ኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና እኔ ለእናንተ ተሰቅዬ ልሞት መሆኑን እመኑ” በማለት እንዴት ሳይሰብክ ቀረ?
-
ማቴዎስ 4፡17 “ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመረ” ይላል፡፡ ክርስትና መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ “ኢየሱስ ለኛ ሲል ተሰቅሎ መሞቱን ማመን ግዴታና ብቸኛው መዳኛ ነው” ሲል ያስተምራል፡፡ ኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” በማለት ከሚሰብክ ብቸኛው መዳኛ እርሱ ለሰው ልጅ ኃጢአት ቤዛ ሆኖ መሰቀሉንና መሞቱን ማመን ከሆነ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና እኔ ለእናንተ ተሰቅዬ ልሞት መሆኑን እመኑ” በማለት እንዴት ሳይሰብክ ቀረ?
ኢየሱስ በአገልግሎቱ መጀመርያ ላይ መሠረታዊ የሆነውን የእግዚአብሔር መንግሥት ትምህርት በማስተማር ነበር የጀመረው፡፡ ትምህርቱን ተቀብለው ይበልጥ ለማወቅ ወደ እርሱ ለቀረቡት ኒቆዲሞስን ለመሳሰሉት ተከታዮቹ እና ለሐዋርያቱ መንግሥተ ሰማያት የመግቢያው መንገድ የእርሱ መስዋዕትነት መሆኑን ያስረዳ ነበር (ዮሐንስ 3፡13-18፣ ማቴዎስ 26፡26-28)፡፡ የጠያቂው ድምዳሜ ከሰንበት ትምህርት ቤት ህፃናት እንኳ የሚጠበቅ አይደለም፡፡