ኢየሱስ “አንተ እንደላከኽኝ ያውቃሉ ሲል” ሐዋርያት ኢየሱስን ምን መሆኑን ያውቃሉ ተባለ?

 


5. ዮሐንስ 17፡25 “ፃድቅ አባት ሆይ ዓለም ባያውቅህም እኔ አውቅሃለው እነዚህም አንተ እንደላከኽኝ ያውቃሉ፡፡” ይላል፡፡ በዚህ ጥቅስ ላይ እንደተገለጸው ሐዋርያት ኢየሱስን ምን መሆኑን ያውቃሉ ተባለ? “እነዚህም አንተ እንደ ላከኸኝ ያውቃሉ፡፡” ታዲያ ክርስቲያኖች ይህን አምነው መቀበል ለምን ተሳናቸው?

ጉድ! አሕመዲን ጀበል ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ እንደተላከ የማያምን ክርስቲያን የት አገር ይሆን የገጠማቸው?? ሰውየው “303 ጥያቄዎች” የሚለውን የመጽሐፉን ርዕስ አስቀድመው ጽፈውት ኖሮ ቁጥሩን ለመሙላት የተቸገሩ ነው የሚመስሉት፡፡