ከጥንት ጀምሮ የነበረውን አሀዳዊውን እምነት ወይስ ከንቂያ ጉባኤ በኋላ የመጣውን የሥላሴን አስተምሮት እንቀበል?

 


4. ኢሳያስ 46:9 “እኔ አምላክ ነኝና ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደኔም ያለ ማንም የለም” ይላል፡፡ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን አሀዳዊውን እምነት ወይስ ከንቂያ ጉባኤ በኋላ የመጣውን የሥላሴን አስተምሮት እንቀበል? ጥቅሱ ግን የጥንቱን ነገር አስቡ እኔ እግዛብሔር ነኝ እንደእኔ ያለም ማንም የለም ፡፡ ይላል፡፡ ታድያ ክርስቲያኖች ምን ነካቸው?

የሥላሴ ትምህርት ልብ የእግዚአብሔር አንድነት በመሆኑ አሐዳዊ ትምህርት ነው፡፡ ጠያቂው ግን “አሐዳዊነት” ሲሉ ነጠላ አሐዳዊነት (Unitarian Monotheism) ለማለት ፈልገው ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሥላሴያዊ አሐዳዊነትን (Trinitarian Monotheism) የሚያስተምር መጽሐፍ እንደመሆኑ ጠያቂው የጠቀሱትን ጥቅስ አዲስ ኪዳንን በሚያጠቃልለው የመጨረሻ እና የተሟላ (Final Marching) መገለጥ፣ ማለትም በአስተምህሮተ ሥላሴ መሠረት መረዳት ያስፈልጋል፡፡