«ይመጣል» ተብሎ የተተነበየው መሲህ ኢየሱስ ከነበረ ይህ መሲህ እንደማይገደልም ተገልጿል፡፡ ታድያ እንዴት ኢየሱስ «ሊገደል ቻለ »ተብሎ ይታመናል?

 


  1. ማቴዎስ 8፡17፣ ኢሳያስ 53፡12፣ ኢሳያስ 53፡4፣ ሉቃስ 2፡30፣ ኢሳይያስ 52፡10 እና ሉቃስ 22፡32 ላይ «ይመጣል» ተብሎ የተተነበየው መሲህ ኢየሱስ ከነበረ ይህ መሲህ እንደማይገደልም ተገልጿል፡፡ ታድያ እንዴት ኢየሱስ «ሊገደል ቻለ »ተብሎ ይታመናል?

ከእነዚህ ጥቅሶች መካከል አንዳቸውም መሲሁ እንደማይገደል አይናገሩም፡፡ ይልቁኑ ኢሳይያስ 53ን መጥቀሳቸው ጠያቂው ስለ መሲሁ አለመገደል ሳይሆን ስለ መሲሁ መገደል ማስረጃ እየሰጡ ያሉ ያስመስላቸዋል፡-

የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም፡፡ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም፡፡ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቁጠርነው፡፡ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቁሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን፡፡ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል፡፡ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል፡፡ ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቁጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ፡፡

ይህንን ክፍል በመጥቀስ መሲሁ እንደማይሰቀልና እንደማይሞት ለመሟገት የሚሞክር ሰው ምንኛ የታወረ ነው!