ምንም ቢሰሩ ሁሉም ክርስቲያኖች በኢየሱስ መሰቀል በማመን ብቻ መንግስተ ሰማያት ይገባሉ?

 


  1. ምንም ቢሰሩ ሁሉም ክርስቲያኖች በኢየሱስ መሰቀል በማመን ብቻ መንግስተ ሰማያት የሚገቡ ከሆነ የኢየሱስ አስተምህሮት ምኑ ላይ ነው ጥቅሙ? ኢየሱስ “መልካም” “እኩይ” እያለ ሲያብራራቸው የነበሩት አስተምህሮቶች ሁሉ ምን ይፈይዳሉ? ካላችሁ በኢየሱስ መሰቀል አምነው ኢየሱስ «ክፉ» ያላቸውን ተግባራት ቢፈጽሙና ባይፀፀቱ ገሀነም የገባሉ ማለት ነውን?

መጽሐፍ ቅዱስ “ምንም ቢሰሩ ሁሉም ክርስቲያኖች በኢየሱስ መሰቀል በማመን ብቻ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ” አይልም፡፡ ጠያቂው ይህንን ቅጥፈት ከየት እንዳመጡ ማስረጃ እንዲጠቅሱ እንጠይቃቸዋለን፡፡ ከሙስሊሞች ውጪ የሚገኙት የዓለም የታሪክ ተመራማሪዎች ሁሉ ኢየሱስ መሰቀሉን ያምናሉ፡፡ ኢየሱስን የሰቀሉት ሮማውያንና እንዲሰቀል አሳልፈው የሰጡት አይሁዶችም ጭምር መሰቀሉን ያምናሉ፡፡ ሰው የዘለዓለምን ሕይወት የሚያገኘው ኢየሱስ ስለ ኃጢአቱ ሲል መሰቀሉን፣ መሞቱንና መነሳቱን በማመን እርሱን ሲከተል እንጂ “ተሰቅሏል” ብሎ በማመን ብቻ አይደለም፡፡ እምነቱ ደግሞ በሥራ የሚገለጥ መሆን ያስፈልገዋል፡፡ አምኛለሁ እያለ እንደ ልቡ ፈቃድ የሚኖር ሰው እምነቱ የውሸት ነው፡፡ ለበለጠ ማብራርያ ምዕራፍ 4 ቁጥር 8ን ይመልከቱ፡፡