ኢየሱስ ተናገራቸው የሚባሉት ቃላት ከግሪክ ጣዖቶች የተወሰዱ አይደሉምን?

 


  1. ከነብዩ ኢየሱስ (ዒሳ) የተላኩትን ቃላት የዓለም መጀመሪያና መጨረሻ (አልፋና ኦሜጋ)፣ የሰውን ልጅ በደም ወደ ቀጥተኛው ለመመለስ ነው የመጣሁት ካለው ከባኮስ ቃላት ጋር ለማነጻጸር ይህን ብሩህ አመለካከት ይሰጠን የለም ወይ? በነዚህ ቃላትና ዘግየት ብሎ በነብዩ ኢየሱስ ላይ በተላኩት ቃላት መካከል ያለው መመሳሰል የጉዳዩን ሁለንተናዊ እውነታ ለማጥናት አዲስ ስሜት ሊቀሰቅስ አይችልም ወይ?

ሮማውያን ባከስ በማለት የሚጠሩት ዲዮኒሰስ የተሰኘው የግሪካውያን ጣዖት ከኢየሱስ ጋር የሚመሳሰሉ ነገሮች እንዳሉት ቢነገርለትም ከልክ በላይ ተለጥጠው ለማመሳሰል የተሞከሩና ታሪኮቹ ከክርስቶስ በፊት ስለመኖራቸው ማስረጃ የሌላቸው በመሆናቸው በምሑራን ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ባከስ “የዓለም መጀመሪያና መጨረሻ (አልፋና ኦሜጋ)፣ የሰውን ልጅ በደም ወደ ቀጥተኛው ለመመለስ ነው የመጣሁት” በማለት እንደተናገረ ጠያቂው ያስቀመጡት ንግግር ምንጭ አልተጠቀሰለትም፡፡ ምንጩንም ለማወቅ ፍለጋ ብናደርግም ለማግኘት አልቻልንም፡፡ ከራሳቸው ፈጥረው የጻፉት ላለመሆኑ ዋስትና የለንም፡፡