ቃል ስጋ ከሆነታድያ አምላክ ስጋ ሆነ ማለት ነው?
31. ዮሐንስ 1: 14 “ቃልም ስጋ ሆነ” ይላል፡፡ እንደ ክርስቲያኖች እምነት ‹ቃል› አምላክ ነው፡፡ ታድያ አምላክ ስጋ ሆነ ማለት ነው?
አዎ አምላክ ሥጋ ሆኗል፡፡ ይህ ማለት መለኮታዊ ባሕርዩ ጠፍቶ ወደ ሥጋነት ተለውጧል ማለት አይደለም፡፡ ሥጋውም መለኮት ሆኗል ማለት አይደለም፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ እንደተናገረው “አምላክ ሰው ሆነ” ወይም “ቃል ሥጋ ሆነ” ማለት የሰውን ህላዌ ወሰደ፣ ተቀበለ፣ ተገነዘበ፣ የራሱ አደረገ ማለት ነው፡፡[13]