ደቀ መዛሙርትም ለመጀመረያ ጊዜ በአንጾንኪያ “ክርስቲያን” ከተባሉ እንዴት ኢየሱስ ክርስትናን ሰበከ አስተማረ ሊባል ይችላል?

 


4. የሐዋርያት ሥራ 11፡25-26 “ከዚህ በኋላ በርናባስ ሳውልን ለመፈለግ ወደ ጠርሴስ ሄደ ባገኘውም ጊዜ ወደ አንፆኪያ አመጣው፡፡ ሁለቱም እዚያ ካለችው ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን አንድ ዓመት ሙሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ አስተማሩ፣ ደቀ መዛሙርትም ለመጀመረያ ጊዜ በአንፆኪያ ክርስቲያን ተብለው ተጠሩ፡፡” እንደዚህ ጥቅስ አገላለጽ ሰዎች ለመጀመረያ ጊዜ በአንጾንኪያ “ክርስቲያን” ከተባሉ እንዴት ኢየሱስ ክርስትናን ሰበከ አስተማረ ሊባል ይችላል?

“ክርስቲያን” ማለት “የክርስቶስ ወገን” ማለት ነው፡፡ የክርስቶስን ትምህርት የተከተሉ ሰዎች የእርሱ ወገን ካልተባሉ ምን ሊባሉ ነው? ደቀ መዛሙርት ይህንን ስም እንዲያገኙ ያስቻላቸው የክርስቶስን ትምህርት መከተላቸው ነው፡፡ ማንኛውም የእምነት ቡድን ስያሜውን የሚያገኘው ከተጀመረ በኋላ ነው፡፡ ክርስቶስ ክርስትናን ጀመረ፡፡ እርሱ የጀመረውም ትምህርት ተስፋፍቶ ከተደራጀ በኋላ ስያሜውን ከእርሱ አገኘ፡፡ ስያሜው እርሱ ላስተማረው እምነት የተሰጠ መሆኑን ከተገነዘብን እንዴት ክርስቶስ ክርስትናን አላስተማረም ልንል ይቻለናል?