላይ ቀጥታ ሲያርፍ በሰውነታችን ቆዳ የሚገኘውን 7 ዲሀይድሮኮሌስትሮል የተሰኘውን ንጥረ ነገር ወደ ቫይታሚን ዲነ’ት እንዲቀየር ያደርገዋል። ሰውነታችን የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኝ ያስፈልጋል ሲባል በየትኛውም ሰዓት ፀሐይ ላይ መገኘት ማለት አይደለም። ከበቂ በላይ የሆነ ፀሐይ የቆዳ መቃጠልን ጨምሮ በርካታ እክሎችን ያስከትላል። በኅክምና የሚመከረው የጠዋት ፀሐይ ነው። ነገር ግን ግለሰቡ ደቂቃዎችንም ቆርጦ አስቀምጧል። “ዕውቁ ድረገፅ፣ በዘርፉ አንድ እርምጃ የተራመደው እገሌ” ወዘተ… በሚል ሐሳባቸውን በቅጡ እንኳ ሳያነብ አስቀምጧል። ወንድም ዳንኤል በዚህ ጉዳይ በቂ ምላሽ ስለሰጠ እዚህ ጋር መድገም አያስፈልግም። ይህ ወዳጃችን ሌላው ቀርቶ የምንጭ አጠቃቀስ እንዴት እንደሆነ እንኳ በቅጡ የተረዳ አይመስልም። ተለማማጅ ፀሐፊ መሆኑ ባይጠፋኝም ለጀማሪ ፀሐፊ ቀርቶ ለመጻፍ ፍላጎቱ ብቻ ላለው ሰው፣ ይህ ብቻም ሳይሆን ጀማሪ አንባቢ እንኳ የማያጣው ነገር እንዴት ሊሰወርበት እንደቻለ ግራ ነው። ግለሰቡ ስድብ፣ ዘለፋ፣ በእርሱ አነጋገር “ቅስም ሰባሪ ሐረጎች” ላይ ጊዜውን ከሚያጠፋ ምንጭ አጠቃቀስ ላይ የተወሰነ ትንሽ ጊዜ ቢሰጥ መልካም ይሆን ነበር። አንዲት ሐረግ ለመጥቀስ በርካታ ገፅ ማስቀመጡ አስገርሞን ሳያበቃ እንዲህ ብሎ ምንጩን አስቀምጧል፦

(📗The U.S. News Health team delivers accurate information about healthApril 12, 2021)

ይቅርታ ይደረግልኝና እንዲህ የሚል ምንጭ አጠቃቀስ ሳይ የመጀመርያዬ ነው። እንዲህ ያለ አጠቃቀስ ከየት እንዳገኘውም አልገባኝም። ለማንኛውም ወደ ሐሳቡ ስመለስ በሰአት ተለክቶ  “አንድ ሰው በቀን ውስጥ ይሄን ያህል ደቂቃ የፀሐይ ብርሃን በቂው ነው ” ተብሎ ሙግት አይቀርብም። ወዳጃችን ያነበበው “ሙያዊ ምክርን” (recommendation) ነው። ያ ሙያዊ ምክር የሚያገለግለው በየትኛው አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች ነው? ምን ዓይነት የቆዳ ቀለም ላላቸው ሰዎች ነው? አመጋገባቸው እንዴት ለሆነ ሰዎች ነው? የሰውነት መጠናቸው እንዴት ለሆነ ሰዎች ነው? በምን ዓይነት የእድሜ ክልል ላለ ሰው ነው? ይህን ሁሉ ማጣራት መቻል ነበረበት። ከላይ የዘረዘርኳቸው በጠቅላላ ከፀሐይ ብርሃን አወሳሰዳችን ላይ ሰፊ ልዩነት ያመጣሉ። ታድያ እንዲያው በደምሳሳው አስር አምስት ደቂቃ ነው ብሎ መደምደም፣ ብሎም ሙግት ማዋቀር እስከ ዛሬ ከሰማኋቸው ሙግቶች ሁሉ እጅግ የወረደው ነው። ይህ ግለሰብ ያገኘውን “ሙያዊ ምክሩን” እንኳ ሙግት ሲያዋቅርበት “ምን እንደሚልና ማንን እንደሚል” በቅጡ አልተረዳም። በእቅድ የፀሐይ ብርሃንን  ለማግኘት ወደ ባሕር ዳርቻዎች አልያ የፀሐይ ብርሃን ባለበት ስፍራ ለሚገኙ ሰዎች የሚመከርን ምክር እንደ እማኝ  በማቅረብ ሙግት  አዋቅሯል። ምንጭ አጠቃቀሱ ችግር ያለበት ቢሆንም በእኛ እገዛ ወዳጃችን የጠቆመንን ድረ ገፅ “እውነት ምን እንደሚል” ለማየት እንሞክር። እውነት ድረገፁን ጎብኝቶት ከኾነና ምን ዓይነት ሐሳብ እንዳስተላለፈ ተረድቶት ከኾነ ይህንን እንዴት ብሎ ተረድቶት ይሆን?

ምንጭ፡ https://health.usnews.com/health-care/patient-advice/articles/how-much-sun-do-you-need-for-vitamin-d

ወዳጃችን ጥሩ ሞጋች ቢሆን ቫይታሚን ዲ ከፀሐይ ብቻ አይገኝም የሚል ሙግት ማቅረብ ይችል ነበር። እኔም ብሆን ሌሎቹን እንጂ ይህንን ጉዳይ ጠንከር ብዬ ድምዳሜ አልሰጠሁበትም። ይህ በእንዲህ ቢሆንም ሰውነታችን በእራሱ በፀሐይ ብርሃን ብቻ በቂ ቫይታሚን ዲ ማምረት እየቻለ ሙስሊም በዝ በሆኑ ሀገራት ይህ ወረርሽኝ መሆኑ የሚነግረን ብዙ ነገር አለ። ወዳጃችን በሌላ አስተያየት መስጫ ሳጥን እንዳከለው በእውቀት ውስንነት ምክንያት “ፎሮፎር ይፍረድ” ብሎ ተሳልቋል። “The conversation” የተሰኘ መነሻውን አውስትራልያ አድርጎ በተለያየ አለም እንዲሁም በተለያየ ቋንቋ ጥናታዊ ፅሁፎችን በየዘርፉ ጥርሳቸውን በነቀሉ ሰዎች አማካኝነት የሚያስነብብ ድረገጽ ነው። እዚህ ድረገጽ ላይ ፕሮፌሰር ፒተር ምካፍሪ የተሰኘ የዘርፉ ባለሙያ እንዲህ ሲል ስለሒጃብ ያስቀምጣል። 

The niqab and burqa do prevent the intake of vitamin D from sunlight. But problems only occur when the person is unaware of the potential damage due to lack of sunlight and does not redress this by increasing their vitamin D intake through diet or supplements.

McCaffery, Peter. (2017). Fact Check: do the niqab and burqa prevent intake of vitamin D from sunlight? Accessed on 23 September 2022, from https://theconversation.com/fact-check-do-the-niqab-and-burqa-prevent-intake-of-vitamin-d-from-sunlight-78691

ትርጉም፦

ኒቃብ እና ቡርቃ ከፀሐይ ብርሃን  የሚገኘውን ቫይታሚን ይከለክላሉ። ነገር ግን ችግሮች የሚከሰቱት ግለሰቧ በፀሐይ ብርሃን እጥረት ምክንያት የሚደርስባትን ጉዳት ሳታውቅ በመቅረት [ከዚህ ያጣችውን] በአመጋገቧ የምታገኘውን የቫይታሚን ንጥረ ነገር በመጨመር ወይንም ተጨማሪ ማሟያ (መድኃኒት) በመውሰድ ሳታስተካክለው ስትቀር ነው።  (ፒተር ማካፈሪ)

በዚያው መጣጥፍ ውስጥ “Review” በሚል ንዑስ ርዕስ ስር እንደሚነበበው በዚህ ጉዳይ የፒተርን (ፕ/ር) ሐሳብ በመደገፍ የበርሚንግሀም ሙስሊም ዶክተር [ዘኪ ሐሰን-ስሚዝ] ሐሳቡን አስቀምጧል። ስለ ጉዳዩ የሚያውቅ ሰው ምንም እንኳ በእምነቱ ሙስሊም ቢሆን ልክ እንደ ኂስ አቅራቢው እንደልቡ አይናገርም።

ሙስሊም እህቶቻችን በበረሃ ተሸፋፍነው መዋሉ ምን ያህል ስቃይ እንደሆነ አይጠፋቸውም። ፀጉሯ በቂ ኦክጅን ባለማግኘቱ ፎሮፎር፣ መነቃቀል፣ ተባይ ወዘተ. ሊያጋጥማት እንደሚችል አይጠፋትም። ሒጃብ የፀሐይ ብርሃንን ብቻ ሳይሆን ንፋስን ጨምሮ ብዙ ነገሮችን እንዳናገኝ ይከለክላል። ኣካላዊም ብቻ ሳይሆን ስነ ልቦናዊና አእምሯዊ ተጽእኖዎች አሉት። ለድባቴ ይዳርጋል። የሒጃብ ማድረግ ችግሮች ቀላል የሚባሉ አይደሉም።

ስለ ግለሰቡ በሁለተኛው አስተያየት እንዳልኩት ይህንን ለመረዳት ከእራስ ጫማ፣ ሳጥን ውጭ መሆን ያስፈልጋል። ኅያሲው ወንድ እንደመሆኑ ከሌሎች ምልከታዎቹ እንደተገነዘብነው ካለበት ሳጥን ከቆመበት ጫማ ስለማይወጣ ብዙ ከእርሱ ልንጠብቅ አይገባንም።

ምክር እና መደምደምያ

ወዳጃችን ሃይማኖቴን ነቀፉብኝ በሚል ደምፍላት፣ ሰዎችን በማቃለል ሙግት እንደማይካሄድ ማወቅ አለበት። ይህ ዓይነቱ አካሄድ Ad hominem fallacy በመሆኑ በምክንያታዊ ሙግት ረገድ ፅዩፍ ነው። በርግጥ እኔ ይህንን ጽሑፍ ሳዘጋጅ ሙግት ለማዋቀር አይደለም። ግለሰቡ ለሙግትም የሚቀርብ ደረጃውን የጠበቀ ጽሑፍም አላዘጋጀም። ስለጉዳዩም በቅጡ አልተረዳም። ከላይ እንዳልኩትም የእኔን ጽሑፍ ለመተቸት የሚያበቃውን ነገር ቀርቶ የእኔን ጽሑፍ እንኳ በቅጡ አላነበበም። ሌላው ቢቀር ጽሑፉ ጨዋነት የለውም፣ ለምላሽም አይጋብዝም። ከዚህ ቀደም በሦስት ኡስታዞች የቀረበ ቪድዮ ተመልክቼ መልስ አዘጋጅቻለው። ታድያ ልክ እንደ እዚህ ግለሰብ ኡስታዞቹም ስላወሩት ነገር በቂ ግንዛቤ አልነበራቸውም። ነገር ግን ጨዋነት የተሞላበት አካሄዳቸው የምክንያት አቀራረባቸውም የሚያስመሰግናቸው ነው። ከማወቅ ጨዋ፣ ከተሳዳቢነት  ደግሞ ልሂቅ ሲኮን ለአካሄድም ጥሩ አይመጣም። ስድቦችህን ባበዛህ ቁጥር ቅስማቸው የሚሰበረው የምትፅፍባቸው ሰዎች ሳይሆኑ የምትፅፍላቸው አንባቢዎችህ ናቸው።


ሴቶች በእስልምና