ኢየሱስ እንደ መልከ ፄዴቅ ሊቀ ካህናት ተብሎ መሾሙ ተገልጿል፡፡ ሳይሾም በፊትስ ምን ነበር?
-
ዕብራውያን 5፡8-10 “የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም እንኳ ከተበቀለው መከራ መታዘዝን ተማረ፡፡ በዚህም ፍፁም ሆኖ ከተገኘ በኋላ እርሱን ለሚታዘዙ ሁሉ የዘለዓለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው፡፡ እንደ መልከ ፄዴቅ ሹመትም ሊቀ ካህናት ተብሎ በእግዚአብሔር ተሾመ፡፡” ይላል፡፡ በዚህ ጥቅስ ኢየሱስ እንደ መልከ ፄዴቅ ሊቀ ካህናት ተብሎ መሾሙ ተገልጿል፡፡ ሳይሾም በፊትስ ምን ነበር?
ለዚህ ጥያቄ መልስ ቁጥር 59ን ይመልከቱ፡፡ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ!
ኢየሱስ የዘለዓለም ድነት ምክንያት የሆነው በርሱ ለሰው ኃጢአት መሰቀል ላመኑት ነው ወይስ እርሱን ለታዘዙት? ጥቅሱ የሚለው “ለሚታዘዙ ነው” ታድያ ክርስቲያኖች ትዕዛዛቱን በጳውሎስ አስተምህሮት ተመርተው “የዘለዓለም ህይወት እናገኛለን” በማለት ለምን ተቃረኑ?
እውነተኛ እምነት በመታዘዝ ስለሚገለፅ እምነትና መታዘዝን ለያይቶ ማየት አይቻልም፡፡ ይህንን ደግሞ ከሐዋርያው ጳውሎስ በላይ ያስተማረ ማንም የለም፡፡ ለዚህም በምዕራፍ 4 ጥያቄ ቁጥር 8 ላይ በቂ ማስረጃዎችን ጠቅሰናል፡፡ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ!
ጠያቂው ጳውሎስን በጭፍን ጥላቻ የሚጠሉ እንጂ ትምህርቶቹን የሚያውቁ ሰው አለመሆናቸው ግልፅ ነው፡፡