ኢየሱስ እግዚዝብሔርን ከፈራ እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ይፈራል?

 


17. መጽሐፍ ቅዱስ (የ1980 እትም) በዕብራዊያን 5፡7-8 ላይ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ተገልጿል፡- “እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ተሰማለት፤ምንም ልጅ ቢሆን ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ”ይላል፡፡ ክርስቲያኖች እንደሚሉት ኢየሱስ “አምላክ” ከሆነ አምላክ እንዴት ከልምድ ይማራል? ጥቅሱ ይቀጥልና “እግዚአቢሔርንም ስለመፍራቱ ተሰማለት” ሲል ይገልጻል፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሔር ከሆነ እግዚአብሔር ራሱን ይፈራልን? ኢየሱስ አምላክን እንደሚፈራ በዚህ ጥቅስ ተገልጿል፡፡ ታዲያ “ኢየሱስ አምላክ ነው” ከተባለ እንዲሁም “አምላክ አንድ ነው” ካልን ኢየሱስን የፈራው እራሱን ነው ማለት አይሆንምን? እንዴትስ አምላክ ራሱን ይፈራል? ወይስ ከሦስት አማልክ ውስጥ አንዱ ሌላኛውን ይፈራል?

ጠያቂው የጠቀሱትን ጥቅስ ትኩረት ሰጥተው ቢያነቡት ኖሮ ባልተደናገሩ ነበር፡፡ ጥቅሱ “እርሱም በሥጋው ወራት…” በማለት ነው የሚጀምረው፡፡ ስለ ኢየሱስ ሰብዓዊ ባሕርይ እንጂ ስለ መለኮታዊ ባሕርዩ እየተናገረ አይደለም፡፡ ጌታችን በምድር ላይ የኖረው ፍፁም ሰው በመሆን ስለነበር ለአብ በመገዛት ፍፁም ሰው የሆነ ሰብዕ ለአብ ሊሰጥ የሚገባውን ተገቢውን ክብር በመስጠት ነበር፡፡ ጠያቂው ደግመው ደጋግመው የሥላሴን አስተምህሮ በመዘንጋት ከራሳቸው የተሳሳተ ዕይታ አንፃር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ትእግስትን የሚፈታተኑ ናቸው፡፡

 

 

ለአሕመዲን ጀበል 303 ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ ማውጫ