ኢየሱስ የሰረየው የውርስ ኃጢአትን ነው ወይስ በየጊዜው የሚፈፀምን ኃጢአት?
-
ኢየሱስ የሰረየው የውርስ ኃጢአትን ነው ወይስ በየጊዜው የሚፈፀምን ኃጢአት? ምላሹ የውርስ ከሆና በየጊዜው ለፈፀሙት ኃጢአቶች ክርስቲያኖች ሊቀጡ ነው ማለት ነው፡፡ ምላሹ ለሁለቱም ከሆነ “መልካም ስራ” መስራት እንደሚገባ የሚያስተምሩ ጥቅሶች ፋይዳቸው ምንድነው?
በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑት ክርስቲያኖች ሁሉም ኃጢአቶች ይሰረዩላቸዋል (1ዮሐንስ 1፡7)፡፡ መልካም ሥራ መሥራት የእውነተኛ እምነት መገለጫ እንጂ ኃጢአትን ማስተሰረያ አይደለም፡፡