መዝሙር 34፡17 ላይ “ቅኖች” ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ እርሱም ይሰማቸዋል ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል” ይላል፡፡ ታዲያ «አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውከኝ?» እያለ ኢየሱስ ሲጮህ «ቅን» ስላልሆነ ነው ያልተሰማው?

 


  1. መዝሙር 34፡17 ላይ “ቅኖች” ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ እርሱም ይሰማቸዋል ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል” ይላል፡፡ ታዲያ «አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውከኝ?» እያለ ኢየሱስ ሲጮህ «ቅን» ስላልሆነ ነው ያልተሰማው? ከሞትስ ያላዳነው? ወይስ ቅን ስለሆና ከሞት ድኗል?

ኢየሱስ ለምን ይህንን እንዳለ እዚሁ ምዕራፍ በቁጥር 8 ላይ አብራርተናል፡፡ ጠያቂው ይህንን ጥቅስ የተረጎሙበት መንገድ ትክክል ከሆነ በብዙ ስቃይና ሰቆቃ ውስጥ ሆነው ወደ አምላካቸው እየጮኹ የሞቱት ቅዱሳን ሁሉ ቅኖች ስላልሆኑ ነው እግዚአብሔር ያልሰማቸው የሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ልንደርስ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ቅኖችን ከመከራቸው የሚያድናቸው በመከራ ውስጥ እንዳያልፉ በማድረግ ብቻ ሳይሆን መከራቸውን የሚቋቋሙበትን ኃይል በመስጠት እና ከመከራቸው በኋላ እውነተኛነታቸውን በማረጋገጥ ጠላቶቻቸውን በማሳፈርም ጭምር በመሆኑ የጠያቂው ትርጓሜ በእጅጉ የተሳሳተ ነው፡፡