ኢየሱስ “ካስፈለገ አባቴን ብጠይቀው ከዐስራ ሁለት ክፍል ሰራዊት የሚበልጡ መላእክት የማይሰድልኝ ይመስልሃል?” ካለ ‘አምላኬ’ አምላኬ ለምን ተውከኝ? ሲል እንዴት የተባለው ጦር መጥቶ ሳያድነው ቀረ?

 


  1. ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ “በዘጠኝም ሰዓት ኢየሱስ ኤሎሄ ኤሎሄ ለማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸለ፤ ትርጓሜውም “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው (የማርቆስ ወንጌል 15: 34 እና ማቴዎስ 27: 46) ሲል አምላክ ከስቅለቱ እንዲያድነው በጩኸት ለምኗል በማቴዎስ 26: 53 ላይ “ካስፈለገ አባቴን ብጠይቀው ከዐስራ ሁለት ክፍል ሰራዊት የሚበልጡ መላእክት የማይሰድልኝ ይመስልሃል?” ሲል ተናግሮ ነበር፡፡ ታድያ ኢየሱስ ‘አምላኬ’ አምላኬ ለምን ተውከኝ? ብሎ በጩኸት እየለመነ እንዴት የተባለው ጦር መጥቶ ከስቅለት ሳያድነው ቀረ?

ምክንያቱም ኢየሱስ በዚህ ቦታ ጸሎት አልጸለየም ነገር ግን ስለ እርሱ የተተነበየውን ትንቢት ክፍል የመጀመርያ ስንኝ ነው የጠቀሰው፡፡ እዚሁ ምዕራፍ ለጥያቄ ቁጥር 8 የተሰጠውን መልስ ይመልከቱ፡፡