አምላክ በፉጨት ይጣራል?
16. ኢሳይያስ 7:18 “በዚያን ቀን እግዚአብሔር ራቅ ካሉት ከግብጽ ወንዞች ዝንቦችን፣ ከአሦርም ምድር ንቦችን “በፉጨት ይጠራል፡፡” ይላል፡፡ እንደዚሁም “የእግዚያብሔር ቁጣ በህዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው፡፡ ከሩቅ ያሉትን ሕዝቦች የሚጠራበትን ምልክት ያቆማል፤ ከምድር ዳርቻም በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነርሱም እየተጣደፉ በፍጥነት ይመጣሉ፡፡” (ኢሳይያስ 5:25-26)፡፡ እውን ይህ የአምላክ ባህሪ ነውን?
እግዚአብሔር የአሦራውያንና የግብፃውያንን ሰራዊት በቅፅበት ትዕዛዝ ወደ ምድረ እስራኤል በማምጣት አመፀኞችን እንደሚቀጣ የተነገረ ዘይቤ እንጂ እግዚአብሔር የፏጫል ማለት አይደለም፡፡ ጠያቂው ስለ ዘይቤያዊ አነጋገሮች ምንም ዕውቀት የሌላቸው መሆናቸውን በተደጋጋሚ አሳይተዋል፡፡