“እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ” ሲል ምን ለማለት ተፈልጎ ይሆን?

 


13. ዘፍጥረት 18፡20-21 “የሰዶምና ገሞራ ሕዝቦች የሚፈፅሙትን በደል ሰምቻለሁ፤ ኃጢአታቸውም እጅግ ከባድ ነው፤ ስለ እነርሱ የሰማሁት ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ እነርሱ እወርዳለሁ” ይላል፡፡ እንዲሁም ዘፍጥረት 11፡5 እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ” ይላል፡፡ ምን ለማለት ተፈልጎ ይሆን ? ታዲያ እግዚአብሔር የሰማውን ለማረጋገጥ  እንደ ሰው በቦታው መገኘት ካስፈለገው ምኑን አምላክ ሆነ? ሁሉን ማወቅ ተስኖት? በዚህ አምላክ ነው ክርስቲያኖች የሚያምኑት?

የ1954 ዕትም እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔርም አለ፦ የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥ እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደ ሆነ ወርጄ አያለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ፡፡”

ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔርን ሁሉን አዋቂነት አጠያያቂ የሚያደርግ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ ነገር ግን በሰዎች ሁኔታ ውስጥ እንደሚሳተፍና ሰዎች ወደ እርሱ ስለጮኹ ብቻ በስሜት ተነሳስቶ እንደማይፈርድ ነገር ግን ነገሮችን ከስር መሠረታቸው መርምሮ እንደሚፈርድ ለማሳወቅ የገባ ዘይቤ ነው፡፡