ሰው ገነት የሚገባው በኢየሱስ በማመን ብቻ ከሆነ ጳውሎስ ለምን ያላመነ ሚስት/ባል ያለው ሰው በአመነው ምክንያት ገነት እንደሚገባ ተናገረ?

 


  1. ሰው ገነት የሚገባው በኢየሱስ በማመን ብቻ ከሆነ ለምን ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 7፡8-16 ላይ ያላመነ ሚስት/ባል ያለው ሰው በአመነው ምክንያት ገነት እንደሚገባ ተናገረ?

ሐዋርያው እንዲህ ዓይነት ትምህርት አላስተማረም፡፡ ይህ የጠያቂው የተሳሳተ መረዳት ነው፡፡ ያላመነው ወገን ትዳሩን መፍታት ባይፈልግ አማኞቹ መፍታት የለባቸውም፤ ምክንያቱም በእነርሱ ሰበብ የመዳን ዕድል ይኖራቸዋልና፡፡ ይህ ማለት ያላመነው ወገን ባመነው ወገን አማካይነት የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ በማመን የመዳን ዕድል እንደሚያገኝ ለማመልከት የተነገረ እንጂ ካመነ ሰው ጋር በትዳር በመጣመሩ ምክንያት ይድናል የሚል ትምህርት የለም፡፡