ስለ ሮማውያን ገዢ ስለ ጲላጠስ ማንነትና ባህሪ ምን ያህል ነው የምናቀው?
-
ስለ ሮማውያን ገዢ ስለ ጲላጠስ ማንነትና ባህሪ ምን ያህል ነው የምናቀው? እርሱን በመቃወም ሮም ላይ ከከሰሱት ከዘመኑ አይሁዶች ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው ወይ? በይሁዳ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ በእርሱ የነበረውን ጥላቻና ንቀት አያመለክትም ወይ? ጉቦ (መደለያ) እንዲቀበል አላቀረበም ወይ? ነገሩ እንዲያ ከሆነ ዘንድ ፍላጎታቸውንና ትዕዛዛቸውን ለማስፈጸም ለምን ይቸኩላል?
ጲላጦስ ከአይሁድ ጋር መልካም ግንኙነት እንዳልነበረው ቢታወቅም ነገር ግን በኢየሱስ ላይ ከቀረቡት ክሶች መካከል አንዱ “ንጉሥ ነኝ ብሏል” የሚል ስለነበር እና ከቄሣር ውጪ ንጉሥ እንደሌላቸው በመናገር ጉዳዩን ከቄሣር ጋር ስላያያዙ ኢየሱስን አሳልፎ ሰጣቸው (ዮሐንስ 19፡15)፡፡ ጥያቄያቸውን ባይመልስ ከዚያ ቀደም በቄሣር ዘንድ እንደከሰሱትና እንዳስወቀሱት ሁሉ አሁንም በጥሩ ምክንያት እንዳይከሱት ስጋት እንዳደረበት ግልፅ ነው፡፡
የኢየሱስ አድናቂ የሆነውን ከበርቴ ጉቦ እንደነዮሴፍ ካሉት ለምን አልተቀበለም? ሉቃስ ባለው መሠረት ይህ ዮሴፍ በጣም ባለጸጋ የሆነ ለነብዩ ኢየሱስ በጣም ያስብ የነበረ የምክር ቤቱ አባል ሲሆን አል-መሲሕ እንዲሰቀሉ በሚለው የምክር ቤቱ ውሳኔ ላይ ግን ያልተስማማ ሰው ነበር፡፡ ለብልሹው ገዥ ጉቦ በማቅረብ እንኳ ቢሆን በምክር ቤቱ ውስጥ ባይሳካለትም የዒሳን ሕይወት ለማዳን መምከር ይችል አልነበረም ወይ?
በአይሁድ ክስ ምክንያት ከዚያ ቀደም አስደንጋጭ የግሳፄ መልዕክት ከቄሣር የደረሰው ጲላጦስ[10] ከአርማቲያሱ ዮሴፍ ጉቦ ከመቀበል እና በአይሁድ ሕዝብ በቄሣር ፊት ተከሶ ከሥልጣኑ ከመባረር የትኛውን እንደሚመርጥ ግልፅ ነው፡፡ የአርማቲያሱ ዮሴፍ ያንን አላደረገም፡፡ ጲላጦስም ጉቦ የሚቀበልበት ሁኔታ ውስጥ አልነበረም፡፡ ጠያቂው ምኞታቸውን ከሚያስነብቡን ማስረጃ ቢሰጡን መልካም ነበር፡፡