መጽሐፍ ቅዱስ “ፈጣሪሽ ባልሽ ነው ፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው” ሲል ፈጣሪ ሚስት አለችው?
12. በትንቢት ኢሳይያስ 54፡4-5 ላይ “አታፍሪምና አትፍሪ ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእግዲህ ወዲህ አታሥቢው ፤ ፈጣሪሽ ባልሽ ነው ፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው ፡፡” ይላል፡፡ እግዚአብሔር ሚስት ያገባልን? ይህ ለዓለም ፈጣሪ አምላክ የሚገባ ነገር ነውን?
ጥቅሱ እየተናገረ ያለው ስለ ሴት ሳይሆን ስለ እስራኤል ነው፡፡ እግዚአብሔር የእስራኤል ተንከባካቢ፣ አስተዳዳሪና ጠባቂ መሆኑን ለመግፅ የተነገረ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ ጠያቂው ጥቅሶችን በአውዳቸው ውስጥ ያለማንበብ አባዜ በእጅጉ ተጠናውቷቸዋል፡፡