ሙሐመድ ማንበብ እንደማይችል ጅብሪል አያውቅም ነበርን?

ሙሐመድ ማንበብ እንደማይችል ጅብሪል አያውቅም ነበርን?


በኢስላም ዕድሜ ጠገብ ትራኬ መሠረት ጅብሪል ወደ ሙሐመድ መጥቶ “አንብብ” (ኢቅረዕ) ሲለው የሙሐመድ ምላሽ “ማንበብ አልችልም” የሚል ነበር። ጅብሪል ሙሐመድን ሦስት ጊዜ ጨምቆ ቢያሠቃየውም ሦስቱንም ጊዜ የሙሐመድ ምላሽ “ማንበብ አልችልም” የሚል ነበር። “ጅብሪል የተባለው መንፈስ እውነተኛ መልአክ ከሆነ ማንበብ የማይችለውን ሰውዬ ጨምቆ ያሠቃየው ለምንድነው?” የሚል ጥያቄ ስናነሳ የሙስሊም ወገኖቻችን ምላሽ “ኢቅረዕ” የሚለው ቃል ሁለት ትርጉም እንዳለው፤ አንዱ “አንብብ” የሚል፣ ሌላኛው ደግሞ “በቃልህ አነብንብ” ማለት መሆኑን፤ ጅብሪል “ኢቅረዕ” ሲለው ሙሐመድ ጽሑፍ ማንበብ መስሎት “ማንበብ አልችልም” ብሎ እንደመለሰ ይነግሩናል። ይህንን ምላሽ በመስጠት ችግሩን የፈቱ ቢመስላቸውም ችግሩ እንዳልተፈታ ለመረዳት አእምሮን ትንሽ ማሠራት በቂ ነው። መልሳቸውን እንቀበልና ጅብሪል “ኢቅረዕ” ሲለው ጽሑፍ ሳይሆን በቃል የሚነበነበ ነገር እንዲያነበንብ እየነገረው ነበር እንበል። ሰው አንድን ነገር የሚያነበንበው አስቀድሞ በቃሉ ካወቀ ወይም ከተነገረው ነው። ሙሐመድ ጅብሪል ይዞት የመጣውን ቃል አስቀድሞ ባላወቀበት ሁኔታ ጅብሪል እንዲያነበንብ ብቻ ጠይቆት ጨምቆ ማስጨነቁ ተገቢ ነበረን? ምንም ነገር ሳይነግረውና ሐሳቡን ሳያብራራለት ዝም ብሎ ብቻ “አነብንብ!” ብሎ ጨምቆ ማሠቃየት ምን የሚሉት አረብኛ ነው? እስኪ ሙስሊሞች መልስ ስጡን?


ሙሐመድ