ኢየሱስ ለሰው ልጅ ኃጢአት ሲል ተሰውቶ ከሦስት ቀናት በኋላ ነፍሱ ተመልሶለታል፡፡ መስዋዕትነቱ ጊዜያዊ ነበር ማለት ነው?

 


  1. እንደ ክርስቲያኖች አስተሳሰብ ኢየሱስ ለሰው ልጅ ኃጢአት ሲል ተሰውቶ ከሦስት ቀናት በኋላ ነፍሱ ተመልሶለታል፡፡ መስዋዕትነቱ ጊዜያዊ ነበር ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው መስዋዕት ሲያደርግ መሰዋዕቱን መልሶ አይወስድም፤ ኢየሱስ ግን ወሰደ፡፡ ከሰው መስዋዕት ያንስ ነበርን?

በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት ኃጢአትን የሚያስተሰርየው ደም ነው (ዘሌዋውያን 17፡11፣ ዕብራውያን 9፡22)፡፡ ክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ ነው ኃጢአታችንን ያስተሰረየው (ማቴዎስ 20፡28፣ ኤፌሶን 1፡7፣ ዕብራውያን 9፡7-14፣ 1ጴጥሮስ 1፡18-19፣ 1ዮሐንስ 1፡7፣ የሐዋርያት ሥራ 20፡28)፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ አካል ሥጋና አጥንት ነበረው (ሉቃስ 24፡39)፡፡ ነገር ግን ስለ ኃጢአታችን ስርየት ያፈሰሰውን ደሙን ይዞ መነሳቱን የሚጠቁም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ባለመኖሩ የኢየሱስ መስዋዕት ጊዜያዊ እንደነበር ለመናገር የሚያበቃ ምንም ነገር የለም፡፡