ኢየሱስ “በእውነት እልሃለሁ፣ ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” ብሏል። ኢየሱስ አምላክ ከሆነ እንዴት አምላክ ገነት ይገባል?

 


22. እንደ ሉቃስ ወንጌል 23፡43 አገላለጽ መስቀል ላይ ሆኖ አብሮት ከተሰቀለው ለአንዱ “በእውነት እልሃለሁ፣ ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ”አለው” ይላል፡፡ ክርስቲያኖች እንደሚሉት ኢየሱስ አምላክ ከሆነ እንዴት አምላክ ገነት ይገባል? አምላክ ገነት ይገባል ወይንስ አማኞችን ያስገባል?”

በጠያቂው አባባል ኢየሱስ አምላክ ለመሆን ገነት አካባቢ ድርሽ ማለት የለበትም፡፡ ገነት ውስጥ መታየት በቅፅበት ከአምላክነት መስፈርት ውድቅ ያደርጋል፡፡ ይህ መስፈርት ለራሳቸው አምላክ ይሰራ ይሆን?

ጌታችን ኢየሱስ በሠልስቱ ቀናት ውስጥ ወደ ገነት ብቻ ሳይሆን ወደ ሲዖልም በመሄድ ታስረው ለነበሩት ነፍሳት የምስራቹን እንደሰበከ ተጽፏል (2ጴጥሮስ 2፡4-5)፡፡ ኡስታዙ ከተናገሩት በተፃራሪ ጌታችን ኢየሱስ ሰዎችን ገነት የማስገባት ሥልጣን እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ በበርካታ ቦታዎች ላይ ይናገራል፡- (ማቴዎስ 24፡31-40፣ ዮሐንስ 14፡1-3፣ ራዕይ 2፡7፣ ራዕይ 22፡12)፡፡

 

 

ለአሕመዲን ጀበል 303 ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ ማውጫ