አብ እና ወልድ ሁለቱም የአንዱ እግዚአብሔር አካል ከሆኑ እንዴት ሁለት ፍላጎት ኖራቸው?

 


7. በማቴዎስ 26:39 ላይ ኢየሱስ “አባት ሆይ ቢቻልህ ይህ ፅዋ ከእኔ ይለፍ ነገር ግን እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን አንተ እንደምትፈልገው ይሁን” ብሏል፡፡ ይህ አባባል የኢየሱስ ፍላጎትና የአብ ፍላጎት ሁለት የተለያዩ መሆናቸውን ያስረዳል ፡፡ ታድያ አብ እና ወልድ ሁለቱም የአንዱ እግዚአብሔር አካል ከሆኑ እንዴት ሁለት ፍላጎት ኖራቸው?

ኢየሱስ ሰውም አምላክም እንደመሆኑ መጠን ሰብዓዊ ባሕርዩ የመስቀሉን ሥቃይ ከማስተናገድ ይልቅ አለማስተናገድን እንደሚመርጥ ግልጥ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ እርሱ ፈቃድ ሳይሆን እንደ አብ ፈቃድ እንዲሆን ጸለየ፤ ጸሎቱም ተሰማለት፡፡ ይህ ኢየሱስ በመለኮታዊ ባሕርዩ ከአብ የተለየ ፈቃድ እንዳለው እንድንናገር አያስችለንም፡፡