ኢየሱስ አምላክ ከነበረ እንዴት በሰው ይከዳል?

 


  1. ኢየሱስ አምላክ ከነበረ እንዴት በሰው ይከዳል? አምላክ በሰው ይከዳልን?

ጠያቂው ሰው አምላኩን መካድ አይችልም እያሉ ነውን? እንደርሱ ከሆነ የቁርአኑ አላህ ሰዎች እንዳይክዱት ስለምን በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃል? “አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና ለኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡” (ሱራ 2፡152)፡፡ ስለምንስ ሰዎችን “አማኞች” እና “ከሃዲዎች” በማለት ለሁለት ይከፍላል? (ሱራ 2፡161፣ 4፡102፣ 4፡140 9፡120፣ 9፡37፣ 42፡48፣ 47፡10፣ ወዘተ.)፡፡ ኡስታዙ ይህንን ጥያቄ የጻፉት የእንቅልፍ ሰዓታቸው ካለፈ በኋላ ይመስላል፡፡