“እግዚአብሔር ወልድ” ሞቷልን? አምላክ (እግዚአብሔር) ይሞታል?
-
“እግዚአብሔር ወልድ” ሞቷልን? ክርስቲያኖች “አዎን” ይላሉ? ታዲያ አምላክ (እግዚአብሔር) ይሞታል? የአምላክ ክፍልና አካል ይሞታል? እንዲያው እንዴት ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን “እግዚአብሔር ወልድ” ብሏልን? እስቲ የቱ ጋር?
የኢየሱስን ሞት በተመለከተ ቀደም ሲል በምዕራፍ 1 ጥያቄ ቁጥር 8 ላይ መልስ ስለሰጠን አንደግምም፡፡ ጠያቂው ሙግታቸው ደካማ መሆኑን ስለተገነዘቡ ተጨማሪ ጥያቄ በማከል ለማጠናከር ሞክረዋል፡፡ ኢየሱስ ወይም ወልድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታዎች ላይ አምላክ ወይም እግዚአብሔር ተብሏል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ወልድ መባሉ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው? ወልድ እግዚአብሔር መሆኑ ከተነገረባቸው ጥቅሶች በመነሳት “እግዚአብሔር ወልድ” ማለት ስህተት ከሆነ ሙስሊሞች “ነቢዩ ሙሐመድ”፣ “ቅዱስ ቁርኣን”፣ መልአኩ ጂብሪል፣ ወዘተ. በማለት ስለምን ይናገራሉ? እንዲያው አንዴም ቢሆን ቁርኣን ሙሐመድን “ነቢዩ ሙሐመድ በሉት”፣ ቁርኣንን “ቅዱስ ቁርኣን ብላችሁ ጥሩት” ጂብሪልን “መልአኩ ጂብሪል በሉት” ብሏልን? እስኪ የቱ ጋር?