በደም ቤዛነት ማመን ከጥንታውያን የግሪክ ጣኦታውያን ከሮማውያን በስተቀር በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ተከስቶ ያውቃል ወይ?

 


  1. በስቅለት ወይም በደም ቤዛነት ማመን ከጥንታውያን የግሪክ ጣኦታውያን ከሮማውያን፣ ከህንዶችና ከፔርሺያውያን እምነቶች ውስጥ በስተቀር በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ተከስቶ ያውቃል ወይ?

ይህ ጥያቄ ሁለት መሠረታዊ ችግሮች አሉበት፡፡ የመጀመርያው በደም መቤዠት በይሁዲ፣ በክርስትናም ሆነ በእስልምና ውስጥ መታመኑን መዘንጋቱ ነው፡፡ (ለጥያቄ 34 የተሰጠውን መልስ ይመልከቱ፡፡) ሁለተኛው ችግር ደግሞ አንድ ነገር በጣዖታውያን ወይም በአረማውያን የሚፈፀም ከሆነ ትክክል ሊሆን አይችልም የሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ማንጸባረቁ ነው፡፡ ከአቤል ዘመን ጀምሮ ሰዎች ለእግዚአብሔር መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር፡፡ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ኢዮብ፣ ሙሴ፣ ዳዊት እና ሰለሞንን የመሳሰሉት ታላላቅ ስብዕናዎች ይህንኑ ፈፅመዋል፡፡ አረማውያን እውነተኛ ላልሆኑ አማልክት መስዋዕት ማቅረባቸው ነው ትክክል ያልሆነው እንጂ ሥርአቱን መፈፀማቸው አይደለም፡፡