ይሄድልናል ወይስ ይሄድላቸዋል? ለሙስሊም ሰባኪ ስሁት ሙግት የተሰጠ መልስ

ይሄድልናል ወይስ ይሄድላቸዋል?

ለሙስሊም ሰባኪ ስሁት ሙግት የተሰጠ መልስ

የቅዱሳት መጻሕፍትን የመጀመርያ ቋንቋዎች ያለ ዕውቀት መጥቀስ የሚያዘወትር አንድ ሙስሊም ሰባኪ ኢሳይያስ 6፡8 ላይ የሚገኘው ኃይለ-ቃል የአማርኛ ትርጉም ትክክል አይደለም የሚል ሙግት አቅርቧል፡፡ ጥቅሱ በ1954 ነባር ትርጉም እንዲህ ይነበባል፡-

“የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።”

ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር ከአንድ በላይ አካላት እንዳሉት ከሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መካከል አንዱ ሲሆን የሥላሴን አስተምህሮ የማይቀበሉ አንዳንድ ወገኖች ለማስተባበል ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላሉ፡፡ ሙስሊሙ ሰባኪ ለዚሁ ዓላማ ያዘገጋጀውን ጽሑፍ ሙስሊም ወገኖቻችን በማሕበራዊ ገጾች ሲቀባበሉት ስለተመለከትን መልስ ለመስጠትና ስህተቶቹን ለማረም ወስነናል፡፡ እንዲህ ሲል ይጀምራል፡–

አብዱል

“ሰፕቱጀንት” ወይም “ሰፕቱአጀንት” Ἑβδομήκοντα” ማለት “ሰባ” ማለት ሲሆን በ 280 ቅድመ-ልደት በአሌክሳንድያ ይኖሩ የነበሩ የግሪክ አይሁዳውያን 70 ምሁራን ስም ነው፥ በሮማውያን ቁጥር ምልክት”LXX” ይባላል። እነዚህ ምሁራን 72 ነበሩ፥ ሁለቱ ሲሞቱ ሰባው ሊቃናት የዕብራይስጡን ቅዱሳን ጽሑፎች ወደ ሄለናዊ ግሪክ ኮይኔ ተርጉመውታል። እዚህ ትርጉም ላይ ለዚህ ሕዝብ ማንስ ይሄድላቸዋል? የሚል ኃይለ-ቃል አለ፦
ኢሳይያስ 6፥8 የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ለዚህ ሕዝብ ማንስ ይሄድላቸዋል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ”። καὶ ἤκουσα τῆς φωνῆς Κυρίου λέγοντος· τίνα ἀποστείλω, καὶ τίς πορεύσεται πρὸς τὸν λαὸν τοῦτον; καὶ εἶπα· ἰδοὺ ἐγώ εἰμι· ἀπόστειλόν με.

ልብ አድርግ የሚለው “ይሄድላቸዋል” ነው። ለማን ሲባል “ለዚህ ሕዝብ” ኢሳይያስም በብዜት “እኔን ላኩኝ” ሳይሆን በነጠላ “እኔን ላከኝ” ብሏል፥ ጌታም፦ “ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም” በላቸው” አለ፦

ኢሳይያስ 6፥9 ”እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም” በላቸው”።

ነገር ግን ከግሪክ ሰፕቱጀት 1000 ዓመት በኃላ 875 ድኅረ-ልደት የተዘጋጀው ማሶሬቲክ እደ-ክታብ ላይ በተቃራኒው ማንስ ይሄድልናል? የሚል ኃይለ-ቃል አለ፦

ኢሳይያስ 6፥8 የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ”። וָאֶשְׁמַ֞ע אֶת־קֹ֤ול אֲדֹנָי֙ אֹמֵ֔ר אֶת־מִ֥י אֶשְׁלַ֖ח וּמִ֣י יֵֽלֶךְ־לָ֑נוּ וָאֹמַ֖ר הִנְנִ֥י שְׁלָחֵֽנִ

ትክክሉ የቱ ነው? ይሄድላቸዋል የሚለው የግሪክ ሰፕቱጀንት ወይስ ይሄድልናል የማሶሬቲክ እደ-ክታብ? ሁለቱን ለመዳኘት ከግሪክ ሰፕቱጀንት በፊት የነበረውን የነቢያት ፓሌዎ ዕብራይስጥ ጽሑሮች ጠፍተዋል፥ ግን ከደኃራይ ማሶሬቲክ ይልቅ ቀዳማይ ሰፕቱጀንት ሚዛን ይደፋል።

መልስ

ወደ ዋናው ነጥብ ከመግባታችን በፊት በነዚህ ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ስህተቶች ስለሚታዩ ማስተካከል አስፈላጊ ነው፡፡ የመጀመርያው ሰብቱጀንት የላቲን ቃል ነው፤ በመሆኑም Ἑβδομήκοντα የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን “ሄብዶሜኮንታ” ተብሎ ነው የሚነበበው፤ ትርጉሙም ሰባ[ዎቹ] ማለት ነው፡፡ ሙስሊሙ ሰባኪ ግሪክ ማንበብ ስለማይችል ጽሑፉ ምን እንደሚል ሳያውቅ ነው ኮፒ አድርጎ የለጠፈው፡፡ የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ታሪክ ዋና ምንጭ እንደሆነ ከሚታመን አርስቲያስ ከተሰኘ አይሁዳዊ ጸሐፊ የተላለፈ እንደሆነ ከሚገልፅ ጥንታዊ ደብዳቤ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው አይሁዳውያን ሊቃውንቱ በግብፁ ፈረዖን ፕቶለሚ ፍላዴልፈስ ጥሪ ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ የተላኩ እንጂ የእስክንድርያ ነዋሪዎች አልነበሩም፡፡ ቁጥራቸውም በአንዳንድ አፈ ታሪኮች መሠረት ሰባ የነበረ ሲሆን የአርስቲያስ ደብዳቤ ደግሞ ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ስድስት ስድስት ሊቃውንት እንደተመረጡና ቁጥራቸውም ሰባ ሁለት መሆኑን ይናገራል፡፡ ሁለቱ ሞተው ሰባዎቹ ተርጉመዋል የሚለውን ታሪክ ሙስሊሙ ሰባኪ ከየት እንዳመጣው ግልፅ አይደለም፡፡

ወደ ዋናው ነጥብ ስንገባ፤ ይህ ሙስሊም ጸሐፊ ከማሶሬቱ የእብራይስጥ ብሉይ ኪዳን የእጅ ጽሑፍ የሚቀድም ሌላ የእጅ ጽሑፍ የሌለ በማስመሰል የተናገረው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በቁምራን ዋሻዎች ውስጥ ከተገኙት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው የኢሳይያስ ጥቅልል ከማሶሬቱ ቅጂ ቢያንስ በ1000 ዓመታት የሚቀድም ሲሆን ኢሳይያስ 6፡8 ላይ የሚገኘው ጥቅስ ከማሶሬቱ ቅጂ ጋር ፍፁም አንድ ነው፡፡ የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ሙሉ በሙሉ ተተርጉሞ የተጠናቀቀው 132 ዓ.ዓ. ገደማ ሲሆን የኢሳይያስ ጥቅልል የተገለበጠበት ዘመን ከዚህ ጋር ተፎካካሪ እንዲያውም ሊቀድም የሚችል ነው፡፡ ከኢሳይያስ ጥቅልል የሚቀድም የሰብዓ ሊቃናት የትንቢተ ኢሳይያስ የእጅ ጽሑፍ አለመኖሩና ከአንድ ሺህ ዓመታት በኋላም ቢሆን ልዩነት ሳያሳይ መቆየቱ በእብራይስጡ ላይ ይበልጥ እንድንተማመን ምክንያት ይሆነናል፡፡ ስለዚህ ትክክለኛው ንባብ በሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ውስጥ የሚገኘው ሳይሆን በእብራይስጡ ውስጥ የሚገኘው “ማንስ ይሄድልናል” የሚለው መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህ ንባብ በአሌፖ ኮዴክስም ሆነ በዌስትሚንስትር ሌኒንግራድ ኮዴክስ የተረጋገጠ ነው፡፡ ለዚህም ነው የታወቁት የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ሁሉ “For Us” በማለት ወይም ተመሳሳይ የሆነ ሐሳብ ባላቸው ቃላት የተረጎሙት፡፡ በማስከተል 40 ትርጉሞችን በማስረጃነት እናቀርባለን፡-

New International Version
Then I heard the voice of the Lord saying, “Whom shall I send? And who will go for us?” And I said, “Here am I. Send me!”

New Living Translation
Then I heard the Lord asking, “Whom should I send as a messenger to this people? Who will go for us?” I said, “Here I am. Send me.”

English Standard Version
And I heard the voice of the Lord saying, “Whom shall I send, and who will go for us?” Then I said, “Here I am! Send me.”

New American Standard Bible
Then I heard the voice of the Lord, saying, “Whom shall I send, and who will go for us?” Then I said, “Here am I. Send me!”

King James Bible
Also I heard the voice of the Lord, saying, Whom shall I send, and who will go for us? Then said I, Here am I; send me.

Holman Christian Standard Bible
Then I heard the voice of the Lord saying: Who should I send? Who will go for us? I said: Here I am. Send me.

International Standard Version
Then I heard the voice of the LORD as he was asking, “Whom will I send? Who will go for us?” “Here I am!” I replied. “Send me.”

NET Bible
I heard the voice of the sovereign master say, “Whom will I send? Who will go on our behalf?” I answered, “Here I am, send me!”

GOD’S WORD® Translation
Then I heard the voice of the Lord, saying, “Whom will I send? Who will go for us?” I said, “Here I am. Send me!”

Jubilee Bible 2000
After this, I heard the voice of the Lord saying, Whom shall I send, and who will go for us? Then I answered, Here am I; send me.

King James 2000 Bible
Also I heard the voice of the Lord, saying, Whom shall I send, and who will go for us? Then said I, Here am I; send me.

American King James Version
Also I heard the voice of the Lord, saying, Whom shall I send, and who will go for us? Then said I, Here am I; send me.

American Standard Version
And I heard the voice of the Lord, saying, Whom shall I send, and who will go for us? Then I said, Here am I; send me.

Douay-Rheims Bible
And I heard the voice of the Lord, saying: Whom shall I send? and who shall go for us? And I said: Lo, here am I, send me.

Darby Bible Translation
And I heard the voice of the Lord saying, Whom shall I send, and who will go for us? And I said, Here am I; send me.

English Revised Version
And I heard the voice of the Lord, saying, Whom shall I send, and who will go for us? Then I said, Here am I; send me.

Webster’s Bible Translation
Also I heard the voice of the Lord, saying, Whom shall I send, and who will go for us? Then said I, Here am I; send me.

World English Bible
I heard the Lord’s voice, saying, “Whom shall I send, and who will go for us?” Then I said, “Here I am. Send me!”

Young’s Literal Translation
And I hear the voice of the Lord, saying: ‘Whom do I send? and who doth go for Us?’ And I say, ‘Here am I, send me.’

Lexham English Bible

Then I heard [the] voice of the Lord saying, “Whom shall I send? And who will go for us?” And I said, “I [am] here! Send me!”

The Orthodox Jewish Bible

Also I heard the voice of Adonoi, saying, Whom shall I send, and who will go for Us? Then said I, Hineini; send me.

ትክክለኛው ንባብ “ማንስ ይሄድልናል?” የሚለው መሆኑ በበቂ ማስረጃዎች የተረጋገጠ በመሆኑ ምክንያት የዚህ ጥቅስ አንድምታ የማይመቻቸው የይሖዋ ምስክሮች ከላይ ከሚገኙት ትርጉሞች ጋር በሚስማማ መንገድ ተርጉመውታል፡-

Then I heard the voice of Jehovah saying: “Whom shall I send, and who will go for us?” And I said: “Here I am! Send me!” (New World Translation)

ይህንን በአማርኛ ትርጉማቸው እንዲህ አስቀምጠውታል፡- “ከዚያም የይሖዋ ድምፅ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁ። እኔም “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!” አልኩ።” (የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም)

የጥቅሱን ትክክለኛ ንባብ የይሖዋ ምስክሮች እንኳ እየመረራቸውም ቢሆን ተቀብለውታል፡፡ ሙስሊሙ ጸሐፊ የእብራይስጡን ንባብ ለማጣጣል የሄደበት መንገድ አላዋቂነቱን የሚገልጥ ነው፡፡

ኢሳይያስ በብዙ ቁጥር “እኔን ላኩኝ” ሳይሆን በነጠላ “እኔን ላከኝ” ብሏል የሚለው ሙግት “ማንስ ይሄድልናል” የሚለው በብዙ ቁጥር የመነገሩን እውነታ አይለውጥም፡፡ ኢሳይያስ ከሥለሴ አካላት መካከል እያናገረው ለነበረው ለአንዱ አካል፣ ማለትም ለመንፈስ ቅዱስ “እኔን ላከኝ” ብሎ ምላሽ እየሰጠ ነበር፡፡ ይህንን በምን እናውቃለን? አዲስ ኪዳን ላይ ሄደን ስንመለከት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ንግግር ለኢሳይያስ የተናገረው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ይነግረናል፡-

“እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን፦ ወደዚህ ሕዝብ ሂድና፦ መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም…” (የሐዋርያት ሥራ28፡25-26)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እየጠቀሰ የነበረው ኢሳይያስ 6 ላይ የሚገኘውን ቃል ነው፡-

“የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ። እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም በላቸው።” (ኢሳይያስ 6፡8-9)

ስለዚህ ኢሳይያስ “እኔን ላከኝ” ብሎ መልስ የሰጠው ለመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን ለኢሳይያስ የተናገረው አዶናይ በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ መሆኑ መነገሩ የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት በማረጋገጥ የሥላሴን አስተምህሮ የሚደግፍ ጠንካራ ማስረጃ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

አብዱል

ሙግቱን እናጥብብ እና “ይሄድልናል” ቢባልስ ሥላሴን ያሳያልን? በፍጹም። ምክንያቱን አንድ ማንነት ብዜት ተሳቢ ተውላጠ-ስም ተጠቀመ ማለት ያ ማንነት ሥላሴ ነበር ማለት አይደለም፥ “ኒ” נִי የነበረው ነጠላ ተሳቢ ተውላጠ-ስም በብዜት “ኑ” נוּ በሚል መጥቷል፦

ዕዝራ 4፥7 ”በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤል ተባባሪዎቹም ለፋርስ ንጉሥ ለአርጤክስስ ጻፉ”።
ዕዝራ 4፥18 ሰላም! ”አሁንም “ወደ እኛ” עֲלֶ֑ינָא የላካችሁት ደብዳቤ በፊቴ ተተርጕሞ ተነበበ”።

ልብ አድርግ “አርጤክስስ” የሚለው ቃላ ላይ መነሻ ቅጥያ ያለው “ለ” የሚለው መስተዋድድ ለንጉሡ ብቻ የተላከ ደብዳቤ ነው። ንጉሡ ግን በዐረማይክ “ና” נָא ብሎ በብዜት ተጠቅሟል፥ ግን ንጉሡ አንድም ሦስትም ሆኖ አይደለም፦

መልስ

ለንጉሥ የሚጻፍ ደብዳቤ ለግለሰብ ሳይሆን ለመንግሥት የሚጻፍ ነው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ በዙርያው ያሉትን አማካሪዎቹንና የመንግሥቱን ባለሥልጣናት ሁሉ በመወከል “እኛ” ብሎ መናገር ይችላል፡፡ ንጉሡ “እኛ”ብሎ የተናገረው ራሱን ለማክበር ነው እንዳይባል እንዲህ ያለው አገላለፅ በዚያ ዘመን በፋርስ ምድር የተለመደ ስለመሆኑ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡ ስለዚህ ጥያቄው እግዚአብሔር ሉኣላዊ ሥልጣኑን በማጋራት ፍጡራንን በራሱ ላይ ደምሮ “እኛ” ይላል ወይ? የሚል ነው፡፡

አብዱል

ዳንኤል 2፥25 የዚያን ጊዜም አርዮክ ዳንኤልን ፈጥኖ ወደ ንጉሡ አስገባውና፦ “ከይሁዳ ምርኮኞች ያለውን ለንጉሡ ፍቺውን የሚያስታውቀውን ሰው አግኝቼአለሁ” አለው። ዳንኤል 2፥36 ሕልሙ ይህ ነው፥ ”አሁንም ፍቺውን በንጉሡ ፊት እንናገራለን” נֵאמַ֥ר ።

“አማር” אֲמַר በሚል ግስ ላይ “ኔ” נֵ የሚል “ባለቤት ተውላጠ-ስም አለ። አርዮክ ወደ ንጉሡ ያስገባው ዳንኤልን ብቻ ሆኖ ሳለ ዳንኤን በብዜት “እንናገራለን” ብሏል፥ ግን ዳንኤል አንድም ሦስትም ሆኖ አይደለም።

መልስ

ነቢዩ ዳንኤል እየተናገረ የነበረው ሦስቱን ጓደኞቹን (አናንያ፣ አዛርያ እና ሚሳኤልን) በመወከል መሆኑን ከአውዱ መገንዘብ እንችላለን፡፡ የሕልሙ ትርጓሜ የዳንኤልና የጓደኞቹ የጸሎት መልስ እንጂ የዳንኤል ብቻ አይደለም (ዳን. 2፡17-18)፡፡ ስዚህ ዳንኤል ብዙ ቁጥር መጠቀሙ ጓደኞቹንም ጭምር በመወከል በንጉሡ ፊት መቅረቡን የሚያሳይ እንጂ አንዳንዶች አንደሚሉት ራሱን በማክበር ነገሥታት “እኛ” እንደሚሉት (pluralis majestatis) እየተናገረ አይደለም፡፡ በባቢሎን ምድር ምርኮኛ የነበረው ዳንኤል በንጉሥ ፊት ቀርቦ ልክ እንደ ንጉሥ በእኛነት ራሱን ሊገልፅ ይችላል ተብሎ ማሰብ በራሱ የማይመስል ነው፤ በዘመኑም የሚታወቅ ልማድ ስለመሆኑ ማስረጃ የለም፡፡

አብዱል

ሙግቱን አሁንም እናጥብበውና “ይሄድልናል” የሚለው ከአንድ በላይ ላሉ ማንነቶች ነው ነው ብንል እንኳን አሁንም ሥላሴን በፍጹም አያሳይም። ዐውዱ ላይ መላእክት አሉ፥ ኢሳይያስ ሲናገር ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እርሱ መጥቶ፦ “እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ” አለው፦
ኢሳይያስ 6፥2 “ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር”። ኢሳይያስ 6፥5-7 ”እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ። ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ። አፌንም ዳሰሰበትና፦ እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ፡ አለኝ።

እንደ ባይብሉ እግዚአብሔር የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው አሉ፥

መልስ

መላእክት እንደ ኢሳይያስ ሁሉ የእግዚአብሔር ባርያዎችና ተላኪዎች እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ላኪዎች አይደሉም፡፡ ቀደም ሲል በአዲስ ኪዳን ጥቅስ አስደግፈን እንደተመለከትነው ኢሳይያስን ሲያናግረው የነበረው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሲሆን “ማንስ ይሄድልናል” ብሎ ሲጠይቅ አብና ወልድን በመወከል መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ሉኣላዊ ሥልጣኑን በማጋራት ፍጡራንን በራሱ ላይ ደምሮ በብዙ ቁጥር ተናግሮ አያውቅም፡፡ ነገር ግን ሙስሊሙ ጸሐፊ እግዚአብሔር ከፍጡራን ጋር ራሱን ቆጥሮ “እኛ” ያለበትን ጥቅስ አግኝቻለሁ ይለናል፡፡ እስኪ እንስማው፡-

አብዱል

ያዕቆብ ከእግዚአብሔር እና ከመልአኩ ጋር ስለተነጋገረ “ከእኛ ጋር ተነጋገረ” ብሏል፦
1ኛ ነገሥት 22፥19 “እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
ሆሴዕ 12፥4 ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ ”በዚያም “ከ-እኛ” ጋር עִמָּֽנוּ ተነጋገረ”።

አየክ “ኑ” נוּ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ከመላእክት ጋር እንዳገለገለ? በምንም ሒሳብ ሥላሴን አያመለከትም።

መልስ

ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔርን ሥላሴነት ከሚያመለክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በመጀመርያ ደረጃ “መላክ” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ትርጉም “መልእክተኛ” ማለት ሲሆን ቅዱሳን መላእክትን ብቻ ሳይሆን የሰው መልእክተኞችን እንዲሁም ከአብ ዘንድ የተላከውን ወልደ እግዚአብሔርን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡ በእብራይስጥ ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ “መላክ ያሕዌ” ተብሎ የሚታወቅ፣ አምላክ መሆኑ የተነገረለትና “ያሕዌ” በሚለው ስመ እግዚአብሔር የተጠራ አንድ አካል አለ፡፡ ይህ አካል በልደት ወደ ዓለም ከመግባቱ በፊት ወልደ እግዚአብሔር የተገለጠበት መልክ መሆኑን ቅዱስ አውጉስጢኖስ፣ ኢዮስቢዮስ እና ጠርጡሊያኖስን የመሳሰለሉት ጥንታውያን የቤተክርስቲያን አበው ይናገራሉ http://www.newadvent.net/cathen/01476d.htm ይህም “ቴዎፋኒ” በሚል ነገረ መለኮታዊ ቃል የሚታወቅ ሲሆን ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች አሉት፡፡ ለምሳሌ ያህል ነቢዩ ሆሴዕ “መልአኩ” ብሎ የጠራው ለያዕቆበ የተገለጠለት አካል እንደ ማንኛውም መልአክ ሳይሆን መለኮት መሆኑን በዘፍጥረት ውስጥ የተጻፈውን ታሪክ ስናነብ በግልፅ እንመለከታለን፡-

“ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር። እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ ያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ። እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው። እንዲህም አለው፦ ስምህ ማን ነው? እርሱም፦ ያዕቆብ ነኝ አለው። አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና። ያዕቆብም፦ ስምህን ንገረኝ ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው።” (ዘፍጥረት 32፡24-30)

ይህ ጥቅስ ከያዕቆብ ጋር የታገለው አካል እግዚአብሔር ራሱ መሆኑን ይነግረናል፡፡ ሙስሊሙ ጸሐፊ ቆርጦ የተወውን ወሳኝ ክፍል በማከል ሆሴዕ የተናገረውን በማንበብ ከዚህ ጋር ብናስተያይ ይህ እውነት ይበልጥ ግልፅ ይሆንልናል፡-

“በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፤ ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ። እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤ የመታሰቢያው ስም እግዚአብሔር ነው።” (ሆሴዕ 12፡4-6)

ነብዩ ሆሴዕ ያዕቆብ የታገለው አምላክን፥ ታግሎ ያሸነፈውም መልአኩን መሆኑን ይነግረናል። ያዕቆብ አንዴ አምላክን ሌላ ጊዜ ደግሞ መልአክን አልታገለም፤ ነገር ግን አንድ አካልን ነው አንዴ የታገለው፡፡ ከዝያ ገጠመኝ በኋላ ያዕቆብ የተገለጠለትን አካል “እግዚአብሔር” በማለት ጠርቶታል፡፡ ሆሴዕም የሚያረጋግጥልን ይህንኑ ነው፡፡ ስለዚህ “በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ” ሲል በሥላሴነት የሚኖረው አምላክ እንዳናገረው የሚያሳይ እንጂ እግዚአብሔር ከፍጡር ጋር ራሱን በመቁጠር “እኛ” እንዳለ አያሳይም፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ በሌላ ጽሑፍ እንመለስበታለን፡፡

አብዱል

በተረፈ አንዱ አምላክ አንድ ማንነት ኖሮት ለግነት እኛነት ሲጠቀም በውስጡ ሦስት አባላት አሉት ብሎ ሌሎችን ማንነቶችን በማንነቱ ላይ ማጋራት ሺርክ ነው። እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ፦
6፥19 «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

መልስ

በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ እግዚአብሔር አምላካችን በእኛነት ራሱን ገልጿል፡፡ ለምሳሌ ያህል የመጀመርያውን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የመጀመርያውን ምዕራፍ ስንመለከት እንዲህ ይላል፡-

“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” (ዘፍጥረት 1፡26)

የሥላሴን ትምሕርት የማይቀበሉ ወገኖች ይህንን ጥቅስ በሁለት መንገዶች ለማብራራት ሞክረዋል፡፡ የመጀመርያው እግዚአብሔር “እንፍጠር” ሲል ከመላእክት ጋር መማከሩ ነው የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ራሱን በማክበር ልክ ነገሥታት “እኛ” በሚሉት መንገድ መናገሩ ነው የሚል ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁለቱ ምላሾች በፍጹም የሚያስኬዱ አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር ፍጥረትን በመፍጠር ሂደት ውስጥ መላእክትን እንዳሳተፈ የሚገልፅ አንድም የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃ አናገኝም፡፡ በተጻራሪው እግዚአብሔር አምላካችን ብቻውን ፍጥረትን እንደፈጠረና አጋዥ እንዳልነበረው ይናገራል (ኢሳይያስ 44፡24)፡፡ ስለዚህ በሥላሴነት ከሚኖረው አንዱ አምላክ ውጪ የሚገኝ አካል በመፍጠር ሒደት ውስጥ አልተሳተፈም፡፡ ራስን ለማክበር በብዙ ቁጥር መናገር በጥንቱ እብራይስጥ ውስጥ ቅዱሳት መጻሕፍት በተጻፉበት ዘመን ስለማይታወቅ ሁለተኛውም ምላሽ ሊያስኬድ አይችልም፡፡ እንዲህ ያለ አነጋገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ቢሆን ማስረጃ የለውም፡፡ ስለዚህ ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር ከአንድ በላይ አካላት እንዳሉት የሚያመለክት ነው፡፡

ማጠቃለያ

የሥላሴ አስተምህሮ እግዚአብሔር በመለኮቱ ፍፁም አንድ መሆኑን አፅንዖት የሚሰጥ በመሆኑ ሙስሊሞች በመድብለ አማልክታዊነት መፈረጃቸው አላዋቂነት ነው፡፡ አስተምህሮው በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የፀና መሠረት ያለው፣ ቅድመ ኒቅያ በነበሩት ሐዋርያውያን አበው የተብራራ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ሆነ ታሪካዊ መሠረት ያለው አስተምህሮ ነው፡፡

በአንፃሩ ግን “አላህ አንድ ነው” የሚለው የእስልምና አስተምህሮ በቁርአን ያልተብራራ እንዲሁ በደፈናው የሚነገር ትርጉም አልባ መፈክር ነው፡፡ ሙስሊሞች አላህ አንድ መሆኑን ሲናገሩ በማንነት (Person)፣ በባሕርይ (Essene) ወይንስ በባሕርያተ መለኮት (Divine Attributes)? ለሚለው ጥያቄ ከቁርአን በቂ ምላሽ መስጠት አይችሉም፡፡ ቁርአንም ሆነ ሐዲስ ስለ አላህ አንድነት ሲናገሩ “እርሱ እንዲህና እንዲያ አይደለም” ከሚል አሉታዊ አገላለፅ በዘለለ ምን ማለታቸው እንደሆነ ስለማያብራሩ ሙስሊም ወገኖች አላህ አንድ ነው ሲሉ የሒሳብ ቁጥር አንድ ነውን? በማንነቱ አንድ ነውን? በባሕርዩ አንድ ነውን? በቅርፁ አንድ ነውን? በመንፈስ አንድ ነውን? ወዘተ. የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ አይችሉም፡፡

እስላማዊውን አሓዳዊነት ለመግለፅ ጥቅም ላይ የሚውለው “ተውሒድ” የሚለው ቃል በቁርአንም ሆነ በሐዲስ ውስጥ የማይገኝ ሲሆን ሙስሊም ሊቃውንት ከሙሐመድ ሞት ከክፍለ ዘመናት በኋላ የፈጠሩት ነው፡፡ የቃሉ ትርጉም ነጠላ አንድነትን የሚገልፅ ሳይሆን የተለያዩ ነገሮችን ማዋሓድን ወይም ወደ አነድነት ማምጣትን (Unification) የሚያመለክት ነው፡፡ ስለዚህ በተውሒድ ፅንሰ ሐሳብ የተገለፀው የአላህ አንድነት ብዝሃ አንድነት እንጂ ነጠላ አንድነት አይደለም፡፡ ሙስሊም ሊቃውንት ይህንን አስተምሕሮ ለማጎልበትና ለመተንተን በክፍለ ዘመናት መካከል ብዙ ፍትጊያዎችን ያሳለፉ ሲሆን አንዳንድ ጥያቄዎችን ለማስወገድ ደም አፋሳሽ ፍልሚያዎች ተደርገዋል፡፡ የግጭት ሰበብ ከነበሩት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል አንዱ የቁርአንን ዘላለማዊነት የተመለከተው ነው፡፡ ቁርአን ዘላለማዊና ያልተፈጠረ ከሆነና ከአላህ የተለየ ነገር (distinct from Allah) ከሆነ መለኮታዊ ባሕርይ ያለው ከአላህ ጋር ሁለት ተብሎ የሚቆጠር ሌላ ነገር ስለሚሆን ከአላህ አንድነት ጋር የማስታረቂያ መንገድ ሊገኝለት አልቻለም፤ በዚህም ሳቢያ بلا كيف‎ “ቢላ ከይፈ” (እንዴት ተብሎ መጠየቅ የማይቻል) ተብሎ ተዘግቷል፡፡ ሙተዚላት የተባሉ ከስምንተኛው እስከ አሥረኛው ክፍለ ዘመናት መካከል በኢራቅ ምድር የተነሱ ሙስሊም ቡድኖች ቁርአን ያልተፈጠረ ነው የሚለው አስተምህሮ በአላህ አንድነት ዙርያ የሚፈጥረው መልስ የሌለው ጥያቄ ስላሳሰባቸው ቁርአን ፍጡር መሆኑን ያምኑ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ጭፍጨፋ ተፈፅሞባቸው ቁርአን ፍጡር አለመሆኑን የሚያምነው ቡድን ድል በመንሳት የሙተዚላትን ጥያቄዎች ሳይመልስ “ቢላ ከይፈ!” በሚል ኢ-ምክንያታዊ ቃል ዘግቶታል፡፡ ስለዚህ ሙስሊም ኡስታዞች በወጉ ያልተረዱትን የሥላሴ አስተምህሮ ለማስተባበል ከሚቸገሩ የገዛ ሃይማኖታቸው መሠረት የሆነው ተውሒድ እንዴት የእውነተኛውን አምላክ አንድነት ሊገልፅ እንደሚችልና የቁርአንን ዘላለማዊነት ከመሳሰሉት አስተምህሮዎቻቸው ጋር እንዴት ሊታረቅ እንደሚችል ቢያብራሩ ጥሩ ነው፡፡

ሥላሴ

መንፈስ ቅዱስ ያሕዌ ነው!

ለእስልምና ሙግቶች ምላሽ