ኢየሱስ አምላክ ከሆነ በማር 15፡37 ላይ ነፍሱን ለማነው የሚሰጠው?
-
ማርቆስ 15፡37 “ኢየሱስ በታላቅ ድምጽ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ” ይላል፡፡ ለመሆኑ ነፍሱን ለማነው የሚሰጠው? ራሱ ለራሱ ነው ወይስ ሰጪውና ተቀባዩ የተለያዩ ናቸው?
ማርቆስ ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን መስጠቱን እንጂ ምን ብሎ እንደጮኸ አልነገረንም፡፡ ነገር ግን ሉቃስ ነግሮናል፡- “ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ፡፡ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ፡፡” (ሉቃስ 23፡46)፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ነፍሱን የሰጠው ለአብ ነው፡፡